ከኢንጂነር ዘለቀ ረዲ
የተከበራችሁ አንባቢያን ባለፈው ሳምንት በተቃጠርነው መሠረት ዛሬም ስለወሎ ትንሽ ልበላችሁ። የደቡብ ወሎ ዋና ከተማ ደሴ ደርሰው ሐይቅን ፣መርሳን፣ ጉባ ላፍቶን፣ ኡርጌሳ፣ ሳንቃን፣ወልዲያን፣ጉብዬን፣ ሮቢትን ፤እያሉ ቆቦ ይገባሉ። ሁሉም የኦሮምኛ ትርጉም ያላቸው ስሞች ናቸው ቋንቋቸው ግን አማርኛ ኢትዮጵያውያንን በዘር መለየት አይቻልም። ተፈጥሮ ይገርምዎታል። ወሎዬዎች መልክና ቁምነገር ሲታደል ከፊት ተሰልፈው የወስዱ ይመስልዎታል። ህጻን አዋቂው ያምራል። የሰባ ዓመት ሽማግሌዎችና አሮጊቶች በሚገርም ሁኔታ አሁን በዚህ ዕድሜያቸው ላይ ሆነው በልጅንታችው የነብራቸውን ውበት ያሳብቅባቸዋል።
ወጣቶቹን በሙሉ ዓይን ለማየት እንኳን ያሳሳሉ። ውበት ለመጨመር ምንም የሚቀባቡት ነገር የለም። ለነገሩ ተፈጥሮ ቀብታችው የለ? ለመዋቢያ ብለው ቢቀቡ ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን ውበት ከማበላሽትና ወጪ ከማብዛት የዘለለ ጥቅም የለውም። የሚገርም ነው። ወሎዮቹ ቁመተ ለግላጋ ጸጉረ ረጂም፣ አፍንጫ ሰልካካ ፈጽሞ ክፋት የሚባል ነገር የሌለባቸው ገራገሮች ነቸው።
ወልዲያ እንደገቡ በውልዲያ ያሉ ወያላዎች የመኪና ተራ አስከባሪዎች መኪና ከሌለዎት የሚሔዱበትን አካባቢ ይጠይቁዎታል ልክ እንደነግሩዋቸው ተሩዋሩጠው ከፈለጉበት ቦታ ይሸኙዎታል። በመኪና ከሆነ የሄዱት ወደሚሄዱበት አከባቢ ሰው እንዲጭኑ ይጠይቅዎታል። ፈቃደኛ ካልሆኑ በደስታ ተቀብለው መኪናዎን እንጠብልዎት ይሉዎታል። ፈቃደኛ ከሆኑ በደንብ አድርገው ያጥቡልዎታል። ፈቃደኛ ካልሆኑም ምሳም ይሁን ቡና ብለው እስኪመለሱ ድረስ መኪናዎ ተቆለፈም አልተቆለፈም እንደነበረ ያገኙታል።በወልድያ መኪናዎትን ቆለፉ አልቆለፉ እንግዳ በመሆንዎ ብቻ እቃዎ እንዳይጠፋ ወያሎቹ ይጠብቅሉዎታል። ለነገሩ ማን ይሰርቃልና ወልድያ የሰው ንብረት መንካት ነውር ነው።
በቻይና ጉዋንዙ አፍሪካ ጎዳና ምሳ በልቼ መልሥ ሲሰጥኝ የተወሰነ ገንዘብ በመልስ መስጫው ውስጥ ትቼ እሄዳለሁ ቲፕ መሆኑ ነው። ነገር ግን ወይተሩ ገንዘብ መተዌን ሲያውቅ ተከታትሎ መጥቶ ገንዘብ ረስትሃል አለኝ። ላንተ ነው የተውኩት ስለው አይ ለኔ ደመወዜ ይበቃኛል። በመንገድ ለሚለምኑት ስጥ ያለኝ በወልዲያ አይቼዋለሁ። ልጆቹ ሁሉ ዋጋ መቀበል የሚፈልጉት ለሠሩበት ብቻ ነው። በሁሉም ወሎ ማለት ይቻላል። ወንዱን ጋሼዋ ሴቱን እቴዋ ብሎ መጥራት የተለመደ ነው። ጋሼዋ ብለው ሲጣሩ ልዩ መስህብ አለው። ካፋቸው ማር ጠብ ይላል።
በወልድያ አለፍ፣አለፍ ብሎ ጀበናቸውን ጥደው ቡና የሚያፈሉ ሴቶች አሉ። ሁሉም ሴቶች ማለትይቻላል። በአዲስ አበባ ቡና ስታፈላ የተሰቀልችውን ስዕል ይመስላሉ። ያምራሉ ለማለት ነው። ቡናዎን አዘው ሲጠጡ የመንደር ተርቲበኛ ወሬ ሁሉ ያጫውትዎታል። በዚህም ቡና በመንገድ ሱስ ይዞዎት የሚጠጡ ሳይሆን በቤትዎ ባለቤትዎ አፍልታ ከጎረቤትዎችዎ ጋር የሚጠጡ ይመስልዎታል። እርስዎ ቡና ሊጠጡ ገና እንደቀረቡ ቡናው በትንሽ ጀበና ተቀንሶ በገል እሳት ይቀርብልዎታል፡፡ እንዲያጨሱ የሚቀርብልዎት የወሎ ጢስ የሚባል የተቀመመ ሽታው እውድ የሚያደርግና አልባብ አልባብ የሚሸት ነው። ይህ የወሎ ጭስ ከተለያየ የእጽዋት አይነቶች ተቀምሞ የሚዘጋጅ መሆኑን ጠይቄ ተረድቻለሁ። ለእናንተም ትጠቀሙበት ዘንድ እነሆ፤ የሚዝጋጀውም፣ ውግርት፣አደስ፣ ቀጣዮ፣ ጠጄሳር፣ የባህርዛፍ ፍሬ፣የናና ቅጠል፣ እና ከሎሚ ልጣጭ ነው። እዚህ አዲስ አበባ ለራሱ አነዚህ እጽዋትና ፍራፍሬ ማግኘት ስለሚቻል የወሎን ጪስ አዘጋጅቶ ቤትን ማሽተት ይቻላል።
በዚህ በወልድያ እኔ እንደገባሁ ወያላው ወዴት እንደምሔድ ጠየቀኝ። ቆቦ አልኩት ወድዚያ የሚሔድ ሰው እንድጭንለት ጠየቅኝ። ቆቦን የሚያስጎበኙኝ ሰዎች ቀጥሬ እንደነበረና እነርሱ ስለሉ እንደማይመቸኝ ስነግረው ገብቼ መቆያ እስክበላ መኪናየን ልጠብልህ ብሎ እንዲያጥብ ፈቅጀለት መቆያ ወይም መክሰሴን በልቼ ስመጣ አጥቦ አልጨረሰም ነበርና አስመሸህብኝ ብዬ በጣም ተበሳጨሁ። እና ደጋግሜ በጣም ተቆጣሁት። ተራ አስከባሪው ወይም ወያላው ይቅርታ ጠይቆኝ ውሃ ስላልነበረ ከሩቅ ነው ያመጣሁት አንደሚችኩሉ ስለነገሩኝ መጀመር አልነበረብኝም። ነገ ግን መኪናዎ እንዲጽዳልዎት ካለኝ ጉጉት ተነስቼ አስቀይሜዎታለሁና ይቅርታ አለኝ። ከፍተኛ ይቅርታ ጠይቆ አጥቦ ጨረሰልኝ። ገንዘብ ልከፍለው ዋጋውን ስጠይቀው ምን ስላደረግሁ አቆይቼ ስላበሳጨሁዎት ሊከፍሉ አይግባም። ከልብዎት ይቅርታ ካዳርጉልኝ እርሱ ክፍያየ ነው አለኝ።
እኔ በእጅጉ ደነገጥሁ ያንን ሁሉ ስናገረው ያልተነገረ ልጅ እንደውም ክፍያው በይቅርታ ይለወጥልኝ ማለቱ በእጅጉ አስደመመኝ። ሌላው ልቤን የነካው የልጁ አነጋገር እንዲህ የሚለው ነው። ዛሬ እርስዎ ተበሳጭተው ከሄዱ ነገ ወልድያ አይቆሙም ሌሎች ጓደኞችዎትንም ከነሯቸው ወልዲያን ይጠሉዋታል። እኛ የምንጠቀምው በወልዲያ እርስዎ ከሚያገኙት ደስታ በተደጋጋሚ ሲመጡ ነው አለኝ። አያችሁዋት ቱሪዝም ምን እንደምትመስል? ይህ በወልዲያ ያለ ወጣት የሚያስበውን ህሳብ የኢህአዴግ የቱሪዝም ሚንስትር ሰራተኞቸ ያስቡታል የሚል ግምት የለኝም።ሌላው ይወልዲያ ሆስፒታል ሀኪሞችና ሰራትኞች ለህዝቡ የሚሰጡት አግልግሎት በእጅጉ ማራኪና አስደሳች ከመሆኑ የተነሳ ሆስፒታል የሄዱ ሳይሆን ምግብ ሊበሉ አንድ ትልቅ ሆቴል ገብተው የሚስተናገዱ ይመስልዎታል። ሰው አካበቢውን ይመስለል ይሉሀል እንዲህ ነው። በእርግጥ ይህ ሁሉ ቢሆንም የብዙ ትላልቅ ሰዎች ሀገር ወልዲያ ውሃ መጠማትዋ ግን አሳዛኙ ክፍል ነው። ያ ሁሉ መስተንግዶና ፍቅር እያለ የውሃ ችግር ስላለ ወልዲያን ለህዝቡ ፍቅር መሄድ ቢፈልጉም የውሃው ነገር ያሳስብዎታል። እንግዲህ ከልማታዊ ጋዜጠኞችና ልማታዊ ነኝ ከሚለው ብአዴን ብዙ ይጠበቃል። ብአዴን ሆይ ልማታዊነትህን በቴሌቪዥን ሳይሆን በመሬት ላይ እንየው።
ቆቦ ለጥ ባለ ሜዳ በሞቃታማው የሰሜን ወሎ ክፍል የተመሰረተች ውብ የውቦች ከተማ፤ በመስኖ ልማት በሀግራችን ካሉት ሁሉ በመጀመሪየው ተርታ ትቀመጣለች። በቆቦ ወንዶች ዘንድ ቅድሚያ ለሴት የሚለው አንጋገር የቃላት ሳይሆን በተግባር ነው። ወደገብያ የሚሄዱ ከሆነ የሚሸከሙት ነገር ካለ ወንዱ ያግዛታል። ባልና ሚስት ፊትና ሁዋላ ሳይሆን ጎን ለጎን ነው የሚሄዱት ለሴቶች ቅድሚያ መስጠትና የበለጠውን ከባዱን ሥራ ባል መስራትን ሌሎች አካበቢዎች ከንዚህ ከቆቦ ወንዶች ቢማሩ መልካም ነው። ምክንያቱም በአንድ አካባቢ ሴቶች ከባድ ሸክም ተሸክመው ሲሄዱ ወንዶች ባዶ እጃቸውን ጃንጥላ ይዘው የሚሄዱበት አንዳንድ ቦታ ስላለ ማለቴ ነው።
ባለፈው ሰምንት የጀመርኩትን ርዕስ ስለተጫዋቾቻችን እና ስለስፖርት ፌዴሬሽን በትንሹ ለመነካካት ሞክሬ ነበር። ከላይ በርዕሴ ካነሰሁዋችው ያልነካሁት የተመልከቾችን ጉዳይ ዛሬ ለመንካት እሞክራለሁ ብየ የነበረ ቢሆንም የመለያየት ፖለቲካ ከአባቶቻችን ልብ አልወጣ ስላለ ዛሬ አቶ ቡልቻ በተደጋጋሚ ስለሚናገሩት ነገር አንድ ለማለትት ፈለግሁ ተክታይ ጽሁፌን ሳምንት ስለምመለስበት አንባቢን ይቅርታ እጠይቃለሁ።
እንግዲህ የተከበራችሁ አንባቢያን ከላይ የጠቀስኩት ወጣት ትምህርቱ ከስምስንተኛ ክፍል ያልዘለለ የተሻለ የእውቀት ደረጀ የሌለው ነገር ግን የተሻለ አስተሳሰብ ያለውንና የዓለም ባንክ ድርጅት ውስጥ ይሰሩ የነበሩትን የአዋሽ ባንክ መስራችና የተሻለ የትምህርት ደረጀ ያላቸውን እቶ ቡልቻን ከዚህ የታክሲ ድንብ ተራ አስጠባቂ ጎን በጎን እንድታዩልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
በመጀመሪያ ምንም የቋነቋ ተማሪ ባልሆንም ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ላይ በነበርኩበት ጊዜ አስተማሪየ ስለቋነቋ ሲነግረኝ ቋነቋ እንደሚወለድ እንደሚያድግ፣ እንዲሁም እንደሚሞት የነገረኝ ሲሆን በእርግጠኝነት ያን ቀን አቶ ቡልቻ ይህ ትምህርት በሚሰጥበት ዕለት ፎርፈው ካልሆነ የእርሳቸውም አስተማሪ እንደሚያስተምር እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላልሁ። አቶ ቡልቻ ከምን አንጻር እንደሆነ ባይገባኝም በተደጋጋሚ ስለአመርኛ ቋነቋ ሲገዳቸው አያለሁ። መቼም ቋነቋ ብሎ ጨቁዋኝ የለም። የትኛውም ቋነቋ ከመግባቢያነት የዘለለ አንዳች ጥቅም የለውም። በእጅጉ የሚገርመው ነገር ሁሉም ቋነቋ ጎዶሎና መሆንሲሆን ቋነቋ ሁሉ ምሉዕ ስላልሆነ አንዱ ከአንዱ መዋዋሱ ነው። ቋነቋ ለራሳቸው ጎዶሎ መሆናቸውን አምነው እርስ በራሳቸው ተደጋግፈው አንዱ የሌለውን ካለው ተውሰው ተጠቃሚያቸውን እያገለገሉ ባሉበት ሰዓት እንደ አቶ ቡልቻ ዓይነቱ ቋነቋዎችን ብቻ ሳይሆን ተናጋሪዎቹንም ጭምር ለመልያየት በዚህ ባለቀ ዕድሜ መኩዋተን አስቸጋሪም አሳዛኝም ነው።
እኔ መቼም የአቶ ቡልቻንያህል ዕዉቀት የለኝም። ይህ የአቶ ቡልቻ የመከፋፈል አባዜ ከእኛ ሳይሆን ከአፍሪካ ቅኝ ገዢዎች የመጣ ሀሰብ ነው። ምዕራብያውያን አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሥጋ በተከፋፈሉ ጊዜ ሰሜን ሶማሊያን የደረሰቻት እንግሊዝ ነበረች። ታዲያ እንግሊዝ የደረሰቻትን ሶማሊያን የከፋፍለህ ግዛ ዘዴዋን ተጠቅማ ሱማሌያውያንን በአመለካከት ከፋፍላ ከመግዛትዋም በላይ እንድ ቋነቋ፣ አንድ ሀማኖት ያላቸውን ሀዝብ ዳግመኛ እንዳይገናኙ አድርጋ እንድ ህዝብ የነበሩት በመብታትን እስከሁን ፈጽሞ አንድ ሀሳብ አንዳይሆኑ ስለ ሰራቻችው ሶማሊያውያን በአምስት ተከፍለው ተበታትነው ቀርተዋል።
በዚህ ወቅት ለቅኝ ገዥዎች ራስ ምታት የነበረው ጀግናው ሙላ ሙሐመድ አህመድ የነበረ ሲሆን ለዚህ ሰው እንግሊዛውያን ዘማድ ሙላ ሙሐመድ አህመድ ይሉት ነበር፡፡ እብዱ ማለት ነው። እነርሱ ሶማሊያን ሲበታትኑ ጤናማ እርሱ ስለሀገሩ አንድነት ሲታገል እብድ ይገርማል። አሁንም አቶ ቡልቻ የመበታትን ዓላማ ሲያራምዱ ትክክል እኛ ስለ አብሮነት ስንታገል ነፍጠኛ! እንግሊዞች እብድ የሚሉት ሙላ መሀምድ አህመድ አንገዛም ስላለ ነበር። ለመብቱ የሚታገል በገዥዎች አይወደድም። ኢህአዴግም እምቢ ለመብቴ የሚሉትን እንዴ ምንትሴ አንዴ ቅብርጥርሴ እያለ በየ እስር ቤቱ እንደ ሚያሰቃየው ማለት ነው።
አቶ ቡልቻ እያራመዱት ያለው አስተሰሰብ የማንን እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። እኔ አቶ ቡልቻን ብሆን ኖሮ የማደርገው በተለያየ ምክንያት በፖለቲካ አመለከክታቸው ብቻ ታስረው በየእስር ቤቱ እየተሰቃዩ የሚገኙ የኦሮሞ ልጆች እንዲፈቱ እታገል ነበር። ዛሬ እነ ከበደ ገርባን የመሰለ ታጋይ ኦሮሞ በፖለቲካ አስተሰሰቡ ብቻ ታስሮ በሚስቃይባት ሀገር ተባብሮ የፖለቲከ እስረኞችን እንደማስፈታት የማይጠቅምና የማይደረስበት ዘር ቆጠራ ማንን ይጠቅመል?
ሌላው እቶ ቡልቻ በተደጋጋሚ ስለነፍጠኛው ስርዓት ለመንቀፍ መሞክራቸው ምን ያለበት ምን አይችልም። አይነት አይሆንምን? በመጀመሪያ በአጼው ዘመነ መንግስት ተምሮ ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ ነፍጠኛ ወይም የንፍጥኛው ስርዓት ደጋፊና አጫፋሪ ላባላዚያ ካላይ ካጣቀሰኳቸው ቤተሰብ አባለ መሆን ግድ ነበር። ከዚህም በላይ በአጼው ስርዓት የተሻለ ቦታ ለመያዝ የዚያ ሥርዓት ቀኝ እጅ መሆን ደግሞ ትልቁ ክራየቴሪያ ነበር። እርስዎ በአጼው ስርዓት እጅግ ታማኝ ባለሙዋሎች ከሚቀመጡበት የተሻለውን ቦታ ይዘው እንደነበር የታዋቃል፡፡ በዚህም የወቅቱ የሥርዓቱ ደጋፊ አሜሪካ ከሥርዓቱ ጋር ለነበረው ወዳጅነት ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ በዓለም ባንክ የመጀመሪያው ጥቁር ሆነው በቀጥታ እነዲገቡ ተደረጓል፡፡
በነፍጠኛው ሥርዓት ብዙ ጋሻ መሬት ኖሮአችሁ በርካታ ኦሮሞዎችን ጭሰኛ አድርጋችሁ ስታስገብሩ አልነበርን ጅብ እንኩዋን ቁርበት አንጥፉልኝ የሚለው በማያውቁት ሀግር ሄዶ ነው፡፡ እርስዎ ግን እዚሁ ይህን ሁሉ ባደረጉበት ቦታ ነዎት፤ ሌላው እርስዎ በአሜሪካን ሀገር ሄደው የተማሩት በወቅቱ የነፍጥኛው ስርዓት ማገር ስለነበሩ ነው። በተጨማሪ የእክሊሉ ሀብተወልድ ሥርዓት አልፎ አጭርና የሶስት ወር ቆይታ በነበረው የልጃችው የልጅ መኮንን ሥርዓት ውስጥ ባለሙሉ ስልጣን የግብርና ሚንስቴር ተደርገው የነብረው የውቅቱ የነፍጠኛው ሥርዓት ምሰሶና አቀንቃኝ ስለነብሩ እንጂ ለኦሮም ህዝብ ይታገሉ ስለነበረ አይደለም።
በወቅቱ እርስዎ የዓለም ባንክ ስራተኛ በነብሩበት ጊዜ ከእርስዎ ቀጥሎ ሁለተኛ ጥቁር በቦታው እንዲገባ ጠቁመውና ምሥክርነት ሰጥትው እንዲቀጠር ያደረጉት አክሎክ ቢራራን ነው። እርሳቸው ደግሞ አማራ እንጂ ኦሮሞ አይደሉም። ያን ጊዜ የተማረ ኦሮም ጠፍቶ አይደለም። እርስዎ አማራ ወዳጅዎን ያስቀጠሩት ገንዘብህ ባለበት በዚያ ደግሞ ልብህ አለ ያለውን የመጽሐፍ ቃል ለመፈጸም እንጂ፤ እኔ ማንም ኢትዮጵያዊ የተሻለ ቦታ ቢቀመጥ ግድ የለኝም። እርስዎ ደርሰው የኦሮሞ ተቆርቁዋሪ ነኝ ስላሉ ሲያደርጉ የነብሩት ነገር እንዳይሸፈን ገለጥ ለማድረግ ነው። በዚህ ጉዳይ ከኔ የተሻለ ዕውቀት ያለቸው ሰዎች አሉና ከዚህ በመነሳት ዘርዘር አድርገው እንደሚጽፉት እሙን ነው። ሌላው ለአስራ ሰባት ዓመት ደርግ ይህቺን ሀገር ሲገዛ በእርግጥ ከአሁኖቹ ተቃዋሚዎች አንደንዶች የኢሠፓ ከፍተኛ አምራር የነበሩ ሲሆን አንዳንዶች ግን ባሉበት ሆነው ስልብሔራቸው ሲጮሁ ነበር። እርስዎ ግን ኢህአዴግ ሀግሪቱን ሲቆጣጠር ነው ኦሮሞ ፌዴራሊስት የሚል መታውቂያ ይዘው የገቡት። ያም ሆኖ በፊትም ቢሆን የኖሩት ከፊውዳሎች ጋር ስለነበረ ቀጥሎም በአሜሪካ ሲቀማጠሉ በመኖርዎ የኦሮሞን ህዝብ ባህል ባለማወቅ የኦሮሞን ህዝብ ከሌላው ለመለየት ሲሰሩ የታያል፡፡ ዋናው የእርስዎ ዓላማ ግን በፊውዳሉ ሥርዓት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ሲደርስ ለነበረው በደል ከበዳዮቹ ጎን ቆመው ስለነበረና አብረው ሲበደሉ ሰለነበረ ይህንን በደል የኦሮሞ ህዝብ እንዳይቆጥርብዎት ለማድረግ የሚደክሙ ይመስለኛል። ለነገሩ ከመላዕክት ቀጥሎ በይቅርባይነቱ ተወዳዳሪ የሌለው የኦሮሞ ህዝብ በደልዎን ስለማይቆጥር ተጨማሪ ጥፋት ከመስራት ቢቆጠቡ መልካም ነው።
ልክ አሁነ እርስዎ እንደሚደርጉት በተለያየ ጊዜ የሀገራችንን ህዝብ ለመከፋፈል የተሞከረ ሲሆን ብዙው የመከፋፈል ዓላማ በብልህ መሪዎች እና በጀግኖቹ የኢትዮጵያ አርበኞች ሳይሰካ ቀርቷል። በዋህነት በተደረገ እንግዳ ማክበር ግን አንዱ ተሳክቶለቸዋል። በአንድ ወቅት ሁለት አውሮፓውያን ወደ ንጉሱ ይመጡና ልናስተምር ከሀገራችን ተልከን መጥተን ነው ይሉአችዋል። ምንድን ነው የምተስተምሩት ክርስትና ይሉአቸዋል። ሁለታችሁም አንድ ዓይነት ዶግማና ቀኖና ነው ያላችሁ ሲሉአችው የለም የተለያየን ነን ይላሉ። ዓላማው ክርስትናን መስበክ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንን በዓመለካከት መከፋፈል መሆኑ የገባቸው ንጉሱ። የማን ፊሎሶፊ ትክክል ነው ይሉአቸወል። በአጋጣሚ ሳይዘጋጁበት ስለተጠየቁ፤ አንዱ የኔ ነው አንዱም የኔ ነው ይለል። ንጉሱም ሂዱና ተስማምታችሁ ኑ ብለው ያበርሩአችዋል። አነደነትን የነፍጠኛ ፓረቲ ነው ከማለት በመጀመሪያ ካፋፋዮቻችን ከራሳችሁ ጋር ተስማሙ፡፡
በሌላ ጊዜም እንዲሁ አንዱ ሀይመኖት ለማስተመር መምጣቱን ሲነግራቸው ንጉሱ የእጅ ጥበብ የሚያስተምረን እንጂ ሀይመኖት የሚየስተምሩ መምህራን የምንማርበት መጽሐፍት አሉን ብለው አሰናብተው ወደ ሀግሩ የሚሸኙት መንገድ አሳይ አብረው ሰጡና ያሰናብቱታል። ያም ሰው ወደ ድንበር እንደደረስ አሞኛል በማለት ለተወሰነ ጊዜ ከአንድ ሰው ቤት ይተኛና ሁለቱን ሰዎች አንዱን ሳሎን አንዱን ጓዳ አድርጎ ለአንዱ ጸጋ አንዱን ቅባት ብሎ አንዱን ክርስትና አንድ ተንኮለኛ አውሮፓዊ ሰው ለሁለት ከፍሎ አንድ አሳብ የነበሩ ሁለት ኢትዮጵያውያንን ልባቸውን ለሁለት ከፈላቸው።እነርሱም የጎጃምን ህዝብ ለሁለት ከፍለው አፋጁት። ያም ፈረንጅ ንጉሱ እኔን ሳይቀበለኝ ቢቀርም እኔ ግን በሽተኛ መስዬ ተኝቼ ኢትዮጵያውያንን የተለያየ አመለከክት አስይዤ ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብና የማይነቀል እሾህ ለኢትዮጵያ ተክየባታለሁ፡፡ አለ ይባላል። ያ ችግር እስካሁን አለ የአቶ ቡልቻንም የመከፈፈል ሀሳብ ስር ሳይሰድ መመታት ስላለበት ነው።የእርሳቸው ሀሳብ ለትውልዱ ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ ቦንብ መቅበር ነው፡፡ ዛሬ ትውልዱ ዘር ለመቁጠር ሥራም ኣላጣ ሚስት እንኩዋን ሲያገባ ፍቅር እንጂ ዘር አይቆጥርም። እርግጠኛ ሆኜ ስለትውልዱ መናገር የምችለው ጋብቻን በመግባባት እና በፈቃቀር እንጂ የማን ዘር ነሽ የሚለውን ጥያቄ ትቶታል። ስለዚህ የነ አቶ ቡልቻ ድካም ከንቱ ነው ባይነኝ።
ህዝብ በመከፋፈል የሚገኝ ትርፍ ሀገር መበታተን ብቻ ነው። ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ኖራ አቶ ቡልቻ አዋሽ የሚባል ባንክ ለመመሥረትና ሚኒሊክ ባካለሉት ክልል ያለከልካይ አንዱን በደቡብ ክልል በአዋሳ፣ አንዱን በሶማሊያ ክልል በጂጂጋ፣አንዱን በሐረሪ ክልል በሐረር ፣ በኣማራ ክልል በደሴና በመሳሰሉት ማቋቋም የቻሉት ሚኒሊክ ከአፍሪካ ቅኝ ገዢዎች ጋር እኩሌታውን በሀይል ቀሪውን በመደራደር ድንበር ስላካለሉ በሚኒሊክ ክልል ውስጥ እንደ ፈለጉ ማቆም ሲችሉ ነገር ግን ከድንበሩዋ አንድ ስንዝር አለፍ ብሎ ማቆም ያልተቻለው የሌላ ሀገር ስለሆነ ነው። እዚህች ቅርብ በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ ድንበር ቶጎ ጫሌ ላይ የእኛን ሀገር ባንክ መክፈት የሚቻለው ከድልድዩ ወዲህ ብቻ ነው። ከድልድዩ ማዶ የሱማልያ ክልል ስለሆነ አይቻልም። ሚኒሊክ ያንን በማድረጋቸው ዛሬ ላይ ከማንም በላይ አቶ ቡልቻን ጠቅሟል። መቼም እርሳቸውን በየስርዓቱ እነዲጠቀሙ እግዜር ስለፈቀደ ብዙዎች በሚታሰሩባት ሀገር እርሳቸው እንደፈለጉ ይሆናሉ፡፡ ሀገሪቱ መቼም ለሚገለባበጡት ነው የምትሆነው፡፡ ንጡሐንማ ያልታደለ በር ቆዳው አታሞ የሆናል እንዲሉ ባየእስር ቤቱ ይማቅቃሉ፡፡
ሌላው በዚህ ሰዓት ሚኒሊክን የሚወቅስ ሰው ካለ የዓለምን ስቴት ፎርሜሽን ሂደት ያልተረዳ ሰው እንደሆነ ይገባኛል።ዕልጣንን ተረክቦ ሀገር ለመምራት የሚታገል አንድ ሰው ባማጃማሪያ ስለስቴት አመሠራረት ማወቅ ይጠበቅበታለ፡፡ ስቴት ሲመሰረት የራሱ ሂደት ዓለው ያ ሂደቱ ደግሞ በርካታ የነበሩ መንግስታትን ወደ አንድ የማምጣና ግዛትን የማስፋፋት ሂዳት ስለሆነ ግጭቶች ይፈጠሩና ጦርነቶች ይቀሰቀሱ ዘንድ ግድ ይላል። ዛሬ ላይ አቶ ቡልቻ ሊያስታውሱት ያልቻሉት ሚኒሊክ በዚያን ጊዜ በመላ ሀገሪቱ ዞረው ግዛቱን ባያስፋፉ ኖሮ የአሁኑዋ ኢትዮጵያ ትኖር ነበር ወይ የሚለውን ነው፡፡ደግሞስ እርሳቸው ላቆሙት ድርጅት በደቡብ ለማቆም የደቡብን መንግስትን መጠየቅ ግድ አይሆንም ነበር ወይ? ያስ ቢሆን ደግሞ እንዴት ይቻላል። የተለያየ ሀገር ስለሚሆን የመገበያያ ገንዘቡ አንድ ስለማይሆን ዛሬ በኬኒያ፣ በሱማሌና በሱዳን መክፈት እንዳልቻሉት እንዲሁም በሀዋሳና በደሴ መክፈት እንደማይችሉ እንዴት ሊግባቸው አልቻለም።ለነገሩ ዕወቅ ያለው በአርባ ቀን ሲያውቅ አትወቅ ያለው በአርባ ዓመቱ አያውቅም፡፡ እንደተባለው ነው። ጀርመን ስትመሠረት የነበረውን ከፍተኛ ፍጅት ቢያነቡ በቂ ይሆን ነበር።
አቶ ቡልቻ ይህንን ይሰማሉ ወይም አንብበው ይረዳሉ በሚል ግምት ሳይሆን ሌላው አንባቢ እንዲረዳና ተመዝግቦ ለታሪክ እንዲቀመጥ ብቻ ይህንን ማለት ወደድኩ እርሳቸው በተደጋጋሚ የአንድነት ፓርቲን የአዲሳባ ልሂቃንና የአማራ ፓርቲ ነው ይላሉ። ይህ አንጋገር እርሳቸው ሲናገሩት እንድነትን እየመረቁት ነው ማለት ነው። እኛ ትክክሉን ስንነግራቸው ስድብ ነው ይላሉ። ለማንኛውም ስለዚህ ነገር ሁለት ጥያቄ ልጥይቃቸውና አንዱን ብቻ በትክክል ከመለሱልኝ የእርሳቸው ሀሳብ ትክክል ነው ብየ ልከተላቸው ለነግሩ አንዱን አይደለም ግማሹን አይመልሱትም። የመጀመሪያው ጥያቄ እርስዎ ብሔርዎት ምንድን ነው ይሚለው ነው? እርስዎ ሲወለዱ የስንት ዓመት ልጅ ሆነው ተወለዱ? የተወለዱትስ እንዴት ነበር? እናትዎ እርስዎን ለመውለድ ምጥ በያዛቸው ጊዜ ከጎረቤቶቻችሁ ውስጥ እነማን ነበሩ? ይህንን ግን እናትዎት የነገሩዎትን እና በእምነት የተቀበሉትን ሳይሆን እርስዎ የሚያውቁትን ብቻ እንዲንግሩኝ እፈልጋለሁ። ይህንን በትክክል የሚያውቁትን የተወለዱበትን ቦታ የተወለዱበትን ሰዓት መናገር ከቻሉ እርስዎ የሚናገሩት ሁሉ ትክክል ነው ማለት ስለሆነ ልቀበልዎት።
ያለበለዚያ እርስዎም ሲወለዱ እንደኔና እንደሌላው ሰው ሁሉ ተወልደው ከሆነ እንኩዋን ብሔርዎትን ይቅርና እናትዎትንም በእምነት ነው የተቀበሉት እንጂ እርግጠኛ አይደሉም። ስለዚህ እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ መናገር አይቻልም። ቋነቋም ከሆነ በአጋጣሚ እርስዎ ተወልጄበታልሁ ከሚሉት ቦታ በአሻጋሪ ካለው ቦታ ከሌላ ብሔር ተወልደው በምሥራቅ ወለጋ ስላደጉ ኦሮምኛ ችለው ይሆናል። ምክንያቱም ቋነቋ እንደሆን ያደጉበትን እንጂ የተወለዱበትን ዘር ማንጸባረቂያ አይደለም። ለዚህም ምስክር ከሁለት ኢትዮጵያውያን በእንግሊዝ ሀገር የተወልዱና ያደጉ ልጆች እንግሊዝኛ እንጂ የቤተሰቦቻቸውን ብሔር ቋነቋአለመቻል አንዱ ምሥክር ነው።የመለያየት ፖለቲካ የሠይጣንና የቅኝ ገዥዎች ነው።
አባቶቻችን እንደርስዎ ቢሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያን ማግኘት እንዴት በከበደ ነበር። ምክንያቱም የተለያየ ቋነቋ ባህልና ሀይማኖት ስላለን ለማለት ነው። ግን ሚኒሊክ አትዮጵያን ከመሠረቱ በሁዋላ ጣሊያን ሀግራችንን ሊወር ሲመጣ የከምባታ፣የሶማሌ፣የአፋር፣የሀረሪ፣የቤንሻንጉል፣የ
አቶ ቡልቻ በተደጋጋሚ ስለመለያየትና መበታተን ሲናገሩ ነኝ የሚሉትን ብሔር አለማወቃቸው ያሳዝነኛል። አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ስትመሰረት የአንበሳውን ድርሻ በወቅቱ የነበሩት የኦሮሞ ልጆች ይወስዱታል። ኦርሞ በባህሉ እንግዳ ተቀባይ አብሮት መኖር የሚፈልገውን ሰው በተለየ መልኩ በዘር ባይወለድ እንኩዋን እንደተወላጅ ኦሮሞ አድርጎ የመውሰድ ባህል ያለው ነው።በርካቶች ከአካባቢያቸው ለቀው ሥራ በሔዱበት ኦሮሞዎች ልጃቸውን ሚስት መሬታቸውን ርስት አድርገው ሰጥተው ኑዋሪ አድርገዋቸዋል። ለምሰሌ ጉዲፈቻ፣ሞጋፈቻና የመሳስሉት አንድን ኦሮሞ ያልሆነን ሰው ኦሮሞነትን የመስጫና የመቀበያ ስርዓቶች ናቸው። አንድ ሰው በትክክል ኦሮሞ ከሆነ እንደ አባቶቹ አንድ መሆንን ይሰብካል። አሁን እርስዎ እያራመዱት ካለው አመለካከትዎ ስነሳ በኦሮሞነትዎ ላይ ህሉ ጥያቄ እየፈጠረብኝ ነው።ልጅ አባቱን ካልመሰለ የአባቱ ልጅ አይደለም።
ሁለተኛው ጥያቄ አንድነት የአዲሳባ ልሂቃንና የአማራ ፓርቲ ስለመሆኑ እንዴት እርግጠኛ ሆኑ? ለምሳሌ ተወላጁ በእምነት ይቀበላል ቢባልም ያሰው ሲወለድ በቦታው የነበሩ ሰዎች ግን እርግጥኛ ናቸው። እስኪ አቶ ቡልቻ በእውነት እርስዎ እርግጥኛ ሆነው በተደጋገሚ ስለእንድነት ፓርቲ የአዲሳባ ልሂቃንና የአማራ ፓርቲ እንደሆነ ሲናገሩ እሰማለሁ። እኔን ጨምሮ ከአንድነት አባለት ሲወለዱ በቦታው ስለነበሩበት ሁለት ሰዎች ይጥቀሱ በእርግጥ ሊያደርጉት አይችሉም። ለምን በአንድነት ፓርቲ ላይ ያለዎትን ጥላቻ ከማንጽባረቅ የዘለለ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ተቃውሞ አያቀርቡምና ነው።
በዚህ ላይ አንድ ነገር ማየት ከተቻለ አቶ ቡልቻ ማንም አማራ፣ትግሬ፣ደቡብ፣አፋር፣…ወይም ሱማሌ ሆኖ ለመወለድ አምልክቶ የተወለደ የለም። የሰው ልጅ ድግሞ ሰው ሆኖ መወለዱ ይበቃዋል። ምንም ሆኖ መወለድ ሀጢያት አይደለም። ግለሰቦች እንዲህ ነኝ ብለው ሊገዙ ይችላሉ። ግለሰቦች ሲገዙ ለሚሰሩት ስህተት ደግሞ ህዝብ አይጠየቅም። አቶ ቡልቻ በሚገርም ሁኔታ የኣማራ ህዝብ ያለበትን ሁኔታ ቢያውቁ ኖሮ እርስዎ ለራስዎ ይህን ህዝብ የሚረዳ ፓርቲ ያቋቁሙ ነበር።አንድነት ፓርቲን የአመራ ነው ከማለት በፊት የአንድነትን አደረጃጀት ማወቅ ተገቢ ነው። አንድነት የተሻለ አደረጃጀት ከአማራ ክልል ይልቅ በደቡብ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል፣ በአፋር፣ በቤኒሻንጉልና በትግራይ ክልሎች አሉት። ይህንን ፓርቲ የዚህ አካል ነው ብሎ መክሰስ እርስዎ አሁን የቆሙበት ቦታ በመጀመሪያ ኢህአዴግን ተከትለው መጥተው ቆሜበታለሁ ባሉበት ቦታ ናቸውን የሚል ጥያቄ ያስነሳብዎታልና ቆም ብለው አስበው ስለ አባባልዎ ማስተባብያ ቢሰጡ መልካም ነው።
ሌላው የተከበራችሁት የአንድነት ደጋፊዎች አሁን አንድነት ፓርቲ በመላው ሀገሪቱ የጀመርውን ሀዝበዊ እንቅስቃሴ ማሰናከያ አንዱ መንገድ የአቶ ቡልቻ ክስ ሊሆን ስለሚችል በተለያየ የግል አመለካክት ስለሚስጡ ሰንካላ ምክንያቶች ሳትዘናጉ ከአንድነት ጋር በመቆም በገዢው ፓርቲ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር እንችል ዘንድ የአክብሮት ጥሪየን አስተላልፋለሁ። ለሳምንት ቸር ይግጠመን