July 2, 2021
10 mins read

ሃቅ መስዋዕትነት ከተራራ ይልቅ ትከብዳለች፣ የሸረኛ ሞት ከላባም ትቀላለች! – ሚኪ

በዓለም ላይ ከሚገኙ አገሮች መካከል ከፍተኛ የኃያላን አገሮች ፉክክር የሚታይበት አንዱ የዓለም ቀጠና ቀይ ባህር ሲሆን ኢትዮጵያ ዋነኛዋ ነች። ከአጼ ቴዎድሮስ ዘመን መንግሥት ጀምሮ ኃያላን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ ያሏቸውን ፍላጎቶች በተለያዩ መልኮች አንጸባርቀዋል። አጼ ቴዎድሮስ የእንግሊዝን መሠሪ አካሄድ በጽናት ሲመልሱ ቆይተው መቅደላ ላይ በውጊያ ገጠሟቸው። እንግሊዝ ከግብጽ፣ ኤደን፣ ቦምቤና በርበራ የተውጣጡ 32000 በቅኝ አገዛዝዋ የሚማቅቁ የደሃ ልጆችን ይዛ ነበር አይበገሬውን ቴዎድሮስ ለመውጋት የመጣችው። ይህ አጼ ቴዎድሮስን ለመጣል ሚሊዮን ፓውንድ የወጣበት ጦርነት ከቅኝ ገዥዎች የወረራ ታሪክ ሁሉ ከፍተኛው ነው ሲሉ አንድ ምሁር ተናግረዋል። አጼ ሚኒልክ የኃያላን አገሮችን ጣልቃ ገብነት በመላ አልያም በዲፕሎማሲ ሲያለዝቡ ቆይተው ነገሩ እየከረረ ሄዶ የአድዋው ጦርነት የመጨረሻው መልስ ሆነ።

ኃያላኖቹ አገሮች ይህን ያህል ሽንጣቸውን ይዞ የሚያውገረግራቸው እነዚህን ጦርነቶች ሊያወራርዱ እንደሆነ ሕዝቡና ደጋጉ ምሁራን እንጂ ልባቸው የታወረው ልህቃኑ ይህ ጉዳይ ፈጽሞ የገባቸው አይመስልም። ምዕራብያውያኑን በግጭት ሃሳብ የሚያግዛቸው ቀደም ሲል በተለያየ ዘዴዎች ያሰውጧቸው እውጭ የሚገኘው ፊደል የቆጠረው ጥቂት ልህቅ ነው። እነዚህ የግጭት ሃሳብ አፍላቂ ምሁራን ፊዚክስና ኬሚስትሪ አጥንተው ኖሮ ኒውክለር ደፍድፈው ሃገሪቱን ብርሃን በብርሃን ያደርጓት ነበር። በእርግጥ እንኳንስ ፊዚክስ አላጠኑ ያስብላል። ምክንያቱም ኢትዮጵያን ከኒውክለር ጦርነት በቀር በሁሉም የጦርነት ዓይነቶች መከራ አብልተዋታል። የክፋት ልህቃኑ በሠላም ይኖሩ የነበሩ ጎሳዎች እርስ በእርስ አዋግተዋል፣ የዘር ፍጅትና ሥልጣን የመያዝ ትግል አስደርገዋል። የኃይማኖት ጦርነት ጭረዋል፣ በፖለቲካ አለመስማማት ሠይፍ አማዘዋል። እነዚህ ሁሉ ግጭቶች ልጆቹን እምዕራቡ ዓለም የሚያኖረውን ልህቃን ሳይሆን የደሆችን ልጆች ደም ነው ደመ ከልብ ያደረገው።

የክፉዎቹ ሃሳብ እውን ሆኖ ኢትዮጵያ በክልሎች ብትበጣጠስ ወድያውኑ ዘው የሚሉት ኃያላን አገሮች በጥቅም ምክንያቶች ሲጋጩ የሚያዋጉት ያንኑ የፈረደበት የደሃ ልጅ ነው። የሸር ሃሳብ አፍላቃቂውን ምሁርማ ለውለታው አስቀድመው እስከነ ልጆቹ እውጭ ይልኩታል፣ ደሃ ዘመዶቹን ግን ያጫርሱበታል። ታድያ ከሞራል አኳያ ማስትሬትና ፕሮፌሰርነት ለተሸከመ ምሁር ይህ ያኮራል ወይንስ ይጸጽታልኢትዮጵያን ማፍረስ ጨርሶ እንደማይሆን ሸረኛው ገብቶት ይሆን?

ኢትዮጵያውያን ወያኔ ከተገበረችው የሸር ፖለቲካ መራቅ አለባቸው። መንግሥት ለመቀየር ቢፈልጉ እንኳን ከክፋት መራቅና በችሎታና ሃቅ ተጠቅመው በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ማውረድ ይገባቸዋል። ከሸረኛ ይልቅ ጉልበተኛ ይሻላል። ሸረኛ ጥቂት ጊዜ ይገዝፋል ሞቱም ከንቱ ይሆናል። አንድ የቻይና ሰው የሸረኛ ሞት ከላባ ይቀላል የደጋግ ሞት ደግሞ ከተራራ ይከብዳል” ይሉ ነበር ይባላል። አቶ ኢሳያስ ጥሩ ምሳሌ ናቸው። ይኑራቸውም አይኑራቸውም በራሳቸው ይተማመናሉ።

በምዕራቡ ዓለም ድጋፍ አግኝተው እስልጣን ላይ ቢወጡ ያንኑ ድጋፍ ምዕራብያውያኑ ሲጎትቱት ተመልሶ በጭቃ መለወስ ይመጣል። ምዕራብያውያኑ ዓለም ኢትዮጵያን በእጅ አዙር እንዲገዛ የፈቀዱለት የትግራይ ልህቃን ትግራይን አልምተው እነሱ ደግሞ አዲስ አበባና አሜሪካ ባለፎቅ እንዲሆኑ ነበር ሸር የዘየዱት። ለሃያ ሰባት ዓመት ቦረቁ፣ ጨፈሩ። የትግራይ ልህቃን ደሃውን ወጣት አስፈጅተው አራት ኪሎ ሲቀመጡ የሞቱላቸውን የትግራል ልጆች ረሱ። ከሃያ ሰባት ዓመታት በኋላ ከአዲስ አበባ ወጥተው መቀሌ ገቡ። እንደገና አራት ኪሎ ለመግባት ሸር ሲወጥኑ የሃገር መከላከያውን አጥቅተው ጦርነት ጫሩ። በሰሩት ሸር ሲደቆሱ ደግሞ እውጭ የሚገኙ ተጠቃሚዎችና አስቀድሞ የተከፈላቸው ሎቢይስት ብዙ ጮኹላቸው። ሸር እንጂ ደግነት የሌለቸው የወያኔ ልህቃን ገና ብዙ ያፍጨረጨራሉ፣ መጨረሻቸው ግን ከላባ መቅለል፣ እንደገና መቅለል ነው።

ለትህነግ ሸረኞች የሰው እጅን ማየት እንደ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን ቢራቡ እንኳን ያልተራቡ መስለው ይታያሉ። የትግራይ ሕዝብ ደግሞ እጅግ ኃይማኖተኛ ነው፣ አምላኩን ይፈራል። ከአብራኩ የወጡት ጥቂት ልህቃን ግን በልማት ፈንታ ረሃብ እያባባሱ ወገናቸውን መለመኛ ያደርጉታል። ወያኔ ረሃብን ለምዕራቡ ዓለም እጅ መንሻ ያውሉታል። ይህን ስልት ከየት እንደተማሩት አይታወቅም። አማኙ የትግራይ ሕዝብ ሸርን በእጅጉ ይጠየፋል።የትግራይ ሕዝብ ተራበ፣ የእርዳታ አቅርቦት መንገዶች ይከፈቱ” በሚል ሠበብ እሚገባው የእርዳታ ስንዴ ውስጥ ቦንብና ጥይት ይታጨቅበታል። ደሃው ሕዝብ ትንሽ ስንዴ ሲደርሰው አማጽያኑ ደግሞ አብዛኛውን የጦር መሳርያ ይቀራመታሉ። በደጉ የትግራይ ሕዝብ ረሃብ አራት ኪሎ የሚገባው ወያኔ ኢትዮጵያን እንኩ ፈንኝጩባት” ሲሉ ለምዕራቡ ዓለም ያስረክቧታል። ደሃው የትግራይ ሕዝብ እንደሌሎቹ ደሆቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይጎዳል። ያም መከረኛ የውጭ ነዋሪው ኢትዮጵያዊ ላቡን አንጠፍጥፎ ፈረንጆቹ የማይሰሩትን ሥራ እየሰራ፣ ሳይበላ ሳይጠጣ ገንዘብ አጠርቃሞ አዲስ አበባና እትላልቅ ከተሞች በቀለሳት ቤት ተመልሶ እንዳይኖር ተስፋው ይሟጠታል። ከዛሬ ነገ ይሻላል እያለ በሃሳብ ሲዳክር እዛው ባዕድ አገር ይከርማል። ሃቀኛ ልህቃን እነዚህን ክፋቶች ሊረዱት ይገባል።

ጥቂት የፖለቲካ ልህቃን በትግል ስም የያዙትን የሸር ስልት ሊለውጡ ይገባል። በምዕራቡ ዓለም ተገግፌ ሥልጣን ልያዝ” ማለት ነገ ሌላ መከራ ነው። ረሃብን፣ ሠባዓዊ መብት ጥሰቶች እያባባሱ እነዚህኑ ችግሮች ለምዕራቡ ዓለም ሸጦ እስልጣን መንፈናጠጥ ነገ ሌለ ቀውስ ነው። ሥልጣን ከተፈለገም እውነትንና ምክንያታዊነትን ተደግፎ ወንበሩን መያዙ መልካም ነው። እውነትና ምክንያታዊነት የሌለው የሥልጣን ግብ ላንድ አፍታ እፎይታ ስትሆን ለዘለቄታው ግን ውድቀት ነች። ወያኔ በግፍ ከያዘችው የአማራ መሬቶች ወጥታለች። አማራው ለመሬቱ የሚታገለው ሃቅንና ምክንያትን አዝሎ ነው፣ መስዋዕትነቱም ከተራራ ይልቅ ይከብዳል። ይህን መሬት ዳግም ለመያዝ የሚደረግ የሸር ውጊያ ሙከራ ሃቅና ምክንያት የለውም ሞቱም ከላባ ይቀላል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop