ግርማ ሞገስ (girma.moges@yahoo.com)
አርብ ሚያዚያ 25 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት (Friday, May 03, 2013)
መንግስት በመፈንቀል ስልጣን የጨበጠው የትናንቱ አምባገነን መንግስቱ ኃይለማሪያም የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ አብዮቱን እንድጠብቅ አደራ ሰጥቶኛል ብሎን ነበር። ስልጣን አልለቅም ማለቱ ነበር። የአምባገነኑ መለስ አደራ መፈክሮች ቢለዋወጡም “የልማት ጠባቂ ነኝ” እያለ መሞቱ ይታወሳል። ዛሬ በስልጣን ላይ ያሉት የአቶ መለስ ፍጡራን አምባገነኖች ደግሞ “የአቶ መለስ ራዕይ ሞግዚት” ነን ይላሉ። ሌላ ሃያ አመቶች ሊገዙን። የትናት በስቲያው አብዮት ጠባቂ፣ የትናንቱ ልማት ጠባቂ፣ የዛሬዎቹ ደግሞ ራዕይ ጠባቂ። የአምባገኖች መተካካት በኢትዮጵያ የሚያከትመው የኢትዮጵያ ህዝብ አፉን እና እጁን አንድ አድርጎ አደባባይ በመውጣት የስልጣን ባለቤት እኔ ነኝ ሲላቸው ብቻ ነው። በሰላማዊ ትግል የመንግስት ስልጣን ባለቤት ሲሆን ብቻ ነው።ለማንበብ እዚህ ይጫኑ – የአቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም – ክፍል ሁለት