January 8, 2022
5 mins read

ደም ሳይደርቅ ዕርቅ

ኢትዮጵያን ለማዳን እና ለመታደግ የሚፈልግ ሠዉ አለማግኘቷን እና በፍለጋ ላይ እንደነበረች ለአለፉት  ዓመት እናት አገር ስትባዝን ነበረች ፡፡

ጨርቅ እና ወርቅ እያነፃፀርን ሲረግሙን አሜን ፤ ሳይጠሩን አለን ማለቱን ልማድ አድርገን  ለዕዉነተኛ ዕርቅ እና ዘላቂ ብሄራዊ አንድነት ለማንበር ህዝባዊነት እንደናፈቀን አለን፡፡

በኢትዮጵያ ከአገር ክህደት እና ዘር ፍጂት ወንጀል ተጠያቂነት ቢኖር ኖሮ ገና ከ  ዓመት አስቀድሞ አስካሁን በደም እና ላብ ለላቆጡ እጆች መታሰር መሰብሰብ እንጂ መዘርጋት አለበት ፡፡

በኢትዮጵያ ህዝብ እና በሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ ጥፋት ለፈፀሙት እና በይቅርታም ሆነ በመካስ እንዲሁም በጥፋታቸዉ ልክ ሊጠየቁ ሲገባ ሲሾሙ ፤ሲሸለሙ ይስተዋላል፡፡

በዓማራ ህዝብ ላይ የጠላትነት እና አግላይነት ዕሾክ ተክለዉ ሲያደሙት እና ሲያወድሙት የነበሩት ተጠያቂነት ሳይኖር እና ጥፋቱን ክዶ በአገር ላይ የዘመናት ክህደት እና ሞት እንደዘበት መቁጠር ኢትዮጵያ ምን ያህል እናት አገር ሠዉ መራቧን ያሳያል፡፡

የቀይ ሽብር  የትህነግ ፤ኢህዴግ የሠዉ ዘር ጭፍጨፋ ለሞቱት እና በአገራቸዉ ለተዋረዱት እና ለተካዱት መታሰቢያ ከማድረግ ይልቅ  ከዚህ በተቃራኒ ለጥላቻ ዘመቻ እና ለክደት ጋብቻ መጨነቅ ከዕርቅ ይልቅ ለደም እና እንባ  መራዘም እንደመስራት ነዉ ፡፡

በኢትዮጵያ ዕየሆነ ያለዉ የተለመደ የሚመስል ቢሆንም በኢትዮጵያ ታሪክ በአገር እና ህዝብ ላይ ወደር የለሽ ግፍ ለፈፀሙት ይህም በዘር ፍጂት ፣ በአገር ክህደት እና በጥላቻ ላይ ተወልደዉ ለኖሩት ፀረ ኢትዮጵያዊነት እንደ በጎ ስራ ዕዉቅና መስጠት እና በአገር የችግር ጊዜ ደራሾች ኢትዮጵያዉያን ላይ ክህደት እንዳይሆን በትልቁ ያሳስባል፡፡

የጥላቻ መጋራጃ ባልተቀደደበት ፣ የጥፋት እና ሞት ግርዶሽ ባልተናደበት ፣ የዘመናት አግላይ እና በዳይ  አሰራር መሰረቶች ሳይደረመስ ዘላቂ እና ዕዉነተኛ ዕርቅ ብሎ መጠበቅ ከንቱ እና ደም ሳይደርቅ ዕርቅ ስላቅ ነዉ ፡፡

እናም ዓለም ኃይል ወዳለበት …ትቆማለች እና ኢትዮጵያዊ እና ራሱን የሚል በአንድነት እና ህብረት ከመቆም ዉጭ ለነፃነት እና ለአንድነት የሚደረገዉን ፍለጋ እና ጉዞ ከማንም መጠበቅ ከድንቁርና ዉጭ ምንም ሊሆን እንደማይቻል ካለፉት የኋላ ታሪኮቻችን እና ሁነቶች መማር አለብን፡፡

በኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነት ፣ የደም እና የህይዎት መስዋዕትነት….. ዋጋ ሳይኖራቸዉ የሚደረግ ጉዞ የጭለማ ሩጫ እንደሚሆን ለመናገር ጠንቋይ መቀለብም ሆነ ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡

በንቀት እና በህዝብ ጠልነት በአገር እና በህዝብ ለተፈፀመ ዘግናኝ የዘመናት በደል ሳይበቃ በበደል ላይ በደል ተርፎ እየፈሰሰ ዕርቅ ….ይግደልህ ብሎ ይማር እንደማለት ከንቱ ፀሎት ነዉ፡፡

መልካም አባት ርስት ….ክፉ አባት ደም እንዲሉ በእኛ አገር ላይ ለህዝብ እና ለአገር ዕዉነተኛ ነፃነት እና ሉዓላዊነት ፣ ክብር እና ፍቅር ……መሆን ያለበት ባለመሆኑ በአዞ አንቢዎች እየተከፈለ ያለዉ ህዝባዊ እና ብሄራዊ ዋጋ እየከፋ እና እየተስፋፋ መሆኑ የሚያሳየዉ  ደም ማድረቅ ሳይሆን ….የማይታረቅ  ጨርቅ እና ወርቅ  የማስታረቅ ዘይት እና እሳት በአንድ ማሰሮ ይዞ በህልም እንደመሸከም እና ተራራ ለመዉጣት መሞከር  ነዉ፡፡

 

ማላጂ

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop