October 14, 2023
5 mins read

ጥናት አልባ የላቲን ፊደል የማፋፋት ዘመቻ – ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው 

የኢትዮጲያ የቋንቋዎች ጥናት ኢንስቲትዩት የሃገራችንን ቋንቋዎች ለማበልጸግ የተመሰረተ ቢሆንም በክፉ ፖለቲከኞች ጣልቃ ገብነት ሊሰራ ያለመቻሉን አንጋፋ የሃገራችን ምሁራን በተደጋጋሚ የገለጹት ጉዳይ ነው;:
91530 1 1የላቲኑ ፊደል ለኦሮምኛ ስነ- ድምጾች ጨ ቀ ጠ ጰ   ጨጨብሳ ቀልቤሳ  ጣፋ ሂርጳ  ሂንጣኔ  ወዘተ ድምጽ የሌለው ሲሆን ታላቁን መጽሃፍ ቅዱስ ሂካ ኦነሲሞስ ነሲብ በግእዝ ፊደል የተረጎመው በ260 ገጾች ከአማርኛው ጋር ተቀራራቢ ሲሆን የቁቤው ግን ወደ እጥፍ 440  ገጾች ይደርሳል::የኦሮምኛውን ከላቲኑ ይልቅ በግእዝ/ ሳባ ፊደል መሻሻሉን የብሄረሰቡ ተወላጆች ምሁራን በተከታታይ ቢያቀርቡም ያለው የኦህዲድ  ብልጽግና መንግስት ጆር ዳባ ብሏል;:
የኦሮሞው  የጽሁፍ ቋንቋ ጉዳይ በጥናት እልባት ሳያገኝ ባለፈው ጉራጌ አይደለንም ብለው በወያነ ቅስቀሳ ከተቀራራቢ የጉራጌ ወገናቸው ስልጢዎችን ለያያቶ ዛሬ ብልጽግና መጫውቻ ባደረጋቸው ዘይቤ ብልጽግና ኦህዲድ ቀቤና የተባለውን ከጉራጌ የማይለየውን ማህበረሰብ በተለያያ መልኩ የኦሮሞን ክልል ተብዬ ማስፋፋቱን ለመቀጠል ጉራጌን በወያኔ ፈለግ በማሰቃየት ላይ የሚገኘው ብልጽግና ኦህዲድ  ቀቤኛዎችን ከሚመቻቸው የሳባ የግእዝ ፊደል ተጠቃሚነት በፖለቲካ ጫና የማለያየት ይፋ ዘመቻውን  ጀምሯል::
በሌሎች  ሃገሮች የተባረከው ሁሉንም ዘር የሚቀበለው የክርስትና ወንጌል መልክትን በትውልድ ህዝቦች ልሳንና ጽሁፍመጠቀሙ የቅኝ ተገዥነትን ስነልቡና የሚያድን መሆኑ በምሁራን በሚቀርብበት ወቅት የኦነግ ፓስተሮች በሃገራችን በተቀጣሪ ጠማማ ምሁራኖቻቸው ተሰማ ተአና መስሎቹ ፍቃዱ ጉርሜሳ ሕዝቅኤቄል ጋቢሳ አቀናባሪነት ባደረጉት ዘመቻ  የኦሮሞ ክልል ትውልድ የቁቤ ትውልድ ሆኖ ከሚቀርበውና ከሚመቸው ከሚዛመደው ስልቻና ቀልቀሎ ብለው ታላቆች ከመሰከሩለት ተለይቶ የተዋህዶ ኦርቶዶክስና የኢትዮጲያን ጥላቻ  ያተርፍ ዘንድ የተደረገ ጥላቻ ያፈራ እርም በደልን የሰማዩም የምድሩም ፈራጅ ሚፈርድበት ቀን ይመጣል::
ዘረኞቹ በአማራ ላይ ባላቸው ጥላቻ የአማርኛ ቋንቋ በአፍሪካ ከሚነገሩት ታላቆቹ ዋነና የሆነውን ለማጥላላት ምን ክፉ ዘመቻ ቢያደርጉበት አማርኛ በህዝቅኤል ስላቅ ኢትዮጲያዊያኛ ይባል ያለው በትክክልም በስነቋንቋ ሊቃውንት Ethiopic ተብሎ ከሁሉም የኢትዮጲያ ቋንቋዎችና ከውጭም በቋንቋ የመዋዋስብና የመስፋፋት ህግ አድጎ በአውሮፓ በእስያ በሰሜን አሜሪካ ትምህርት ከሚሰጥባቸው  አንዱ ለመሆን በቅቷል:: ይህም ሲባል ሰዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የመማር አለም አቀፍ መብት ቢሆንም በጥላቻ  የሌላውን ባህል ታሪክ ሃውልት ለማጥፋት የኦዲድ ብልጽግና መንግስትና ተባባሪዎቹ ከምኒሊክ ድኩላ እስከ ሃውልቱ ከሰሞኑ ደማቅ ውብ የሆነውን የኢትዮጲያን አረግንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ /ባንዲራ የማጥፋት የቅናትና የጥላቻ አብደት ደርሰዋል::
 የወያኔ የጡት ልጅ ኦህዲድ ብልጽግና የክፋት  ጉዞ በጅፕሲዎች በይሁዲዎች  ላይ ተስፋፊነቱን መሰልቀጡን ሲጀምር ዝም ተብሎ መጨረሻ ላይ ሁሉንም የአውሮፕና የአለም መንግስታት ለመስልቀጥ የሶስተኛውን የአለም ጦርነት የጀመረ የናዚ ጀርመን  ስራን ያስታውሳልና ጆሮ ያለው ይስማ በፍጥነት በተቀናጀ ትብብር የኦህዲድ ብልጽግና  መፋለሙ ይቀጥል::
ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop