November 18, 2022
15 mins read

ብልፅግና ሆይ ከፖለቲካ ቁማር /Political Conspiracy/ ና ከፖለቲካ አስመሳይነት /Political Correctness/ አባዜ ውጣ

5169መንግስት የሚያዋጣውን እራሱ ቢያውቅም ሃገርን በሰላም ፣ በሕግና በአንፃራዊነት በተረጋጋ መንገድ ለመምራት ከብልጣብልጥነትና ከተንኮል በፀዳ  / far from Conspiracy/ መልኩ ሊያስተዳድር የግድ ይለዋል እንላለን።

ፈረንጆች አንድ የሚከውኑት አፀያፉ ና ተንኮል የበዛበት አካሄድ አላቸው እሱም የፖለቲካ ጂዋጂዌ(አስመሳይነት) / Political Correctness/ ይሉታል።

ይህ ማለት ፖለቲከኞች ወይም መንግስታት እውነቱን እያወቁና ትክክለኛ አደጋ የሚያስከትሉ ጉዳዮች እንዳሉ እየተገነዘቡ ለሚቃወሟቸው ፣ ለተፃራሪዎቻቸው፣ ለአደጋ ፈጣሪዎች እና ለአሸባሪዎች በመርዝ የተለወሰ ከለላ ፣ እሽሩሩ ማለትና ድጋፍ መስጠት የሚታይበት በሴራ የተተበተበ አካሄድ አላቸው።

ይህንም አካሄድ ብልፅግና እየተከተለና እየፈፀመ ይመስላል ። ኢትዮጵያዊነቱን ክዶ ልገንጠል ያለን ቡድን ፣ ወልቃይት ጠገዴን ቡጉልበት ይዞ ከሃገር ኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተጣምሮ ሃገርን ድምጥማጧን ሊያጠፋ ካሰብ ሕወሃት ጋር መለሳለስ ፣ አጥያቱን ማቅለል “የወገንን ቁስል ረስቶ “ ወያኔን “እመ አሰረ ዐጥያት ፣ እግዚአብሔር ይፍታችሁ” ብሎ በድፍረትና ሕዝብን ንቆ ከጠላት ጋር የመላላስ በፖለቲካ ሻጥር /Political Conspiracy/ና በፖለቲካ ሸለመጥማጥነት / Political correctness/ በሽታ ብልፅግና የተለከፈ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ እየታየበት ነው።

ለምሳሌ አሜሪካኖችና አውሮፖዊያን አሸባሪነትን በጣም ይጠየፋሉ ፣ ይከላከላሉ ፣ አሸባሪነት ይፈልቅበታል በሚባለው ሃገራት አፍጋኒስታን ፣ ኢራቅ ወዘተ ያለውን ቡድን ይፋለማሉ።

ነገር ግን በአሜሪካና በምዕራብ ሃገራት የሚኖሩ የአሸባሪ ቡድን ሰለባ ወይም ሰለባ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉትን ግለሰቦች ፣ ቡድኖችና ተቋማት መንከባከብ ፣ ተለሳልሶ ማቅረብ ፣ አስተሳሰባቸውን “ሙያ በልብ ነው ፣” በሚል ህሳቤ አለመጫን። ይህ ነው እንግዲህ የፖለቲካ አስመሳይነት / አልማጭነት/Political correctness / በአጭሩ ማለት።

ይህን ካልኩ ዘንዳ ሰሞኑን ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር በኢትዮጵያ ፓርላማ ተገኝተው በተለይ ስለወልቃይት የተናገሩትን ሃሳብ እንገመግማለን። አንድ ባንድ እንደሚከተለው ዘርዝረን የፖለቲካ ቁማሩንና የፖከቲካ አስመሳይነት እንተነትናለን;

  • ወልቃይት የወልቃይቴዎች ነው ለሚለው አገላለፅ፣

ወልቃይት የወልቃይቴዎች ነው የሚለው አገላለፅ ለወልቃይቴዎቹ የሚዋጥላቸው አገላለፅ አይደለም።

ነገር ግን እኛ ወልቃይቴዎች አስረግጠን የምናስታውቀው ወልቃይት በቅድሚያ የኢትዮጵያዊያን አጥር ነው። ከዚያም አለፍ ሲል ፣ “የከለው ዘር” “የአኮኖ ወሳባ” ቅድመ አባታችን  ከዘር ግንድ የፈለቀ የመጀመሪያው አማረኛ ተናጋሪና አማራ ወልቃይቴ ነው።  ወልቃይት የአማራ ዐፅመ እርስትና ዋና ከተማው በዳባት ተሰይሞ በበጌምድር ጎንደር ለዘመናት ሲተዳደር የነበረ መሬት ነው። ከዚህ ባለፈ ሊታወቅ የሚገባው ወልቃይቴ የጎንደር መስራች አማራ እንጂ ወልቃይቴ የሚል የብሔር ማንነት ልንሰጠው ሞሞከር ነውር ነው።

  • የወልቃይት ሕዝብ የተጎላደፈ ትግረኛና አማረኛ ተናጋሪ ነው ለሚለው ታሪክን ያላጣቀስ ንግግር በተመልከተ ፣

እኛ የምንለው  ወልቃይት የአማራና የአማርኛ ቋንቋ መፍለቂያ እንደመሆኑ ወልቃይት ጥርት ያለ አማረኛ ተናጋሪ ነው። ወልቃይት ከሱዳን ፣ ከኤርትራና በተከዜ በኩል ከትግራይ ጋር ስለሚዋስን አብሮ በመኖር ዘየ የአረበኛ ፣ የተወላገደ ትግረኛና የግህዝ ቋንቋ ተናጋሪ ለመሆን አስችሎታል። ህውሃት በተወላገደ ፓሊሲው ወልቃይትን ያለሕግና አግባብ በትግራይ ክልል ለ27 ዓመታት አካሎ የወልቃይት የ30 ዓመታት ትውልደ ውጤቶችን አፈ ሙዝ ደቅኖ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አማረኛ ሳይሆን በትግረኛ እንዲማሩ ስላደረገ ልሳነ ንግግረ ዜያቸው (  Accents) የትግራይ ሊመስል ይችላል ። ነገር ግን ቋንቋ የመግባቢያ መሳሪያ እንጂ የማንነት መገለጫ ስላልሆነ ሳይንሱም ( Language is not a reliable reflection of once identity, but a mince of communication) ስለሚል ይህ አነጋገር ወንዝ አያሻግርም።

የወልቃይት ሕዝብ ትግረኛን ከሆነም የኤትራን የትግረ ቋንቋ ይወላገድበታል እንጂ የአማረኛ ቋንቋና የአማራ ቅድመ መሰረቱ ወልቃይት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

  • የወልቃይትና የትግራይ ሕዝብ የተጋባና የተዋለደ ሕዝብ ነው ለሚለው ።

ይህ አነጋገር ሊያስኬድ ቢችልም ታሪክና ቱፊት እንደሚያሳየው ወልቃይትና ትግራይ በየብስ /በመሬት/ ብዙም የደንብር ግንኙነት የላቸውም። በዚህም  ምክንያት ብዙም የጋብቻ ጥምረት አልነበራቸውም። ነገር ግን በ 27 ዓመታት የህውሃት ያገዛዝ ዘመን በኃይልና መሳሪያ በመደቀን በወልቃይት የትግራዮችን ቁጥር ለማብዛት ሲባል የለ ፈቃዳቸው የወልቃይት ልጃገረዶች የአስገድዶ ጋብቻ ሰላባ ሁነው ሊሆን ይችላል።

  • የወልቃትን ጉዳይ በደቡብ አፍሪካው ድርድር ሙድረክ የማቅረብ ሕጋዊ መሰረት የለንም፣ ይህን ካደረግን በአማራና ኦሮሞ በምስራቅ ሸዋና  በሲዳማና ወላይታ መካከል ያለውን የመሬት የይገባኛ ጥያቄን አብረን ይዘን መቅረብ አለብን ማለት ነው ?“ ለሚለው አመክንዮ መሰል ገልፃን በተመለከተ።

 

አንዳንዴ “ኑሮውበት እንጂ ሰምቶ መናገር መልካም አይደለም ፣ያስተዛዝባልና። የወልቃይት ሕዝብ ከሕወሃት/ወያኔ/ ጋር ለ43 ዓመታት ተፋልሟል። ይህም የሆነው የወልቃይትና የሁመራን ለም መሬት ህወሃት ቡስግብግብነትና በመሰሬነት ለመውሰድ ያደርገው በነበረው ትንኮሳ ለ18 ዓመታት ፣ ከዚያም በወልቃይቴዎች ጣምራ ፍልሚያ ደርግን ካንበረከኩ በኋላ ከሃዲው ሕወሃት እንደዶለተው ከስልጣን ኮረቻው ከተፈናጠጠ በኋላ ወልቃይቴወችን ክዶ መሬታቸውን ወደ ትግራይ ሲያካልል ህውሃትን ለ27 ዓመታት ተፋልሞታል። ይህን የረጅም ዘመን የማንነት ፣ የነፃነትና የህልውና ጥያቄ በግጦሽ መገፋፋት የተነሳ የመሬት የይገባኛል ጥያቄን ከወልቃይትና ከእራያ ጥያቄ ጋር ማወዳደር የሆነ የፖለቲካ ብልጣብልጥነት / Political conspiracy/ እንዳለ ፍንትው ብሎ ያሳያል እንላለን።

 

  • የመሬት የይገባኛል ጥያቄ ያቀረቡ አካባቢዎች እራሳቸውን ያዘጋጁ የሚለውን ጉንጭ እልፍ  ንግግር በተመለከተ ፣

ታስቦበት ይሆን ወይም የምላስ መጎላደፍ / Sleep of the tonge/ ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ሃሳብ ደጋግመው ገልፀዋል።

ይህ አነጋገር ግልፅነት የጎደለው ሲሆን ፣ የወልቃይት ሕዝብ ጊዜው ደርሶና የግፉ ፅዋው ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቶ ሲፈስ ህውሃት በሕዝብ ኃይል ወደ ጎራው መቀሌና ደደቢት ሲፈነጠር ወልቃይቴዎች በመራር ትግላቸው ወልቃይትን በኃይል እንደተወሰደው በኃይል አስመልሰዋል። ያገኘቱን ነፃነት ለመሸራረፍ መሞክር “ከድጡ ወደ ማጡ” የሚያስገባ መሆኑን መግለፅ እንወዳለን።

የንግግሩ ውስጠ ወይራ የህዝብ ድምፀ ውሳኔ “Referondom” ይደረጋል ከሆነ ፣ የብልፅግና መንግስት ከአምና ጋሻ ዣግሬዎቹ ሊማር የሚገባው ኤርትራን ያለኢትዮጵያዊያን ፍቃድ በተንሸዋረረና አግባብ ባልሆነ ሪፈረደም ሕወሃት አስገንጥሎ የደረሰበትን ኪሳራ ፣ ጦርነትና ፀፀት ነው።  ብልፅግናም ይህን ታሪካዊ ስህተት ከደገመ የሃገር ክህደት እንደፈፀመ ይቆጠራል ፣ ዋጋም ይከፍላል።

ሊከናወን ከታሰበ የሕዝብ ድምፀ ውሳኔ /Referendum/ በወልቃይት ምድር ውጤቱ ምን ይሁን ምን ፣ ይህ አካሄድ መታሰብ የሌለበት ከመሆኑ ባሻገር አይበለውና ከሆነ ብልፅግና ታሪካዊ ቀርሾው ፣ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፣ ከአማራው ፣ ከጎንደሬውና ከወልቃይቴዎች ጋር ሲሆን ወደማይታረቅ የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ መግባት እንደሚያስከትል ግንዛቤ ሊወሰድቡት ይገባል እንላለን።

በፖለቲካ ውሳኔ የተወሰደን መሬት የቀደም አጋር ፓርቲን ለማስደሰት  ወይም ከላይ እንዳልነው “አካፋን አካፋ” ብሎ ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ካልከወኑ በፖለቲካ ቁማር /ሸብጥ/ (Political Correctness) በሕገ መንግስት ይፈታል ብሎ መወሰን የሕዝብን ድምፅ ፣ ዋይታና ፍላጎት አለማክበር ነው እንላለን።

ማጠቃ

ይህን ካልን ዘንዳ በኢትዮጵያ ታሪክ መንግስታት በጥሩም በመጥፎም ይነሳሉ። እንደ እኛ ግን እንደ ሕወሃት ታሪካዊ ስህተት የፈፀመ የለም እንላለን ። እሱም ኤርትራን በስመ ድምፀ ውሳኔ / Referondom/ ማእቀፍ አስገብቶ አስገንጥሏል፣ በፖለቲካ ውሳኔ ለኢኮኖሚ ጠቀሜታ ብሎ ወደ ክልሉ ወልቃይትና ራእያን በማነለብኝነት አካሏል። በየመንግስታቱ የግዛት ዘመን የአስተዳደር ስህተቶች ሊኖሩ ይችላሉ ፣ ይህ ዓይነት ዕፀፅ በጊዜ የሚፈታ ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ “ ኋላ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” እንዲሉ ብልፅግና የሕውሃትን ዓይነት ስህተት በብልጣብልጥነት ፣ በማለብኝነት፣ እውነትን በመንሻፈፍ፣ ታሪክን በማወላገድ /Political correctness and conspiracy/ በመከተል በኢትዮጵያ ላይ ሕዝብ ይቅር የማይለው ስህተት  እንዳይፈፅም እንመክራለን።

የወልቃይትን ጉዳይ በአግባቡ ፣ የ 3000 ዓመታት ታሪካችን ፣ እውነታንና ለኢትዮጵያ ሰላም የሚበጀውን አስቦ ብልፅግና ወልቃይትን ሆነ እራያን በፖለቲካ ውሳኔ ለባለእርስቶቹ ከመለሰ ብልፅግና ያተርፋል ፣ አስተዳደሩ በአንፃራዊነት የተረጋጋ ይሆናል፣ ወዳጅም ያበዛልና ኢትዮጵያም በአንድነት የቆመች የተረጋጋች ሃገር ትሆናለች ። ብልፅግና ልቡና ይኑርህ “ እንደሸማኔ መወርወሪያ ወዲህ ወዲያ ካበዛህ” ሃሳርህና መከራህ ይበዛል ፣ መጨረሻህም አያምርም።

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop