ከወንድማገኘሁ አዲስ
ወያኔ በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለሀገራችንና ለህዝቧ ከቀመመው መርዝ የቀረውንና የከፋውን በፍጥነትና በትጋት እየረጨ ይገኛል። ከዚህ በከፋ ሁኔታ አደጋ የተጋረጠበት አገር ያለ አይመስለኝም::
በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተቀነባበረው በቅማንት የማንነት ጥያቄ ሽፉን የተለወሰው መሰሪ ተንኮል የቅማንትን ህዝብ አብሮት ለዘመናት በፍቅርና በትስስር ከኖረው የአማራ ህዝብ ጋ ለማፋጀት የተቀመመ እና በእጅጉ የከፋ መርዝ ነው። ይህን ደርጊት እንደ ከዚህ ቀደሞቹ የወያኔ ስውርና ግልፅ ክንውኖች በዝምታ ከተመለከትነው ውጤቱ በአሰከፊነቱ ተወዳዳሪ የሌለው ከመሆኑም በላይ ለጎንደርና ለአማራው ህዝብ ብቻ ሳይሆን ጦሱ ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ እንደሚተርፍ ልንገነዘብ ይገባል።
እነሆ ወያኔ የመጨረሻውን ካርድ መዟል። የሰሜን ምእራብ መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የክህደቱን የመጨረሻ ውል ተዋውሎ ለተግባራዊነቱ ደፋ ቀና እያለ ይገኛል። ይህንን ለማድረግ የቀረው እጅግ በጣም አጭር ጊዜ ነው።
ይህንን ድርጊት ካላመከንነው አገራችን ዳግም ዳር ድንበሯ ሊገሰስ፣ ሉአላዊነቷ ሊደፈር ነው። ባካባቢው ያሉ ኢትዮጲያዊያን በሁለት ቢላ ሊታረዱ እጅግ ከተሻለም በባርነት ሲሸማቀቁ ሊኖሩና ቀያቸውን ጥለው ሊሰደዱ ነው። አያት ቅድመ አያቶቻቸው ደማቸውን ዋጅተው አጥንታቸውን ከስክሰው ያቀኑት ፣ ተወልደው የወለዱበት ፣ አድገው ያሳደጉበት፣ ተድረው የዳሩበትን ቀዬ ሊነጠቁ ነው። ከአንድ ወር ገደማ በኋላ የሚያርሱት መሬት፣ የሚጠምዱት በሬ ፣የሚገበያዩበት ገበያ፣ የሚስሙት ቤተስኪያን፣ የሚፀልዩበት መስጅድ አይኖራቸውም።ሩዋንዳ እየተደገመ ነው። የቁጥር ልዩነት ካልሆነ በቀር ሰው እየታረደ ሁሉም ዘግናኝ ድርጊቶች ዘርን መሰረት አድርገው እየተካሄዱ ነው።
ስለዚህ ማንኛውም አገሬንና ወገኔን የሚል ኢትዮጲያዊ ሁሉ
_ ይህንን እኩይ ድርጊት ከወዲሁ ማውገዝ
_ በየአካባቢው ተደራጅቶ የፋሽስቱን መንግስት አገር አጥፊ ተግባራት መመከት
_ በተለይም የጎንደርና የቅማንት ህዝቦች አብሮነታች ሁን ሊያጨልሙ በማንነት ጥያቄ ሽፋን አገራችሁንና ነፍሳችሁን ጭምር ሊነጥቋችሁ ወያኔዎች ደጃፋች ሁ ላይ ናቸውና እምቢታችሁን ዛሬውኑ በማሳዬት
_ በድንበር አካባቢ ያላችሁ ኢትዮጲያዊያንም ምንም አይነት የማካለል ድርጊት እንዳይደረግ በማሰናከልና አንገት ላንገት በመተናነቅ
_ በውጪ የምትገኙ ኢትዮጲያዊያን ለተመድ ፣ ለአለምአቀፉ ማህረሰብ አና ተፅእኖ ሊፈጥሩ ለሚችሉ አገራት እንዲሁም ለታላላቅ የዜና አውታራትበማሳወቅ፣ በከፍተኛ ደረጃ በተደራጀ እና ለየት ባለ መልክ በረሀብና በመቀመጥ በሰላማዊ ሰልፍና በተለያዩ የፈጠራ እንቅስቃሴዎች አለም አቀፍ ትኩ ረትን በመሳብ
_ ኢሳትና ሌሎች የኢትዮጲያውያን የመረጃ ተቋማት ድረገፇች የፓልቶክ ሩሞች ሁኔታውን አሰረመልክቶ ሰፊ ሽፋን በመስጠት፣ ህዝቡን በማስተባበርና በመቀ ስቀስ
_ የፖለቲካ ድርጅቶች ቢያንስ በዚህ ክፉ ቀን ለዚህች መከረኛ አገርና ለዚህ እንግልት ህዝብ ሲባል ልዩነታ ችሁን በይደር አስቀምጣችሁ ሁኔታውን ለመቀልበስ በጋራ በመስራት
_ በትጥቅ ትግል የሚታገሉ ድርጅቶች ከተቻለ ድንበር የማካለሉን እንቅስቃሴ የማወክ ኦፕሬሽን በማድረግ
_ አገር ወዳድ ምሁራን ዲፕሎማቶችና የፖለቲካ ድርጅ መሪዎች ለሱዳን መንግስት ሁኔታው ውሎ አድሮ የሚያስከትለውን መዘዝ በማስረዳት ከዚህ አጥፍቶ
ሊጠፋ እየተዘጋጀ ካለ ስርአት ጋ ምንም አይነት ውል እንዳይዋዋልና አስቀድሞ የተዋዋለውንም ተግባራዊ እንዳያደርግ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም አገሪቱ በህዝብ በተመረጠ መንግስት በምትመራበት ወቅት ድርድር ማድረግ ለሁሉም የሚበጅ አማራጭ መሆ ኑን በማስረዳት::
እንዲሁም የተለያዩ ፈጣን የትግል ስልቶችን በማቀነባበርና በማጣመር ተግባራዊ ማድረግ የወቅቱ አገር አድን ተግባር ሊሆን ይገባዋል። ይህንን የወያኔ አገር አፍራሽ ሴራ እያዬንና እየሰማን በዘርና በቡድን ተከፋፍለን የመፍትሄው አካል መሆን ካቃተን የምናጣው የጋራ ቤታችን የሆነችውን አገራችንን ነው።የምናጣው ህዝባችንን ነው። ተጎናፅፈነው የምንዋብበት ባንዲራ እውነትም ጨርቅ የሚሆነው ያኔ ነው። ስለ ኢትዮጲያ የምንቀኘውና የምንዘምረው ሁሉ ውሸት የውሸት ውሸት ነው ማለት ነው። መቼም ሊጠግግ የማይችል የህሊና ቁስል እንደተሸከምን ኖረን ነው የምናልፈው። ለልጆቻችንም የምናወርሳት ኢተዮጲያ አትኖረንም። ለልጆቹ አገር ያላስረከበ አባት ለልጆቿ አገር ያላስረከበች እናት እሱም አባት አይደለም እሷም እናት አይደለችም።
ለዚህ ጊዜ ያልሆነ ኢትዮጲያዊነት ኢትዮጲያዊነት አይደለም::