August 4, 2022
15 mins read

“ሎጋው ሽቦዬ!…የጫረው እሣት … ሲፈጀው ታየ።…” ( አባ ታጠቅ  ምንዳሁነኝ )

tplf 2 713x509

የትህነግ አመራሮች በዚህ በ11ኛው ሰዓት የበደሉትን የኢትዮጵያ ህዝብ  ይቅርታ ለመጠየቅ የሚያመነቱ ከሆነ ፣ ከሲዖል የበለጠ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ይረዱት ። ማን ይቀጣናል ካሉ ደግሞ በሚሊዮን የሚቆጠረው የትግራይ ህዝብ ነው ። የትግራይ ህዝብ የሞኝ ክምር እንደማይሆን በቅርቡ በተጨባጭ ያሣያቸዋል ።

ህዝቡ  ሙቅ በሚያኝኩት ፣ ጎንፎ በሚያላምጡት አመራሮች በጌታቸው ምላሡ እና በደፂ አኩሮባቲስቱ ሞኝነት እጅግ ተማሯል ። የትግራይ ወጣቶች ቀሥበቀሥ  እየተመዘዘች እንደተመናመነችው የሞኝ ክምር መሆን አይፈልጉም ። ይኼ ወንድም ወንድሙን የመግደል እብደት እሥከ ወዲያኛው እንዲወገድ ይሻሉ ።

የትግራይ ህዝብ ፣ እንደ ማንኛውም ሞራል ያለው ህዝብ ሰውን ለመግደል የሚፈልግ ህዝብ አይደለም ። አንደማንኛውም የኢትዮጵያ ባለአገር ያሳደገው እንሥሣ እንኳ ሲሞት ዘመዱ እንደሞተ ቆጥሮ የሚያለቅሥ ነው ። እሥከዛሬም ፤ የትላንትናውን የጥቂት ሤረኞች ግፍ እያሥታወሰ ይንገበገባል ?

” ከእኛ ውሥጥ እንዲህ ዓይነቶቹ ነፍሰ በላዎች ፣ ሰው በላዎች ፣ የጓዶቻቸውን አንገት ቆራጮች እንዴት ሊፈጠሩ ቻሉ ? እውን እነዚህ የአሉላ አና የዮሐንስ ደም በውሥጣቸው አለን ? እውን እነዚህ በፂዮን ደጀፋ ዙሪያ እትብታቸው የተቀበረ የፃድቃን ልጆች ናቸውን ? እውን እነዚህ በነጋሽ መሥጊድ ቅጥር ውሥጥ አባቶቻቸው የሰገዱ ፣ አላህን ፈሪ የነበሩ አባቶች ነበራቸውን ? ከየት ነው እነዚህ በክላሸሰ ኃይማኖተኛውን ጭምር የሚያሥፈራሩ ፣ በሰው አምሳል የተፈጠሩ ዳቢሎሶች የተፈጠሩብን ? ” እያለ ።

ትላንት ቀተፈፀመው ፣ ዛሬ ደግሞ እየሆነ ባለው የሚቆጩ የትግራይ ተወላጆች ሚሊዮኖች ናቸው ። የሰሜን ዕዙን የወገናቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ጭፍጨፋ ሲያሥታውሱ አካላቸው በቁጭት ይንዘፈዘፋል ።

እነዚህ የአይን   ምስክሮች በሰሜን ዕዝ ላይ ስለተፈጸመው  ሲናግሩ በቁጭት ነበር ።  እጠቅሳለሁ ፣ “ወደ ሰላሳ የሚጠጉ በሰሜን ዕዝ ውስጥ የሚገኙትን ወታደሮችን ገድለው፤ ልብሳቸውን አውልቀው፤ አስከሬናቸውን አንድ ላይ ከምረው ሌሊቱን ሲጨፍሩ አደሩ፤ አሁንም ድረስ አስከሬናቸው አልተቀበረም፤ አሞራና ጅብ እየበላው ነው።”  አካባቢው ላይ የነበሩ ጨዋ የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን  የቁጭት ምሥክርነታቸውን ሲቀጥሉ  ፣

“ቁልፍ የሆኑ አመራሮችን እና በአገር ፍቅር የተሞሉ    የሰሜነ ዕዝ አባላትን ከረሸኑ እና በአካላቸው ላይ  መኪና ካሥነዱ በኋላ ፣ ጥቂት ወታደሮችን ለሽብር ጥቅም ሲሉ ፣   ልብሳቸውን አውልቀው ራቁታቸውን ወደ ኤርትራ ጠረፍ  አባረሯቸው ። የኤርትራ ጦር ነው ፣ በድርጊቱ ፣ በእጅጉ በማዘን ፣ የአያቶቹን ደግነት  ፣ የራሱን ትርፍ  ልብስ   በማልበስ ፈረሃ አግዚአብሔር የነገሰበት ልብ እንዳለው ያሳያቸው  ። ”  በማለት ትላንት የአይን እማኝ ሆነው መሥክረዋል ።

ለመሆኑ ይኽንን ዘግናኝ ፣ የግፍ ኩንን  ተግባርን ማነው ያቀነባበረው  ?

ይኽንን ጥቃት ፣ በመከላከያ ውስጥ ያሉ ዘረኛ እና  ሥግብግብ የሆኑ ፣ ሥልጣን ናፋቂ   የጁንታዎች እና የነሱ  የደህንነት ኔት ወርኮች  ፣ በደብረ ፅዮን ና በጌታቸው አሰፋ አማካኝነት እንዳቀነባበሩት  ተገማች ነው ። … በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነት ቡድንም በዚህ አድራጎቱ ፣  ሞራለ ቢስነቱን እና ጨካኝነቱን በገሃድ አሥመሥክሯል ። ትላንት ፣  በማዕከላዊ ማጎሪያ ጣቢያ አሰቃይቶ የገደላቸው የማይታወቁ  አያሌ ንፁሐን ሊኖሩ እንደሚችሉ ይኽ ድርጊቱ ፍንጭ ሰጪ ነው ።

የሰሜን ዕዛችን ፣ ከትግራይ ሕዝብ  ጋር አንድ አካል ሆኖ የሚኖር ሆኖ ሣለ ፣ በችግሩ ተገኘቶ ፣ በአዝመራው ተሳትፎ የሚረዳው  ሆኖ ሣለ  ፣ የአንበጣ መንጋ በተከሰተበት ወቅት እንኳ  ከወገኑ ጋር አንበጣውን በመከላከል ስራ ተሰማርቶ ሲያግዝ እንደነበረ አየታወቀ ፣ በዕዙ ላይ  ከበባ በማድረግ ትህነግ ፣  ለእኩይ ዓላማ የሰለጠነው የትግራይ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሽያ ታሪክ ይቅር የማይለው ክህደት ፈፅሞበታል ።ይህ ታላቅ  ክህደት ታሪክ ይቅር የማይለው ነው ። ትህነግ /ህውሃት  ይኽንን ዓለም ያወቀውን ክህደት በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ፈፅሞ ፣ ዛሬም በሆዳቸው በተገዙ ሞራለቢሥ ገዳይ እሥኳዶቹ በመተማመን በትግራይ ህዝብ ላይ እያላገጠ ይገኛል ።

የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ አካሉን የትግራይ ህዝብን የሚጠላ አንጀት ኖሮትም አያውቅም ። ይሁን እንጂ በምቾት ባህር እየዋኙ ያሉት ፣ ከድህነት እንዳይላቀቅ በማድረግ ፣ የኢትዮጵያ መሪ ሆነው እንኳን ሥንዴ እየሰፈሩ በእርጥባን ኗሪ ያደረጉት፣ የተገንጣይነት ሥማቸውን  ለብዝበዛቸው ሲሉ የሙጥኝ ያሉት የዛሬዎቹ የደም ነጋዴዎቹ የህወሓት አመራሮች ናቸው ። ይኽ እውነት የሚያሳብቀው ሃቅ  የትህነግ እና የኦነግ ፈጣሪ ገብፅ መሆኗን እና እሥከዛሬም ድጋፏ ያለመቋረጡን ነው ። የአሜሪካንና የእንጊሊዝ ቱጃሮችን እነሱ ላይ ሥትደምር ደግሞ አላማቸው ይገባሃል ።  ምናልባትም በውጭ አገር ፣ በነደብረፅዮን እና በቀጣፊው ጌታቸው አካውንት ሚሊዮን ዶላር አይታጣም ።  ዛሬም ከፌደራል መንግሥት ቁጥጥር ውጪ መሠረተ ልማቶች አሥገቡልን የሚሉት ።

ይኽ ህቡ ድጋፍ ሥላላቸው የልብ ልብ አግኝተው ነው ። ድጋፍ  ባይኖራቸውማ ቀጥታ ወደ እውነቱ በመምጣት  ፣ በሰሜን ዕዝ ላይ እና በአማረ ክልል በሚኖረው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ላይ ( በዘረኝነት አመለካከታቸው ወያኔውች  እንደ ጦር በሚፈሩት አማራ ላይ ) በፈፀሙት ግፍ ተፀፅተው የኢትዮጵያን መንግሥትና ህዝብ ይቅርታ በጠየቁ ነበር ።  በህገ መንግሥቱ በተቀመጠው አግባብም በትግራይ ነፃ ምርጫ እንዲደረግ ፈቃደኛ ይሆኑ ነበር ። ህገ መንግሥት ጥሰው ” የጨረባ ምርጫ ” ማድረጋቸው ትክክል ያለመሆኑንም ያምኑ ነበር ። አሁን ግን እንደ ተለመደው የጄኖሳይድ እና የዘር ማፅዳት ኤክስፐርቶቹ ” እነ ጌች ምላሱ እና እነ ደበረ ፅዮን አክሮባቲስቱ  ” ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ የማሥታወስ ችሎታው ቅርብ ወይም አድማሥን የማይሻገር  መሥሏቸው ሲቀለማምዱ እየተሥተዋለ ነወ ። የኢትዮጵያ ህዝብ የበደለውን ና ግፍ የዋለበትን ምን ጊዜም እንደማይረሳ ፣ ታሪክን አንብቦ መረዳት  መልካም ነው  ። ከቶ ለምን ይሆን ኢትዮጵያ የባሩድ በርሜል የተሰኘቸወ ? ( የባሩድበርሜል የተሰኘውን የደበበ እሸቱን የትርጉም መፀሐፍ አንብቡ ) ጌች ና ጀፂ በመቀባጠርና በማምታታት እራሳቸው የማንነት ውድቀት ውሥጥ ገብተው ፣ ዛሬም ነፁሐን ሰዎች ፣ ወያኔ ሞኙ በለኮሰው የጦርነት እሳት ውስጥ ለዳቦ ብለው እንዲማገዱ  ጥረት እያደረጉ እንደሆነ የነጋ ጠባ መግለጫቸው ያሳብቃል  ።

መላው የኢትዮጵያ ግዛት ፣ የአፋር ፣ የትግሬ፣የሱማሌ፣የቤንሻጉል የደቡብብ ብሔር ብሔረሰቦች ፣ የኦሮሚያ፣የአማራ ፣ የቤንሻንጉል የጋምቤላ ፣ የሐራሬ ፣ የድሬ የአዲስ አበባ ወዘተ ህዝብ ሁሉ  ነው ። ህዝብ ደግሞ የግለሰብ ስብስብ ነው ።  ትግሬ ነኝ ብሎ የሚያምን አንድ ግለሰብ በየትኛውም የአገራችን ግዛት በዜግነቱ ፣ ሰርቶ የመኖር ፣ ንብረት የማፍራት እና ደህንነቱ ተጠብቆ የመኖር መብት አለው ። ሌላውም ጎሣ እንደዚሁ ። በዚህ የሠለጠነ ዓለም መታገል ያለብን ይኽንን ግለሰባዊ ነፃነት ለማምጣት መሆን አለበት ።

ወዳጄ ምድረ ሥግብግብ አይጠረቄ ቱጃር ፈረንጅ እየሳቀ ከአንተ ጋር ፎቶ የሚነሳው ለብዝበዛው ሲል እንጂ ለፅድቅ ብሎ  አይደለም ። ይሁን እንጂ ይኽንን እያወቁ አንዴ ለሆዳቸው የሞቱ የወያኔ ቁንጮ አመራሮች በሰው ደም ከመነገድ ዓላማቸው ዝንፍ አይሉም ። ለምን ቢሉ በባንዳነት ተሰልፈው አገርን ለመሥበዝበዝ ቆርጠዋልና !!

ይኽንን እውነት የሚያረጋግጥልን አገር እና ህዝብን የሚጠብቀውን መከላከያ ሠራዊት ሀገር ሰላም ነው ብሎ በጦር ሰፈሩ በወገኑ ተማምኖ ገደም ያለውን ሠራዊት   መሳሪያውን ለማንሳት በማይችልበት ሁኔታ ውሥጥ ሣለ ፤ አንዳችም   ለመገመትም ሆነ ለመጠራጠር እንኳን እንዳይችል በማደረግ  በጦር ሠፈሩ ያሉ ጥቂት የማይባሉ  የትግራይ ተወላጅ  የሠራዊቱ አባላት ፤ ከውጭ በትግራይ ልዩ ኃይል አስከብበው እነሱ ደግሞ ከውስጥ ሆነው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ ተኩስ ከፍተው በተኛበት  መጨፍጨፋቸው ነው ።

በዚህ ፀሐፊ እምነት  ደብረፅዮን በሉት እነ ታደሰ ወረደ ፤ እነ ጌታቸው ምላሱ በሉት እነ  ምግበ የመሣሠሉት ፤  ከሃዲዎችና ወንጀለኞች ሥለሆኑ የእጃቸውን ማግኘት አለባቸው ። በመቶ ሺ ሰው አፈናቅለውና በሺ የሚቆጠሩ የደሃ ልጆች በጫሩት የሞኝ እሣት አቃጥለው ገለው ፣ ዛሬ ለመደራደር ዐይናቸውን ሣያሹ መቀረባቸወ እና ጭራሽ ” የአብዬን ወደ ዕምዬ ” ለማምጣት  በቀጣፊ ምላሣቸው መፍጨርጨራቸው ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ያለማወቅ ብቻ ሣይሆን በኩሩው ፣ በጨዋው ፣ በአሥተዋዩና በጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ ማላገጣቸው መሆኑንን ተረድተው ከዚህ የመጥፊያ ሃሳባቸው ሳይረፍድባቸው ቢመለሱ መልካም ነው ። ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ ቢጠይቁ ደግሞ ቅጣታቸው ይቀልላቸዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop