መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
ወያኔ ፤ ( ትህነግ ፣ ህውሃት ፤… ወዘተ ። ይባል ። የሰው ሥብሥብ ነው ። ሆኖም በዘር ላይ የተመሠረተ ጠባብ የፖለቲካ ቡድን እንደሆነም ይታወቃል ። ) ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ጋር ታረቀ ። ” ትጥቄን እፈታለሁ ። የጦር መሣሪያም አሥረክባለሁ ። አዲስ ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም ና ነፃ ምርጫ በትግራይ እንዲካሄድ እንቅፋት አልሆንም ። ሠላምን በትግራይ ክልል ለማንገሥ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተባብሬ እሰራለሁ ። ” አለ ። ወዘተ ። ብሎ በደቡብ አፍሪካ በፕሪቶሪያ ከተማ የሠላም ሥምምነት ሰነድ ፈረመ ። ሲባል ፣ ” እፎይ ! ቀየደቂቃው ፣ በከንቱ የሚሞተውን ወገናችንን መታደግ በራሱ የሚያሥመሠግን ተግባር ነው ። ምንም የማያውቀው ምሥኪን ህዝብ ፀሎቱን ፈጣሪ ሰማው ። ” ነው ያልነው ። አብዛኛው ሠላም ወዳድ ህዝብና ብዙዎቹ ምሁራን ። በቀና ልቦና ይኽንን ነው ያሉት ። ( በበኩሌ ጦርነት መቆሙን ብቻ ሣይሆን ፍፁም ከአገራችን ቢጠፋ ደሥተኛ ነኝ ። ” ሰው የሚገድልና የሚያሰቃይ ሤጣን ብቻ ነው ። ” ብዬ የማምን ሰው ነኝ ። ሤጣን ደግሞ በልዩ፣ልዩ መንገድ የሰውን አእምሮ ተቆጣጥሮ እንደ ሰው ፣ ሰው ሆኖ በሰዎች ህሊና ውሥጥ በያዳንዱ ሰው ይሁንታ የሚኖር ነው ። መጥፎ ና እኩይ ድርጊት ከየትም አይመጣም ። ሴጣን ከተጠናወተው ለበጎና ለሠናይ ምግባር ካልተገዛ አእምሮ እንጂ ! )
… ይኽንን ድንገታዊ የእርቅ ዜና ሥሰማ ግን ( ልብ በሉ ፤ ወያኔ ግብዓተ መሬቷ ሊፈፀም አንድ ሐሙሥ ሲቀረው የተደረገ የሠላም ሥምምነት ነው ። ) ” ከእንግዲህ በሬ ወለደ ቢሉኝ አምናለሁ ። ” ነው ያልኩት ። ” The Impossible is possible . How the dead man Woking ? ” … ። …
” ኩበት ሰምጦ ዲንጋይ ዋኘ ። አህያ በቅጥር ጊቢ ውሥጥ ተወስና የውሻን ተግባር ፈፀመች ። የቤት ፣የሠፈር ጠባቂነት ላይ የተሰማራው ውሻ ሣር ሊግጥ ና ሊያናፋ ፣ ወደ ዳ ወጣ ። ወተት ጠቆረ ። ኑግም ነጣ ። ” ቢሉኝ ከእንግዲህ በኋላ አምናለሁ ። ነበር ያልኩት ። ነገሩ ሁሉ ፣ ” ድመት መንኩሳ ፣ ዓመሏን አትረሳ ! ” እንደሚሆን ግን አላጣሁትም ነበር ። ዛሬም እየሆነ ያለው ይኸው ነው ።
ዛሬ እየሆነ እያሥተዋልን ያለነው እውነት ግን ፣ዓይናችንን ለሠላም ብለን ሥንጨፍን ፣ ከበፊቱ በተጠናከረ መልኩ ዘመናዊ ቢላዋ እና ልዩ፣ልዪ ኃይልን የመሣል ተግባር ነው ። ኃይል በማደራጀት ና በሥልጠና በማብቃት ፤ ምናልባትም በጠላቶቻችን የታገዘ ወታደራዊ ሥልጠና በማግኘት ለዳግማዊው መብረቃዊ ጥቃት ወያኔ እየተዘጋጀች ሊሆን ይችላል ። ይሁን እንጂ ይኽንን እኩይ የጥፋት ዕቅድ እንዳናውቅባቸው የሠላም ሥምምነት የጊዜ ማራዘሚያ ድራማ ትህነግ ከግብረ አበሮቹ ጋር እየተወነ እንደሆነ የሚያጠራጥሩ ድርጊቶች አልፎ፣አልፎ ሲከወን እየታዘብን ነው ።
ለመሆኑ ፣ ” የኤርትራ ጦር ከራሱ ደንበር ይልቀቅ ፤ ካለቀቀ ሥምምነቱን አንተገብርም ። ” ማለት ምን ማለት ነው ? ” ህውሃት የትግራይ ክልል ምክር ቤትን ጠርታ መሠብሰቦ ምን መልዕክት ና ለማሥተላለፍ ፈልጋ ነው ? ‘ የሞትነውም እኛ ያለነው ና በጠብ መንጃ እየስፈራራን ህዝብን የምንመራው እኛ ነን ። ” ማለቷ ይሆንን ? መከላከያን ያለ ደጀን ለማሥቀረት እና ተረት ለማድረግ ነው እንዴ …” የኤርትራ ጦር ከድንበሩ ይልቀቅ ። ” እየተባለ በዘወርዋሬ የሚጮኸው ። የኢትዮጵያን መከላከያ አለአጋር ለማሥቀረት ተፈልጎ እንደሆነ የማይገባው ማነው ?
ወዳጄ ሆይ ! ሠላም !ሠላም ! የሚለውን የማዘናጊያ ዘፈን አብረህ በማንጎራጎር አትዘናጋ ። ወደድክም ጠላህም የተቀሩት ጥቂት እባቦች ጭንቅላታቸው ተቀጥቅጦ እሥካልሞቱ ጊዜ ደረስ የአማራና የአፋር ልቂት እና የኢትዮጵያ መድማት ቀጣይ እንደሆነም ተገንዘብ ። ለሚቀጥሉት አራት ወራት ወያኔ እፎይታን ካገኘች ለታአምር የሚበቃ ዘግናኝ ድርጊት መፈፀሞ አይቀርም ። ይልቁንስ ከኤርትራ ጦር ጋር እንደ አገር ተባብሮ የተቀናጀ የጦር ልምምድ ማድረግ የሚያዋጣ እና ጥሩው አማራጭ መሆኑንን ተገንዘብ ። ወያኔ “በዓምበሉ “ አማካኝነት አሣልፎ የሰጠውን አገር ዛሬ በጠላትነት የሚመለከተው ከምዕራባውያን ጥቅም አንፃር መሆኑንም አትዘንጋ ። የዛሬው የወያኔ ዓምበልም የህውሓትን ማሊያ ለብሶ ለአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም እንደሚጫወት እወቅ ። የሚሊዮኑ ደሃ የትግራይ ወጣት ከንቱ ሞት ለእርሱ የሆሊውድ ፊልም ነው ። ( የሚያሳዝነው በዚህ እጅግ ዘመናዊ ዓለም እኛ እንደ ዲንጋይ ዘመን ህዝቧች በጭፍን እና በመንገኝነት ፤ በጉልበት መሪ የሆኑትን አላዋቂ ጥቂት ግለሰቦች መከተላችን ነው ። )
ወያኔዎች ለአሜሪካ መንግሥት ባለሥልጣናት ፣ በሰጡት የወርቅ ገፀ በረከት በዘመናዊ መሣሪያ ብቻ ሣይሆን በዘመናዊ መንገድ የትግራይን ልዩ ጦር እየሰለጠኑ እንደሚገኙ አጠራጣሪ ምልክቶች ከታዩ ይኽ እጅግ አደገኛውና ደግማዊ አደዋን ከሳች ሴራ እንደሚሆን ከወዲሁ ይወቁት ። … ( የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ጥቅም እንጂ ሌላ የሚገዛቸውም ሆነ የሚገዙለት ምድራዊኃይል እንደሌለ እናውቃለን ። በሱማሌያ የተዋረዱትም ነዳጇን አይተው ነው ። በዩክሬንም ይኽ የጥቅም ታሪክ ነው ከዘሌኒሥኪ ጋር እንዲወግኑ ያደረጋቸው ። ሥጋ ባለበት በዛ ፣ አሞራ እንደሚሰባሰብ እወቅ ። )
ከትህነግ የጭራቅ መንገድ ለመላቀቅም የኢትዮጵያ ህዝብ ያለው ምርጫ አንድና አንድ ነው ። አሁን እና ዛሬ እያባለን ያለውን የዘረኞች የከፋፍለህ ግዛ የፖለቲካ መንገዳችንን ወደ ሰውና ዜጋ ዘመናዊ የፖለቲካ ሥርዓት መቀየር ። ይኽንን ሥታደርግ ብቻ ነው ወያኔንን በአፍጢሙ የምትከሰክሰው ። ይህንን ሥርዓት ካነበርን ፣ በአንድ ቀን የትግራይ ኗሪ ህዝብ ህውሃትን ታሪክ ያደርጋታል ። እነዚህ ከ50 ዓመት በፊት ፣ በወቅቱ ባለው ነባራዊ ሁኔታ አሥገዳጅነት ህሊናቸው ውሥጥ በተሰነቀረ የጥላቻ መርዝ የታመሙ ወያኔዎችና ርዝራዦቻቸው ፣ እሥከ አሥተሣሠባቸው ይጠፋሉ ። ይኽ ከፋፋይ ና የሰው እና የዜግነት ጠላት የሆነ የፐለቲካ ሥርዓት እሥካልተቀየረ ጊዜ ድረስ ፤ በአገር ምድሩ ሤጣናዊ ድርጊትና የድረሱልን ጩኸቱ እንደማያባራ እወቁ ።
ነገ ተነገወዲያ ፣ የሰሜኑ እኩይ እና ከኢትዮጵያዊው ክቡሩ እና ጨዋ አስተሳሰብ ያፈነገጠ እና ኃይማኖታዊ ሥነምግባርን የጣሰ ድርጊት በሁሉም ክልሎችም እጅግ መስፋፋቱም አይቀርም ። ( የዮናታንም ( The devils advocacy የተባለ የሆሊውድ ፊልም ዓይነት ) ሥብከት ይኽንኑ የተቀናጀ ኢትዮጵያን የማፈራረስ አጀንዳ የሚያመለክት ነው ብዬ አሥባለሁ ። ማንም እየተነሳ ለምን “ በዋቄ ፈታ “ ታምናለህ ሊለኝ አይችልም ። ምን አገባው ? እያንዳንዱ የኃይማኖት አሥተሣሠብ ከህግ ተቃራኒ እሥካልሆነ ጊዜ ድረስ ይከበራል ። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነትና አሥተምህሮም በኢትዮጵያ ትልቁን የህዝብ ቁጥር የያዘ ነውና ሊከበር ይገባዋል ። አንድአንዱ ሰባኪ አወቅህ ፣ አወቅህ ሲባል “ እኔ ኢየሱስ ነኝ ። “ እንደሚል በኢትዮጵያ የኃይማኖት ታሪክ ተደጋግሞ መታየቱንም አሥታውሱ ። በግሌ “ አዩም ሆነ ዮናታን ) ለእኔ ተራ ሟቾች ናቸው ። ከሞቱ በኋላ የሚፈጠረውን የሲኦልና የገነቱን ቅጣት ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያቅላቸው ። …
እና ዛሬ ከጎጠኞች ጋር ተዳብለወ በኃይማኖት ሥም ህዝብን የሚከፋፍሉ የነማን ቅጥረኞች እንደሆኑ የታወቀ ነው ። እሥቲ ለልማት እና ለደሃው ህዝብ እንሰራለን ካሉ በሚሊዮን የሚቆጠርን ወጣት ወደ ሥራ የሚያሰማሩ የተለያዩ ለአገር የሚበጁ ፋብሪካዎችን በአገራችን እንዲገነቡ ለወሬ ብቻ የሚደጉሟቸውን ፈረንጆች ይማፀኑ ። አገር የምትገነባው እኮ ፀሎት ከሥራ ጋር ሲጣመር እንጂ ቸርች ውሥጥ ዝንጥ ብሎ በርዕቱ አንደበት በማውራት አይደለም ።…
ዛሬ እና አሁን ፣ መርዘኞቹም ሆነ መርዙ ሳይኖር ፤ በጥቅም የተሣሠሩ ፣ መሞታቸውን የዘነጉ ዘረኞች ና ጎጠኞች ከ 50 ዓመት በፊት በሚሰቃዩበት ህመም እየተሰቃዩ ነው። እነዚህ ህሊናቸው የታመመ ፖለቲከኞች እና ደቀመዝሙሮቻቸው ፤ ቢያንስ በተፈጥሮ ሞት ከምድሪቱ እሥካልጠፉ ጊዜ ድረስ ዜጎች አጭርና ጣፋጪ መሆን የሚገባትን ህይወታቸውን በስቃይና በሰቆቃ መኖራቸውን ይቀጥላሉ ።
በበኩሌ እነዚህ እብድ ፕለቲከኞች ከኢትዮጵያ ጥርግርግ አድርጎ ፈጣሪ እንዲያጠፋቸው እና በአገራችን የዜጎች ሰብዓዋ መብት እና የዴሞክራሲ መብት ተከብሮ ፤ ፍትህ ለሁሉም እኩል ተዳርሶ … ህግም በአገራችን የሁሉም የበላይ ሆኖ ፣ የሁሉም ሰው መብት በቋነቋ ሥም ሳይረገጥ ዜጋ በአገሩ እንዳሻው ተዞዙሮ በመሥራት ህይወቱን አጣፍጦ ፣ለትውልዱም ጥሪት አፍርቶ የሚሞትበት መልካም ሥርዓት እንዲመጣ እፀልያለሁ ። …