ኢት-ኢኮኖሚ/ET- ECONOMY
(ክፍል አንድ)
ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)
‹‹ከዚህ በኃላ መሞት የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ለቀይ ባህር ይሙት›› አብይ አህመድ
ቀይ ባህር፣ የአፍሪካ ቀንድና መካከለኛው ምስራቅ አገሮች
እነደ መፅሃፈ ኤክሶደስ፣ ከሶስት ሽህ አመታት ገደማ፣ ‹‹ ሙሴ እጁን በቀይ ባህር ላይ ዘረጋ፣ እናም ጌታ ሌቱን ሙሉ ጠንካራ የምስራቅ አውሎ ንፋስ እንዲነፍስ አደረገና ባህሩ ወደኃላ ተመለሰ፡፡ እናም ባህሩ ነጥፎ ውኃው ለሁለት ተከፍሎ እንደግድግዳ ደርቆ ቆመ፣ በመኃሉ የሚገኘው መሬት ደረቀ፡፡ ሙሴ ተከታዬቹን እስራኤሎች ይዞ፣ ቀይ ባህርን በሠላም እንዲሻገሩ አደረገ፡፡ ግብፃዊያኖቹ እግር በእግር ተከትለዋቸው ኖሮል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ድጋሚ ሙሴን አዘዘውና ዳግም እጁን በባህሩ ላይ ዘረጋ እናም የባህሩ ደራሽ ውኃ እየገዘፈ፣ ተጥለቅልቆ ወታደሮቹን ጠራርጎ ይዞቸው ሄደ፡፡›› እናም እንደ ቅዱስ መፅሃፍ ቃል እስራኤሎች ከፈርኦን አገዛዝ ነፃ ወጡ፡፡ “About 3,000 years ago, according to the Book of Exodus, Moses “stretched out his hand over the sea; and the Lord caused the sea to go back by a strong east wind all that night, and made the sea dry land, and the waters were divided.” And then, according to the Bible, the Israelites were free from Pharaoh’s rule….When the Israelites reached the Red Sea Moses stretched out his hand and the waters divided, allowing his followers safe passage. The Egyptians followed them but God again commanded Moses to stretch out his hand and the sea engulfed the army. ” ……………………………………….…………(1)
የቀይ ባህር ድንበርተኛ ስድስቱ አገሮች በስተ ምዕራብ የቀይ ባህር ዳርቻ በኩል የመን፣ እስራኤል፣ ጆርዳን፣ ኩዌትና ኢራቅ ሲሆኑ በስተ ምስራቅ የቀይ ባህር ዳርቻ በኩል ደግሞ ግብጽ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡
ቀይ ባህር የባህር ዳርቻ በስተ ሰሜን በኩል የመንና ሳውዲ አረቢያ አገሮች የሚያዋስኑ ሲሆን፣ ግብፅን በስተ ሰሜንና ምዕራብ በኩል በስተ ምዕራብ በኩል ሱዳን፣ ኤርትራና ጅቡቲን ያዋስናል፡፡ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች በዓለማችን ዋነኛ የግጭት ቀጠናና በጣም የተወሳሰበ የፖለቲካ ሴራ የሚጠነሰስበትና የሚጠመቅበት ሥፍራ ነው፡፡ እያንዳንዱ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ሱማሌ፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በተራዘመ ልዩ ልዩ ግጭቶች በክልላዊና በብሔራዊ ደረጃ የፖለቲካ ጥላቻና ግጭት፣ የፖለቲካ የማንነት ጥያቄና ክልላዊ ውስጠ መንግሥት የተፎካካሪዎች ሽኩቻ ይቀጣጠላል፡፡ የአፍሪካ አገሮች ዋነኛ የፖለቲካ ችግር ሽበርተኛነት፣ የእርስ በእርስ የዘርና የኃይማኖት ግጭቶች ፣ የኩታ ገጠም የወሰን ግጭቶችና የድንበሮች መዘጋትና የስደተኞች ፍልሰት በአህጉሩ ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡
በድህረ-ቅኝ ግዛት ዘመን፣ከ1950 እኤአ እስከ አሁን ድረስ፣ የአፍሪካ ቀንድ አገሮች በመንግሥታቶች መኃል የተደረጉ ብዙ የጥፋትና የውድመት ጦርነቶች ውስጥ በ(1964, 1977-78, 2006-9) እኤአ በኢትዮጵያና ሱማሌ የተደረጉት ጦርነቶች፣ በ1963 እኤአ በኬንያና ሶማሊያ የተካሄደው ጦርነት ፣ ከ1978 እስከ 1979 እኤአ በኡጋንዳና ታንዛኒያ የተደረገው ጦርነት እንዲሁም ከ1998 እስከ 2000 እኤአ በኢትዮጵያና ኤርትራ የተካሄደው የመቶ ሽህ ወጣቶችን ህይወት የቀጠፈው የድንበር ጦርነት ታሪክ መዝግቦታል፡፡
“The situation in Ethiopia, if allowed to continue, will be one of the most severe security challenges Africa has ever experienced. It will also have global consequences, the kind of challenges that will invite proxy wars, mercenaries, private armies, war lords, human, arms and drug traffickers and above all violent extremism which is already behind some of the political organizations operating inside Ethiopia. Regrettably the media and the self-centered politicians prefer to deliberately avoid discussions on the deeper problems that face country, the region and the continent. The diverse stake holders are tall determined to make Ethiopia the scene of a bloody war from which they will profit either financially, politically, or strategically.” ……………………………..……………………..(2)
የአፍሪካ ቀንድ አገሮችን በቅኝ ገዢዎች በእንግሊዝ፣ ፈረንሳይና ጣሊያን የተቀበረ የሰዓት ቦንብ የተከወነ ሲሆን በኃላም በቀዝቃዛው የዓለም ጦርነት ዘመን አሜሪካና ሶብየት ህብረት ልዕለ ኃያል መንግሥቶች ሆነው ወጡ፡፡ከ1990እኤአ አንስቶ የተባበሩት መንግሥታት በሰላም አስጠባቂ ኃይል በማሰማራት ጣልቃ መግባት ሥራ አከናውኖል፡፡ በተመሳሳይ በአፍሪካ ቀንድ አገሮች ላይ የፖለቲካ ተፅዕኖ ለማድረግ በአንድ በኩል የተባበሩት አረብ ኢምሬትስና ሳውዲ አረቢያ አገሮች የሚመሩት ስብስብ በሌላ በኩል በቱርክና ኮታር አገራቶች የሚመሩት ቡድን በቀጠናው አለመረጋጋት በመፍጠርና የፀጥታ ደህንነት እጦት በማስፈን ተጨማሪ ግጭት በመጫር ልፅለ ኃያሎ አሜሪካ ላሉዎት የተለያዩ ፍላጎቶችን በተለይም በፓልስታያኖች ምድር ላይ በ1948 እኤአ የተመሠረተውን የእስራኤል መንግሥትን ጥቅም ለማስጠበቅ የማይፈነቀል የጅብራልተር ቆጥኝና የቀይ ባህር ቆጥኝ የለም፡፡ የአፍሪካ ቀንድና የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ዋነኛ የፖለቲካ ጥያቄ በእስራኤል ህልውና ላይ ያጠነጠነና ያነጣጠረ ነው፡፡ በአጠቃላይ የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች ከአረቢያን ፒንዩሱላ አጠገብ የሚገኙ አገሮች ውስጥ ግብፅ፣ ኢራን፣ ኢራቅ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ የመን፣ ሲሪያ፣ ጆርዳን፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ፣ እስራኤል፣ ሊባኖስ፣ ኦማን፣ ፓልስታይን፣ ኩዌት፣ ኮታርና ባህሪን አገሮችን ያካትታል፡፡
{0} ኢትዮጵያና ጎረቤት አገራቶች ሁኔታ ‹‹በኢትዮጵያ የሰሜኑ ጦርነት መቀስቀስ በተዘዋዋሪ መንገድ የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት ታውኳል፡፡ ኢትዮጵያ ትጫወት የነበረው ሰላም የማውረድ ሚና በፕሬዜዳንት ሳልቨኬርና በተፎካካሪው መሪ ሬክ መቻር በ2015 እና በ2018 እኤአ የሠላሙ ውይይትና ስመምምነት የተካሄደው በኢትዮጵያ ውስጥ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በመቶ ሽህዋች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ጦርነት በመፍራት ድንበር ተሸግረው ወደ ጋምቤላ ክልል ገብተዋል፡፡ በደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ኃይል መውጣትና ከፊሉም ጥገኝነት መጠየቅ የጦርነት ስጋት አስከትሎል፡፡ በኢትዮጵያ ጦርነት ከቀጠለ የስብዓዊ እርዳት ድጋፍ ስደተኞቹ የማግኘት ችግር ይገጥመዋል ተብሎ ይፈራል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ ሰባት ሚሊዮን ህዝብ እንዲሁም በትግራይ አምስት ሚሊዮን ህዝብ የርሃብ ቸነፈር በጦርነቱ ምክንያት ተከስቷል፡፡ ››.ዲ ደብሊው ኒውስ…………………………………………………… (3)
‹‹የኬንያ መንግስትም ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስነውን 800 ኪሎ ሜትር ድንበር ላይ ጥብቅ ጥበቃ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የኦነግ ሸኔ ታጠቂዎችና ሌሎችም ድንበር እየጣሱ ወደ ኬንያ በመግባታቸው ነው፡፡ በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ስደተኞች በመቶ ሽህና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወደ ኬንያ ይፈልሳሉ በሚል ስጋት ድንበር ጥበቃቸውን አጠናክረዋል፡፡›› (ዲ ደብሊው ኒውስ)
በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሦስተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ለማስተጎጎል ግብፅና ሱዳን በየአመቱ እንቅፋት በመሆን ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የአሜሪካ መንግሥትና እስራኤል ተባባሪ ሆኖ መገኘት የአፍሪካ ቀንድ አገሮችን ጅኦ ፖለቲካል ሁኔታ ይበልጥ እያወሳሰበው ይገኛል፡፡
{1} ጅቡቲና የዓለም አቀፍ ኃይሎች ወታደራዊ የጦር ሠፈሮች
የዓለም ፖለቲካ ሁኔታ ተለዋውጦል፣ በምድረ ጅቡቲ የጀርመን፣ ስፔን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ቻይና፣ ሳውዲ አረቢያ በትንሽ እርቀት ላይ የጦር ሠፈራቸውን መሥርተዋል፡፡ ራሽያና ህንድም በጅቡቲ የጦር ሠፈር ለመገንባት ፍላጎታቸውን ገልፀዋል፡፡ በአፍሪካዊቶ የጅቡቲ መሬት ቆሚ ወታደራዊ የጦር ሠፈሮች ገንብተው የጦር መሣሪያዎች እግዚቢሽን የሚያስጎበኙ ይመስላሉ፡፡
Djibouti hosts military bases belonging to Germany, Spain, Italy, France, the United States, the United Kingdom, China, and Saudi Arabia at a very little distance from one another. Russia and India too have strong interests in setting up military bases there.
የዓለም አቀፍ ኃይሎች የጦር ሠፈራቸውን በምድረ ጅቡቲ የከተሙበት ዋነኛ ምክንያት የባብ-ኢል መንደብ ዋናው መግቢያ ከተንበሬ ወደ ገልፍ ኦፍ ኤደንና የህንድ ውቅያኖስ መግቢያ በመሆኑ ነው፡፡ ከሁለቱ ገልፎች ምንም ያህል አይርቅም ከኦማን ገልፍና ከአረብ ፕርሽያን አቻው ጋር ሌላ ቀጥታ የሚገናኝ ሆርሙዝ ይገኛል፡፡ በዚህ ሥነ- ምድራዊ ገፅታ ጠቀሜታ ብዙ ዓለም አቀፍ ኃይሎች መልህቃቸውን ከ ጅቡቲ መሬት የጦር ሠፈራቸውን አኑረዋል፡፡ “The Bab-el-Mandab overlooks the entrance to the Gulf of Aden and the Indian Ocean. Not far away, two other gulfs, that of Oman and its Arab-Persian counterpart, linked by another strait, Hormuz. This geographical advantage explains why so many international powers have installed military bases in Djibouti.”
የሻለቃ ዳዊት ወልደጊዬርጊስ ስጋታቸውን እንደገለፁት ‹‹የአፍሪካ ቀንድ አገሮች በዓለማችን በጣም የተወሳሰበ የደህንነትና ፀጥታ ቀጠና ዞን መሆኑን ዋነኛ ማረጋገጫው በጅቡቲ ምድር ብቻ ስድስት ወታደራዊ የጦር ሠፈሮች መኖራቸው ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ኃይሎች በጅቡቲ የጦር ሠፈር ማቆቆማቸው ዓላማና ከበስተጀርባው ያለ ድብቅ አጀንዳ የፖለቲካ ሴራውንና አስቀድሞ መረዳት ሰው ሰራሽ ጥፋትንና ውድመትን ለመከላከል ያስችላል፡፡ እንደ እኛ እምነት የአፍሪካ ቀንድ አገሮች የቀጠናው ችግር ከመቼውም ጊዜ የከፋ፣ የስብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ያስከተለ ሲሆን እንዲሁም የስብዓዊ ፍጡር ስቃይና ችግር ርሃብ፣ በሽታና ስደት በቀጠናው ትኩረት ተነፍጎታል፡፡ ዛሬ በዓለም ትኩረት ያገኘው የሃገረ ዩክሬን ስብዓዊ ቀውስ ሲሆን የአፍሪካ ቀንድ አገሮች የባሰ እንደሚሆን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ይህንንም ጉዳይ በተለይም አምኒስቲ ኢንተርናሽናልና ሂውማን ራይት ዋች የዓለምን ህብረተሰብ ማሳወቅ ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው እንላለን፡፡›› “The Horn of Africa is the most complex security zone in the world as confirmed by the presence of more than six foreign military bases in Djibouti alone. It is the thorough understanding of this complex picture and the motives of those behind it, that may prevent the catastrophe that may follow. We also believe Amnesty International and Human Rights Watch have responsibility to warn the world of the expected human cost and the unfolding of unprecedented humanitarian crisis graver than the one in Ukraine that the world seems to be obsessed about today.” DWG
{2}ልዕላ ኃያሏ አሜሪካና ሱዳን
የዓለም ፖለቲካ ሁኔታ ተለዋውጦል፣አሜሪካና ሱዳን መንግሥትን መንግሥታዊ ሽብርተኝነትን ያራምዳል “state sponsor of terrorism” በማለት አሜሪካ ለበዙ አስርት አመታት የሁለቱ አገሮች ዲፕሎማሲያዊ ግንኑነት ተቆርጦ ነበር፡፡ አሜሪካ የፕሬዜዳንት አልበሽር አገዛዝ ከአከተመ በኃላ ከሱዳን ጋር አዲስ ግንኙነት መስርታለች፡፡ አሜሪካ ከአዲሱ የሱዳን ወታደራዊ አገዛዝ ጋር ወዳጅነት በመመሥረት ሱዳንን ከፀረ አሸባሪነት ሊስት ሰርዛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አደሳለች፡፡ አሜሪካ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ከእስራኤል መንግሥት ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያድስ አስማምታለች፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ መንግሥት የሰባት መቶ ሚሊዮን ዶላር የኢኮኖሚ ድጋፍና ለዴሞክራሲ ግንባታ አስተዋፅዖ እንዲያደርግ አበርክታለች፡፡ “Ties between the US and Sudan have been warming for the past two years after decades of tensions and mistrust during al-Bashir’s rule. Last year, the US removed Sudan’s designation as a “state sponsor of terrorism”, and the two countries restored diplomatic ties. The transitional government also agreed to normalise relations with Israel in a US-brokered agreement.” US says it will evaluate ‘entire relationship’ with Sudan.
ከህወሓት እሰከ ኦህዴድ ብልፅግና የሃገር ክህደት በአል-ፋሽካ ለም መሬት
የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበር የመሬት ይገባኛል ጥያቄ፣Ethiopian-Sudanese border
የአል-ፋሽካ ምድር ‹‹ ይህ መሬት 1600 ኪሎሜትር ርዝመትና ከ20 እስከ 60 ኪሎሜትር ስፋት ያለው ቦታ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ብሄረሰቦች በመሬቱ መነጠቅ ተጎጅዎች ይሆናሉ፡፡ በህወሓት ኢህአዴግ ክህደት ለሱዳን የተበረከተ መሬት ነው፡፡ በጎረቤታሞቹ የኢትዮጵያና ሱዳን ህዝቦች ጥሩና የጋራ መተሳሰብ፣ ጥቅምና መልካም ጉርብትናን ለሚቀጥለው ትውልድ ድረስ የሚያናጋ ውሳኔ ተፈፅሞል፡፡ እንደ ትሪቡን መረጃ መሠረት ‹‹አል-ፋሽካ መሬት 250 ስኩየር ኪሎ ሜትር የሚገመት ሲሆን 600,000 acres ለም መሬት አለው፡፡ በአል-ፋሽካ መልክዓ-ምድር ላይ የሚያቆርጡ የአትባራ፣ ሰቲትና፣ በሰላም ወንዞች መሬቱን እያረሰረሱ ሥነ-ህይወቱን ዕደት ይታደጋሉ፡፡ የአል-ፋሽካ ጉዳይ የሚመለከታቸው ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወለጋና ኢሉባቡር ጠቅላይ ግዛቶች ናቸው፡፡ ሱዳኖች የአል-ፋሽካን ጉዳይ የአማራ ጉዳይ ብቻ አድርገው ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ የአል-ፋሽካ ጉዳይ የመላው ኢትዮጵያዊ ጉዳይ ነው፡፡ የሱዳን ምሁራን የአል-ፋሽካ አዲስ የታሪክ ትርክት መረጃ አልባ ስንኩል የታሪክ ቅመማ ሲሆን፣ በህወሓት መፅሃፍ ገላጮች የሱዳናዊ ሊሂቃን በአማራ ብሔርና በቀሪው ኢትዮጵያዊ መኃል ልዩነት እንዳለ አድርገው የአል-ፋሽካን ቆጥኝ ከመኃላቸው ያስቀምጣሉ፡፡››››
“This land mass span 1,600 kilometers in length and 20 to 60 kilometers in breadth. All of the country’s ethnicgroups will be affected by this treachery. Good and mutually beneficial neighborly relations between the Ethiopian and Sudanese people will be affected for generations to come. ”
“According to the Tribune “Al-Fashaga covers an area of about 250 square kilometers and has about 600,000 acres of fertile lands. Also there are river systems flowing across the area including Atbara, Setait and Baslam rivers.”
“The issue mainly affects the regions of Gondar, Gojam, Wolega, and Ilubabor. In stating the outlandish, the Sudanese are trying to create a wedge between the Amhara nationality and the rest of Ethiopians. ”
ፕሮፊሰር መስፍን ወልደማርያም የአል-ፋሽካ መሬት የኢትዮጵያ ግዛት እንደሆነ በጥናት የቀረበ መረጃዎቻቸውን አቅርበውልናል፡፡ ህወሓት ኢህአዴግ ነፃ አውጭ በነበረበት ጊዜ ሥልጣን ስንይዝ አል-ፋሽካን የሱዳን ግዛት እንደሆነ ተስማምተው የሰሩት የአገር ክህደትን ነው ተፈፃሚ ያደረጉት፡፡ ኦህዴድ ብልፅግናም የአማራ መሬት ነው፣ ይወሰድ በማለት አማራን የማዳከም ሴራ ፈፅሞል፡፡ ኦህዴድ ብልፅግና በድንቁርና እንጂ የወለጋና ኢሉባቡር ግዛቶችም የአማራ ብቻ ሳይሆኑ የመላ ኢትዮጵያዊ መሬት እንደዋዛ ሲወሰድ ወያኔም (መለስ፣ደብረፂዮን፣ ስዬ ዝም አሉ)፣ ኦዴፓ ብልፅግና (አብይ አህመድ ከነካቢኔውም ዝም አሉ!) የኦነግም (ዳውድ ኢብሳ ዝም!)፣ ኦነግ ሸኔም (ጃል መሮ ዝም!)፣ ኦፌኮም (መራራ ጉዲና፣ ጁሃር መሃመድ፣ በቀለ ገርባ ዝም ብለዋል፡፡) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣(በለጠ ሞላ፣ ደሳለኝ ጫኔ፣ ክርስቲያን ታደለ ዝም አሉ) የድንቁርና የጥቅም የድኅነት ጥልቅ ዝምታ ሆነ እንጂ በኢትዮጵያ የሚገኙ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የአል-ፋሽካን መሬት ለማስመለስ ዝምታችሁን ስበሩ፡፡ የአል-ፋሽካን መሬት የተማሩ የጎንደር፣ ጎጃም፣ ወለጋ፣ ኢሉባቡርና የኢትዮጵያ ልጆች ታሪኩን አጥንተው በማህበራዊ ሚዲያ ለህዝብ ማሳወቅ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባችሁ እንላለን፡፡ ሱዳን የአል-ፋሽካን መሬት ለኃብታም አረብ አገሮችና ኢንቨስተሮች ለመሸጥ በመደለል ላይ ናት፡፡ የአል-ፋሽካ ምድር ለሱዳን መንግሥት የሸጡ ከህወሓት እሰከ ኦህዴድ ሹምባሾች የኢትዮጵያን ህዝብ ለማስተዳደር የሞራል ብቃት የላቸውም፡፡ ‹‹ከዚህ በኃላ መሞት የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ለቀይ ባህር ይሙት›› አብይ አህመድ ላለው ‹‹ከዚህ በኃላ መሞት የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ለአል-ፋሽካ ይሙት››…………… ‹‹ከዚህ በኃላ መሞት የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ለአዲሰ አበባ ይሙት›› ኢትዮጵያኖች ይሉታል፡፡
{3} ልዕለ ኃያሏ ራሽያና ኤርትራ
የዓለም ፖለቲካ ሁኔታ ተለዋውጦል፣ ኢሳያስ አፈወርቂ የቀድሞው የኤርትራ ነፃ አውጭ ግንባር መሪ አገዛዙ አንባገነናዊ ነው፡፡ ኤርትራ እስከ 2018 እኤአ ድረስ በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ እቀባ ስር ትገኛለች፡፡ የእቀባው ዋናው ምክንያትም የሱማሌያ አሸባሪ ድርጅቶችን ትደግፋለች በማለት ነበር፡፡ ኤርትራ በአፍሪካ ህብረት ሃገሮና በዓለም በዲፕሎማሲ ሥራ የደሞ ዝውውሯ የቀዘቀዘ ነው፡፡ በ2015 እስከ 2021 እኤአ የወታደራዊ ጦር ሠፈር ለተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በአሰብ ወደብ ላይ በመስጠት የአየር ጥቃት በየመን ላይ ፈፅማለች፡፡ አሰብ የሁቲ እስረኞችን የምርመራ ማዕከል ሆኖ አገልግሎል፡፡ እንዲሁም ኤርትራ ለአረብ ህብረት ተጠባባቂ ጦር በመሆንም ድጋፍ ሰጥቶል፡፡ በ2019 እኤአ ኤርትራ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል የሚያደርገውን ጦርነት በመደገፍ በጦርነቱ በመሳተፍ በሲቨሊያን ሰዎች ላይ ወንጀል በመፈፀምና ሆን ብሎ ቅርሶችን በማጥፋት ወንጀል ፈፅመዋል፡፡……..ራሽያ በኤርትራ ምድር የፖታሲየም ማዕድን ለማውጣትና ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችል መሠረተ-ልማት ለመገንባት ፍቃድ አግኝታለች፡፡ እንዲሁም በቀይ ባህር ዳርቻ ለኔቪዋ የሎጅስቲክ አቅርቦት ሥፍራ አግኝታ ለመገንባት ትሻለች፡፡ ለኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚማአቀብ እንደተነሳ፣ የኤርትራ ወታደራዊ ኃይል ሁለት አንሳት ሂሊኮፕተር (Ansat helicopters) ከራሽያ ገዝታለች፡፡ Isaias Afewerki, the liberation movement’s former leader rules as a dictator. Until November 2018, the country was subject to UN sanctions for supporting Somali terrorist groups. Although Eritrea is diplomatically inactive (e.g., in the African Union), in recent years it has been involved militarily in the region. In 2015-2021, it hosted a military base of the United Arab Emirates in the port of Assab that was used for airstrikes on positions in Yemen and as a centre for interrogating Houthi prisoners. It also set up a contingent to Yemen for the Arab coalition. In 2019, Eritrea supported the Ethiopian government in its war in the Tigray province. Eritrean forces committed crimes against civilians there and systematically destroyed its cultural heritage. …Russia then obtained permission to build export infrastructure for potassium mined in Eritrea and to locate a logistic base for its navy on the Red Sea coast. After the UN sanctions were lifted, the Eritrean military bought two Ansat helicopters from Russia, and two weeks before the invasion of Ukraine, Afewerki was visited by Russia’s deputy foreign minister responsible for Africa, Mikhail Bogdanov. Although the investment plans remain unrealised, they position Russia as a leader among Eritrea’s potential partners……………………………………………………….(4)
የዓለም ፖለቲካ ሁኔታ ተለዋውጦል፣ ራሽያና ኤርትራ በጊዜው አጀንዳ ላይ ተመሳሳይ አመለካከትና በዓለም አቀፍ የፖለቲካ ጉዳይና ዴሞክራሲያዊ አመለካከትና የብሄሮች የራሳቸውን መብት የመወሰንና መሪያቸውን የመምረጥ መብትና የወደፊት ህይወታቸውን የፖለቲካ፣ የሶሻልና ኢኮኖሚ እድገት የመወሰን መብትና ነፃነት እንዳላቸው ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
Highlighting the general developments in the African Horn region, Lavrov reassured Moscow’s continuous contribution towards stronger stability and security in Africa, including on the basis of the African Solutions to African Problems principle…..Eritrea, bordered by Ethiopia in the south, Sudan in the west, and Djibouti in the southeast, has an extensive coastline along the Red Sea. It could be the busiest shipping lanes, with the controlling access to the Red Sea and the Indian Ocean. The commercial activities revolve around this strategic location as a transit point and the strategic location also makes the country prime for an increased military presence. This is the strategic importance for Russia……According to official website of the Foreign Ministry, the information posted in 2018 to media questions concerning the Russian side that noted positive trends on the Horn of Africa, and steps being taken by both sides to settle conflicts in the region, Lavrov replied: “we cooperate in many diverse areas: natural resources, all types of energy engineering, including nuclear and hydroelectric energy, and new sources of energy, infrastructure in all its aspects, medicine, the social sphere, transport and many more.” ………………………………………………………………………………………(5)
{4} ልዕለ ኃያሏ ቻይናና የአፍሪካ ቀንድ አገሮች
ቻይና በዓለም አቀፍ ንግድ፣ የአፍሪካ አህጉር ዋነኛዋ የንግድ ሽርካ በመሆን በአህጉሩ ውስጥ በቀጥተኛ ንግድ 200 ቢሊዮን ዶላር በ2019 እኤአ እንደደረሰ መረጃ ይገልፃል፡፡ ከቻይና አጠቃላይ ወደ ሃገር ውስጥ ከምታስገባው የአፍሪካ ምርትና ሸቀጥ አራት በመቶ ይይዛል፡፡ ቻይና በአፍሪካ የተፈጥሮ ኃብቶችና ወደ አፍሪካ በሚላኩ ምርትና ሸቀጦች ትኩረት ታደርጋለች፡፡ ከ2000 እስከ 2020 እኤአ ቻይና በአፍሪካ አገሮች ውስጥ ያደረገችው እርዳታ 13000 ኪሎ ሜትር መንገድና የባቡር ሐዲድ ግንባታ፣ 80 ከፍተኛ የኃይል አገልግሎት እንዲሁም 130 የህክምና አገልግሎት ፣ 45 የስፖርት መዝናኛዎች፣ 170 ትምህርት ቤቶችን ገንብታለች፡፡ ቻይና ለአፍሪካ ውስጥ ለ32 አገሮች የሁለትዬሽ የብድር ስምምነት በማድረግ ከፍተኛ አበዳሪ ሃገር ሆናለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ለአንጎላ 21.5 ቢሊዮን ዶላር፣ ለኢትዮጵያ 13.7 ቢሊዮን ዶላር፣ ለኬንያ 9.8 ቢሊዮን ዶላር፣ ኮንጎ 7.42 ቢሊዮን፣ ዛምቢያ 6.38 ቢሊዮን፣ካሜሩን 5.57 ቢሊዮን ዶላር ወዘተ ብድር አበድራለች፡፡ ቻይና አንድ ሦስተኛ የነዳጅ ፍጆታዋን ወደ ሃገሮ የምታስገባው ከአፍሪካ አገሮች ነው፡፡ የቻይና ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በአፍሪካ በተፈጥሮ መዕድን ኃብትን በማውጣት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ (Belt and Road Initiative)
ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ የዓለም አቀፍ የመሠረተ ልማት የትራንስፖርት ግንባታ ስትራቴጅ የቻይና መንግስት ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ እድገትና በአህጉሮች የኢኮኖሚ ትስስር ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በ2013 እኤአ የቻይና መንግሥት የዓለም አቀፍ ልማትና ግንባታ በሰባ አገሮች ውስጥ የመንገድ፣ የባቡር፣ የወደብና የዓየር መሠረተ-ልማት ግንባታ ያካተተ ነው፡፡ ቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ 2631 ፕሮጀክቶች በ3.7 ትሪሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ወጪ እየተረነባ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ያሳተፈ የልማት እቅድ ነው፡፡ ከአፍሪካ ከሳህራ በታች ባሉ 43 አገሮችን ያካተተ ፕሮጀክት ነው፡፡ ቻይና በአፍሪካ አህጉር የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ወታደራዊ ዘርፎች ቁልፍ ሚና በመጫወት ላይ ትገኛለች፡፡ የቻይና ፕሬዜዳንት ዢ ጂንፒንግ በቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ የዓለም አቀፍ ንግድና ኢኮኖሚን በመቆጣጠር ላይ ይገኛሉ፡፡ ቻይና የፋይፍ ጂን (5G) የሞባይል ቴክኖሎጅ በመፍጠር በዓለማችን የቴሌኮሙኒኬሽን እደገት እየመራች ትገኛለች፡፡
ቻይና መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ አገሮች የኢኮኖሚ ግንባታና የትራንስፖርት መሰረተ-ልማት ግንባታ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጅ፣ የፋይናንስና ባንኪንግ ዘርፍ ለአፍሪካ አገራት፣ የባንክ ብድር አገልግሎት በመስጠት ለአፍሪካ ህዝብ ተደራሽ በመሆናቸው የቻይና ልዕለ ኃያልነት በአፍሪካ ተመራጭ ለመሆን ችለዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ባንክ፣ አይ ኤም ኤፍ ወዘተ የበሰበሰ ሥርዓት ለመገርሰስ ታዳጊ አገራቶች ከቻይና፣ ሶብየት ህብረት፣ ህንድ፣ ወዘተ ጋር ህብረት ፈጥሮ የዓለም አቀፍ ሥርዓት መለወጫው ጊዜ በአሜሪካ የውሸት ዴሞክራሲ በአፍሪካ አገራቶች የቻይና መንግሥት የልማት አቅጣጫ ደጋፊ መሆናቸው ምዕራባዊ አገሮችን ስጋት ላይ ጥሎቸዋል፡፡ ምዕራባዊ አገሮችና አሜሪካ በኢራቅ ህዝብ፣ በሲሪያ ህዝብ ላይ፣ በየመን ህዝብ ላይ፣ በሊቢያ ህዝብ ላይ የፈጸሙት የመንግሥት ለውጥ ‹‹régime Change ›› የአሜሪካ ልዕለ ኃያል መንግሥት አገዛዝ ታሪክ ይቅር አይለውም፡፡
‹‹ምሥራቅም፣ ምዕራብም ሳትል ብሔራዊ ጥቅምህን እየተመለከትህ ሁለቱን እንዴት ነው የማጣጥመው ነው የምትለው፡፡ ስለዚህ ይኼ የፋይናንሻል ዘርፍ ክርክር አይደለም፡፡ የዴቨሎፕመንት ስትራቴጂ ክርክር ነው፡፡ ለምሳሌ ነጮቹ ለምን ይኼን ያደርጋሉ? ብለህ ብታስብ በቀይ ባህር በኩል ያለውን መስመር ይፈልጋሉ፡፡ የቻይና ‹‹ቤልት ኤንድ ሮድ›› በዚህ ጋር ነው የሚያልፈው፣ እነሱን መቋቋም ይፈልጋሉ፡፡ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮችን ለመደገፍ ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ የፋይናንሻል ነገር ነጥብ ናት፡፡ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ፖለቲካል ስትራቴጂውን ዓይተህ መንገድ ማውጣት አለብህ ማለት ነው፡፡›› ፕሮፊሰር አለማየሁ ገዳ
አዲሱ የውክልና ጦርነት በኢትዮጵያ ሁለት ረድፎች አቌም፡-
- ትህነግ ለሃያ ሰባት አመታት ኢትዮጵያን በአንባገነን አገዛዝ በመምራት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በፈጸመው የስብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት፣ በእስረኞች ኢስብዓዊ አያያዝ በግድያ በቶርቸር ጥሰት፣ በስብዕና ላይ ሰለፈጸማቸው ወንጀሎች በዘር ማፅዳት በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በሱማሌ፣ በኦሮሞ፣ ወዘተ ህዝብ ላይ የፈጸመው ህግ ጥሰት፣ ህዝብ በማፈናቀል፣ በማስደድ ወዘተ አገዛዙ የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብን በዘር ፌዴራሊዝም ከፋፍሎ በመግዛት ጸረ-ህዝብ ሽብርተኛ ድርጅት ነው፡፡ በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ በመቆም ፀረ-ትህነግ ጦርነት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያዊ ሃገር ፍቅርና በህብረ-ብሄር አንድነት ሁሉም ዘብ ቆሞል፡፡
- ምዕራባዊያን አገራት ትህነግን በመደገፍና ለማዳን አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአረብ ሊግ ፣ ግብፅ፣ ሱዳን ወዘተ በአንድ ረድፍ ቆመዋል፡፡ ምዕራባዊያን አገራት ለትህነግ በሱዳን በኩል ኮሪደር ለማስከፈት፣ በእህል እርዳታ ማቅረብ ስም የጦር መሣሪያ ለማስታጠቅ፣ የመገናኛ ሳተላይት ስልኮችና ዘመናዊ የመገናኛ ሬዲዩን ለማቅረብ፣ መድኃኒቶች ለማድረስ፣ ከሱዳን ያሉ አርባ ሽህ የትህነግ ሠራዊትን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ወዘተ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የማይፈነቅሉት ድንጊያ የለም፡፡ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥት የኮነሬል አብይ ለህወሓት ሁሉን ነገር እያመቻቸ አሜሪካንን ተንበርክኮ እየለመነ ነው፡፡ ኮነሬል አብይ ወያኔ በአማራ ክልል አድርቃይ፣ ፀለምትና አበርገሌን ወሮ እንደያዘ እያወቀ ጦርነቱ አልቆል ብሎ አውጆል፡፡ኮነሬል አብይ ወያኔ በአፋር ክልል መጋሌ፣ በርሃሌ፣ አባላና ኮኖባ ወሮ እንደያዘ እያወቀ እንዳላወቀ ሆኖ የሃገር ክህደት የፈፀመ መሪን በህዝባዊ እንቢተኝነት ታግሎ መንቀል የጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ነው፡፡
- በሌላው ረድፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን በመደገፍ አቆማቸውን በፅናት የገለፁ የቻይና መንግሥት፣ የራሽያ መንግሥት፣ የቱርክ መንግሥት፣ የህንድ መንግሥት፣ የአፍሪካ ህብረት ወዘተ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት በመደገፍና የትግራይ ጉዳይ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ ምዕራባዊያን አገሮች ጣልቃ መግባት እንደሌለባቸው በማውገዝ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል፡፡
- ‹‹የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ!!!›› ግድቡ ለመቶ አስር ሚሊዮን ህዝብ የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ አገራችን በዓለም የፖለቲካና ኢኮኖሚ ሴራ የግብፅ፣ ሱዳን፣ የአረብ ሊግ፣ እስራኤል፣ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት ወዘተ አገራቶች በታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግብፅና ሱዳንን መንግሥት በመደገፍ ጸረ- ኢትዮጵያ አቌም ወስደዋል፡፡
- የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አራት የኒውክለር ማብላያ እምቅ ኃይል ያላት አገር ሆናለች፡፡ የህዳሴ ግድቡን ለማስቆም በባዕዳን ኃይሎች ከሃገር ውስጥ የትህነግ ሽብር ኃይሎች ጋር የውክልና ጦርነት ከተለያየ አቅጣጫ ጦር የሚወረወርባት፡፡ ኢትዮጵያን የነካ!….ግድቡን የነካ!.. የውኃ ጥፋት ዘመን … የኖህ ዘመን ያሸጋግራቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ሆኖ ጠላቶቹን በመመከት የሚቀጥለውን ዘመን መሻገር የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያዊያን ህልውና ኢትዮጵያ ስትኖር ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል እንላለን፡፡
ምንጭ
(1) This story is recounted in the Old Testament (Exodus 14: 19-31).
(2) Speaking Truth to Power: United Nations Human Rights Council, Amnesty International, Human Rights Watch Dawit W Giorgis May 3, 2022
(3) Ethiopian conflict exacerbates hunger, malnutrition DW news 2021
(4)PISM Bulletin no 44 (1961) 22 March 2022.pdf/
(5) Russia’s Growing Strategic Interest in Eritrea – Modern Diplomacy