ኢትዮጵያን ለማዳን እና ለመታደግ የሚፈልግ ሠዉ አለማግኘቷን እና በፍለጋ ላይ እንደነበረች ለአለፉት ፴ ዓመት እናት አገር ስትባዝን ነበረች ፡፡
ጨርቅ እና ወርቅ እያነፃፀርን ሲረግሙን አሜን ፤ ሳይጠሩን አለን ማለቱን ልማድ አድርገን ለዕዉነተኛ ዕርቅ እና ዘላቂ ብሄራዊ አንድነት ለማንበር ህዝባዊነት እንደናፈቀን አለን፡፡
በኢትዮጵያ ከአገር ክህደት እና ዘር ፍጂት ወንጀል ተጠያቂነት ቢኖር ኖሮ ገና ከ ፴ ዓመት አስቀድሞ አስካሁን በደም እና ላብ ለላቆጡ እጆች መታሰር መሰብሰብ እንጂ መዘርጋት አለበት ፡፡
በኢትዮጵያ ህዝብ እና በሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ ጥፋት ለፈፀሙት እና በይቅርታም ሆነ በመካስ እንዲሁም በጥፋታቸዉ ልክ ሊጠየቁ ሲገባ ሲሾሙ ፤ሲሸለሙ ይስተዋላል፡፡
በዓማራ ህዝብ ላይ የጠላትነት እና አግላይነት ዕሾክ ተክለዉ ሲያደሙት እና ሲያወድሙት የነበሩት ተጠያቂነት ሳይኖር እና ጥፋቱን ክዶ በአገር ላይ የዘመናት ክህደት እና ሞት እንደዘበት መቁጠር ኢትዮጵያ ምን ያህል እናት አገር ሠዉ መራቧን ያሳያል፡፡
የቀይ ሽብር የትህነግ ፤ኢህዴግ የሠዉ ዘር ጭፍጨፋ ለሞቱት እና በአገራቸዉ ለተዋረዱት እና ለተካዱት መታሰቢያ ከማድረግ ይልቅ ከዚህ በተቃራኒ ለጥላቻ ዘመቻ እና ለክደት ጋብቻ መጨነቅ ከዕርቅ ይልቅ ለደም እና እንባ መራዘም እንደመስራት ነዉ ፡፡
በኢትዮጵያ ዕየሆነ ያለዉ የተለመደ የሚመስል ቢሆንም በኢትዮጵያ ታሪክ በአገር እና ህዝብ ላይ ወደር የለሽ ግፍ ለፈፀሙት ይህም በዘር ፍጂት ፣ በአገር ክህደት እና በጥላቻ ላይ ተወልደዉ ለኖሩት ፀረ ኢትዮጵያዊነት እንደ በጎ ስራ ዕዉቅና መስጠት እና በአገር የችግር ጊዜ ደራሾች ኢትዮጵያዉያን ላይ ክህደት እንዳይሆን በትልቁ ያሳስባል፡፡
የጥላቻ መጋራጃ ባልተቀደደበት ፣ የጥፋት እና ሞት ግርዶሽ ባልተናደበት ፣ የዘመናት አግላይ እና በዳይ አሰራር መሰረቶች ሳይደረመስ ዘላቂ እና ዕዉነተኛ ዕርቅ ብሎ መጠበቅ ከንቱ እና ደም ሳይደርቅ ዕርቅ ስላቅ ነዉ ፡፡
እናም ዓለም ኃይል ወዳለበት …ትቆማለች እና ኢትዮጵያዊ እና ራሱን የሚል በአንድነት እና ህብረት ከመቆም ዉጭ ለነፃነት እና ለአንድነት የሚደረገዉን ፍለጋ እና ጉዞ ከማንም መጠበቅ ከድንቁርና ዉጭ ምንም ሊሆን እንደማይቻል ካለፉት የኋላ ታሪኮቻችን እና ሁነቶች መማር አለብን፡፡
በኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነት ፣ የደም እና የህይዎት መስዋዕትነት….. ዋጋ ሳይኖራቸዉ የሚደረግ ጉዞ የጭለማ ሩጫ እንደሚሆን ለመናገር ጠንቋይ መቀለብም ሆነ ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡
በንቀት እና በህዝብ ጠልነት በአገር እና በህዝብ ለተፈፀመ ዘግናኝ የዘመናት በደል ሳይበቃ በበደል ላይ በደል ተርፎ እየፈሰሰ ዕርቅ ….ይግደልህ ብሎ ይማር እንደማለት ከንቱ ፀሎት ነዉ፡፡
መልካም አባት ርስት ….ክፉ አባት ደም እንዲሉ በእኛ አገር ላይ ለህዝብ እና ለአገር ዕዉነተኛ ነፃነት እና ሉዓላዊነት ፣ ክብር እና ፍቅር ……መሆን ያለበት ባለመሆኑ በአዞ አንቢዎች እየተከፈለ ያለዉ ህዝባዊ እና ብሄራዊ ዋጋ እየከፋ እና እየተስፋፋ መሆኑ የሚያሳየዉ ደም ማድረቅ ሳይሆን ….የማይታረቅ ጨርቅ እና ወርቅ የማስታረቅ “ዘይት እና እሳት” በአንድ ማሰሮ ይዞ በህልም እንደመሸከም እና ተራራ ለመዉጣት መሞከር ነዉ፡፡
ማላጂ
“አንድነት ኃይል ነዉ ”