መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ
ሥለ ሳርስ ኮቪ 2 ወይም ሥለ ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ማወቅ ያለብን ወቅታዊ መረጃ በየቀኑ ከሞላው ዓለም
ይጎርፋል፡፡ ያለማቋረጥ፡፡ይኸው ዛሬም ፣ ከቻይና በስተቀር በሌላው ዓለም የሚኖር ሰው ሁሉ በቫይረሱ እነዲሸበር
የሚደርግ መረጃ በተከታታይ በየደቂቃው መነዛቱ ቀጥሏል፡፡…
በመረጃው መሰረትም፣ ኢጣሊያን፣አሜሪካን፣እንግሊዝ ፣ኡ! ኡ! ታ፣ በዘቷል፡፡አብሶ በኢጣሊያ የሞቹ ቁጥር
ማሻቀቡ ህዝቡን አሸብሮታል፡፡ቻይና የዓለምን ሽብር ለማብረድ መከላከያ ክትባት ይዛ ለመምጣት ሽርጉድ እያለች
ነው፡፡ደስ ይላል፡፡ትላንት በሙከራዋ ሰዓት ያልሸሾትን ሀገራት በግንምባር ቀደምትነት ለመደገፍ እነደማታቅማማ
ተስፋ እናደርጋለን፡፡እንደ ቢሊዮነሩ ቤል ጌት፣በወሬ አሸባሪዎችና አስፈራሪዎች ባሉባት ዓለም፣ ከቻይና በቀር
ለአፍሪካስ ማን ነው ተስፋ የሚሆናት?
SARS-COV-2 (Severe Acute Respiratory syndrome cov 2) የተሰኘው ዓለማ አቀፋዊ
ወረርሽኝ ፣ሣንባን በማስጨነቅ ፣ ትንፋሽ አሳጥቶ ለሞት ቢዳርግም ፣እንደ አውሮፓና አሜሪካ በአፍሪካ በፍጥነት
ለመዛመት የሚችልበትን አመቺ የአየር ሁኔታ ያገኛል ብሎ በማሰብ እንደ “ቱጃሩ ቢልጌት” 10 ሚለዮን ሰው
በአፍሪካ ይሞታል ብሎ በድፍረት የሚናገር የህክምና ሣይንቲስት ባለመኖሩ አፍሪካዊያን ተጽናንተናል፡፡ ዛሬ
መፅናናትን አጥተው እጅግ የተሸበሩት አውሮፓና አሜሪካ ናቸው፡፡
መፅናናትን አጥተው ክፉኛ ከመሸበራቸው የተነሳ፣ ድንበራቸውን ጠርቅመው ዜጎቻቸው በየቤታቸው እንዲመሽጉ
እና ቫይረሱን እንዲዋጉ አድርገዋል፡፡መሪዎቻቸውም በየቴሌቪዢኑ፣እየቀረቡ በቫይረሱ ላይ መደንፋት ቀጥለዋል፡፡
“ድል እናረገዋለን፡፡እንቆጣጠረዋለን፡፡እንደመስሰዋለን፡
ትራምፕ፣ “በቻይና ቫይረስና ሄሪካን በተበላው የባህር ማዕበል ” ስጋት ቢወጠሩም ቫክሲኑን በሰው ላይ ሞክረው
ካረጋገጡ በኋላ
ቀድመው ወደተግባር ለማግባት ከቻይና ጋር እየተፎካከሩ እንደሆኑ በመግለፅ የጦርነቱን ስኬት ለማብሰር እየጠሯሯጡ
እንደሆነ አሳውቀዋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ፕሬዝዳንቱ፣ ለህክምና በለሙያዎች የሰጡትን ክብር አደንቃለሁ፡፡ከቫይረሱ ጋር ከባድ ጦርነት
እያደረጉ ያሉት እነሱ ናቸውና !!
“ውጊያችን ፣ከቻይና ቫይረስ ጋር ቢሆንም ፣ እናሸንፋለን!! ” ማለታቸውም ዓለምን አስገርሟል፡፡
እኔም፣ ምንም የሚንያቦቀቡቅ ነግር የለም እላችኋለሁ፡፡ “ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሏችሁ አንዱን ግባ ማለት
ነው፡፡”ስምንቱን ካሰቀረህ ጀግና ነህ ማለትም አይደል፡፡መቼም አንድም ሞት እነዳይመጣ ማድረግ አይቻልም፡፡ ይህ
አሪፉ የኢትየጵያዊያን አባባል ነው፡፡ኮሮናንን የሚስበረግግ ጥቅስ ነው፡፡ለጀግንነት አርአያነት የሚበቃ ምሳሌ
ነው፡፡ ጀግንነትን መስካሪ፣ፈርሃትን አባራሪ የአበው ምሳሌያዊ አነጋገር በመሆኑ ደስ ይለኛል፡፡ዘጠኝ ሞት
ቢመጣብህ ከአንዱ በቀር ግባ የምትለው ነገር የለም፡፡እና ከመጣ ምን ታረገዋለህ?እየኖርህ እንጂ ከቶም እየሞትክ
አጠብቀውም፡፡ ጭንቀትን በሚየባብስ ፣ በቢሆን ፈርሃት እናትህ ቀሚሱ ውስጥ ገብተህም አትወሸቅም፡፡እደግመዋለሁ
እየኖርክ ትሞታለህ እንጂ፣እየሞትክ አትኖርም፡፡
ለወቅታዊውና ነገ ለሚያልፈው ፣ ታሪክ ለሚሆነው በሽታ እንደአቅመህ ትጠነቀቃለህ እንጂ ለምን በፍርሃት
አስቀድመህ ትሞታለህ?ከቶም ቫይረሱ ባልተሰራጨበትን እና ህመምተኞች እነደልባቸው እነዲፎልሉ ባልተፈቀደበት ሀገር
በጠራራ ፀሐይና በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ማስክ በመተንፈሻ አካለህ ላይ ደቅነህ በገዛ እጅህ ፣በሰፊ ጎዳና ላይ
ታፍነህ ነፍስህን በፈርሃት ለምን ታስጨንቃታለህ ?…አትሞኝ፡፡ቫይረሱን እንዳይስፋፋ የበኩልህን እገዛ
አድርግ እንጂ ከመጠን ያለፈ ፈርሃት በራሱ ሳትሞት ይቀብርሃል፡፡
አትሞኝ፡፡የምንኖረው በድሃ አገር ውስጥ ነው፡፡ በዚ ሀገር እኮ ፣ ምድሩን ከአጥለቀለቀው የጀበና ቡና
ጀምሮ ዜጎች የሚኖሩት ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ኑሮ መሆኑን አትዘንጋ፡፡ “የምንበላውን ባገኘን እና መታጠቡ
በቀረብን ፡፡” የሚሉ በዚች ሀገር ነፍ ናቸው፡፡ ስለአንተም ሆነ ሥለእኔ ብጤዎቹ ወሬ የማይገዳቸው ቁጥሩቸው
ትንሽ የሚባል እንደይደለም አትዘንጋ፡፡
እኛ አውሮፓና የትራምፕ ሀገር አሜሪካ አይደለንም፡ ፡መያዤና መጨበጫ ከሌለው አጉል ፈርሃት
እንውጣ፡፡እነሱ ተቦቅቡቀው ሊሞቱ ነው፡፡ በእኛ ሀገር ግን፣ የተጣለ ምግብ ከቆሼ ላይ የሚበላው እና ጎዳና ላይ
አዳሪው፣ ከእኛ ይልቅ የመዳን ተስፋ እንዳለው በማሰብ ፤በፈጣሪችን ላይ ተስፋ በማድረግና ከአጉል ፈርሃት በፀዳ
አስተሳሰብ ራሳችንን በየፈርጁ በመጠበቅ ቫይረሱን ከወረርሽኝነት እንግታው ፡፡
ሰዎች ሆይ ወደቀልባችን እንመለስ ፡፡በየፈርጃችንም በሽታውን ለመቆጣተር ቆቅ እንሁን እንጂ አንቦቅቦቅ፡፡
እውነት እውነት እላችኋለው፡፡አትሳቱ ፤ ሸማ በፈርጁ ነው ና የሚለበሰው ፣ ከመቦቅቦቅ ይልቅ ሁሉም በየፈርጁ
የድርሻውን ይወጣ፡፡
እንሆ እኔም ድርሻዬን ለመወጣት የሚከተለውን መረጃ እንካችሁ ብያለሁ፡፡
1. ይህ በሽታ ከእንስሳ ወደ ሰው የተላለፈ ነው፡፡ ይላሉ የቫይረስ ተመራማሪዎች፡፡ በመጀመሪያ ይህ በሽታ
የተከሰተው በውሃን ግዛት በቸይና እነደሆነ ይታወቃል፡፡ሥለ ቫይረስ የሚያጠኑ ሣይንቲስቶች SARS-COV-2 ሲሉ
ሰይመውታል ፡፡አጣዳፊ የመተንፈሻ አካለት ህመም ማለት ነው፡፡(Severe Acute Respiratory
syndrome cov-2)
2. SARS-COV-2 ሲጀምር ጉንፋን መሰል ምልክት ያለው ነው፡፡ ይህ ድንበር ተሻጋሪ በሽታ ፣ከጥንቃቄ እና
ለምልክቶቹ ከሚረዳ ፣ማለትም ለትኩሳቱ ፣ለራስ ምታቱ፣ለሳሉ፣ ለተቅማጡ መደሃኒት በመስጠት በለይቶ
ማቆያ፣ከማሰታመም ባለፈ ለቫይረሱ መድሃኒት አልተገኘለትም፡፡
3. አንድ ሰው በዚህ ቫይረስ ከተያዘ ከ 3–5 ቀን ምልክት ያሳያል፡፡በአጠቃለይ ተጠርጣሪዎች ለ14 ቀናት
ክትትል ያስፈልጋቸዋል፡፡
4. SARS-COV-2 ቫይረስ ሁሉንም ሰዎች ፆታና ዕድሜ ሳይለይ ይይዛል፡፡ በአብዛኛው፣ህመሙ ከያዛቸው በኋላ
በራሳቸው ነጭ የደም ሴል ተዋጊነት ማገገም ሳይችሉ ለሞት እጅ የሚሰጡት ፣ከልብ፣ከሳንባ፣ከኩላሊት፣ከመተንፈሻ
አካላት፣ ከደም ግፊት እና ከስኳር ህመም ጋር የሚኖሩት ናቸው፡፡ከ40 ዓመት በላይ በሆኑ ጎለማሶች እና
አዛውንቶች ላይ ቫይረሱ ጉልበተኛ ነው፡፡
5. ቫይረሱ የያዛቸው 90 ፐርሰንት የሚሆኑት ከፍተኛ ትኩሳት እና ደረቅ ሳል ያላቸው ሲሆኑ ፣በተቀሩት ላይ
ጉንፋን መሰል ፤ማስነጠስና እና የአፍንጫ ፈሳሽ ምልክት ይስተዋልባቸዋል፡፡ አንዳንዶችም ፣ማቅለሽለሽ፣ተውከትና
ተቅማጥ ሊኖራቸው ይችላል፡፡
6. ገዳይነቱ ይህን ያህል የተጋነነ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሁላ ለአልተያዘው
አምሳያው ሲል ራሱን አጋልጦ በለይቶ ማቆያ ቦታ እስከሚድን ካላቆየ በስተቀር፣ቫይረሱን በፍጥነት ለመቆጣጠር
አይቻልም፡፡ከዘህ አንፃር ፤አያምጣውና ከመጣብን፣ ሰዎች አንዳችን ለአንዳችን መኖር መስዋት መክፈል
ይጠበቅብናል፡፡ ያገሉኛል ብለን ህመማችንን መደበቅ የለብንም፡፡ያልተያዝንም ነግ በእኔ ብለን ህሙማንን
እነደአቅማችን መርዳት ይኖርብናል፡፡(በእርግጥ ቀደም ብሎ እኛ አገር በሽታው እነደነበር እና ልክ
እንደጉፋን፣እንደኒሞኒያ አክመነው እነደሆነም አናውቅም፡፡እነሱ ስለአዲሱ ቫይረስ ስም አውጥተው ነገሩን እንጂ…
እነሱ ኃይለኛ ክርምት ውስጥ እንዳሉም አንዘንጋ፡፡ሆኖም አንዘናጋ! )
7. የቫይረስ ተመራማሪዎች፣ ይህ ወረርሽኝ በወራት ውስጥ ሥጋት ከመሆን ይገታል ይላሉ፡፡ምክንያቱም ከግዜ ብዛት
ቫይረሱን የተቋቋመ ሰውን ብቻ ቫይረሱ ስለሚያገኝ አዲስ ተጠቂ አይኖርም ፡፡ ለዚህም ነው ፣ክትባትን በጥድፊያ
እያዘጋጁ እንዳሉ፣ኃያላኑ ሀገራት የሚነግሩን፡፡ከ1 ወር በኋላ በእርገጠኝነት ፀረ ቫይረስ ክትባት ለዓለም
እነደሚቀርብ ይገመታል፡፡ለእኛም ረጂዎቻችን ጀባ ይሉናል፡፡
8. እሰከዛው አትጨናነቁ፡፡አላስፈላጊ ፍርሃት ውስጥ አትግቡ፡፡አትቦቅቦቁ፡፡ይህ የእኛ ባህል አይደለም፡፡
9. ከባድ የህመም ማሰታገሻዎችን አትጠቀሙ፡፡ፓራሲታሞል የመጀመሪው ተመራጭ የትኩሳትና የራስ ምታት መድሃኒት
መሆኑን እወቁ፡፡፡አነስተኛ የጎንዮሽ ጉዳት
ስላላቸው፣ አይቡ ፕሩፊን፣ ቮልታሪን፣ ናፕሮክሶን፣ ወዘተ፡፡ተሸቀዳድማቸሁ አትጠቀሙ፡፡
10. ነጭ ሽንኩረት ፤ቀይ ሽንኩረት ፤ሌሎችም ፀረ ባክቴሪያ ጸባይ እንዳላቸው ቢታወቅም ለቫይረስ እብዛም
አይፈይዱም፡፡ይህ የቫረስ በሽታ መሆኑን ተገንዘቡ፡፡ እናም ቫይረሱን አይገሉትም፡፡ከበሽታውም
አይፈውሱም፡፡በባክቴሪያ የመያዝ እድላችሁን ግን መቀነሳቸው እርግጥ ነውና ሁሌም በምግባቸው ውስጥ እነዚህ
አታክልቶች ባይጠፉ መልካም ነው፡፡የሰውነታችሁን መከላከያ አቅም የሚጨምረው የአኗኗር ዘይቤአችሁ አመጋገባችሁ
መሆኑ እሙን ነው፡፡
11 ጓንት እና የመተንፈሻ አካል መሸፈኛ ለህክምና ባለሙያዎችና፤በቅርብ ህመም ተኞችን ለሚያገለግሉ ሰዎች እና
ለራሱ በጠና ላልታመመው ሆኖም በቫይረሱ ለተያዘው ለተቀሳቃሹ ህመምተኛ ብቸና ብቻ ነው ጠቀሜታው፡፡ላልተያዘው
መጠንቀቅ አለበትና፡፡ማንኛውም የሚስል ሰው ለወገኑ ማሰብ እና አፍንጫና አፉን በማህረብ መሸፈን ይገባዋል፡፡
12፣ ደረጃውን የጠበቀ የመከላከያ አልባሰት ህመምተኛውን ለሚረዱ እና ለሚያክሙ የህክምና ባለሙያዎች መቅረብ
አለበት፡፡ይህ እሰታንደርዱን የጠበቀ አለባበሰ ነው፣የጤና ባለሙዎችን ከቫይረሱ የሚታደጋቸው፡፡
13 ማንኛውም 60 ፐርሰንት አልኮል በህመሙ ሳንያዝ በፊት ይረዳናል፡፡በአረቄ እና ጂን እጃችንን ብንታጠብ
፣ሳናውቅ ጨብጠነው ፣ይዘነው፣ከነበረ ቁስ ላይ እጀችን ላይ የተጣበቀ ቫይረስ ቢኖር ይገለዋል፡፡ብንጠጠው ግን
ውስጠችን ገብቶ ያሳመመንን ቫይረስ አይገለውም፡፡ምክንያቱም ቫይረሱ ረቂቅ ህዋስ ነውና፡፡ በራሱ ሂደት ነው፣
የመተንፈሻ አካላችንን ለሳንባ ምች ዳርጎ አየር በማሳጣት ለከፋ አደጋ የሚዳርገን፡፡
እርግጥ ነው እንደእኛ ላለ ሀገር ሳይኮሎጂካል የሆነ እርዳታ የለውም ተብሎ ግን አይደመደምም፡፡ “ከአምንክ
ባመንከው ነገር የማትድንበት ምክንየት የለም፡፡” ይልሃል እምነትም ሆነ ሣይነስ ፡፡ይህ በሳይንሱ “ኖሴቦ
ኢፌክት” ሲባል ፤በእምነትም ፣ “የሰናፍጪ ቅንጣት እምነት ካላችሁ ይህንን ተራራ ተነቀልና ሌላ ቦታ ተተከል
ብትሉ ያላችሁት ይፈፀማል፡፡ “እንዳለው ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት ነው፡፡በዓለማዊው ሳይንስ ደግሞ የሰው ልጅ ምን
ያህል ተጠራጣሪና ለራሱ እነኳን አስቸጋሪ እነደሆነ ለመወቅ ከፈለጋችሁ ጉግልን ኃይፖኮንድሪያሲስ ብላቸው
በመጠየቅ አንብቡ፡ “፡እንዲህም አለ ለካ ” በማለት ትገረማላችሁ፡፡