February 9, 2022
78 mins read

ለመሆኑ እኛ ኢትዮጵያውያን ፍልስፍናና ስነ-ምግባር አለን ወይ? – ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

ኡቡንቱ (Ubuntu) በመባል ከሚታወቀው በተለይም በደቡቡ የአፍሪካ ክፍል ከተስፋፋው ፍልስፍና ምን ቁም ነገር ልንማር እንችላለን?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)
የካቲት 8 2022
 

ሁላችንም እንደምናውቀው በተለይም የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የክርስትናን ሃይማኖት ከተቀበሉት አገሮች ውስጥ ከአርሜንያ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚቆጠር ነው። በሁለቱ አገሮች መሀከል ማን ተቀዳሚውን ቦታ እንደሚይዝ አለመግባባት ቢኖርም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የከርስትና ሃይማኖት የገባው በአራተኛው ክፍለ-ዘመን እንደሆነ ይታወቃል። የክርስትና ሃይማኖት የአገዛዙ ሃይማኖት ከሆነ በኋላ የተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል በጉልበት እንዲቀበለው እንደተደረገ የማይታበል ሃቅ ነው።

የክርስትና ሃይማኖት በአገራችን ውስጥ መግባት ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ አስተዋፅዖን እንዳበረከተ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። እስከ አራተኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ በስርዓት መልክ የማይጻፈው የግዕዝ ፊደል ተናባቢዎች(Vowels) እንደተካተቱበትና፣ ቀስ በቀስም በሰዋስው መልክ በመጻፍ ሊዳብር ችሏል። ለአነጋገርም ሆነ ለስነ-ጽሁፍ መዳበር አስፈላጊ የሆነ የሰዋስው አገባቦችና ዐይነቶች፣ እንደ ስምና ተውላጠ-ስም፣ ግስና ተውሳከ-ግስ፣ ቅጽልና መስተጻምር.. ወዘት. የመሳሰሉት በሙሉ መፈጠራቸው በጊዜው የግዕዝን ቈንቋ፣ የኋላ ኋላ ደግም ከአስራ አምስተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ የአማርኛን ቋንቋ መልክ ለመስጠት በቀሳውስት ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የጭንቅላት ስራ እንደተሰራ ነው የሚያረጋግጠው። የአማርኛ ቋንቋም ስነ-ስርዓት ባለው መልክ መዳበርና የስነ-ጽሁፍ ቋንቋ ለመሆን መቻል የሚያረጋግጠው በጊዜው የነበረውን አንድ የተወሰነ የዕድገት ደረጃ ነው። ከቋንቋ መዳበር ጋር የፊዩዳሉ ስርዓት ቀስ በቀስ ተቀባይነት ማግኘትና፣ በፊዩዳሉ ስርዓት ውስጥ የአስተራረስ ዘዴ መዳበሩና ልዩ ልዩ እህሎችን በማብቀል ለምግብ መጠቀምና፣ ልዩ ልዩ የምግብ ዐይነቶችና መጠጦች፣ እንደጠላና ጠጅ፣ እንዲሁም ካቲካላ የመሳሰሉት መፈጠርና መጠቀም የሚያረጋግጡት የባህል የፈጠራ(Cultural Innovation) ውጤቶች ናቸው ማለት ይቻላል።  ይህም ማለት እነዚህ ነገሮች ዝም ብለው ከሰማይ ዱብ ያሉ ወይም ደግሞ በሌላው የህብረተሰብ ክፍል፣ በዛሬው አጠራር ጎሳ ብለን በምንጠራቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ለመጫን የተፈጠሩ ሳይሆኑ፣ ከረጅም ጊዜ ሂደት በኋላ በመቀላቀል፣ እርስ በርስ በመገናኘትና፣ አንዱ ከሌላው በመማርና የሁሉም መለያዎች ሊሆኑ የቻሉ የዕድገት መገለጫዎች ናቸው። በተጨማሪም የእነዚህ ነገሮች መፈጠር የሚያረጋግጠው የሰው ልጅ ከእንስሳ የሚለይና ራሱንና አካባቢውን በመለወጥ አዳዲስ ነገሮችን በመፍጠር የተሻለ ማህበረሰብም እንደሚገነባ ነው። ሰውም ሰው ነው የሚያሰኘው የተወሰኑ ህግጋትን በመጠበቅ የመፍጠር ችሎታውን በማዳበርና አዳዲስ ነገሮች በመፍጠር ወደፊት መራመድ ሲችል ነው። በዚህ መልክም መንፈሳዊ ኃይልን ያገኛል። ሌላውን የሚያጠቃ ተሳስቦ የሚኖር ይሆናል።

ለማንኛውም፣ ለባህላችን መዳበር የሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች አስተዋፅዖ እንዳሉ ሆኖ፣ ምክንያቱም አንድ ባህል የሚባልና በልዩ ልዩ መልክ የሚገለጽ ነገር በአንድ አካባቢ ሌፈጠር ቢችልም መልክ ሊይዝና በተሻለ መልክ ሊዳብርና ሊያድግ የሚችለው ከሌሎች ባህሎች ጋር ሲቀላቀል ብቻ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ ባህልና ስልጣኔዎች በሙሉ ሊዳብሩ የቻሉት ዲያሌክቲካዊ በሆነ ውስጣዊ ህግ( Thesis, Anti-thesis and Synthesis) አማካይነት ብቻ ነው። ይህንን በቀላል ቋንቋ ለመረዳት ለምሳሌ አንድ የስንዴ ወይም ሌላ ዘር እንዘራለን። ዘሩ አስፈላጊውን ነገሮች፣ ሲያገኝ፤ ውሃና ሚኒራሎች፣ እንዲሁም ፀሀይ ዘሩ ወደ ስር፣ ወደ ግንድ፣ ወደ ቅርንጫፍና ቀጠል ይለወጣል። ቀሰ በቀስም እያደገ ሲሄድ ብዙ የስንዴ ፍሬዎችን ያፈራል። በዚህ መልክ የተዘራው ዘር ወደ ሌሎች ነገሮች በመለወጥ እንደገና ብዙ ፍሬዎችን ያፈራል። የሰው ልጅም መጸነስና መወለድ በእዚህ ዐይነቱ ክንዋኔ የሚጓዝ ነው። ይህም ማለት በህብረተሰብ የዕድገት ታሪክ ውስጥ አንድ ብሄረሰብ ለብቻው ባህል የሚባለውን ነገር ሊፈጥር ቢችልም፣ በተሻለ መልክ ሊዳብር የሚችለው ከሌሎች ጋር ሲቀላቀልና ስይንቴቲክ በሆነ መልክ ተጨምቆ ሲወጣ ብቻ ነው። ይህ ዐይነቱ ክንዋኔ የተፈጥሮ ህግ ነው። ከዚህ ውጭ ማሰብ ፀረ-ሳይንስ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን ፀረ-ዕድገት የሆነ አመለካከት ነው። ዕውነተኛ ዕድገት ሊመጣ የሚችለው ራስን በመነጠል ሳይሆን በመቀላቀል፣ ሃሳብ ለሃስብ በመለዋወጥና፣ አንደኛው ከሌላው ሲማር ብቻ ነው። እርስ በርሱ፣ ወይም ጎሳውን እየመረጠ የሚጋባ በሃሳብ ይቀጭጫል፤ በራሱ ላይም ዕምነት አይኖረውም። ራሳቸውን ነጥለው ለመኖር የሚፈልጉ፣ ወይም ደግሞ በስግብግብ ዓለም ውስጥ የሚከንፉ የመጨረሻ መጨረሻ የተስተካከለና ለጠቅላላው ህዝብ የሚሆን ሁለ-ገብ ዕድገት እንዳይፈጠር መንገዱን ሁሉ ይዘጋሉ። ባህልንም እንዲዘበራረቅ በማድረግ አንድ ማህበረሰብ እንዳይኖር አቅጣጫውን እንዲስት ያደርጉታል።

ወደ ዋናው ቁም ነገር ልምጣ፤ በታሪካችን ውስጥ ከምሁራዊ መዳበር እጦት የተነሳ አንዳንድ ስህተቶች እንደተፈጸሙ ይታወቃል። በእኛ አገር ውስጥ በማዕከለኛው ክፍለ-ዘመንም ሆነ የኋላ ኋላ በአፄ ምኒልክ አማካይነት ኢትዮጵያ  እንደ ህብረ-ብሄር(Nation-State) ስትመሰረትና ዘመናዊ የሚባሉ ነገሮች ወደ አገራችን ውስጥ ሲገቡ ካለማወቅ የተነሳና በአስተዳደር ውስጥ ሊሰራ የሚችል የሰለጠነ ሰው ባለመኖሩ ምክንያት አንዳንድ ስህተቶች ቢሰሩም፣ በእኛ አገር ውስጥ በብሄረሰቦች ላይ “ተፈጽሟል የሚባለው ወንጀል” ከአውሮፓውና ከአሜሪካው የህብረ-ብሄር አመሰራረትና አገነባብ ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የሚባል። የታሪክን ማህደር ላገላበጠ ህብረ-ብሄርን ለመመስረት እንደ አውሮፓና አሜሪካ  የመሳሰሉት አገሮች ውስጥ ከፍተኛ ወንጀል የተፈጸመበት ሌላ አህጉርና አገር የለም ማለት ይቻላል። በታሪክ ውስጥ ዘግናኝ ድርጊትን የፈጸሙት አውሮፓውያንና አሜሪካኖች ናቸው። የባርያ ንግድንና የቅኝ-ግዛትን አስተሳሰብ የፈጠሩ እነሱ ናቸው።

በአገራችን ምድር ተፈጽሟል የተባለውን ስህተት ወደ ጎን በመተው፣ በአንትሮፖሎጂና በሶስይሎጂ እንደተረጋገጠው አንድ ህዝብ ከዘላንነት ወደ እርሻ ተግባርና ወደ ሌላ ሲዘዋውር ጭንቅላቱን የመሰብብና ሰብአዊ የመሆን ኃይሉ እየጨመረ ይመጣል ይላሉ። በእርሻና ቀስ በቀስም እየዳበረ በሚመጣ የስራ-ክፍፍልና በንግድ አማካይነት እርስ በርሱ ሲገናኝ ቋንቋውን ከማዳበር ባሻገር እየተጋባና እየተሳሰረ በመምጣት፣ ጎሳ የሚባለው ነገር እየከሰመ በሙያ የሚገለጽ የህብረተሰብ ክፍል ይፈጠራል። ጎሳዊ ከመሆን ይልቅ ሶስዮሎጂያዊ ይሆናል ማለት ነው። በሶስይሎጂ አጠራርም፣ ገበሬ፣ አንጥረኛ፣ ሰራተኛ፣ ባላባትና ሌላም በመፈጠር አንድ ህብረተሰብ በሂራርኪያዊና በስራ-ክፍፍል የሚገለጽ ይሆናል። በዚህም መልክ የሚገለጽ ማህበረሰብ ቀስ በቀስም ከአንድ ደረጃ ወደ ተሻለ በመሸጋገር ውስጣዊ ኃይል ያገኛል። ይሁንና ግን አዲስ ከተፈጠረው ህብረተሰብአዊ አወቃቀር ጋር ሊጓዝ የሚችል ምሁራዊና ሳይንሳዊ ኃይልም ብቅ ማለትና ከአዲሱ ሁኔታ ጋር የሚሄድ የአሰራርና የአኗኗር ስልት መንደፍ መቻል አለበት። የህዝብ ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ አዳዲስ ሁኔታዎችና ችግሮችም ስለሚፈጠሩ ችግሮችን ሊቀርፍና በቁጥር እየጨመረ የመጣውን ህዝብ ለማስተናገድ የሚችል ዕቅድ መንደፍ ያስፈልጋል። ስርዓት ለማስያዝ ከግብታዊና ከችኮላ፣ እንዲሁም ከስግብግብ አስተሳሰብ በመላቀቅ ሳይንሳዊና ፍልስፍናዊ በሆነ ዘዴ ችግሮችን ለመቅረፍ መቻል ያስፈልጋል።

በሌላው ወገን ግን አገራችንን የዕድገት ታሪክ ስንመለከት እንደ እርሻ የመሳሰሉ ተግባራትን ለመስራት በተለይም ሰብል በሚደርስበት ጊዜ አንድ ላይ በመተጋገዝ ሰብሉን ያጭዳሉ፤ ይሰበስባሉም። ሌሎች እንደ ማህብር የመሳሰሉትን አብሮ  ማክበር፣ ቤተክርስቲያን ሄዶ በመጸለይና ለምዕመናንም አስፈላጊውን ዕርዳታ በማድረግ፣ በሰርግና በሌሎች ባህላዊ በዓላትም ጊዜ አንድ ላይ ተስብስቦ በማክበር፣ በመብላትና በመጠጣት ማህበራዊ መሆኑንና እሴትም ያለው መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ዐይነቱ ማህበራዊና ባህላዊ ክንዋኔ ለመነፈስ መፈወስና ራስን በራስ ለማግኘት የሚጫወተው ሚና የሚናቅ አይደለም። ባጭሩ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የህብረተሰባችን መገለጫዎችና እርስ በርስም እንድንተሳሰር ያደረጉን ናቸው።  ወደ ኋላ ስንመጣ ደግም፣ ኢትዮጵያ እንደ ህብረ-ብሄር ከተመሰረተችና በአንድ አገዛዝ ስር ስትወድቅ የማይናቅ ባህላዊ እንቅስቃሴ ተካሂዷል። በአጭሩ የኢትዮጵያን የባህል ዕድገት ስንመለከት አብዛኛዎች በጥንታዊ ቃና ላይ የተመሰረቱት ዘመናዊ ሙዚቃዎች በሙሉ ከ1940ዎች ዓ.ም መጨረሻና ከ1950ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ ነው እየዳበሩ መምጣት የቻሉት። ጥላሁን ገሰሰ፣ አህሙድ አህመድ፣ አለማየሁ እሼቴና ብዙነሽ በቀለ የ1950ዎች ውጤቶች ናቸው። ይህም ማለት እየተሳባሰብን ስንመጣ ከአውሬ ባህርያችን በመላቀቅ በመሳሪያ እየተደገፈ የሚዘፈን ዘፈን ማዳበር ችለናል። ሰነ-ጽሁፍንና ሌሎች እንደምግብ አሰራር የመሳሰሉ ነገሮችን በተሻለ መልክ አዳብረናል። ካለፉት 25 ዓመታት ጀምሮ የኢትዮጵያ ምግብ በዓለም አቀፍ ውስጥ ከታወቁትና ጣዕም ከሚሰጡት ምግቦች ውስጥ ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣ ነው። ይህ ሁሉ እየተሰባሰብን በመጣን ቁጥር ውስጣዊ የመንፈስ ኃይል ያገኘን መሆናችንና የመፍጠር ችሎታችንንም እንዳዳበር ነው የሚያረጋግጠው። ባጭሩ ከመቶና ከሁለት መቶ  ዓመት በፊት የነበረውን የኢትዮጵያ ሁኔታ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ከተለወጠው ሁኔታ ጋር ስናወዳድረው የባህል ሬናሳንስ ለማካሄድ ችለናል ማለት ነው። በማራቶን፣ በአስርና በአምስት ሺህ ሜትር ዕርቀቶች በመወዳደር ማሸነፍና ዝናን መቀዳጀት ይህ ሁሉ ከመሰባሰብና መንፈስን ከማዳበር ጋር የሚያያዝ ነው። በእነዚህና በሌሎች ነገሮችም ነው አንድ አገርና ማህበረሰብ የሚገለጹት፤ እንዲሁም ወደ ኋላ ዞር በማለት ያለፈውን ጊዜ ካሁኑ ጋር በማገናዘብና በማነፃፀር ነው የተሻለ የዕድገት ደረጃ ላይ የደረስን መሆናቸን የምንገነዘበው። ይህም ማለት የአንድ አገር ታሪክ ዝም ብሎ በጭቆና ብቻ የሚገለጽና፣ ጨለማ የሰፈነበት ነው በማለት አይደለም።

የእኔ ጥያቄ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ለማዳበር የቻለ ማህበረሰብ በተለይም ባለፉት አርባ ዓመታት ጥራዝ ነጠቅነት በተሞላው አዲስ የህብረተሰብ ክፍል መናወጡን ስመለከተና፣ እስከዛሬም ድረስ በማያቋርጥ መልክ ህዝባችን ፍዳውን እንዲያይ መደረጉን ሳይ በእኛ በኢትዮጵያኖች ዘንድ በተለይም ተማርን በምንባለው፣ የንዑስ-ከበርቴው መደብ በመባል በሚታወቀው የህብረተስብ ክፍል ዘንድ አንድ የሚጎድለን ነገር ያለ ይመስለኛል። በተለይም ሰሞኑን መምህሩ አቶ ታየ ቦጋለ አዲስ አበባ አንድ አዳራሽ ውስጥ ተጋብዞ ያደረገውን ንግግር ስሰማ አንዳንድ ጥያቄዎችን እንዳነሳ ተገድጄያለሁ። በእኛ በኢትዮጵያኖች ዘንድ ብሄረሰብን አሳቦ የሚታየውን አለመግባባት ለማስረዳት ሲሞክር፣ ይቅርታ ይደረግልኝና ትንሽ ዘረኝነት በተሞላበት አነጋገር እኛ ኢትዮጵያውያኖች ከሌሎች አፍሪካውያን ጋር ስንወዳደር የተሻለ ስነልቦና አለን  በማለት ለመግለጽ ሞክሯል። በሌላ ወገን ግን ከተቀሩት የአፍሪካ አገሮች ጋር ስንወዳደር ባለፉት አርባ ዓመታት በንዑስ ከበርቴው በሚካሄደው ፋሺስታዊ መልክን በሚይዝ አሰቃቂ ድርጊት የሚሰቃይ እንደ ኢትዮጵያ የመሰለ ሌላ አፍሪካዊ አገር በፍጹም የለም። ህዝባችን ይህን በመሰለው ከተማረውና ጥራዝ-ነጠቅ ከሆነው የህብረተሰብ ክፍል በሚነሳውና በሚደረገው አሰቃቂ ድርጊት የሚሰቃይ ብቻ ሳይሆን፣ በከፍተኛ ደረጃ ለውጭ ኃይሎች ፣በተለይም ለአሜሪካን ኢምፔሪያሊዝም በመመልመል አገራችንና ህዝባችንን በስለላ የሚያተረማምስና በብልግና ኢንዱስትሪ ውስጥ በመሰማራት አገርንና ባህል የሚያወድም የህብረተሰብ ክፍል በሌሎች የአፍሪካና የአጺያ አገሮች በፍጹም አይታይም። ይህ ብቻ አይደለም አሜሪካንን እንደ ጌታው የሚያመክና ሁሉም ነገር ካለ አሜሪካን ሊሆን አይችልም እያለ የሚማጸ ከእኛ አገር ምሁራን በስተቀር በሌሎች የአፍሪካ አገሮች በፍጹም አይታይም።

ኢትዮጵያችንን ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ስናወዳድር፣ ሁላችንም እንደምናውቀው በቅኝ-ግዛትና በባርያ ንግድ አልተሰቃየችም። ህዝባችንና በጊዜው የነበሩት ነገስታት አገራችንን ለመውረር የመጡ ወራሪዎችን በጀግንነትና በአገራዊ ስሜት በመነሳሳት ከአንዴም ከሁለቴም በላይ መክተው ለመመለስና ነፃነታችንን ለመቀዳጀት ችለናል። ይሁንና  አባቶቻችን ጥለው የሄዱልንን ክብርና ጀግንነት ወደ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ጥበብና ሌሎች ባህላዊ ነገሮች ከመለወጥና፣ አገራችንን በጸና መሰረት ላይ ከመገንባት ይልቅ እጅግ አደገኛና ዝቅተኛ በሆነ አስተሳሰብ ጭንቅላታችንን በማወርና ከውጭ ኃይሎች ጋር በማበር አገራችንና ህዝባችንን ለማውደም የማንፈነቅለው ዲንጋይ የለም። ይህ ዐይነቱ ዝቅተኛ አስተሳሰብ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ በትግሬና በኦሮሞ ኤሊቶች ዘንድ የሚንፀባረቅ ቢሆንም፤ በተለይም ከአማራው ብሄረሰብ የተወለዱ ምሁራነን ባዮችም በስለላና በአመጽ በመሰማራት አገራችንና ህዝባችንን ዛሬ ወደ አሉበት ደረጃ ላይ ለመጣል ችለዋል ብዬ ብናገር እንደተራ ውንጀላ እንዳማይወሰድብኝ ተስፋ አደርጋለሁ።

ወደ ሌሎች አፍሪካ አገሮች ጋ ስንመጣ፤ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ከአስራአምስተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ በባርያ ንግድና፣ በኋላ ደግሞ በቅኝ-ግዛት፣ አሁን ደግሞ በእጅ አዙር የቅኝ-አገዛዝ የተሰቃዩና የሚሰቃዩ ናቸው። በአስራአምስተኛውና በአራስድስተኛው ክፍለ-ዘመን አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች እንደሰንሰለት የተያያዘ አገዛዝና በስራ-ክፍፍልም የዳበረ ማህበረሰብ እንደነበራቸው ይታወቃል። በተለይም አፍሪካን ለመውረርና ሀብቷን ለመዝረፍ የፈለጉት በጊዜው ኃያል መንግስታት የሚባሉት እንግሊዝና ፈረንሳይ፣ የኋላ ደግሞ ጀርመን፣ ቀደም ብሎ ደግሞ ስፔይንና ፖርቱጋል ወደ አፍሪካ ለመሄድ ዕቅድ ሲያወጡ ያሳበቡትም የክርስትና ሃይማኖት የሌለውንና ያልሰለጠነውን ጥቁር አፍሪካዊ ለማስልጠን በሚል ነበር። ይሁንና እዚያ ሲሄዱ ግን ከተደራጀና የራሱ የሆነ፣ በተለያዩ የዕደ-ጥበብና ስራዎችና ስዕሎች የሚገለጽ ማህበረሰብ ጋር ነበር የተጋጩት። አገዛዞችም የራሳቸው ቤተ-መንግስት የነበራቸውና፣ በደንብ የተደራጁም ነበሩ። እንዳሰቡትና እንድገመቱቱ እንደ አውሬ እዚያና እዚህ እየዘለሉ የሚኖሩ አልነበሩም። ታዲያ አፍሪካን እናስለጠናለን ብለው የሄዱት አውሮፓውያን የአፍሪካን በደንብ የተደራጀ ማህበረሰብ ነው ማዘበራረቅና ሀብቱንም መዝረፍ የጀመሩት። ስልጣኔን ከማምጣት ይልቅ ቀጥተኛ ጦርነት ነው የከፈቱብት። በደንብ የተሰሩ መንደሮችንና ቤተ መንግስቶችን ነው እንዳለ ያፈራረሱባቸው። ወደፈረንሳይ፣ ወደ እንግሊዝ፣ ወደ ስፔይንና ፖርቱጋል፣ የኋላ ኋላ ደግሞ ወደ አሜሪካ ተዘርፈው የሄዱ የታሪክ ቅርሶችን ብቻ ሳንቆጥር፣ እዚህ ጀርመን አገር አንድ ሙዜየም ውስጥ ብቻ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ከነሃስ፣ ከእንጨትና ከዲንጋይ የተሰሩ የሚያማምሩ ቅርፃ ቅርፆች ብቻ ሳይሆኑ ስዕሎችም ይገኛሉ። በዚህ መልክ በጊዜው ኢቮሊሺነራዊ በሆነ መልክ ከታች ወደ ላይ በማደግ ላይ የነበረውን ማህበረሰብ ነው አውሮፓውያን ያዘበራረቁትና የወደፊቱንም የማደጉን ሂደት ያጨናገፉበት። ይህ ሁሉ ግፍና በደል፣ እንዲሁም ዝርፊያ ተካሂዶባቸው አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች እንደኛ መስመራቸውን አልሳቱም። በነጩም ላይ ቂም በቀል በመያዝ ጦርነት አልከፈቱበትም። ለምሳሌ የደቡብ አፍሪካን ሁኔታ ስንመለከት በአፓርታይድ ስርዓት እንደዚያ ተሰቃይተው ነፃ ወጡ ከተባለ በኋላ ጥቁሩ ህዝብና መንግስት አንድ ላይ በመነሳት በነጩ ኗሪ ህዝብ ላይ በአንድነት በመነሳት ጦርነት አልከፈቱባቸውም። ከአገር እንዲወጡም አላደረጓቸውም። ወደ አሜሪካም ስንሄድ ተመሳሳይ ነገር እናያለን። የነጭ የበላይነት ከሰፈነበት ጊዜ ጀምሮ ጥቁሩ አሜሪካዊ እንደ ባርያ የሚታይና በፕላንቴሽን ኢኮኖሚ ውስጥ የሚሰራ ነበር። የሚገረፍ. የሚሳደድና የሚገደልም ነበር። አብዛኛውም ትምህርት የመማር ዕድል አልነበረውም። ትምህርት ቤት ለመግባት ዕድል ያገኘው ደግሞ በትምህርቱ ጎበዝ ከሆነ ይህ ለአንተ አይሆንም በመባል ተስፋ እንዲቆርጥ ይደረጋል። ይሁንና ጥቁር አሜሪካኖች ይህንን ግፍ ሁሉ ተቋቁመው በፕላንቴሽን ኢኮኖሚ ውስጥ ተሰማርተው በሚሰሩበት ወቅት እንደ ብሉስና የኋላ ኋላ ደግሞ እንደ ጃስ የመሳሰሉትን ሙዚቃዎች በመቃኘት ለአሜሪካን ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው የዓለም ህዝብ እንዲዳረስ ያደርጋሉ። በእነሱ አማካይነት የሙዚቃ አብዮትና ዳንስ እንዲፈጠርና እንዲደረግ በማድረግ የዓለም ህዝብ በሙሉ እንዲደሰትበት ለማድረግ በቅተዋል። እስከ 1960ዎቹ አጋማሽ ድረስ የሚደረግብቻውን ዘረኝነትና በመንግስት የተደረፈ ጭቆና በመቋቋም ተስፋ ሳይቆርጡ በሁሉም ዘርፍ ጠንክረው በመስራት በአሁኑ ወቅት በሁሉም ደረጃ የሚወዳደሩ ናቸው።  በሆሊውድም ውስጥ የማይናቅ ቦታ ሲኖራቸው፣ በጥሩ ስራቸው ተሸላሚዎችም ናቸው። ብዙ ሳንቲስቶችና ፈላስፋዎች አተፈጥረውባቸዋል። በ2003 ዓ.ም የተመሰረተውና በ2016 ዓ.ም የተከፈተው፣ በአንድ ጋናዊ አርኬቴቸር በ400 000 ስኩዌር ሜትር መሬት ላይ የተሰራው በዋሽንግተን የሚገኘው፣ በአሜሪካ በጣም ትልቁ የጥቁር አሜሪካ ሙዜየም በመባል የሚታወቀው  የሚያሳየው ከባርነት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ አሁን ድረስ ያደረጉትን ጉዞና ተቋቁመው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱበትን ደረጃ ነው።  ትልቅ የታሪክም ቅርጽ ነው። ይህ ሁሉ የሚያረጋግጠ ምንድነው ሌሎች ጥቁር አፍሪካውያንና አሜሪካውያን ወደ ቂም በቀል ሳይሸጋገሩ ያገኙትን ዕድል በመገጠም የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚችሉና ተወዳዳሪም ለመሆን እንደሚችሉ ነው።

ወደ እኛ አገር ስንመጣ ግን ከሰላሳ ዓመት ጀምሮ ጉድ ነው የምንመለከተው። የተወሰነውን ብሄረሰብ እንወክላለን የሚሉ ጥቂት የአገራችን ኤሊቶች በአመረረ መልክና፣ ዛሬ ደግሞ በራሱ በገዢው መደብ በሚደገፍ ስርዓት ባለው መልክ፣ በተለይም በአማራውና በክርስትያኑ፣ አሁን ደግሞ በአፋሩ ወገናችን በሆነው ህዝብ ላይ የሚካሄደው ጭፍጨፋና፣ ከተማዎችንና መንደሮችን ማውደም ስንመለከት መጠየቅ ያለብን ከትግሬና ከኦሮሞ ብሄረሰብ የተወለዱት ኤሊቶች ኢትዮጵያ፣ በተለይም አማራ የሚባለውን የህብረተሰብ ክፍል ለምን በአመረረ መልክ እንደዚህ አድርገው ይጠሉታል? ምክንያቱስ ምንድነው? ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለይ ባህል አላቸው ወይ? በተጓዙበት የዕድገት ሂደት ውስጥ ስነ-ምግባርንና ግብረ-ገብነትን፣ እንዲሁም ሰብአዊነትንና አርቆ-አሳቢነትን አልተማሩም ወይ? እነዚህን ለሰው ልጅ ተሳስቦ እንደ ማህበረሰብ ለመኖር የሚያስፈልጉ ነገሮችን በፍጹም አያውቋቸውም ወይ? በነገራችን ላይ አሁንም ቢሆን በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ካሜሩን ውስጥ ያሉ ፒግሚዮች የሚባሉና ፓፓ ኒው ጊኒዩዋ የሚኖሩ ህዝቦች እንደ ትግሬዎችና የኦሮሞ ኤሊቶች እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በጥላቻና በዝቅተኛ መንፈስ የታወሩ አይደሉም። በአንፃሩ ጫካ ውስጥ ከተፈጥሮና ከዱር አራዊት ጋር በመፈቃቀርና ተፈጥሮን ሳያናጉ የሚኖሩ ናቸው። ከአክራሪዎቹ የኦሮሞና የትግሬ ኤሊቶች በብዙ ሺህ እጅ የሚቆጠር የተሻለ አስተሳሰብ ያላቸውና አርቆ-አሳቢም ናቸው። እርስ በራሳቸውም አይጠፋፉም። አውሮፓውያኖች የደንና በመሬት ውስጥ የሚገኙ ህብቶቻቸውን ከየአገሩ አገዛዞች ጋር በመመሰጣጠር ለመዝረፍ ሲሄዱ ከሚረብሿቸው በስተቀር በመሃከላቸው የሚካሄድ ችግር የለም። አሁንም የእኔ ጥያቄ የትግሬና የአኦሮሞ ኤሊቶች ችግር ምንድነው? ከእነዚህ ብሄረሰቦች የወጡ ኤሊቶችና ተከታዮቻቸው ምናልባትም ለጭንቅላት መዳበርና በተሟላ መልክ ለማሰብ የሚያገለግሉ ንጥረ-ነገሮች ይጎላቸዋል ወይ? ጭንቅላታቸው በተሟላ መልክ ለማሰብ እንዳይችል ያገዳቸው ምናልባትም የንቃተ-ህሊና አለመዳበር ችግር አለባቸው ወይ? መንፈስ የሚባል ነገርስ አላቸው ወይ? የጭንቅላት ኢቮሉሺናቸውን አልጨረሱም ወይ? ለመሆኑ እንደ ጥቁር አሜሪካኖችና ጥቁር አፍሪካውያን እህቶቻችንና ወንድሞቻችን በዕውቀት በመላቅና፣ እንዲህም በባህል ኢንዱስትሪ ውስጥ በመሰማራት ለምን ብቃትነታቸውን አያሳዩም? ለማንኛውም ይህ ዐይነቱን ጭንጋፍ አስተሳሰብና የጥፋት ባህላቸውንም እንወክለዋለን ለሚሉት ህዝብም እያስተማሩት ነው። በተለይም ወደፊት ከትግሬዎች ጋር አብሮ ለመኖርና፣ አንድ በሳይንስና በቴክኖሎጂ የሚገለጽ ጠንካራ አገር ለመገንባት የሚያስቸግር ይመስለኛል። እንደሚታወቀው ማንኛውም ሰው ወይም ጎሳ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ሲኖር ህገ-መንግስትን ማክበር አለበት። ከሌላው ጋር በመቀላቀል ባህላዊና ለዕድገት የሚጠቅሙ አስተዋፅዖችን ማበርከት አለበት። አንድ አገር በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት በተለይም የተማርኩ ነኝ በሚለውና በኤሊቱ ዘንድ ከፍተኛ ብሄራዊ ስሜትና የጠነከረ ስነ-ልቦና መኖር አለበት።  በአጭሩ አመኔታ የሚጣልበት መሆን አለበት። ካለበለዚያ የሚሆን የማይሆን አሻጥር የሚሰራና ከውጭ ኃይሎች ጋር በመመሰጣጠር ወሬ የሚያቀብል ከሆነና ከውስጥም ረብሻ የሚፈጥር ከሆነ የባህልና የዕድገት ጠንቅ ይሆናል ማለት ነው። አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ስንነሳ የትግሬ ኤሊት ብቻ ሳይሆነ በኦነጋውያን መንፈስ የተጠመቁት የዛሬው አገዛዝና ካድሬዎቹ በሙሉ ለአገር ግንባታ፣ ለሳይንስና ለቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም ሰፋ ላለ ባህላዊ ክንዋኔና ዕድገት የሚሆን እሴት በፍጹም የላቸውም። ለኢትዮጵያችን ብቻ ሳይሆን ለጠቅላላው ጥቁር ህብም ጠንቅ የሚሆኑ ናቸው። በተለይም እነሱ በሚያካሂዱት የዘር ጭፍጨፋ የእርስ በርስ ጦርነት ከተነሳ ኢትይፕያችን ብቻ ሳትሆን ጠቅላላው አፍሪካም ይናጋል። ከዚህ አስተሳሰባቸውና ከድርጊታቸው ስንነሳ እንደነዚህ ኃይሎች ስልጣንን እስከተቆናጠጡና በስልጣንም ውስጥ እስከተካተቱ ድረስ ጠቅላላውን ህዝብ ከድህነትና ከረሃብ በፍጹም ማውጣት አይቻልም፤ ስላምና መረጋጋትንም ማስፈን አይቻልም።

አሁንም የሌሎች የአፍሪካ አገሮችን ሁኔታ ስንመለከት፣ ላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት ዛሬ በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ በጎሳና በሃይማኖት ተሳበው የሚነሱት ግጭቶች በሙሉ አውሮፓውያን የፈጠሯቸው ናቸው። በጊዜው በአገሮች መሀከል የነበረውን መተሳሰር በመበጣጠስና በማስመር ኢቮሉሺነራዊ ዕድገታቸውን ስለአጨናገፉባቸው ነው በዛሬው ወቅት እንደዚያ ዐይነት አልፎ አልፎ የሚካሄድ ግጭት የሚታየው። አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገሮች ከስድሳዎች ዓመታት ጀምሮ ነፃነታቸውን ተቀዳጅተዋል ቢባሉም አሁንም ቢሆን በእጅ አዙር የቀኝ-አገዛዝ ሀብታቸው የሚዘረፍና፣ ስልጣን ላይ ያሉትም የየአገራቸውን ህዝቦች ጥቅም የሚያስጠብቁ ሳይሆን የአሜሪካንና የአውሮፓውያንን ጥቅም የሚያስጠብቁ ናቸው።  ከትላልቅ የአውሮፓና የአሜሪካ፣ እንዲሁም የካናዳና የአውስትራሊያ ኩባንያዎች ጋር በመመሰጣጠር ሀብታቸው እንዲዘረፍ፣ አካባቢዎቻቸው እንዲወድሙ የሚያደርጉና፣ ፀረ-ዲሞክራሲያዊና ኢ-ሰብአዊ አገዛዞች በመስፈን በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖሩ የተደረጉ ናቸው። ባጭሩ  በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ያለው ችግር በቀጥታ ከባርያ ንግድ፣ ከቅኝ-ግዛትና ከእጅ አዙር የቅኝ-አገዛዝ ጋር የተያያዘ ነው። ይህም ሆኖ አንዱ ብሄረሰብ፣ ወይም የአንደኛው ሃይማኖት ተከታይ በሌላው ላይ በመነሳት ችግር ሲፈጥር አይታይም፤ ህዝብም ሲፈናቀል፣ ከተማዎችና መንደሮችም ሲወድሙ በፍጹም አይሰማም። ከዚህ ስንነሳ አቶ ታየ ቦጋለ ያለው አነጋገር ካለቦታውና ዘረኝነት የተሞላበት ነው ብል እንደ ውንጀላ አይቆጠርብኝም። መስደብ የነበረበት እህቶቻንና ወንድሞቻችን የሆኑትን አፍሪካውያንን ሳይሆን ከማሰብ ኃይል ጋር ያልተፈጠሩትን የእኛን ጉዶች ነው።

ያም ተባለ ይህ በአጠቃላይ ሲታይ በእኛ ኢትዮጵያውያን ኤሊቶች ዘንድ አደገኛ አስተሳሰብ ይታያል። በአንድ በኩል የሶስት ሺህ ዓመት ታሪክ አለን፤ የክርስትናና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችም ነን ብለን እንኮራለን። ይሁንና ግን የምንሰራቸው ነገሮች በሙሉ የክርስትናንና የእስልምናን ሃይማኖት ስነ-ምግባሮች የሚጻረሩ ናቸው ማለት ይቻላል። በእኔ ዕምነትና አጭር ምርምር ጥሩ ባህልና ታሪክ ያለን ቢሆንም፤ ባህላችንና ታሪካችንን በተከታታይ የሚያድሰው ፍልስናዊ አመለካከትና ምርምር አልተካተተበትም። እንደሚታወቀው ሃይማኖት ዕምነት ነው። ይሁንና ግን ለመንፈስ መጠንከር፣ ተፈጥሮንና ኮስሞስን ለመቃኘት፣ በራሳችንና በተፈጥሮ መሀከል ያለውን ግኑኝነት ለመረዳት፣ እኛ በተፈጥሮ ላይ ጥገኛ  እንደመሆናችን መጠን ተፈጥሮ እንዳይዛባ ወይም እንዳናጋ በተፈጥሮ ውስጥ ያሉ ነገሮችን እንዴትና በምን ዘዴ እያወጣን መጠቀም እንዳለብን  የሚያስችለን፣ እኛ ብቻ ሳንሆን በአገራችን ምድር የምንኖረው ተከታታይም ትውልድ እንደሚተካ በማሰብ ለእሱ ጥለንለት የምንሄደው ጤናማ ህብረተሰብ እንዴት እንደሚገነባ የሚያስችለን፣ ከምንጨብጠውና ከሚታየው ሰውነታችን ባሻገር መንፈሳችንን በየጊዜው ሊያድስልን የሚያስችል የራሳችን የሆነ ልዩ ፍልስፍና ያስፈልገናል። ይህም የሚጎድለን ይመስለኛል። አለ የምንል ከሆነ ደግሞ የሚያውቁ ሰዎች ካሉ ይህንን ስርዓት ባለው መልክ በመጻፍ እንዲያስተምሩን ያስፈልጋል። እንደሚታወቀው የራሱ ፍልስፍና የሌለውና፣ ክወጭ የሚመጡ ዕውቀት የሚመስሉ ነገሮችና ፖሊሲዎች ለሰው ልጅ ዕድገት ጠቃሚ መህናቸውን ወይም አለመሆናቸውን ለመመርመር የሚያስችል የራሳችን ሳይንስና ፍልስፍና እስከሌለን ድረስ፣ ወይም ደግሞ የተለያዩ ሳይንሳዊ አመለካከቶችን በሚገባ በመገንዘብ ኣንዱ ከሌላው የሚለይበትንና፣ ለምንስ አንደኛው በዚህ መልክ ሲረዳው ሌላው ደግሞ በሌላ መልክ ይረዳዋል ብለን ለመመርመር እስካልቻልን ድረስ በቀላሉ ልንታለል እንችላለን። የመጨረሻ መጨረሻም ሳይመረመርና ሳይብላላ ተግባራዊ የሚሆን የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደምናየው ህብረተሰብአዊ መዘበራርቅን ከመፍጠሩ ባሻገር አመጸኛና አገር አፍራሽ የሆነ ኃይል ይፈጥራል ማለት ነው። ስለሆነም ባለፉት አርባ ዓመታት አገራችንና ህዝባችን ከፍተኛ ትርምስ ውስጥ ለመግባት የቻሉት በተሳሳተ ዕውቀትና ፖሊሲ በመመራታችንና ጠቃሚነታቸውን ሳንገነዘብ በጭፍኑ ተግባራዊ በማድረጋችን ምክንያት የተነሳ  ነው።

በ1950ዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደ አገራችን እንዲገባ የተደረገው ዘመናዊ የሚባለው ሳይንሰ-አልባ የሆነ ትምህርትና ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ ከፖሊሲው ጋርም ሰተት ብሎ የገባው በመሰረቱ መንፈስን የማያድስና ሰው መሆናችንን እንድንገነዘብ የማያደርግ ባህል መንፈሳችንን እንዳዘበራረቀው የማይታበል ሃቅ ነው። ይህ ዐይነቱ ጥራዝ ነጠቅ-ዕውቀትና ህብረተሰብን የሚያዘበራርቅ ፖሊሲ ከፊዩዳላዊ አስተሳሰብ ጋር በሚዋሃድበት ጊዜ በሚዋሃድበት ጊዜ አርቆ-አሳቢ ትውልድ ሳይሆን የሚፈጠረው አመጸኛና የነገሮችን አመጣጥና ዕድገት ለመረዳት የማይችል የህብረተሰብ ክፍል ነው። ይህ ዐይነቱ ጥራዝ-ነጠቅ ዕውቀት ራሳችንን ወደ ውስጥ እንዳንመለከትና ሰው መሆናችንንም እንዳንገነዘብ አድርጎናል ማለት ይቻላል። ሰልሆነም በአገራችን ምድር ሰተት ብሎ የገባው ዘመናዊነት የሚባለው ፖሊሲ ጥራዝ-ነጠቆችን፣ ግበዝተኞችንና ትዕቢተኞችን፣ ብሄራዊ ስሜት የሌላቸውንና፣ ሌላውን አልተማረም የሚባለውን የህብረተሰብ ክፍል የሚንቁ ኃይሎችን ለማፍራት በቅቷል። በእኔ ምርምርና ዕምነት መሰረት ማርክሲዝምና ሶሻሊዝም ሳይሆኑ በአብዮቱ ዘመን ለተፈጠረው የወንድማማቾች መጨራረስና አገር መፈረካከስ የዳረጉን በጊዜው የቀሰምናቸው ዕውቀት መሰል ነገሮች ጭንቅላታችንን በተበላሸ መልክ በመቅረጻቸው ነው። ከዚህ ስንነሳ የተማሪው ማህበርና መሪዎች የማርክሲዝም ፍልስፍና በመቀበላቸውና በማራመዳቸው ሳይሆን እንደዚያ ዐይነት መተላለቅ ሊፈጠር የቻለው፣ የተማሪው ማህበር መሪዎች የማርክሲዝምን አስተሳሰብ በደንብ ባለመረዳታቸው ነው። እንደሚታወቀው የማርክሲዝም አስተሳሰብ የተጸነሰውና የተስፋፋው በ19ኛው ክፍለ-ዘመን በአደገ የካፒታሊስት ስርዓት ውስጥ ነው። ምሁራዊ እንቅስቃሴና ብስለት በዳበረበት ስርዓት ሲሆን፣ በጊዜው የነበረውን የብዝበዛ ስርዓት ለመዋጋትና ሰራተኛው ከሚኖርበት የድህነት ኑሮ በመላቀቅ የተሻለ ኑሮ እንዲኖር ለማድረግ ነው። ስለሆነም የማርክስና ከማርክሲዝም ጋር ተያይዘው የተጻፉ ሊትሬቸሮችን ላነበበ ማርክስና ሌሎችም የጠለቀ ዕውቀት የነበራቸው ምሁራን ነበሩ። ይህን ዐይነቱን አስተሳሰብ ሲያስፋፉም ዝም ብለው ሳይሆን በጊዜው የነበረውን ተጨባጭ የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጣዊ ህግና ፖለቲካዊ አወቃቀርን በሚገባ በመረዳታቸው ነው። ማርክስ የፍልስፍና፣ የተፈጥሮ ሳይንስ፣ የሶስዮሎጂ፤ እንዲሁም የጠለቀ የኢኖሚክስ ዕውቀት የነበረው ሰው ነበር። ዝም ብሎ ከመሬት በመነሳት አይደለም ያንን ያህል በብዙ ቅጾች የሚቆጠሩ መጽሀፎችንና አርቲክሎችን ለመጻፍ የቻለው። ሌላው ቢቀር ዳስ ካፒታል በመባል የሚታወቅውን የሶስት ቅጾች መጽሀፍ ላነበበ ሊገነዘብ የሚችለው ስንትና ስንት ምርምር የተደረገበትና ብዙ ዓመታትን የፈጀ ሳይንሳዊ ስራ መሆኑን ነው። ይህ ዐይነቱ ፍልስፍና በመዳበሩም ነው ቀስ በቀስ የከበርቴው መደብ ሳይወድ በግድ ጥገናዊ ለውጥን ማድረግ የተገደደው። በጊዜው የጀርመን ቻንስለር የነበረው ኦቶ ቢስማርክ የሚባለው እያየለና ስር እየሰደደ የመጣውን የሰራተኛውን እንቅስቃሴ ለማዳካም ሲል የግዴታ የማህበራዊ የጥገና ለውጥ ማድረግ ነበረበት። ዛሬ በጀርመን ምድር የሚሰራበት የጤና ኢንሹራንስና ሌሎች የማህበራዊ መሻሻሎችና ህጎች በሙሉ በዚያን ጊዜ በስንትና ስንት ትግል የተገኙ ናቸው ማለት ይቻላል። ወደ አገራችን ስንመጣ ግን፣ 1ኛ) የአገራችን ኢኮኖሚና የህብረተሰብ አወቃቀር ያደገ አልነበረም። በሌላ አነጋገር፣ ወዛደር የሚባለው መደብ በቁጥር ሲለካ እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። ከ80% በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ኑሮው በቀጥታ ከእርሻ ጋር የተያያዘ ነው። 2ኛ) የተማሪው እንቅስቃሴ መሪዎች ማርክሲዝምን በኦሪጂናል መልኩ ያነበቡ ሳይሆኑ፣ በተለይም እነ ስታሊን ያፈለቁትን ታሪካዊና ዲያሌክቲካል ማቴሪያሊዝምን ነው። በዚህ አስተሳሰብ መሰረት ማንኛውም ህብረተሰብ በቀጥታ ከታች ወደ ላይ እንደመስመር የሚጓዝ ነው። ማርክስ እንደዚህ ብሎ አልጻፈም። በተለይም ግራውንድ ወርክ የሚባለው በጣም ጥሩ መጽሀፉን ላነበበና፣ ሌሎችም የእሱን አስተሳሰብ መሰረት በማድረግ ምርምር ያደረጉ የአውሮፓ ምሁራን በአንድ አገር ውስጥ የተለያዩ የአመራረት ስልቶች ተመሰጣጥረው እንደሚኖሩ(Articulation of mode of Production) ነው። በዚህም ምክንያት የተነሳ ከአንድ የአመራረት ስልት ወደ ሌላኛው ቀጥተኛ የሆነ ጉዞ ሊኖር አይችልም። 3ኛ) ማርክስና ኤንግልስ በአንድ ህብረተሰብ ውስጥ ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በአመጽ ብቻ ነው ብለው አላስተማሩም። በእነሱ አመለካከትና ምርምር በአንድ አገር ውስጥ ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ ምሁራዊ ብስለትና የቲክኖሎጂና የሳይንስ መሰረቶች መጣል አለባቸው። በዚህ አማካይነትም ሰራተኛው ንቅታ-ህሊናውን ስለሚያድብር በምሁራዊ መልክና ለተሻለ የኑሮ ሁኔታ ይታገላል። በፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥም በመሳተፍ መብቱን ያስጠብቃል የሚል ነው። ሶሻሊዝምም ከላይ ወደ ታች የሚደነገግ ሳይሆን የመንፈሳዊና የማቴሪያል ሁኔታዎች ከዳበሩና ሁኔታው ከበሰለ በኋላ ቀስ በቀስ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ነው የሚል ነበር አስተሳሰባቸው። ከዚህ አጭር ሀተታ ስንነሳ ማርክሲዝምንና የሶሻሊዝምን አስተሳሰብ ለደም መፋሰስ ተጠያቂ ማድረግ አንችልም ማለት ነው።

ለማንኛውም ከዚህ ማጥ ውስጥ ለመውጣት ራሳችንን ኡቡንቱ(Ubuntu) ከሚባለው የአፍሪካ ፍልስፍና ጋር ማስተዋወቅ ያስፈልጋል። ኡቡንቱ ማለት አንድ ሰው ሰው መሆኑን የሚያውቀው በሌላው ሰው አማካይነት ብቻ ነው። በሌላ አነጋገር አንድ ሰው ብቻውን ተነጥሎ ብቻውን ሊኖር በፍጹም አይችልም። ማንኛውም ግለሰብ ራሱን መግለጽና ማግኘት የሚችለው ከሌላ ሰው ጋር ሲሆንና በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ብቻ ነው። በአገራችን “ የሰው ልጅ ለሌላው መድሃኒቱ ነው” እንደሚባለው ዐይነት በአፍሪካ ውስጥም የተለመደ ፍስልፍና ነው። ሌላው የኡቡንቱ ፍልስፍና ዋናው መሰረት ጠቅላላው የኮስሞስ ዓለምና የምንኖርባት ዓለም የተያያዙና፣ ተፈጥሮ በጸሀይና በሌሎች ከዋክብት ኃይልና አስተዋፅዖ ብቻ ነው ለመኖር የሚችሉት። ካለጸሃይ መሬትና ጠቅላላው ተፈጥሮ ሊኖሩ አይችሉም። በምድር ላይ የሚገኙት አትክልቶች፣ ባህሮችና ውቅያኖሶች፣ እንዲሁም እንስሳዎች ካለጸሃይና ከሌሎች ከዋክብቶች ውስጭ የሚታሰቡ አይደሉም። ለምሳሌ ጸሃይ ስራዋን ብታቆም፣ ወይንም እግዚአብሄር በመናደድ እንደ ኢትዮጵያ ያለውን ህዝብ መቅጣት አለብኝ፣ የፈጠርኩልትን ነገር ሁሉ በመስማማት አብሮ እየሰራ ከመኖርና ከመብላት፤ ፈጣሪና፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ባለቤት ከመሆን ይልቅ እርስ በርሱ የሚተላለቅ ከሆነ፣ በኢትዮጵያ ምድር ብቻ ጸሃይ እንዳይወጣ አደርጋለሁ ቢል ሰውም ሆነ ተፈጥሮ እንዳለ ይወድማሉ። ይህንን ቀልድ እንተውና ጸሃይ ስራዋን ብታቆም ተፈጥሮ በፍጹም መኖር አትችልም። ተፈጥሮ ከሌለች ደግሞ የሰው ልጅም እንዳለ ይወድማል ማለት ነው።

ሌላው የኡቡንቱ ትምህርት የእኔ ብሎ ነገር የለም። ተፈጥሮና ምድር በአንድ አገር ውስጥ የሚገኙ የጠቅላላው ህዝብ ሀብት ናቸው። አንዱ ከሌላው ጋር በመተሳሰብ የሚጠቀምባቸው ናቸው ማለት ነው። ስለሆነም በኡቡንቱ ፍልስፍና በተለይም የተፈጥሮን ሀብት በሚመለከት የግል ሀብት የሚባል ነገር የለም። ይህ ዐይነቱ አስተሳሰብ የአውሮፓውያን ፍስልፍናና፤ በተለይም ኤንላይተሜንት የሚባለው አስተሳሰብ ከተፈጠረበትና ልዩ ልዩ ነገሮችን በመሰበጣጠር መተያት ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የዳበረ አመለካከት ነው። በመሆኑም በአውሮፕያውያን ፈላስፋዎችና ሳይንቲስቶች፣ በተለይም በፍራንሲስ ቤኮንና በሬኔ ዴካን አመለካከት ሁሉም ነገር ተነጣጥለው የሚታዩና፣ ተፈጥሮም በሰው ልጅ ቁጥጥር መሆን ያለባትና ንጹህ በንጹህ መልክ ወደ ተበዝባዥነት የምትለወጥ ነች። ከዚህም ባሻገር በመንፈስና በሰውነት መሀከል ልዩነት አለ። ይህ ዐይነቱ አስተሳሰብ በዘመነ ካፒታሊዝምና በግሎባላዜሽን ዘመን፣ ሁሉም ነገር ወደ ገንዘብ በመቀየር በሚተመንበት ዘመን ስር የሰደደና የሰውን መንፈስ የሚያሰቃይ ነው። ለዚህም ነው በዓለም አቀፍ ደረጃ አመጽ ለመስፋፋት የቻለውና እንደ አሜሪካ ያሉ አገዛዞችም መንፈሰ-አልባ በመሆን የሰውን ልጅ እንዳለ የሚጨርስና ተፈጥሮንንም የሚያወድም የጦር መሳሪይ በመስራት በዓለም ህዝብ ላይ የሚዝቱት። የተወሳሰቡ የጦር መሳሪያዎችን መስራት የጉብዝና ምልክት አይደለም። ከፍርሃት የመነጨ ነው። በሌላ ወገን አንዳንድ አገሮች፣ ለምሳሌ እንደ ራሺያ፣ ቻይና፣ ሰሜን ኮሪያና ኢራን ራሳቸውን ለመከላከልና ክብራቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የግዴታ እንደ ባልስቲክ ሚሳይል የመሳሰሉትን ሰርተዋል። ይህም የግዴታ ነው።

እንደገና ወደ ኡቡንቱ ፍልስፍና ስንመጣ በፕላኔቶች፣ በከዋክብትና በጸሀይ እንዲሁም በመሬት መሀከል መሳሳብ አለ ማለት ነው። ሁሉም በተወሰነ ህግጋት አማካይነት አንድ ላይ በመተሳሰር የሚጓዙና የሚኖሩ ናቸው። ይህ ባይሆን ኖሮ ጸሀይም ሆነ ሌሎች ከዋክብቶች ዱብ ዱብ እያሉ በመውረድ ተፈጥሮን ያጠፉት ነበር.። ልክ ጣሪያ ካለግድግዳና ካለመሰረት የማይታሰበውን፣ ወይም ብቻውን የማይቆመውን ያህል፣ ጸሀይም ከሌሎች ጋር በመሳሳብ ብቻ ነው የምትኖረው። ይህ ዐይነቱ አስተሳሰብና አመለካከት በፍዚክስም፣  ኳንተም ፊዚክስ በሚባለው ዘርፍ ውስጥ የሚታይ ነው። ኳንተም ማለት ጥቃቅን ነገሮች ማለት ሲሆን፤ ለምሳሌ እንደ ፕሮቶን. ኖይትሮንና ኤሌክትሮን፣ ከዚያም በታች ያሉ ጥቃቅን ነገሮች ማለት ሲሆን፤ ማንኛውም ነገርም ሆነ ሰውነታችን ብዙ ጥቃቅን ነገሮችን በመያያዝ ነው ትልቅን ነገር ሊሰጡ የሚችሉት። የስውነታችንም ሴሎች እንደ ኳንተም መውሰድ እንችላለን። ጨረርና ቀለምም የዌብና የጥቃቅን ነገሮች(Particles) ውጤትች ናቸው። በሌላ አነጋገር የዘመኑ ሳይንስ በተለይም ካለ ኳንተም ሊታሰብ ´አይችልም። የኮምፒዩተር ሳይንሳም በዚህ የሚመካ ነው ማለት ነው። ይህ ሁሉ የሚያመለክተው ፍልስፍናና ሳይንሳዊ አመለካከት በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ውስጥም የሚታወቅና፤ የሰው ልጅ በሙሉ እንደ የአካባቢው የራሱ የሆነ ፍልስፋና፣ የሚያመልክበትና ተፈጥሮን የሚረዳበት ዘዴ እንዳለው ነው። የዕድገትንም ጉዳይ ስንመለከት አብዛኛው ባህላዊ ነገሮች በሙሉ በተራ ማሰላሰል(Intuition.) የተፈጠሩ ናቸው ማለት ይቻላል። የአውሮፓ ማህበረሰብ ያደረገው ነገር ቢኖር ነገሮችን በተናጠል በመውሰድ ነው ሳይንስና ቴክኖሎጂን ማዳበር መቻሉ ነው። ይህም ቢሆን አንዳንድ ሳይንስና ቴክኖሎጂዎች፣ እንዲሁም ፍልስፍና ከውጭ በመምጣት ነው ለአውሮፓው ስልጣኔ መሰረት መጣል የቻሉት። በሌላ አነጋገር አውሮፓውያን እንደሚመጻደቁት ራሳቸው ብቻቸውን የፈጠሩትና ያዳበሩት ነገር በፍጹም የለም። በካፒታሊዝም የሚገለጸው ዕድገት ተያይዞ የመጣና(Cumulative Process) በታሪክ አጋጣሚም የዳበረ ነው ማለት ነው። በሌላ አነጋገር እዚህ ዐይነቱ ደረጃ ላይ መድረስ አለብን ተብሎ ከአራትና ከአምስት መቶ ዓመት በፊት በማቀድ አይደለም የካፒታሊዝም ስርዓት ሊዳብርና ዓለምን ለመቆጣጠር የቻለው።

ሌላው የኡቡንቱ ፍልስፍና መተሳሰብ፡ መራዳዳትና ሰብአዊነት የሚባሉት መሰረተ-ሃሳቦች ናቸው። አንድ ህብረተሰብም ሆነ ማህበረሰብ በመረዳዳትና በመተጋጋዘ ብቻ ነው ተከታታይነት ባለው መልክ ለተከታታዩ ትውልድ የሚተላለፈው። ስለሆነም ስነ-ምግባር፡ በተለይም በማቴሪያላዊና በመንፈሳዊ መሀከል ሚዛናዊነት መኖርት አለባቸው። ይህ ዐይነቱ አስተሳስብ በፕሌቶም ሆነ ስቶይክ በሚባሉት ፈላስፋዎች የሚሰበክና፣ በተለይም ለፍትሃዊነው መሰረት የሚሆን ነው። ስለሆነም ስርዓት ያለው ማህበረሰብ፤ ሁሉንም ነገር ከተፈጥሮና ከኮስሞስ ጋር እያነፃጸሩ መስራትና ማዋቀር ለአንድ ህብረተሰብ ወሳኝ ናቸው። መስገብገብ፣ በስልጣን መባለግና፣ ከዚያም በማለፍ በጊዚያዊ ስልጣን በመመካት በአንድ ህዝብ ላይ ጦርነት ማወጅ…ወዘተ. እነዚህ ነገሮች በሙሉ የፕሌቶንንም ሆነ ኡቡንቱ በመባል የሚታወቀውን የአፍሪካን ፍስልፍና የሚጻረሩና የእግዚአብሄርን ቃል የሚጥሱ ናቸው። መጽሀፍ ቅዱሱም፤ አትግደል፣ አትስረቅ…ወዘተ. ይላል። በመቀጠለም የሰውን ልጅ ሁሉ የፈጠርኩ በእኔ ምስል ነው፤ ሌላውን ወንድሙንና እህቱን የገደለ እኔንም እንደ ገደለ ይቆጠራል ይላል። ስለሆነም እንደዚህ ዐይነቱ ገዳይና አገር አውዳሚ መንፈሱ ሁልጊዜ እንደተረበሸ ይኖራል። ከሞተም በኋላ መንፈሱ ወደ ሴኦል ታመራለች።

ከዚህ ፍስልፍናዊ አስተሳሰብ ስነሳ፣ የትግሬ ኤሊቶችንና ዛሬ ስልጣንን የተቆናጠጡት የኦሮሞ ኤሊቶች ለመሆኑ ታሪክና ባህል አላቸው ወይ? ሃይማኖትስ አላቸው ወይ? በእግዚአብሄርም የሚያምኑ ናቸው ወይ? ስንትናን ስንት እንጀራና ኪሎ ስጋዎች ነው የሚበሉት? ስንት ቪላ ቤቶችና በስንት ሚሊያርድ የሚቆጠር ገንዘብ እንዲኖራቸው ነው የሚፈልጉት? ስንትና ስንት ጠርሙስ ብላክ ሌብል፣ ብሉ ሌብልና ጎልደን ሌብብል ውስኪዎች ነው የሚጠጡት?  ይህ ሁሉ መቅበዝበዝና አገርን ማውደም፣ ወንድምንና እህትን ገድሎ ታሪክን አጠፋፍቶ የመጨረሻ መጨረሻ ምን ለመሆን ነው? ስንት ሺህ ዓመታትስ ነው ለመኖር የሚፈልጉት? የተከታታዩ ትውልድስ ዕጣ ምንድ ነው? እንደዚህ እያልኩ መዓት ጥያቄዎችን ማስቀመጥ እችላለሁ። ራሱን መጠየቅ የሚችል ካለ።

ችግሩ በአንዳንዶቻችን መንፈስ ውስጥ የተቀረፀ የተወላገደ አስተሳሰብ አለ። ስለሆነም ነገሮችን እየገለበጥን ወይም በጭንቅላታችው እያቆምን ነው የምናነበው። ለጭንቅላታችን መዳበር የምንሰራው ነገር የለም። ጠቃሚ መጽሀፎችን በፍጹም አናነብም። ከዕውቀት ጋር ተጣልተን ፖለቲከኞች ነን እንላለን። ፖለቲካ ካለዕውቀት የሚካሄድ ይመስል። አብዛኛዎቻችን በደመ-ነፍስ ነው የምንመራው። ቆም ብለን ራሳችንን ለመጠየቅ አንችልም። ስለሆነም እከሌን፣ ወይም ይህንን ጎሳ ድምጥማጡን ካላጠፋሁት ልኖር አልችልም የሚል አጉል ሰይጣናዊ አስተሳሰብ ጭንቅላታችን ውስጥ በመትከል እንሰቃያለን። በዚህም የተነሳ የአሁኑን ትውልድ ብቻ ሳይሆን የሁለትና የሶስት ትውልድ ዕድልም እናበላሻለን። በመሆኑም ራሳችንን ለማግኝት በአስቸኳይ ሃኪም ቤት በመሄድ መመርመርና በቂ ህክምና ማግኘት አለብን። ሌላው ያለው አማራጭ ሌላውን በመግደል፣ በማስቃየትና ቀዬውን በማፈራሰ እየተደሰቱ ለሚኖሩት አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። እነዚህ እየታደኑ መታሰርና አስፈላጊውን ቅጣት ማግኘት አለባቸው። 115 ሚሊዮን ያህል የሚሆንን ህዝብና የወደፊቱን ትውልድ ዕጣ የማሰቃየት መብት የላቸውም። እንደዚህ ብለው የሚያስቡ ከሆነ በጣም ተሳስተዋል።

ሌላው አስቸጋሪ ነገር በተሳሳተ ዕውቀት የሰለጠኑ፣ በተለይም ሰለ ህብረተሰብ ዕድገት ምንም ዐይነት ዕውቀት የሌላቸው፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሳሳተ መልክ በሚናዛው የነፃ ገበያና የሊበራሊዝም አስተሳሰብ መንፈሳቸው የተመረዘ፣ በመሰረቱ ሰብአዊ የሆነ ሳይሆን እጅግ አደገኛ የሆነ የቀኝ አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሚዲያኖችና የዩትቭ ካናል በመክፈት ወጣቱን በማሳስት ላይ ናቸው። እነዚህ ግለሰቦችም ሆነ በቡድን የተደራጁ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ኢንፎርሜሽን የሚባል ነገር፣ በመሰረቱ ከሳይንስና ከፍልስፍና ጋር ምንም ግኑኝነት የሌለው ነገር በማናፈስ የሰው መንፈስ በትክክለኛና በቀና፣ እንዲሁም ሁለ-ገብ ወይም ደግሞ በኡቡንቱ አስተሳሰብ እንዳይቀረጽ ትልቅ የታሪክ ወንጀል እየፈጸሙ ነው። ከዚህም ባሻገር ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር እየተናበቡ የማይጻፉ አንዳንድ ሳይንሰ-አልባ መጽሀፎችና መጣጥፎች በተለይም የወጣቱ መንፈስ በትክክለኛው ሳይንሳዊ ግንዛቤ እንዳይቀረጽ እያገዱት ነው።፡ የግዴታ ይህ ዐይነቱ አጉል አካሄድ መቆም አለበት። ይህ ግለሰብ በራሱ ተነሳሺነት ድረ-ገጽና የዩቱቭ ካናል ቢያዘጋጅም የአብዛኛው ሰው አስተሳስብ በጊዜያዊና ሞቅ ሞቅ በሚሉ ነገሮች ላይ ያተኮረ ነው። ወደ ኋላ መለስ ብሎ በሚናፍቁ ነገሮችና በሚጻፉ መጽሀፎች ላይ ነው የሚዝናናው። ለካስ እንደዚህ ነበር በማለት በአጉል ትረካ ውስጥ ይኖራል። ራሱን ለማደስና በአንዳንድ ኢትዮጵያውያን የሚጻፈውን ከሌሎች ጋር በማወዳደር ትክክለኛ ግንዛቤ ለማግኘት አይፈልግም። ግንዛቤ ለማግኘት ከታች የሰፉትን በኤለን መስክ በቴሴላ ባለቤት የተመረጡ መጽሀፎችን ተመልከቷቸው። ያም ተባለ ይህ አሁንም ቢሆን በመሃከላችን ያለው ትልቁ ችግር ትምህርታዊ ነክ ነገሮችን የሚፈልጉ በጣም ጥቂቶች ናቸው ማለት ይቻላል። ይሁንና ተስፋ ላለመቁረጥ በዙም የሚዘጋጅ በየአስራምስት ቀኑ የሚካሄድ በተለያዩ አርዕስቶች ላይ ትምህርት ለመስጠት አስቤአለሁ። የሚፈልጉ ቀደም ብለው በኢሜይል አድራሻዬ መመዝገብ አለባቸው። ቢያንስ 20 ተካፋዮች መገኘት ሲኖርባቸው፣ እያንዳንዱ ግለሰብ ትምህርት ለመቅሰም የግዴታ መክፈል አለበት። ክፍያውም እንደየሁኔታውና እንደገቢ መጠን የሚወሰን ሲሆን ይሆናል። የሚዘጋጀው ትምህርት ሳይንሳዊ እንደመሆኑ መጠን ብዙ ጊዜን ይጠይቃል። ሌላው ቁም ነገር ደግሞ በዚህ መልክ የሚሰበሰበው ገንዘብ ከፊሉ አገር ቤት ውስጥ አንድ ከዕድገት ጋር የተያያዘ ሁለ-ገብ ተቋማት ለመገንባት እንዲውል ይደረጋል። ለማንኛውም እንደሁኔታው ተጨማሪ ክፍያ ሳይደረግ የትምህርት ጊዜውን ወደ ተጨማሪ ሰዓት ማራዘም ይቻላል። አርዕስቶችም፣ መንግስት ማለት ምን ማለት ነው? ተግባሩስ ምንድ ነው? የህግ የበላይነት ማለት ምን ማለት ነው? ህብረተሰብ ማለት ምን ማለት ነው? ዕድገትስ ሲባል ምን ማለትነው? ለምን እንደኛ ያሉ አገሮች ውስጥ በሳይንስና በቴክኖሎጂ የሚደገፍ ሁለገብ ዕድገት እይታይም?ካፒታሊዝም ማለት ምን ማለት ነው? በእነ ዓለም የገንዘብና በእነ ዓለም ባንክ ከሚሰበከው የነጽሳ ገበያ አስተሳሰብ በምን ይለያል?  ኒዎሊበራሊዝም ማለት ምን ማለት ነው? የኢኮኖሚ ቲዎሮ አስተሳሰብና የፖሊሲ አመጣጥ ታሪክ? በአንድ አገር ውስጥ ብሄራዊ ሀብት(National Wealth) እንዴት ሊፈጠር ይችላል?… ወዘተ. የሚሉና ሌሎችም አር ዕስቶች ናቸው።  ፍላጎት ያላችሁ በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ መመዝገብ ትችላላችሁ። በተረፈ መልካም ግንዛቤ!!

 

 [email protected]

 

Literatures:

Gordon, J.E; Structures: Or Why Things Don`t Fall Down, New York, 2003

Isaacson, Walter; Benjamin Franklin: An American Life, New York & London, 2003

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop