የላኮመልዛ መንገድ ለወያኔ ለምን ጨርቅ ሆነለት? – መስፍን አረጋ August 15, 2021 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ወያኔና ኦነግ በፀረ አማራት እንደተቀናጁ እነሱ ራሳቸው በይፋ ማወጃቸውን አንድ ይበሉ፡፡ ኦነገ ላኮመልዛን ሰሜን ኦሮሚያ እንደሚል ሁለት ይበሉ፡፡ ጠቅላይ አዛዡዐብይ አሕመድ፣ ኢታማዦር ሹሙ ብርሃኑ ጁላ፣ መከላከያ ሚኒስትሩ ቀንዓ ያደታ፣ አየር ኃይል አዛዡ ይልማ መርዳሳ ወዘተ… በሆኑበት፣ ኦነጋውያን ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ በሚቆጣጠሩት፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ውስጥ አብዛኞቹ አዛዦችና የመስመር መኮንኖች ኦነጋውያን፣ በዚያ ላይ ደግሞ የሙስና ጨምላቆች (ለቃል ምርጫየ ይቅርታ) መሆናቸውን ሦሰት ይበሉ፡፡ የኦሮምያና የትግራይ ክልሎች ልዩ ኃይሎቻቸውን ይበልጥና ይበልጥ እንዲያጠናክሩ በበጀተት ላይ በጀት እየጨመረ፣ ያማራ ክልል ግን ልዩ ኃይል እንዳያሰለጥንና ያሰለጠነውንም እንዲበታትን አብይ አሕመድ በተዛዋሪ መንገድ ቀጭን ትእዛዝ የሰጠው ደሴ ላይ መሆኑን ዐራት ይበሉ፡፡ እነዚህን አራት ነጥቦች ሲያገናኗቸው፣ የአማራ ዋናው በሽታ አቶ አሻግሬ መሆኑን በቀላሉ ይገነዘባሉ፡፡ አማራ ከኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ አፍዝ አደንግዝ ከተላቀቀ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡ መስፍን አረጋ [email protected] Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ Previous Story “አንድ ሆነን አሸባሪውን ትህነግ መቅበር አለብን፤ ያን ጊዜ ነው የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን የምናስመሰክረው” አቶ ግዛቸው ሙሉነህ Next Story “የውሸት ፀሐይ ሲጠልቅ የሤረኞች ወጥመድ ይበጠሳል!!” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ