512667545 4209037802648345 2064548733377711589 n
ስምረት በሚል ሲም፣ የአንዱ የህወሃት አንጃ መሪ፣ ጌታቸው ረዳ ሁመራ ተከስቷል፡፡ እነ አሸተ ደምሌ፣ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ትልቅ አቀባበል አድርገውለታል፡፡ ጌታቸው ረዳ ወደ ሁመራ የመጣው፣ እነ እሸተ ደምሌም ትልቅ አቀባበል ያደረጉለት፣ በአብይ አህመድ ታዘው ነው፡፡ ይህ ማድረግ ለምን አስፈለገ ? ህወሃቶች ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ነው፡፡ ከብልጽግና ጋር ውጊያ ቢደረግ፣ ትግራይ ከዚህ በፊት እንደነበረው በከበባ ውስጥ አትሆንም፡፡ የሚያስፈልገው ነገር በኤርትራ በኩል ወደ ትግራይ መግባት ይችላል፡፡
እነ ኮሎኔል ደመቀ ከኤርትራ መንግስት ጋርም ጥሩ ግንኙነት ነበራቸው፡፡ ያ ግንኙነታቸውን ለብልጽግና ብለው አበላሽተውት ከሆነ፣ እጅግ በጣም ስትራቲጂክ ስህተት ነው የሰሩት፡፡ ኮሎኔል ደመቀ አንድ ጊዜ ኢኤምኤፍ ላይ ብቻ ቀርቦ ነው ትንሽ አላስፈላጊ ነገር የተናገረው፡፡በወቅቱ ስህተት ሰርቷል በልን ወቅሰነዋል፡፡ ከዚያ ባለፈ ግን ከመናገር ተቆጥቦ ያለ ሰው፡፡ በተቃራኔው፣ ካድሬው አሸተ ደምሌ ግን፣ የወልቃይት አስተዳዳሪና የብልጽግና መዓከላዊ ኮሚቴ አባል ፣ ብዙ ጊዜ በተናገራቸው ጸረ ፋኖ አስተያየቶች፣ በፋኖዎችና ወልቃይት ባሉ አመራሮች መካከል ክፍተት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎና የሸዋ ፋኖዎች፣ የአማራ ጠላት ከሆነው ዘረኛው የብልጽግና አገዛዝ ጋር እየተፋለሙ ባሉበት፣ ወልቃይት ያሉ የብልጽግና አስተዳዳሪዎች፣ ከወቅላይት ባለፈ የሌሎች አማራዎች ችግር ማየት፣ መረዳት አለመቻላቸው ለትዝብት ዳርጓቸዋል፡፡
ጌታቸው ራዳ ሁመራ የሄደው በዋናነት ስለ ተፈናቃዮች ለመነጋገር ነው፡፡ እነ ኮሎኔል ደመቀም ሁልጊዜ እንደሚሉት ፣ “ተፈናቃዮች እንዳይመለሱ ከልክለን አናውቅም፡፡ አሁንም ትክክለኛ የወልቃይት ነዋሪ የነበሩ መመለስ ይችላሉ” የሚል ምላሽ ነው የሚሰጡት፡፡ ከዚያ በኋላ ጌታችው ረዳ ፣ ይመስለኛል፣ አዲስ አበበ ሲመለስ፣ “የትግራይ ህዝብ ሆይ፣ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ ከወልቃይት አስተዳደርና ከአማራ ክልል መንግስት ጋር ተነጋግረን፣ የ ኤርትራ አሽከር ህወሃቶች እንቅፋት ሆነው አልተቻለም” ብሎ እነ ደብረ ጽዮንን ያወግዛል፡፡ ምን ለማለት ነው፣ ህወሃቶች ትግራይ ተቆጣጥረው ባለበት፣ ተፈናቃዮች እንደማይመለሱ እየታወቀ፣ ጌታቸው ሁመራ የተላከው ፣ በአብይ አህመድ፣ ለፖለቲካ ፍጆታ ነው፡፡ትያትር ነው እየሰሩ ያሉት እንጂ ለተፈናቃዮች አስበው አይደለም፡፡ ተፈናቃዮች በርግጥም ተመልሰው፣ በሰሜን ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር የኦሮሞ ብልጽግናዎች በጭራሽ አይፈለጉም፡፡ ይሄ በግልጽ ሊታወቅ ይገባል፡፡
ሌላው እነ ኮሎኔል ደመቀ ቅርጫታቸውን በሙሉ ብልጽግና ላይ ሲያደርጉ፣ ምን ያህል ራሳቸውን አጣብቂኝ ውስጥ ሊከቱ እንደሚችሉ አለመረዳታቸው ነው፡፡ በሰሜን በኩል የኤርትራ መንግስት ጸረ ብልጽግና ነው፡፡ በምስራቅ በኩል ህወሃት ጸረ ብልጽግና ነው፡፡ በደቡብ በኩል ፋኖ ጸረ ብልጽግና ነው፡፡ በምእራብ በኩል፣ የአልቡርሃን መንግስት ጸረ ብልጽግና ነው፡፡ በተለይም እነ ኮሎኔል ደመቀ ከኤርትራ መንግስት ጋር የነበራቸውን ጥሩ ግንኙነት ካበላሹ፣ ትልቅ አደጋ ውስጥ ነው የሚገቡት፡፡ በመሆኑም፣ ለዚህ አደጋ አስቸኳይ መፍትሄ መፈለግ አለባቸው፡፡ ምንድን ነው ማድረግ ያለባቸው ? ከአፋብሃ ጋር መነጋገርና መቀናጀት መጀመር አለባቸው፡፡ ቢቻል ደግሞ አሸተ ደምሌ የተባለውን ሰው ማባረር ያስፈልጋል፡፡ ፋኖን እንደ ጠላት አድርጎ የቀረበ ሰው፣ ለወልቃይት ሕዝብ የሚመጥን አይደለም፡፡ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እራሱ የመሪነቱን ቦታ ይዞ፣ እዚያ አካባቢ ላለው ኃይል ስትራቲጂክ አመራር መስጠት መጀመር አለበት፡፡