February 3, 2023
10 mins read

አባታችን “አዋቂ” ነው ያሉበት ንግግር አንድምታዎች* (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በመግለጫቸው በቤተክርስትያን ላይ የተፈጸመውን የተንኮል ጥቃት ያካሄደው “አዋቂ” ነው ብለዋል።  አዋቂ ነው ማለት ምን ማለት ነው?

አንድምታ አንድ

ክርስቶስ  ስለሰቀሉት አይሁድ አባቱን ሲማጸን “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ብሏል። “አዋቂ ነው” ቤተክርስትያኗ ላይ ጥቃት የሰነዘረው ማለት ወንጀለኛው ይቅርታ የሌለው፣ መንፈስ ቅዱስን የተዳፈረ፣ የሲዖል ተወካይ ነው ማለት ነው።  ይቅርታ የሚጠየቅለት ሰው ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሆኖ እንዳስተማረን የሚያደርገውን የማያውቅ አጥፊ ሲሆን ነው። አዋቂ አጥፊ ግን ይቅርታ የሚገባው አይደለም።

እሱ በዳይ ሆኖ እሱ ከሳሽ መሆኑ ያባቱን የሣጥናኤልን ባሕርይ መውረሱን የሚያሳይ ነው።እንደተለመደው ዲስኩሩን አቢይ አህመድ ኃላፊነቱ በሚጠይቀው መሠረት ሕግን ለማስከበር  ሳይሆን ይልቁንም ሁል ጊዜም እንደሚያደርገው ተደራራቢ የማታለያ ውሸቱን ከመንዛትም በላይ የማቃጠር፣ ክብሪት የመለኮስ፣ የማጋጨት ጄኖሳይዳዊ እልቂት የመጥሪያ የተመሠጠረ ኮድ የመርጨት ሥራን ለመሥራት ተጠቅሞበታል።

የጉዳዩ ባለቤት መሆኑንም ያለ እፍረትና ፍርሃት ግልጽ አርጎታል። አንደበተ ርቱዕ ቢሆንም የአማረኛ ቋንቋ ችሎታው ግን እስከዚህም እንደሆነ የማያጠራጥረው ጠ/ሚ  አዋቂ ነው ሲሉት  እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ተሸውደው ብልህ ነው፣ ባለ ምጡቅ አእምሮ ነው ያሉት ሊመስለው ይችላል። እያወቀ የሚያጠፋ ሰው የሠራው ሥራ ነው። በመንፈስ ቅዱስ የምትመራን ቤተ ክርስትያን ሆን ብሎ ለቄሣር እንድትሰግድ ለማስገደድ ሲል ሰይፍ መዝዞባታል ማለታቸው ነው።

እስክንድርን “ግልጽ ጦርነት እናውጃለን” እንዳለው በተዋሕዶ (በሀገርም ላይ)  ግልጽ ጦርነት አውጆ እያፋፋመው መሆኑን አመልክቷል። ሰሞኑን ከዓለም ዙሪያ ያሰባሰበው ቆርቆሮ  (የጦር መሣሪያ) ይሆን ለዚህ ድፍረት ልቡን ያተባው?

 

አንድምታ ሁለት 

አዋቂ ማለት የሚሠራውን የሚያውቅ፣ ለሚሠራው ሥራ በዘፈቀደ እና በይሁነኝ ሳይሆን በቂ ጥናትና በቂ ዝግጅት የሚያደርግ ማለት ነው። አቢይም ለዚህ የጥፋት ሥራ በቂ ዝግጅት**  ማድረጉን ሲያመለክቱ ነው። እዚህ  ላይ አቢይ አህመድ ራሱን ብቻ ሳይሆን ከመቶ አመት በላይ ተዋሕዶን ለማጥቃት ዝግጅት ሲያደርግ የኖረውን ኃይል በተግባርም  በመንፈስም  የሚወክል ነው።

አንድምታ ሦስት

አንድም ደግሞ አባታችን ሕገወጡን ሥራ የሠራው “አዋቂ” ነው ማለታቸው ቤተክርስትያንን የሚያውቃት አሳልፎ እንደሰጣት ሲያመላክቱ ነው። ክርስቶስን ለይተው መያዝ እንዲችሉ የውስጥ አዋቂ በመሆን ስሞ አሳልፎ የሰጣቸው ይሁዳ ነበር። ክርስቶስን የሚያውቀውና የሚለየው የውስጥ ባንዳ ማለት ነው ይሁዳ። በቤተክርስትያን ላይ ጥቃቱን የፈጸመው አዋቂ ነው ማለታቸው እንደ ይሁዳ አሳልፎ የሰጣት የውስጥ አዋቂ ባንዳ ነው ሲሉ የዳንኤል ክብረትን ሚና መግለጻቸው ነው። ይህ በሳጥናኤል ስብሐት ነጋ ተመልምሎ  በቤተክርስትያን ውስጥ የተመስገ ውስጥ አወቅ ለዚህ ለተፈጠረበት የክህደት ሰዐት ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል ማለት ነው።

 

*አንድምታ ማለት አንድ ቃል ወይም ንግግር በተለያየ አውድ፣ መቸት እና እሳቤ የተለያየ ትርጓሜ ሲኖረው አንድም እንደዚህ ተብሎ ይፈታል፣ አንድም ደግሞ እንደዚህ ተብሎ ይነበባል  እያሉ የሚያብራሩ ወይም የሚተነትኑበት ስልት ነው። አንዳንድ ተናጋሪዎች በተለምዶ አንድምታ እንደማለት የነገሩ “እንድምታ” ሲሉ ይደመጣሉ።  ይህ ግን ስህተት ነው።

**የአቢይ አህመድ ዝግጅት ከብዙ በጥቂቱ

  1. 40 አመትበተዋሕዶ ላይ የተደረገው ዘመቻ
  2. የተዘረጋውጸረ ተዋሕዶ መንግሥታዊና ተቋማዊ ሥርዓት
  3. ከ97 ጀምሮ ኢህአዴግ  በአዲስ አበባ የደህንነትና የፖሊስ መዋቅራት ውስጥ ኦርቶዶክስና ኢትዮጵያ ጠል የሆኑ አባላትን በከፍተኛ ቁጥር መሰግሰጉ።
  4. አዲስአበቤ ከከተማው የደህንነትና የፖሊስ ተቋማት ውጭ መደረጉ
  5. የጃርሶሱማሌ ጎሳ የሆኑ በዚያድ ባሬ ጸረ ኢትዮጵያ ስብከት ከተጠመቀው ምሥራቅ ሐረርጌ በኦህዴድና አብዲ ኢሌ ጥምረት ተፈናቅለው አዲስ አበባ ውስጥና ዙሪያ እንዲሠፍሩ የተደረጉ ተዋሕዶ ጠል  ኢስላሚክ ኦሮሞዎች (ለማ መገርሳ ባመነው አንድ ሚልዮን የሚደርሱ)
  6. ብልጽግናመንግሥታዊ ሚድያውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠርና ማፈኑ
  7. ተቋማትንመቆጣጠሩ
  8. በሚልዮንየሚቆጠር ከውጭ በጉምሩክ የገባ ገጀራ
  9. ከሩሲያናሌሎችም  ሀገራት የተገዙ ብረት ለበሶች፣  መትረየሶች፣  ጸረ ሰው ፈንጂዎች፣ መርዞች፣  ድሮኖች ወዘተ
  10. ልዩሥልጠናና ቅለባ ሲደረግለት የከረመ ከግማሽ ሚልዮን በላይ የኦሮሞ ልዩ ኃይል
  11. ልዩሥልጠና እና ቅለባ ሲደረግለት የከረመ የሪፐብሊካን ጋርድ
  12. በተለያየሽፋን የገቡ የባእዳን ሀገራት ሰላዮች፣ አልሞ ተኳሾችና ነፍሰ ገዳዮች
  13. ከተዋሕዶምእመናን ውጭ የተቋቋሙት (ወይም ተዋህዶዎች የጸዱባቸው) የደኅንነት፣ የፖሊስና የሕግ መዋቅሮች
  14. ተዋሕዶስትመታ እኛ እንጠቀማለን ብለው የሚያስቡ የተለያዩ የሃይማኖት ነጋዴዎች
  15. አለማቀፉሲዖላዊ ኃይል
  16. በተለያዩጥቅማ ጥቅሞች የተገዙ፣ በወንጀል ብላክ ሜይል የተደረጉ የውስጥ አርበኞች
  17. በምርጫናበሌሎች ሰበቦች ሲሰነድ የከረመ የተዋሕዶ ምእመናን ሙሉ መረጃ

ይሄ እንግዲህ በዋናነት ኦርቶዶክሳውያንን በጎራ ከፍሎ በጦርነት በማዳቀቁ ምክንያት (በአቢይና በሕወሃትም ጉልህ የፕሮፓጋንዳ ተሳትፎ ጭምር) በተለይ  በብዙ የትግራይ ክርስትያኖች  ላይ ከተፈጠረው  “የምናገባኝ ስሜት” በተጨማሪ ስለተደረጉ ዝግጅቶች ስንመለከት ነው።

በአጭሩ አቢይ አህመድ  ከሚገባው በላይ ተዘጋጅቶ፣  ከበሻሻው የተዋሕዶ ካህናት ጭፍጨፋ ዘመን ጀምሮ ከሃያ አመታት በላይ ልምምድ ወስዶ የገባበት ዘመቻ ነው። ሥልጣን ከመያዙ  አስቀድሞና ከያዘም እለት ጀምሮም ለዚች ቀን መሠረት ሲጥል፣ ወጥመዶቹን ሲዘረጋ የከረመ ነው። በዚህ ዝግጅቱ ምክንያት ከመጠን ያለፈ ስለሚታበይ እንደ ፈርዖን ባሕረ ኤርትራ በላዩ ላይ እስኪከደንበት ከዚህ የእብሪት መንገዱ የሚመለስ አይመስልም። እግዚአብሔር መከራውን ያቅልልን።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop