December 23, 2022
7 mins read

የአማራውን ሕዝብ እንባ ጠባቂዎች ከጽንፈኛው ኦነግ ሸኔ በማመሳሰል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የተሰነዘረውን የእብሪት ዛቻ በመቃወም የተሰጠ መግለጫና የትግል ጥሪ

December 23, 2022
Vision Ethiopia
መግለጫና የትግል ጥሪ

visionየአማራው ሕዝብ ተወላጆች በኦሮሚያ ክልል፣ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝና በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በተደጋጋሚ በዘር ላይ ያተኮረ ጭፍጨፋ ሲደርስባቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከአንድ የሃገር መሪ ቀርቶ፣ ከአንድ ሰብአዊ ህሊና ካለው ሰው የሚጠበቅ መቆርቆር ሳያስዩ ቆይተው፣ በዛሬው እለት (December 23, 2022) የአማራውን ሕዝብ እንባ ጠባቂዎች፣ ከጽንፈኛው ኦነግ ሸኔ በማመሳሰል፣ “የአማራ ሸኔ” ሲሉ የተናገሩት የእብሪት ዛቻ፣ ብዙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን አሳዝኗል፣ አበሳጭቷል፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም እስካሁን የተደበቀ አላማ በግልጽ አሳይቷል።

ምንም እንኳን፣ በአማራው ሕዝብ ላይ ሲካሂድ የቆየው የዘር ማጥፋት ዘመቻና በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ የሚታየው የኦሮሙማ መስፋፋት ዘመቻ በመንግሥት መዋቅር የተደገፈና፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ እውቅና የተሰጠው መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ቢሆንም፣ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያን ስለአገር አንድነት በማሰብ፣ ከዕለት ወደ ዕለት ሁኔታዎች ይሻሻሉ ይሆናል በሚል ምኞት፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስዉር ደባ የሚገባዉን ትኩረት ሳይሰጡትእስካሁን መቆየታቸው ይታወቃል።

በዛሬው እለት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አንደበት የተሰነዘረው የማን አለብኝነት አነጋገር፣ የኦሮሙማ የበላይነት በገሃድ እንዲረጋገጥ የተፈለገበት ደረጃ ላይ መድረሱን ከማረጋገጡም በላይ፣ የአማራውንና ሌሎች ጭቁን ወገኖች ትግልም ከተሸፋፈነት ጋቢ ወጥቶ፣ አግጥጦ ከመጣው አደጋ ጋር በግልጽ መታገል ያለበት እርከን ላይ የሚገኝ መሆኑን በማያሻማ መንገድ ግልጽ አድርጎ አሳይቷል።

የአማራውን ሕዝብ እንባ ጠባቂዎች፣ ከጽንፈኛው ኦነግ ሸኔ አመሳስሎ “የአማራ ሸኔ” በሚል የእብሪት ስያሜ መስጠቱ፣ በድንገት የመጣ የአንደበት ዉልመት ሳይሆን፣ በተራቀቀ መንገድ የታሰበበትና፣ መጪዉን የኦሮሙማ የበላይነት ማረጋገጫ እቅድ በሥራ መተግበሪያ አካል ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ እንደ ኢላማ ያደረጉት፣ የአማራውን ሕዝብ በግፍ መጨፍጨፍ ለመከላከልና የኦሮሙማን ያልተለጎመ መስፋፋት ለመግታት የሚጥሩትን የፋኖ ኃይሎች በጽንፈኝነት በመሰየም፣ ከባድ ዘመቻ አካሂዶ በማያዳግም ሁኔታ ማጥፋት ነው።

ሌላው እቅድ ደግሞ፣ በህቡእና በገሃድ የሚታየው፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የጸጥታና የባህል መዋቅሮችን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አዉሎ፣ ከመልከአ ምድር እስከ መዋእለ ንዋይ ተቀናቃይ የሌለው የኦሮሙማን የበላይነትን ማረጋገጥ፡ነው።

ስለዚህ በዉጭና በአገር ዉስጥ የሚገኙ፣ ለሰላም፣ ለነጻነት፣ ለአንድነትና ለእኩልነት የቆሙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ በዐብይ አሕመድ የሚመራዉን ጸረ ኢትዮጵያና ጸረ አማራ ዘመቻ፣ የሚቻለውን መንግድ ሁሉ በመጠቀም፣ በተቀነባበረ የተቃዉሞ እርምጃ እንዲታገሉ አስቸኳይ ጥሪ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

ትግሉ የረጅምና የአጭር ጊዜ ትልም ቢያስፈልገዉም፣ ከዚህ በታች የተሰነዘሩትን እርምጃዎች በአስቸኳይ መውሰድ አማራጭ የሌለው የህልዉና ማረጋገጫ ስልት ይሆናሉ።

  1. የመዋእለ ንዋይ ዘመቻ። የአገር ዉስጥ ነዋሪዎች በተከታታይ የሥራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ፣ የዉጭ ነዋሪዎች የብልጽግና መንግሥት የዉጭ ምንዛሪ የሚያገኝባቸውን ምንጮች እንዲያደርቁ፤
  2. ሰላማዊ የሕዝብ አመጽ። ተማሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና ሊሎችም የሀብረተሰብ ክፍሎች ሰላማዊ የሕዝብ አመጽ እንዲያካሂዱ፤
  3. የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ። የዲያስፖራ አባሎች በበይነ መረብ የዓለም አቀፍ ተቃዉሞ በተከታታይ እንዲያራምዱ፤
  4. የድርጅቶች ጥምረት።በተናጠል ተሰማርተው የሚገኙት የዉጭና የውስጥ ድርጅቶች፣ ኃይላቸውን በአንድነት የሚያስተባብሩበት መንገድ እንዲፈጥሩ በተናበበ መንገድ ተግሉን እንዲያፋጥኑ፤
  5. የገንዘብና ቁሳቁስ እርዳታ። በውጭ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት አገር ዉስጥ ለሚደረገው የሞት ሽረት ትግል የሚዉል የፋይናንስና የቁሳቁስ አቅርቦት በማዘጋጀትና በማስተባበር ኢትዮጵያዊ ግዴታቸዉን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡

 

ኢትዮጵያ በልጆቿ የአንድነት ትግል የፍትህና እኩልነት አገር ሆና ለዘላለም ትኖራልች!!

መጀመሪያ በሶሻሊስቶች ላይ መጡ፣ እኔም ድምጼን አላሰማሁ-

ሶሻሊስት አልነበርኩምና።

ቀጥለው በሠራተኛ ማሕበረተኞች ላይ መጡ፣ እኔም ድምጼን አላሰማሁ-

የሠራተኛ ማሕበረተኛ አልነበርኩምና።

ከዚያ በአይሁዶች ላይ መጡ፣ አሁንም ድምጼን አላሰማሁ-

አይሁድ አልነበርኩምና።

በመጨረሻ በራሴ ላይ መጡ –

 

ድምጹን ስለእኔ ለማሰማት የተረፈ ሰው ግን አልነበረም።”

— Martin Niemoller

 

Vision Ethiopia is a 501 (c) (3) nonprofit organization incorporated in Washington, D.C. EIN 81-0729204. http://visionethiopia.org. Email:

[email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop