June 22, 2013
66 mins read

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ – ከገብረመድህን አረአያ (አዳዲስ መረጃዎች)

ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 .ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው::

ደርግ

የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ ፣ በተማሪው ፣ በአስተማሪው ፣ በመንግስት ሰራተኛው ፣ በወዛደሩ ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ::

ህዝባዊ አመጹን የሚመራው የተደረጀ ፓርቲ ባለመኖሩ በር የተከፈተለት መለዮ ለባሽ አመቺ ሁኔታ በማግኘቱ በፍጥነት ተደራጅቶ ከተራ ወታደር ጀምሮ የተለያዩ ማእረግ ያላቸው አባላቱን አስመርጦ ወደ 120 የሚጠጉ ተወካዮቹን አዲስ አበባ በሚገኘው አራተኛ ክፍለጦር አሰባሰበ::

ከጦር ሃይሎች ፣ ከክቡር ዘበኛ እና ከፖሊስ የተውጣጡት እንኚሁ መለዮ ለባሾች በሰኔ ወር 1966 ዓ.ም. ተሰብስበው ብሄራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ መስርተው “ኢትዮጵያ ትቅደም ፣ አቆርቋዥ ይውደም” በሚል መርህ ስር ሰፊ ሊባል የሚችል የህዝብ ድጋፍም አግኝተው ነበር::

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም. የተመሰረተው አስተባባሪ ኮሚቴ ንጉሱን ከስልጣን አውርዶ “ጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ” የሚል ስም በመያዝ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ጀመረ:: ቀስ በቀስም ደርግ የስልጣን ወንበሩን በማመቻቸት የሃገሪቷ መንግስት ለመሆን ቻለ::

በወቅቱ በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች ሃገራት ሶሻሊዝም ወይም ህብረተሰባዊነት በሚባል ርዕዮተ አለም እድገት እና ብልጽግና የማይገኝበት “ላም አለኝ በሰማይ ወተቷን የማላይ” ስርዓት በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት እና ቻይና ፕሮፖጋንዳ አለምን እንደማዕበል ሲወዘውዛት የነበረበው ሁኔታ ሆኖ በደርግ የተመሰረተው መንግስት ግራና ቀኙን ሳይመለከት ሶሻሊዝም በኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈጥረውን ቀውስ እና ችግር ሳያጤን እና ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትን ሳያማክር በ1972 ዓ.ም. ኢሰፓአኮን(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን) መሰረተ:: ይህንን ምስረታ ተከትሎም ደርግ አንድ እግሩን ገደል ከተተው::

በዚህ ጽሁፍ ሁለት ነገሮችን ለያይቼ በማሳየት ለማለፍ እሞክራለሁኝ፤

1.      ደርግ እንደ ፖለቲካ ተቋም እና ስርዓት

2.     መለዮ ለባሹ እንደ አገር መከላከያ ሰራዊት

ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኢትዮጵያዊ የሆነ እና በዘመናዊነቱ በአፍሪካ ጭምር ተወዳዳሪ ያልነበረው እንደነበር ነው:: የደርግ ስርዓት ከወታደሩ በወጡ ሰዎች ቢመሰረትም ሰራዊቱ ግን በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ ሰራዊት ለመሆኑ ከጥያቄ ውስጥ ሊያስግባው የሚችል አንዳችም መከራከሪያ ሊቀርብ አይችልም:: አገራችን ዘመናዊ ጦር ማደረጀት ከጀመረችበት ከሃያኛው ክፍለዘመን መባቻ ጀምሮ በስንት ወጪ እና ጥረት የገነባችውን ጦር የ “ደርግ ጦር” የሚል ቅጽል በመስጠት ከፍተኛ የሆነ የስም እና የሞራል ማጥፋት ዘመቻ የፈጸሙበት ጸረ ኢትዮጵያ የሆኑት ወያኔ እና ሻዕቢያ ናቸው::

ይህ ጦር ደሙን አፍስሶ ፣ አጥንቱን ከስክሶ ፤ ራበኝ ፣ ደክመኝ ሳይል ወያኔ እና ሻዕቢያን እግር እግራቸውን እየተከታተለ ሲደመሥሳቸው እና ሲያጠፋቸው የነበረ የኢትዮጵያ ብርቅ ልጅ ነው:: የዛሬው የወያኔ ዘረኛ ሰራዊት ግን እንኳን ስለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ሊከላከል ይቅርና ራሱ የወያኔ ሰራዊት ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ ህዝብ የአንድ ጎጠኛና ዘረኛ ታጣቂ ቡድን ነው:: አሁን ያለው በዘር የተደራጀው ቅጥረኛ እና ባንዳ ሰራዊት በየትኛውም መለኪያ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ተብሎ ሊወሰድ የሚችልበት ሁኔታ የለም::

የደርግ መንግስት በስልጣን በቆየበት 17 አመት ውስጥ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ቀይ ባህርን የጠበቀ ፤ ከገንጣይ እና አስገንጣዮች አገሪቷን እየተከላከለ ሉዓላዊነትን የጠበቀ የኢትዮጵያ ስርዓት ነበር::

በሚከተለው ርዕዮተ አለም ቀስ በቀስ እየተዳከመ በመሄድ እንደነበረው አገርና ህዝብ ለማዳን አልቻለም:: ደርግ በተዳከመ ጊዜም ሰራዊቱ ይዳከማል:: አንድ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከመንግስት የሚቀርብለት ነገሮች ብዙ ናቸው:: ይህ አልሆነም:: ሰራዊቱም መንግስት በመዳከሙ ምክንያት የነበረው አልበገር ባይነት ስሜቱ እና ጀግንነቱ የውጊያ ብቃቱ ተስፋ በመቁረጡ ችግር እየፈጠረለት ሄደ ቢሆንም ግን ወያኔም ሆነ ሻዕቢያ አሁንም ፈቀቅ ሊሉ አልቻሉም:: የማይበገር የኢትዮጵያ ሰራዊት መሆኑን ያውቁታል እና::

ይህ በዚሁ እንዳለ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት መንግስቱ ሃይለማሪያም ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ለቀው ዚምባብዌ ሃራሬ ገቡ:: እዛም ጥገኝነት ጠየቁ:: መሆን የማይገባውን ስራ ሰሩ:: በኢትዮጵያ ሃገራቸው ሰርተው ሂወታቸው ቢያልፍ ታላቅ ስምና ክብር ያገኙ ነበር:: ግን አላደረጉትም:: ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሰራዊት ተበተነ::

ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፕሬዚደንት መንግስቱ እግር የተተኩት ጀነራል ተስፋዬ ገብረኪዳን በዜና እወጃ የኢትዮጵያ ሰራዊት የነበርከው በያለህበት ቦታ መሳሪያህን ለህወሃት(ኢህአዴግ) እና ለሻዕቢያ እያስረከብክ ወደ ምትፈልግበት ሂድ፤ ሻዕቢያም ኤርትራን ህወሃትም ኢትዮጵያን እንዲቆጣጠሩ ፈቅደናል በማለት ፍጹም ክህደት በሆነ መንገድ ኢትዮጵያ እና ህዝብዋን ለደመኛ ጠላቶች አሳልፈው ሰጡ::

ያን በወታደራዊ ሳይንስ እና የጦር ውጊያ የተከማቸ እውቀት እና ችሎታ የነበረውን የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሰራዊት እልም ባለ ገደል ወረወሩት:: ለስንት አመታት የሃገሩን ዳር ድንበር ያስከበረ እና የጠበቀ ጦር ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. ካልምንም መተዳደሪያ እና የአገልግሎት ክፍያ በየበረሃው ተበተነ:: በስንት ሚሊዮን የሚቆጠሩ የምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ አየር ወለድ እና አየር መቃወሚያ አባላት እና ቤተሰቦች ለመከራ እና ለችግር ተዳረጉ::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔና ሻዕቢያ:: ሻዕቢያ ኤርትራን ሲቆጣጠር ወያኔ ህወሃት ደግሞ ግንቦት 15 ቀን 1983 ዓ.ም. በፈንደቀለት ጸሃይ አዲስ አበባን ግንቦት 20 ቀን 1983 ተቆጣጠረ:: ኢትዮጵያም ለፋሺስት መሪዎች ተዳረገች:: ሰራዊቱ እየጫነ ካለምንም ችግር ካለ ምንም ውጊያ ወያኔ ኢትዮጵያን ተቆጣጠረ:: ከግንቦት 20 ቀን ጀምሮ ወያኔ በከፊል የተቆጣጠረው ወሎ ፣ ጎንደር እና ጎጃም ብቻ ነበር:: ቀሪው የኢትዮጵያ ግዛቶች በተለይ ደቡብ ምስራቅ-ምዕራብ ወያኔ የገባው ከሶስት ወር በኋላ ነበር እንጂ:: ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ አልተቆጣጠረም:: ወደ አዳዲስ ክፍለ ሃገራት ሲሄድ ብዙ ገንዘብ በመክፈል በነዋሪዎች እየተመራ ነው:: ምክንያቱም ወያኔ ህወሃት ከትግራይ አይወጣም ነበር::

ስለሆነም ለኢትዮጵያ ነጻነትና ዲሞክራሲ ስል ብዙ መስዋትነት ከፍያለሁ የሚለው ከንቱ ውሃ የማይቋጥር መፈክሩ ይህ ትልቅ ምስክርነት የሚያሳየው ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደማያውቃት ነው::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ምን ይዛ መጣች? በግንቦት 20 ኢትዮጵያ አገራችን በጨለማ ጉም ተሸፈነች:: አገርና ህዝብ ጥቁር የሃዘን ልብስ ለበሱ:: ሲጠሏት እና ታሪኳን እና ህዝቧን ሲያዋርዱን ሲያንቋሽሹ በነበሩት ወያኔ ህወሃት ለእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ተዳረገች:: ዘረኛው እና ጎጠኛው ወያኔ ህወሃት በመለስ ዜናዊ የሚመራው የማፍያ ፋሺስት ግልገል እና ግብረ አበሮቹ ጸረ ሀገር እና ጸረ ህዝብ የሆኑትን ለዘመናት የተከበረው የምኒሊክ ቤተ መንግስት ተቆጣጥረው የግልገል ፋሺስቶች መንደላቀቂያ ሆነ:: እነሱም ስልጣን እንደጨበጡ ኤርትራን አስገንጥለው የቀይ ባህር ንግስት የነበረችው ኢትዮጵያ ወደብ ወይም የባህር በርዋን አጥታ አንገትዋ የተቆረጠ ዝግ አገር አደረጉዋት::

ወያኔ ህወሃት ከደደቢት ይዞት የመጣውን ህገ ደንቡን የኢትዮጵያ ህገ መንግስት አደረገው:: ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት እና ኢትዮጵያዊነት አጠፋዋለሁ ብሎ ያመጣውን የዘረኝነት ህጉን በኢትዮጵያ ዘረጋ::

ይህ በዚህ እንዳለ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ እና ግንቦት 20 ምን ይዞለት መጣ? የኢትዮጵያ ህዝብስ ከግንቦት ሃያ ቀን ምን ተጠቀመ? ምን እድገት አገኘ? ፍትህና ነጻነቱ እንዲሁም ሰብዓዊ መብቱስ እንዴት ሆነ? የሃገሪቷ ሃብትስ በትክክል ለህዝብ ጥቅም ዋለ ወይስ ምን ሆነ? የትምህርት እድገቱስ? የዘመናዊ ቴክኖሎጂስ ለህዝብ ተስፋፋ ወይ? ሌላም ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል:: ለሰው ልጅ አደገኛ ጠንቅ ዕጽ መስፋፋት ለምን? ሽርሙጥና መስፋፋት ለምን? ስራ አጥነት ፣ የወንጀል ድርጊት መስፋፋት እንዴት እና ለምን? የህዝብ መፈናቀል ለምን? የዘር ማጥፋት በኢትዮጵያ ስለምን ተደረገ? ወዘተ ::

ወደ ግንቦት 20 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ከ17 አመታት በፊት ወያኔ ህወሃት እንደተፈጠረ የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. የትግራይ ህዝብ የአደረበትን ስሜት ባጭሩ ልዳሥ::

ወያኔ ህወሃት በዚሁ ቀንና ወር ደደቢት በረሃ ሲወጣ የትግራይ ህዝብ የዚሁ እኩይ ድርጅት ማንነቱን አያውቅም ነበር:: ቀስ በቀስም በየቦታው ብቅ ጥልቅ ሲል የትግራይ ህዝብ አልተቀበለውም::በህዝቡ ወያኔ ህወዋት ተቀባይነት በማጣቱ የተነሳ ምክንያት ጭንቀትን ንዴት የተነሳ በሰላማዊ የትግራይ ተወላጆች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀመረ:: አስገድዶ ንብረቱን መውረስ እና አስገድዶ እርዳታ እንዲሰጥ ተደረገ:: ምክንያቱም የሚከላከልለት ረዳት የሌለው ህዝብ ሻዕቢያ፣ ወያኔ እና ጀብሃ ሶስቱ በየፊናቸው አስቸገሩት:: የትግራይ ህዝብ ከየቦታው እየተለቀመ ተገደለ::

ከዚህም ቀጠል በማድረግ ወያኔ ህወሃት በሃይማኖት ጣልቃ በመግባት ክርስቲያን ጸረ ክርስትና እስላሙ ጸረ እስልምና ሃይማኖታቸውን እንዲያወግዙ የተቻለውን ቢሰራም አልሆነለትም::

ጸረ ህወሃት እና ጸረ ሻዕቢያ እየተባሉ ያልሆነ ያላሰቡት ብዙ ፣  ብዙ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች ሃለዋ ወያኔ (06) እየገቡ እሱም/እርሳውም ተገድለው ቤት ያፈራው ሃብታቸው ተወርሰው ህጻናት አልባሌ ቦታ ወድቀው ቀርተዋል::

በየከተማው ወያኔ ህወሃት ሽብርተኞች () በማሰማራት በጠራራ ጸሃይ ብዙ ሰው ገድለዋል:: ህወሃት የትግራይን ህዝብ እንደግሉ መሳሪያ አድርጎ የሚናገረው የትግራይ ህዝብ ከመጀመሪያ ትግሉ ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም. ለወደፊትም አልተቀበለውም:: አይቀበለውምም:: ህወሃት የሚቀልደው ያለ ጉልበቱ ተማምኖ ነው:: ለዚሁም ዋና ምስክር ምርጫ 97 ዓ.ም. ትግራይ ወያኔ አልመረጠውም:: ለወደፊቱም ወያኔን አይመርጥም:: ሁለቱ ሊታረቅ የማይችል ቂም አላቸውና::

ወያኔ ህወሃት የትግራይ ወጣት ሴት ፣ ወንድ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት በማያውቁት የኤርትራ በረሃዎች ሞተዋል:: እዛው አጥንታቸው ተበታትኖ መቅረቱ የትግራይ ህዝብ እስከ አሁን ደም እያለቀሰ ያለበት ጊዜ ነው::

በአጠቃላይ በትግሉ ወቅት በትግራይ ህዝብ ወያኔ ህወሃት የፈጸመው ግፍ በከፍተኛ ወንጀል የሚይስጠይቀው ነው:: የትግራይ ህዝብ ወያኔ የተፈጠረባት የካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. በሚከበርበት ጊዜ በየቦታው የሚጠራበት ስም አለው:: በተምቤን አካባቢ “የተረገመች ቀን” ሲላት በአድዋና አክሱም አካባቢ “የጨለማ ቀን”” ሲለው በሽሬ አካባቢ ደግሞ “የእልቂት ዘመን” ይለዋል::

ወያኔ ህወሃት በለስ ቀንቶት አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ቀን ግንቦት 20,1983  ኢትዮጵያ እና ህዝቧ በደመኛ ጠላታቸው የወደቁበት እና በእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ የመጣበት ቀን ነው::

ከዚሁ ቀን መነሻ በማድረግ ወያኔ በኢትዮጵያ ህዝብ የነበረው ቂም በቀል በማያቋርጥ ሁኔታ በ22 አመት የወያኔ ህወሃት አገዛዝ የወረደበት ግፍና ሰቆቃ ቀጥለን ባጭር ባጭሩ እንመልከት::

ግንቦት 21 ቀን 1983 ዓ.ም. ወያኔ ኤርትራን አስገነጠለ:: ኢትዮጵያንም ካለ ባህር በር አስቀራት::

ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ዝነኛው ምድር ጦር ፣ አየር ሃይል ፣ ባህር ሃይል ፣ ፖሊስ ወዘተ የጠላይ ጦር በማለት ይደርግ ስርዓት በራሱ ሂደት ተመናምኖ በወደቀበት ለብዙ አመታት የሃገሩ ዳር ድንበር ሲያስከብር ከጠላት ሲከላከል የነበረው ካለምንም ጡረታና መተዳደሪያ የ”ጠላት ጦር” በማለት ለልመና እና ለችግር ዳረገው:: የሚይስተዳድራቸው ቤተሰቡ በሚልዮኖች የሚቆጠር ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ተበታትነው ቀሩ:: ከትግራይ ይዟቸው የመጣ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሃገር መከላከያ ሰራዊት አደረገ:: ቀሪዎቹን ታጋዮች ደግሞ ፖሊስ ፣ ደህንነት በማለት ዘረኛ ሰራዊት በኢትዮጵያ አቋቋመ:: ይህም በምንም አይነት ኢትዮጵያን የማይወክሉ ሁሉም ከላይ እስከ ታች ለነዚህ ተሰጠ:: እነዚህም በፊናቸው በኢትዮጵያ ህዝብ አስከፊ ሰቆቃና ግድያ በህዝቡ እየፈጸሙ ይገኛሉ::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማራ:: ዘር ማጥፋቱን ገና ከ1969 ዓ.ም. የጀመረው ሲሆን በበለጠ ደግሞ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ አማራው ከያለበት እየተፈለገ ዘሩን ማጥፋት ተጧጧፈ ቀጥሎም ኦሮሞ ፣ ጋምቤላ ፣ አፋር ፣ ቤኑሻንጉል ወዘተ :: በትግራይ ውስጥም አደገኛ ጠላት ናቸው የሚላቸውን በዘዴ አጠፋቸው::

ወያኔ ህወሃት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ የአማራው ቋንቋ ስለሆነ ይህ ቋንቋ የትምህክተኛና የነፍጠኛው ቋንቋ በየትኛውም ክልል እንድይነገር በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ መገናኛው እና ሃሳብ ለሃሳብ የሚለዋወጥበት ለስንት ሺህ አመታት ሲጠቀምበት የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔ ህወሃት እያጠፋው ይገኛል:: በየትኛውም ክልል አማርኛ መናገር በህጉ ከለከለው::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ሲያበቃ ለዘመናት ኢትዮጵያዊው ህዝብ በፈለገው ቦታ ሲኖርና በጋብቻ በደም የተዋሃደው ህዝብ ከየክልላችሁ ከሌላ ቦታ የመጣውን ተስፋፊ ህዝብ አስወጡ በማለት እርስ በርሱ በማጋጨት ብዙ ሂወት ጠፍቶ ንብረቱም ተዘርፎ በየበረሃው ተበትኖ ግንቦት 20 ቀን 1983 ይዞት የመጣውን መከራ ገፈት ቀማሽ ሆነ:: በተለይ አማራው::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወደብ አልባ ማድረጉ አልበቃ ብሎት በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሱዳን በእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ በምትደዳርበት ገዳሪፍ በተባለው የሱዳን ግዛት አስተዳዳሪ በነበረው ሻለቃ ጉዌን የወሰን መስመር ለጣልያኖች ይጠቅማል በማለት በ1903 እ.ኤ.አ በህገወጥ መንገድ የነደፈው የመስመር ክልል በአጼ ምኒልክ ኋላም በአጼ ሃይለስላሴ እና በደርግ መንግስት ውድቅ የተደረገው እና ተቀባይነት ያጣውን ወያኔ ህወሃት ከየት እንዳገኘው ሳይታወቅ የኢትዮጵያን የወሰን ድምበር በመጻረር ለወዳጁ ሱዳን ከሰቲት ሁመራ እስከ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ድረስ ወደውስጥ ከ40 እስከ 60 ኪ.ሜ. የሚዘልቅ እና 1,600ኪ.ሜ. ርዝመት ያለው ለሱዳን መንግስት የአንዲት ኢትዮጵያን ሰፊና ለም መሬት የሸጠ ወያኔ የሱዳን መንግስት ለውለታው ከገዳሪፍ እስከ መቀሌ የባቡር መንገድ እንደሚዘረጋ የሃገራችንን ሉአላዊነት በመድፈር ለግል ጥቅሙ ሃገራችን እያወደመ ያለ ስርዓት ነው:: የግንቦት 20 ቀን 1983 መዘዝ::

ወያኔ ህወሃት በተፈጥሮ ባህሪው አምባገነን እና ሽብርተኛ ድርጅት እሱን የሚቃወም እና የሚፈጽመው ግፍ እንዲነሳበት አይፈልግም:: ፍላጎቱ ተሳስተሃል አትበሉኝ:: ስለኔ አትናገሩ ከሚለው ፋሺስታዊ ባህሪው በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ እንዲኖር አይፈልግም:: የህዝቡ በነጻነት መናገር እና ሃሳቡን መግለጽ ለወያኔ እንደ እሳት የሚለበልበው ለመሆን የፕሬስ ነጻነት ያገደው:: ይህም እንደ ገዢ ፓርቲ ህወሃት የታገደ ነው:: በዚሁ ፖለቲካዊ ውሳኔ የነጻ ፕሬስ በማደን ፣ በማሰር ፣ በማንገላታት ሳያበቃ ብዙ የፕሬስ ጋዜጠኞች ሃገራቸውና ቤተሰቦቻቸው ለመከራን ስደት ተዳረጉ:: ነጻ ፕሬስ በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ::

ወያኔ ህወሃት የሽግግር መንግስት ብሎ ከሰኔ ወር 1983 ዓ.ም. እስከ ግንቦት ወር 1985 ዓ.ም.  በስልጣን በቆየበት ምርጫ በማለት በጸረ ዲሞክራሲያዊ መንገድ በ1987 ዓ.ም. , በ1992 ዓ.ም. , በ1997 ዓ.ም. እና በ2002 ዓ.ም. በማካሄድ በተለይ በ1997ዓ.ም. ቅንጅት በተለያዩ ፓርቲዎች ቀስተ ደመና ፣ መኢአድ ፣ ኢዴሊ ፣ ኢዴአፓ-መድህን ወዘተ በተጠናከረ ማዕከላዊ ፓርቲ “ቅንጅት” ተብሎ እንደተመሰረተ እምነቱ መሰረታዊ ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲና እድገት ፣ ብልጽግና ፣ ፍትህ ፣ ነጻነት ፣ ከዘረኝነት የጸዳ በምርጫው ለመወዳደር በቀረበበት ምርጫም ተካሂዶ መሉ በሙሉ አሽንፎ ሲወጣ በአንጻሩ ወያኔ -ህወሃት/ኢህአዴግ በዜሮ ተሸንፎ ከምርጫ የወጣው በጉልበቱ ምርጫውን በመንጠቅ ድምጻችን አይነጠቅም ብለው የወጣውን ሰላማዊ ዜጎች በአግአዚ ቅልብ የመለስ ዜናዊ ጦሮች ግደሉት ብሎ ትዕዛዝ በመስጠት ብዙ ኢትዮጵያውያንን ሲገደሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ በየወህኒ ቤት በማሰር ወያኔ ህዝብ ያጠፋበት ቀን የሌባው አይነ ደርቁ ወያኔ በ2002 ዓ.ም. በተካሄደው ምርጫ እንደልማዱ ኮረጆውን በመገልበጥ 99.6% አሸነፍኩ ብሎ ኢትዮጵያና ህዝብዋን ማውደሙን ቀጠለ:: ይህ ሁሉ ችግርን ግድያ ሰቆቃ የግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. ውጤት ነው::

ወያኔ ህወሃት በፕሮግራም እንዳስቀመጠው የኤርትራ ጥያቄ ያላንዳች ጥርጥር ሃቀኛና ታሪካዊ መሰረት ያለወ ጸረ ቅኝ አገዛዝ ትግል ነው በማለት ወያኔ ያመነበት ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የማያምንበት የኤርትራ ህዝብም ያላመነበት በኢትዮጳዊነታቸእው የማያምኑ መሆናቸው አንዳች ጥርጣሬ የለውም:: ድርጊቱ የወያኔ ብቻ ነው:: ይህ በዚህ እንዳለ አሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኤርትራ ግዛት አልነበረችም ሁሉ ተከታታይ ዘመናት በወሎ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ሆና ስትተዳደር እንደነበረች ሁሉ ኢትዮጵያ በትክክል የሚያውቀው ሃቅ ነው:: አሰብን በኤርትራ ካርታ ጨምሮ በ1967 ዓ.ም. ያወጣው ወያኔ ብቻ መሆኑን በግልጽ የሚታወቅ ሃቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት ይህን የታሪክ እና የሃገር ክህደት የፈጸመው ሆን ተብሎ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳይኖራት ያደረጉት ኢትዮጵያና ህዝብዋ ጠላት ብለው ስለአስቀመጡት የፈጸሙት ጥቃት ነው:: ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ወሮ እንደተቆጣጠረ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የባህር በሯን አጣች::

ይህን በተመለከተ ወያኔ/ህወሃት እና ሻዕቢያ እንግሊዝ አገር ለንደን ከተማ ከግንቦት 5 ቀን እስከ ግንቦት 9 ቀን 1983 ዓ.ም. የቀድሞው የአሜሪካ  ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር የሻዕቢያ መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የወያኔው መሪ መልስ ዜናዊ ባሉበት ስብሰባ ኢትዮጵያ 85 ሚሊዮን ህዝብ ስላለባት የባህር በር ያስፈልጋታል:: አሰብም ከኤርትራ ያልተካለለ በመሆኑ በአጼ ኃይለስላሴም ሆነ በደርግ ስርዓትም ከኤርትራ ውጭ ሆኖ በወሎ አፋር የተካለለ ስለነበር ቀደም ሲልም አሰብ ከኤርትራ ውጪ ሆኖ በጣሊያንም ብዙ ያልተደፈረች የኢትዮጵያ የባህር በር እንደነበረች ይታወቃል:: አሰብ የኢትዮጵያ የባርህ በር መሆን አለበት ብለው ሃሳባቸውን ሲያቀርቡ የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ በጣም ተናዶ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ አገዛዝ የወደቀች ሃገር የነበሩ አመራር አጼ ኃይለስላሴ ሆኑ ደርግ ያስቀመጡት ካርታ ህወሃት አይቀበልም:: አሰብ የኤርትራ መሬት ነው:: እኛ አሁን በኢትዮጵያ ስልጣን የምንቆጣጠረው የወደብ ችግር አይኖረንም:: ችግር አይፈጠርብንም:: ብንፈልግ ጂቡቲን አሊያም የሶማሊያ እና የኬኒያን ወደቦች እንጠቀማለን:: አሰብ የኤርትራ ስለሆነ እምነታችንም ይህ በመሆኑ አሰብ የኤርትራ እንጂ የኢትዮጵያ አይደለም::

ፕሬዚደንት ጂሚ ካርተር እና ሌሎች አደረዳሪዎች አቶ መለስ ዜናዊ አሰብን የኤርትራ ነው ፤ የወደብ ችግር የለብንም ብለው እኛንም ስለአሳመኑን አሰብ በኤርትራ ውስጥ መካተቱን ተቀብለናል በመለት ሲዘጉት ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያን ታሪካዊና ጥንታዊው የባህር በርዎችዋን አሳጥቶ ግንቦት 20 ቀን 1983ዓ.ም. አገራችን ኢትዮጵያን በጠላቶችዋ እጅ የወደቀችበት የኢትዮጵያ ህዝብም በድቅድቅ ጨለማ እና ጭቆና ፋሽስት ስርዓት ይዛ የመጣች ይህች ግንቦት የተረገመች ቀን ናት:: በምስራቅ-ምዕራብ-ሰሜን-ደቡብ የሚገኙ ኢትይጵያውያንም እየተረገመች ነው:: 

ወያኔ ህወሃት በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን በለስ ቀንቶት ወሮ በተቆጣጠረበት ወቅት የኢትዮጵያን ሃብት-ንብረት ወያኔና ሻዕቢያ ተባብረው ዘረፉት:: የወላድ መሃን የሆነችው ኢትዮጵያ ተከላካይ የሌላት ሁለት ከደደቢትን ከሳህል በረሃ የመጡት ሙሉ ሰራዊታቸውን በማሰማራት ሃብትዋን ንብረትዋን ዘርፈውታል:: የተለያዩ ተቋማት ተዘርፈዋል:: ጠቅላላ ጥሬ ገንዘብዋ ተዘርፏል:: ጥሬ ህብቶቿ ተዘርፏል:: የቀራት ነገር የለም:: ለውጪ ገበያ ለሺያጭ የሚመረት ቡና ፣ ሰሊጥ ፣ አደንጓሬ ወዘተ አይን ባወጣው ዝርፊያ ቀን እና ሌሊት ተፈጽሞባታል:: ዝርፊያው በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የጀመረው እስከ አሁን ቀጥለውበታል:: ኤርትራ የቡናና የቅባት ምግብ አምራች በመሆን በአለም ገበያ አቅራቢ ሆና ከዓለም 3ኛውን ደረጃ ያዘች:: ከኢትዮጵያ በተዘረፈው ጥሬ ሃብት ዋና ገንዘብ ወያኔ ህወሃት መሪዎች 1. መለስ ዜናዊ እና ባለቤቱ አዜብ መስፍን 2.ስብሃት ነጋ 3.አባይ ጸሃዬ 4.ስዩም መስፍን 5.አርከበ እቁባይ 6.አዲስ አለም ባሌማ 7. አባዲ ዘሙ 8.ጸጋይ በርሄ እና ባለቤቱ ቅዱሳን ነጋ 9.ተክለወይኒ አሰፍ 10.ብርሃነ ገብረክርስቶስ ወዘተ ሆነው ኢፈርተን አቋቁመው ስልጣኑንም ተቆጣጥረው የናጠጡ ባለብዙ ፋብሪካዎች ትልልቅ ተቋማት መስርተው ቱጃር በለሃብቶች ሆነዋል:: ወያኔ ህወሃት ወደ ስልጣን ባልበቃበት ጊዜ በአጼ ኃይለስላሴና በደርግ ስርዓት ነጻ ተቋም በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያገለግሉ የነበሩትን ብሄራዊ ባንክን ፣ ንግድ ባንክን ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ፣ እርሻ ትራንስፖርት ፣ መአድናት ወዘተ ወያኔን ስልጣን እንደጨበጠ ሁሉን ከህዝብ በጉልበቱ ነጥቆ በመቆጣጠር የሃገርና የህዝብ ሃብት የህወሃት ተቋማት ሆኑ:: ይህም ወያኔ ህወሃት በከፍተኛ ወንጀል የሚጠየቅበት ከዋናዎቹ አንዱ ነው:: 

ወያኔ ከኢትዮጵያ የዘረፈው ገንዝብ እና ጥሬ ሃብት ኢፈርት በትግርኛ ት.እ.ም.ት የሚል ስያሜ በመስጠት በትግራይ ህዝብ ስም ሲያጭበረብር የትግራይ ህዝብ መነገጃ ማድረጉም ህወሃት በዚሁ ሌብነቱ በወንጀል የሚያስጠይቀው ነው:: በትግራይ ህዝብ ስም የወያኔ መሪዎች ነገዱበት እንጂ የትግራይ ህዝብ ከት.እ.ም.ት ተጠቃሚ አይደለም:: ህዝቡም ራሱ የሚናገረው ሃቅ ይህ ነው::

ወያኔ ህወሃት ድርጅት ነው ስንልም ህወሃት የተመሰረተውና እስከ አሁንም ያለው ህወሃት ግለሰቦች ተደራጅተው የፈጠሩት የማፍያ ስብስብ እንጂ በምንም ተአምር የትግራይ ህዝብን የማይወክል ነው:: በድርጅቱ የተሰባሰቡ ግለሰቦችን ያቀፈ:: ህዝብ ሌላ፤ ህወሃት ሌላ:: ህወሃትን የመሰረቱት ሰዎችም ጸረ ህዝብ እና ጸረኢትዮጵያ ናቸው:: ይህ ህወሃት ተብሎ የሚጠራ በሻዕቢያ የተመሰረተ ኤርትራን ነጻ ለማውጣትና ትግራይም የአማራው ቅኝ ግዛት በማለት የተነሳ ከጥዋቱ ኢትዮጵያዊነቱን የካደ የከሃዲዎች ስብስብ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ሰላማዊ ዜጎች የገደለ ጸረ ህዝብ ነው:: በመሆኑም የትግራይ ህዝብ ገና ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ህወሃትን በእውቅና አልተቀበለውም::

ወያኔ ህወሃት ገና በ1968 ዓ.ም. በኢትዮጵያ መሬት እጠቀማለሁ በማለቱ ከባድሜ እስከ አፋር ቡሬ የመሬት ቆዳ ስፋት 1.ታች አዲያቦ 2. ላይ አዲያቦ 3.ጭላ ወይም አንከረ ባሩካ 4. አሕሰኣ 5.እገላ 6.ዛላምበሳ  በዚሁ ውስጥ የሚጠቃለሉ ኢሮብ ፣ ጻልገዳ ፣ ዓውዳ ፣ አይጋ ፣ ሶቦያ ፣ ወዘተ 7.የአፋር መሬት  እስከ ቡሬ 8. አሰብ የኤርትራ መሆንዋን በዚሁ ፊርማቸው በ1969 ዓ.ም. አረጋግጠዋል:: 1. መለስ ዜናዊ 2.አባይ ጸሃዬ 3.ስብሃት ነጋ በዋናነት የሚጠቀሱ በትክክል የኤርትራን መሬት ነው በማለት ፈርመው የሰጡት ህዳር ወር 1969 ዓ.ም. ነው:: በዚሁ መሰረት የትግራይ ህዝብ 1.በሻዕቢያ 2.በጀብሃ 3.በህወሃት  በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ትተዳደራለህ ብለው በመወሰን ህዝቡም በእነኚህ ሶስት ድርጅቶች ቁም ስቃዩን በማየት ተገደለ:: ንብረት ሃብቱ ተዘረፈ:: አቤት የሚባልበት በማጣት በየስደቱ ተበታተነ:: ወያኔ ይህን ወንጀል እንደፈጸመ በአንጻሩ ከሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ለም ወሬት ነጥቆ ወሰደ::

የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ዋና ጦሱ ከላይ እንደተጠቀሰው ነው:: የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት መንስኤ   ው በግልጽ የሚታወቅ ነው:: ወያኔ ህወሃት አመራር የሚያላክኩት በኢኮኖሚ ችግር የተፈጠረነው ሲሉ በተደጋጋሚ በተለይ የወያኔው መሪ ነበር መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማሳመን ለከት በሌለው ውሸቱ ሲለፋደድ ሃገር ሙሉ ያውቃል:: ቀሪዎቹ የሱ የአመራር አባላቱ ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃየ ፣ ስዩም መስፍን ፣ አርከበ እቁባይ ወዘተ የመለስ ዜናዊን ሃሳብ በማስተጋባት በየውጪ ሃገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለማሳመን ብዙ ውጣ ውረድ ቢያደርጉም እስከ ዛሬ ተቀባይነት አላገኙም::

የጦርነቱ መንስዔ በኢኮኖሚ ሳይሆን በትክክለኛው አነጋገር በተጨባጭ ሁኔታው የመሬት ይገባኛል ነው:: ሻዕቢያ የኔ ግዛት ነው:: ከዚህ ቀደምም በ1969 ዓ.ም. ተስማምተን እናንተም የኤርትራ መሬት ነው በማለት ያመናችሁበትን አስረክቡን በማለት ወደ ጦርነቱ ሻዕቢያ እና ወያኔ ገቡ:: እውነቱ ይህ ነው:: ይህ በዚሁ እንዳለም የኢኮኖሚው ጉዳይም አስተዋስኦ ያደረገበት አለ:: ሁሉ ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው ከ1983 ዓ.ም. ግንቦት ወር ጀምሮ እስከ 1990ዓ.ም.  የሻዕቢያው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራ የግላችን የኢትዮጵያ ሃብት ደግሞ የጋራችን ተባብለው በህወሃት መሪዎች መጠነ ሰፊ ድጋፍ ሁለቱ ማለት ሻዕቢያና ወያኔ የሃገራችን ኢትዮጵያን ጥሬ ሃብትዋን መዓድኗን እና ሃገሪቱ ያፈራችውን የተለያዩ ፋብሪካዎቸ እና ባንኮችን አብረው ተባብረው ዘርፈዋል:: ኢትዮጵያ እና ህዝብዋ ለረሃብ እና ችግር ተዳርገው ኤርትራውያን ጤፍ በየአይነቱ ዳጉሳ ፣ ስንዴ ፣ ገብስ ወዘተ በርካሽ ዋጋ ኤርትራ ሲሸጥ የኢትዮጵያ ገበያ ባዶ ቀረ:: ስለዚህ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሲነሳ ያ የለመዱት በሰው ሃገር ሃብት ሲንደላቀቁ የቆዩት አሁን ሲያጡት ለጦርነቱ አስተዋጽኦ ያደረገም ነበር:: በጣም ከሚገርሙ ነገሮች እና አሳዛኝ የሆነው ሁለቱ መለስ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂ በስልክ ጥብቅ ግንኙነት እንደነበራቸው ብዙ ሰዎች ተናግረዋል:: ስብሃት ነጋ ፣ አባይ ጸሃዬ እና ሌሎቹ የወያኔ መሪዎች በጣም የደመቀ ግንኙነት ከጦርነቱ ዋዜማ አንስቶ የወያኔ መሪዎች ይገናኙ እንደነበር ምስጢሩም የሚያውቁ ሰዎች ተናግረውታል::  

ኢሳያስ አፈወርቂ ላቀረበው የአንድ ቢሊዮን ብር ላክልን መለስ ዜናዊ ሳያቅማማ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ተፈቅዶ ገንዘቡ አስመራ እንደገባ በቀናት የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቂ መቀሌ ውስጥ(ሃይደር) የሚገኘው የመዋዕለ ህጻናት ትምህርት ቤት በሚግ አውሮፕላን ደበደበው:: ከተዋጊ አውሮፕላኖቹ የተጣለው ክላስተር ቦምብ ወድያውኑ 53 ህጻናትና አስተማሪዎች ሲሞቱ 185 ደግሞ ከባዱ ቁስል ደረሰባቸው:: ለዚሁም ተጠያቂው መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ ናቸው::

የሻዕቢያ ተዋጊ ጀቶች እንደገና ተመልሰው ቦምብ ጭነው 48 ሰላማዊ ሰዎችን 10 ህጻናትን ሲገድሉ 150 ሰዎች አቆሰሉ:: በማለት ቢ.ቢ.ሲ. እና ሲ.ኤን.ኤን. የዘገቡት ዋቢ ነው:: ይህ ጥቃት የደረሰው በግንቦት ወር መጨረሻ 1990 ዓ.ም. ሆኖ አስራት አብርሃም በአሳማኝ ሁኔታ ከ’ሃገር በስተጀርባ’ በሚል መጽሃፉ እንደገለጸው መለስ ዜናዊን ኢሳያስ አፈወርቂ እስከ ታህሳስ ወር 1991 ዓ.ም. ይገናኙ እንደነበሩም ያስረዳል:: መለስ ዜናዊን ግብረአበሮቹ እነ ስብሃት ነጋ ወዘተ ኢትዮጵያዊ ሳይሆኑ የባዕዳን ቅኝ ገዢዎች መሆናቸው በግልጽ የሚያሳይ እውነታ ነው::

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትም ሆን ብሎ ያሰናከለው መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ እና አባይ ጸሃዬ መሆናቸው ሲታወቅ ምክንያቱም በ1969 ዓ.ም. ከላይ የተጠቀሰ መሬት የኤርትራ ነው ብሎ ወያኔ የፈረመበት በመሆኑ ይህም በአልጀርሱ ስምምነት ወያኔ መሪ መለስ ዜናዊ አሳልፎ ለኤርትራ መስጠቱ የ1969 ዓ.ም. ትልቁ ማሳያ ነው:: የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት እነማን መሩት? ይህን እንመልከት::

 

1. መለስ ዜናዊ የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ እና ጠቅላይ ሚኒስቴር …………………………………………ኤርትራዊ

2. ጻድቃን ገብረተንሳኤ የጦሩ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ……………………………………………..ኤርትራዊ

3. ሳሞራ የኑስ…ከፍተኛ ጀነራል…………………………………………………………………………………….ኤርትራዊ(በናቱ ከርከበት በአባቱ ሱዳናዊ)

 

እነዚህ ሶስቱ አመራር በምንም ተአምር ለኢትዮጵያ ይሰራሉ?? ጦርነቱን በትክክል ይመራሉ ብሎ ማሰብ “ላም አለችኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ” አይነት ነው:: እነዚህ ትልቁ ምኞታቸው የኤርትራ ሰራዊትና ህዝብ እንዳይጎዳ ኢትዮጵያዊው ሰራዊት ቢያልቅ ምንም የማይሰማቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ሁሉም የውጊያና ጦርነት አመራር ብቃት የሌላቸው በአጋጣሚ የተገኘው ጠ/ሚኒስቴርነት እና ጀነራልነት ከንቱ ነው:: ጠቅላላ የወያኔ ህወሃት መሪዎች ጀነራሎች እና ወታደሮች ከወታደራዊ ሳይንስ ያላቸው ርቀት ሰማይና መሬት ነው:: በ1991 ዓ.ም. ያለቀው ሰራዊት ተጠያቂም ናቸው::

2ኛው በዚሁ ኢትዮ ኤርትራ ውጊያ ሲመሩ የነበሩ የመለስ ዜናዊ እና የስብሃት ነጋ ታዛዦች ናቸው:: አታድርጉ ከተባሉ አያደርጉም:: በዋናነት ጎልተው የሚጠቀሱም::

1. ሰዓረ መኮንን

2.ዮሃንስ ገ/መስቀል (ቦጅቦጅ)

3.ታደሰ ወረደ

4.አብርሃ ወ/ማሪያም(ኳርተር)

5.ብርሃነ ነጋሽ ወዘተ ሲሆኑ ሌሎችም አሉ::

ስለሆነም በ1991ዓ.ም የደረሰው ውድመት ከ100,000ሺ ሰራዊት የሞተበት ወደ 200,000 የሚጠጋ ሰራዊት አካለ ጎዶሎ የሆነበት ግምቱ አስቸጋሪ የሆነው የኢትዮጵያ ሃብት ንብረት የወደመበት ተጠያቂው ማነው??

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የተፈጠረበት ምክንያት እና ሰበቡ ምንድነው?? እነዚህ ሁልቱ ጥያቄዎች መልስ በግልጽ ለማስቀመጥ እፈልጋለሁኝ::

1. በኢትዮ-ኤርትራ ለደረሰው ግድያና በጦርነት የወደመው ሃብትና ንብረት ተጠያቂዎች::

1. መለስ ዜናዊ

2. ስብሃት ነጋ

3.አባይ ጸሃዬ

4. አርከበ እቁባይ

5. ጻድቃን ገ/ተንሳኤ

6. ሳሞራ የኑስ

7. ስዩም መስፍን

እነዚህ በሰው ህይወት ለደረሰው እልቂትና ጉዳት በሃገሪቱ የደረሰው ከፍተኛ ውድመት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው::

በጦርነቱ የወደመው ሃብት እና ንብረት ተጠያቂውስ ማነው? ለሚለው::

1. መለስ ዜናዊ

2.ስብሃት ነጋ

3.ጻድቃን ገ/ተንሳኤ

4.አበበ ተክለሃይማኖት

5.ገዛኢ አበራ

6.ጀነራሉ በባለ ሌላ ማእረግ

7.ስዩም መስፍን

8.ብአዴን, ኦህዴድ እና የደቡብ ህዝብ ንቅናቄ

9. በወቅቱ የነበሩ የፓርላማ አባላት በሙሉ

10. የህወሃት ካድሬና ደጋፊዎች በሙሉ::

እነዚህም ግንባር ቀደም ተጠያቂዎች ሲሆኑ፤

3. የጦርነቱ መንስኤ ለሚለው ጥያቄ የህወሃት አመራር በ1969 ዓ.ም. ሻዕቢያ ላቀረበው የመሬት ይገባኛል በወቅቱ አምነት ተቀብለው በፊርማቸው ባረጋገጡት መሰረት በትግራይ ህዝብ ተቀባይነት የሌለው የህወሃት ጥቂት የማፍያ ስብስብ በፈጸሙት ነገር ከሃዲዎች ከሻዕቢያ ጥቅም እናገኛለን ብለው የፈጸሙት ሚያዝያ ወር 1991 ዓ.ም. የፈነዳ ጦርነት ነው:: ተጠያቂዎቹም ህወሃቶች ናቸው::

በብዙ በርካታ ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ሊከሳቸው ዝግጅቱን አጠናቅቆ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ነው:: ህወሃት እና መሪዎቹ ይከሰሳሉ:: አዎን ለፍርድም ይቀርባሉ::

የአይደ መዋእለ ህጻናት የአየር ጥቃትም የትግራይ ህዝብ ካቀረባቸው ክሾች ውስጥ አንዱ ስለሆነ በዚሁም በዋናነት የሚጠቀሱ መለስ ዜናዊ እና ስብሃት ነጋ መሆናቸው ነው::

ግንቦት 20 ቀን1983 ዓ.ም. ይህን አይነት አሰቃቂ ድርጊቶችን አስከትላ ነው ብቅ ያለችው:: የተረገመችው ይህቺ ቀን ኢትዮጵያ ለምለም አገራችንን ለከሃዲ ባንዳዎች አሳልፋ የሰጠች::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ይዛው የመጣችው ሰቆቃ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በፈለገው የሃገሩ ግዛት የመኖር ለዘመናት ተጠብቆ የቆየውን መብቱን በህወሃት ከፋፍለህ ግዛ በሚመቸው ሃገራችን በዘር በቋንቋ ከፋፍሎ ጠባብ ብሄረተኛ በሆነው መንገድ የዘር ፌደራሊዝም መሰረት ይህ የእቅድ ሃሳቡም አማራውን ለማጥፋት እና ለማክሰም የተቀነባበረ ሴራ ነው:: ይባስ ብሎም ሸዋ ጠ/ግዛት ለሌሎች ብሄራት በመስጠት ጎጃም በጌምድር ጠ/ግዛት ወሎ ጠ/ግዛት በታትነው አማራው መኖሪያ አልባ ተደረገ:: በተለያዩ ጠ/ግዛት ይኖር የነበረው አማራ ውጣ እየተባለ በወያኔ ህወሃት ከህጻን እስክ ሽማግሌ እየተገደለ በየበረሃው ወድቆ የዘሩን ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል:: ቀስ በቀስም ኦሮሞ ጋምቤላ አፋር ወዘተ ተመሳሳይ እጣ ደረሰባቸው:: በጠቅላላው ከተወለደበት ካደገበት ኢትዮጵያዊ ከመሬቱ የተፈናቀለ 24 ሚሊዮን ሲሆን በወያኔ ህወሃት የተገደሉ ኢትዮጵያውያን አንዳንድ ጥናቶች የሚያመለክቱተ 7.9ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ወያኔ ህወሃት እንደገደላቸው ያሳያሉ::

ግንቦት 20ቀን 1983 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሁለቱ ሃይማኖቶች እስልምናእና ክርስትና በእጁ አስገብቶ ለመቆጣጠር እና ቀስ በቀስም ሃይማኖቶቹን ለማክሰም ተነሳ::

1. የኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት ለብዙ ዘመናት ወግና ህግጋቱን ጠብቆ የመጣ በብዙ ሚሊዮን እስልምና ተከታይ ያለው የኢትዮጵያ ቅርስና የምንኮራበት ሃይማኖት ዛሬ በወያኔ ህወሃት ተደፍሮ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ሙሉ መብታቸውን ተነጥቀው በእስራት መከራ እየተሰቃዩ በገዛ ሃገራቸው ለክፉ ችግር ተዳርገዋል::

2.የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም በክፉ አደጋ ወድቃለች ቤተ ክርስቲያና እየተቃጠሉ ታሪካዊ ቅርሶችዋን በወያኔ ተዘረፉ::ወያኔ የሚቃወሙ ብጹአን አባቶች ለስደት ተዳርገዋል:: ብዙም ተገድለዋል:: ይህን ሁሉ የፈጸመው የወያኔ አባል የነበረው አባ ገብረመድህን ወይም አባ ጳውሎስ የሚባል በወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ፓትሪያርክ ካደረገው ብዙ ወንጀል በቤተ ክርስቲያናችን ፈጽመዋል::

ለመሆኑ አቡነ ጳውሎስ ማነው??

አቡነ ጳውሎስ ትውልዳቸው ትግራይ አድዋ ያደጉትም እንዳባገሪማ ገጠር ነው:: እንዳባገሪማ የተባለበት ምክንያት በአክሱም ዘመነ መንግስት በንጉስ አልአሜዳ ብ470ዓ.ም. ከመጡት ተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ አባ ገሪማ ሲሆኑ ከአድዋ በስተምስራቅ የ18 ኪሎ ሜትር ርቀት የምተገኘው ተራራማ ቦታ አባ ገሪማ በጣም አስደናቂ ሆኖ የተሰራው ቤተ ክርስቲያናቸው በማነጽ እዛው ሞተው እዛው ስለተቀበሩ በዚሁ ምክንያት እንዳባገሪማ ተብላ ትጠራለች::የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያዋረዱን የቤተ ክርስቲያኗን ህገ ደንብ እና ቀኖናውን የለወጡ እና ያፈረሱ ፣ ለስጋቸው ያደሩ: አቡነ ጳውሎስ የኢትዮጵያን ጥንታዊ ሃይማኖት ለማጥፋት ጸረ ክርስትና የሆኑት ጳውሎስ የአድዋ ልጅ በመሆናቸው በኢትዮጵያ ህጋዊ ሊቀ ቅዱሳን ፓትሪያርክ በቤተ ክርስቲያኑ ህግና ደንብ የተሾሙት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ ወያኔ በሃይል አስወግዶ አባ ጳውሎስን ሾመ:: ይህ ደግሞ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሀይማኖት ወግና ስርዓቱን ለማጥፋት የታቀደ ነው:: የቤተ ክርስቲያኑን ህግና ደንብ የሚጻረርም ነው::

አቡነ ጳውሎስ የወያኔ ህወሃት በአባልነት የመለለመሉት በ1976 ዓ.ም. ነበር:: በወቅቱ የሚነገረው ዶ/ር አባ ገብረመድህን የተባሉ የኛ አባል ስለሆኑ ትግራይ ሃገራችን ከአማራው ቅኝ አገዛዝ ነጻ በምትወጣበት እኚሁ የትግራይ ፓትሪያርክ ይሆናሉ በማለት ስብሃት ነጋ በለመደው ወሬ ማዛመት በታጋይ ውስጥ ተሰራጨ:: ቢሆንም ግን ታጋዩ ብዙ ስሜት አልሰጠውም:: ምክንያቱም ሃይማኖት የለሽ የወያኔ አመራር በትግሉ ወቅት እግዚያብሄር የሚባል አማልክት የሚባሉ በፍጹም የሉም:: ይህ ለአማራው አገዛዝ እንዲመችለት የፈጠረው ከንቱ ሃሳብ ነው:: በማለት ስለአስተማሩን የአባ ገብረመድህንም ይህን ድባብ የሸፈነው ነበር::

ንገሩ እንደገና በ1980 ዓ.ም. መጀመሪያ ታድሶ መጣ የህወሃት አባል አባ ገ/መድህን ከአሜሪካ ሱዳን ድርስ መጥተው ስብሃት ነጋ የወቅቱ የህወሃት ሊቀ መንበርና መለስ ዜናዊ ሱዳን ድረስ በመሄድ እንደተገናኙ በድጋፍ መልክም $15,000 የአሜሪካን ዶላር መስጠታቸውን የሄዱት ሁልቱ የወያኔ አመራሮች በድብቅ ሳይሆን በግልጽ የተናገሩት ነበር:: ከዚሁም በተጨማሪ ሱዳን ካርቱም ውስጥ የሚገኘው ቤተ ክርስቲያን አስቀድሰው በውስጡ የሚገኙ ቀሳውስት ካህናት ወደ ህወሃት አባልነት መልምለው በሶስተኛው ቀን ወደ መጡበት መመለሳቸም ተነገረ::ስብሃት ነጋ አቡነ ጳውሎስ የህወሃት መሪህ ባህታ(vanguard) ናቸው በማለት ይጠራቸዋል::

እንግዲህ የአቡነ ጳውሎስ ነገር ይህ ሆኖ ትግሬ በመሆናቸው ብቻም በደርግ መታሰራቸውን ብዙ ግፍ ተፈጸመብኝ የሚሉት አቡነ ጳውሎስ የኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አባላት እውነት ይሁን አይሁን ለነሱ ልተው:: ከሆነም አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያንዋ ላይ በቂም በቀል ማወካቸው ከአንድ መናኝ አባት መፈጸም የሌለበት ፈጽመዋል:: ነብሳቸውም ለሲዖል ተዳርጋለች::

አቡነ ጳውሎስ የፓትርያርኩ ስልጣን አግባብ በሌለው መንገድ የተረከቡት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያናት በምርጥ ካድሬነታቸው በዋልድባና በተለያዩ ቤተ ክርስቲያናት ብዙ ግፍ ከመፈጸማቸው በላይ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ቅርሶች ከየቤተ ክርስቲያኑ በማስወጣት ሸጠዋል::

ይህ ሁሉ በእስልምና ሃይማኖትና በክርስትና መዘዙ ይዞት የመጣው ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የተረገመች ቀን ናት::

ወያኔ ህወሃት ኢትዮጵያውያን እንደተቆጣጠረ ብዙ የዝርፊያ ተቋማት አመቻችቶ ነበር:: አገራችንን የተቆጣጠረው 1. ዋና ኢፈርት 2. ለም የኢትዮጵያ መሬት ለባዕዳን መሸጥ 3. ኢትዮጵያውያን ከተወለዱበትና ካደጉበት መሬት ማፈናቀል 4. ገዢ የሆኑት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ተቋማት በህወሃት ቁጥጥር ውስጥ መዋል 5. ኢትዮጵያዊው የሃገሩ ዳር ድንበር ጠባቂ አማራው ማጥፋት ከዚህም ጎን ለጎን አማርኛ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ማጥፋት እና ማክሰም:: 6.የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሀ.አየር ኃይል ለ. ምድር ጦር ሐ.ባህር ሃይል መ.ፖሊስ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ አስወግዶ የራሱን የህወሃትን ታጋዮች ከትግራይ የመጡ ሁሉ የኢትዮፕያ ምድር ጦርና አየር ኃይል ለማድረግ ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ በራኡ መዳፍ ውስጥ ለማስገባትና ለመቆጣጠር ደህንነቱም ከላይ እስከ ታች በትግሬዎች ማዋቅር አላማው ነበር::

ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ የወያኔ አመራር መለስና ስብሃት ነጋ ባወጡት እቅድ ተግባራዊ ተደርገዋል::

የኢትዮጵያ ህዝብ በእርሻ የሚተዳደረው መሬቱን ተቀምቶ ለባዕዳን ሳውዲ አረቢያ ፣ ህንድ ፣ እና ለቻይና ወዘተ ህወሃቶች ሸጡት:: በሽያጭ የተገኘው ገንዘብም ሆነ በነ መለስ ዜንዊና ባለቤቱ ወ/ሮ አዜብ እጅ ሲገባ ከመሬቱ የተፈናቀለ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በየበረሃው ወድቆ ለክፉ ችግርና መከራ ተዳርገዋል::

ወያኔ ህወሃት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተሰማርቶ ህዝበ ኢትዮጵያዊ እያለቀ ነው:: አማርኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ ጠላት ነው ብለው ወያኔዎቹ ፈረጁት:: ለመሆኑ የቋንቋ ጠላት አለን?? ይህ ሁሉ በግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. የመጣ የኢትዮጵያ ህልውና አጠያያቂም ሆነ:: ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ያፈረሰ ህዝብዋንም ለችግር እና ለመከራ የዳረገ በጥቁር ታሪክ የሚመዘገብ የፋሺስት ወያኔ ህወሃት አገዛዝ ስርዓትና የጨለማ ዘመን በማለት ታሪ ዘግቦታል::

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. አንቺ ጥቁር የታሪክ አተላ ቀን የስንቱን ኢትዮጵያዊያን ህይወት በላሽ?! ስንቱን ኢትዮጵያዊ ምሁራን የነጻ ፕሬስ እውቅ ጋዜጠኞች ለስደት ለመከራ ዳረግሽ?! ስንቱን ወጣት ሴት እና ወንድ ከሃገሩ ጠፍቶ የባህር ቀለብ ሆነ:: ስንቱስ በስደት ሂወቱ እየማቀቀ ለክፉ መከራ ተዳረገ:: ስንቱ ቤተ ሰብ አፈናቅለሽ የስንቱን ቤት አፈረሽው:: ወጣት የሴት ህጻናት ሽርሙጥና ዳረግሽ:: አደንዛዥ እጽ እና አሺሽ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ተራ የንግድ ገቢ ሆኖ ወጣቱ ትምህርት ተከልክሎ እቅቀት እና ስልጣኔ በኢትዮጵያ የጠፋበት ዛሬ በኢትዮጵያ ስራ አጥነት የተስፋፋበት የወንጀል ድርጊት በስፋት የሚፈጸምበት ህጻናት በየቆሻሻው የተጣሉ ምግብ አይነት ነክ እየለቀሙ የሚበሉበት የጎዳና ተዳዳሪ ጠዋሪ ማደሪትይ ያጡ ህጻናት ለአቀመ አዳም ያልደረሱ ልጆች ወንድ ሴት ማደሪያቸው በየመንገዱ ሆነ:: ህጻናት በርሃብ በየመንገዱ በየትምህርት ቤቱ አእምሮዋቸውን እየሳቱ የሚወድቁበ እርጉዝ ሴት መኖሪያ አልባ ሆና በየዱር ገደሉ እየወለደች ከተወለዱ ህጻናት ከ10 ህጻናት 6 በ3 እና በ 4 ወራቸው እየሞቱ ህክምና ጠፋ:: ውሃ ጠፋ:: መብራት ጠፋ:: አረ ስንት ጉድ ነው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የወረደው ግፍ::

የወያኔ ህወሃት አባል ድርጅቶች ህወሃት ራሱ የነዚህ ቤተሰብ ልጆች ውጭ አገር እየተንደላቀቁ ሲማሩ ሃገር ውስጥ ያሉ አመራሩ ደጋፊዎች በኑሮ ተንደላቀው በሙስና ተዘፍቀው የሃገር እና የህዝብ ሃብት እየዘረፉ ቀኑ ለነሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ የችግር ጨለማ መብቱ የተረገጠ ባሪያ ጥዋት ማታ በወያኔ ስርዓት የሚሰቃይ ግዞተኛ ባዕድ ሆኖ ያለበት ዘመን ነው::

ይህ ክፉ አረመኔያዊ የህወሃት አገዛዝ በዚሁ መንገድ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይቀጥል ሁሉ ኢትዮጵያዊ በአንድነት ይነሳ በህዝባዊ ትግል ወያኔን ከስረ መሰረቱ ነቅለን እንጣለው::

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

ገብረመድህን አርአያ

አውስትራሊያ

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop