የአማራ ማኅበረሰብ ከሚታወቅባቸው ዕሤቶቹ መካከል የዳበረ የሥነ ጽሑፍና የፍትሕ ሥርዓት ባለቤት መሆኑ ዘወትር ይጠቀሳል፡፡ ከሥነ ጽሑፋዊ ትውፊቶቹ ውስጥ በአጭር አገላለጽና በምጥን ምሣሌ መልእክትን ማስተላለፍ የሚቻልባቸው የሥነ ቃላት መድብሎቹ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ከነዚህ አንዱን ለዚህች ጽሑፍ መግቢያነት እንመልከት፡፡ ይቺ ጽሑፍ ትንሽ ረዘም ትላለችና ወቅቱ ለብዙዎቻችን የበዐል እንደመሆኑ አረፍ እያላችሁም ቢሆን እንድታነቧት በትህትና እጠይቃለሁ፡፡
አማራው እንደዬአካባቢው የተለያዬ መጠሪያ ያለው ሌባን የመጠቆሚያ ባህላዊ ወግ-ልማድ አለው – አሁን ጠፍቶ ከሆነም በጥንት ዘመን ነበረው፡፡ ጠቅለል ተደርጎ ሲቀመጥ “አውጫጭኝ፣ አፍርሳታ፣ሌባሻይ” እና ሌሎች ስያሜዎችም ሊኖሩት የሚችል ሥራት ነው፡፡ ከበላ ልበልሃ የፍትህ ሥርዓት በተጓዳኝ እነዚህን መሰል ትውፊቶችም አማራው ነበሩት፡፡… አንድ ወቅት በአንድ ቀዬ ነዋሪዎች በሌቦች ይቸገራሉ፡፡ ሌቦቹን ያውቋቸዋል፡፡ ግን ለፍርድ እንዳያቀርቧቸው የሌቦቹን ብቀላ ፈርተው ዘላለማቸውን ለምንተፋ እንደተጋለጡ በሰቀቀን ይኖራሉ፡፡ በየጊዜው አውጫጪኝ ቢደረግም ሁሉም ፀጥ እረጭ እያለ ሌቦቹን የሚጠቁም ይጠፋል፡፡ ፍርሀት መጥፎ ነው፡፡ ሰው ደግሞ ምናብ የፈጠረውን ታሳቢ ሥጋትም ሆነ ከፊት ለፊት በእውን የተደቀነን አደጋ የመፍራት ተፈጥሯዊ ዝንባሌ አለው፤ ይህም ሁኔታ ነው ብዙዎችን ለችግር እንደዳረገ የሚኖር፤ ሺ(ህ) ዓመት ለማይኖረው! … እነዚያ መንደርተኞች ለሌላ አውጫጭኝ አንድ ቀን ይሰበሰባሉ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ሽማግሌ ይነሱና “እንግዲህ ስሙኝ! ጀምብር በሰረቀ ቁጥር ስንታመስ መኖር የለብንም፡፡ ሌባው እንደሆነ ባገር ምድሩ ለማ፡፡ ቢተው ይተው፤ ካልተወ ግን ወዳጁ ይምከረው፡፡” በማለት በየሰው ሆድ የሚብላላውን (የአደባባይ) ምሥጢር አፍረጥርጠው ይናገራሉ፡፡ ከዚያም መንደርተኛው በሽማግሌው ቅኔ በደስታ አጨብጭቦ የተጠራው ጉባኤ ይፈታል፡፡ ሌቦቹ ሁሉም እንደሚያውቃቸው ጀምበሩ፣ ቢተው፣ ወዳጆና ለማ የሚባሉ ሰዎች ነበሩና ብልኹ አዛውንት በሰም ለበስ ቅኔ አጋልጠው ሕዝቡን ገላገሉት፡፡ አሁን ያልኩት ቀጥዬ ከምለው ጋር ግንኙነት የለውም፤ ወደ ቁምነገሩ ዘው ብሎ ላለመግባት ነው፡፡
አማራ ቤተ ክርስቲያን እንደገባች ውሻ እንዲህ ሁሉም የሚረባረብበትንና ከምድረ ገጽ ሊያጠፋው የፈለገበትን ምክንያት መርምሬ ልደርስበት አልቻልኩም፡፡ የተረዳሁት አንድ ብቸኛ ነገር ግን አለ፡፡ እሱም ይህ እንደዐይጥ በተገኘበት ተጨፍጭፎ እንዲጠፋ በተለይም በሕወሓትና በምዕራባውያን የገናናው ታሪካችን ጠላቶች የተፈረደበት ሕዝብ አንድ ቀን – ምናልባትም በቅርብ – ፈጥሮ የማይረሳውና ይህን ዘግናኝ ቅጣት ሳይወድ በግዱ እንዲቀበል ጀርባውን ያዞረበት አምላኩ ፊቱን የሚመልስለት መሆኑ ነው፡፡ ይህ በፍጹም የማይቀር የታሪክ ቀኝ ኋላ ዙር በሚከሰትበት ጊዜ አሁን በምናስተውለው እጅግ አሣፋሪ የሆነ የወያኔ ድርጊት ምክንያት ለሚፈጠረው ትርምስና የደም ጎርፍ ተጠያቂው የችግሩ ፈጣሪ ሕወሓትና ጌቶቹ እንጂ አማራውም ሆነ ሌላው ጭቁን ሕዝብ ሊሆን እንደማይችል ሁሉም ወገን ከአሁኑ ሊገነዘበው ይገባል፡፡ “የፈሩት መድረሱ፣ የጠሉት መውረሱ” ደግሞ ያለና የነበረ ነው፡፡ የታሰረ መፈታቱ፣ የተፈታም መታሰሩ የነበረ እንጂ አዲስ ግኝት አይደለምና ተራራው ሲናድ ከሚስቁ ጅሎች ጋር መናጆ ሆነን ሳይሆን ከሚያለቅሱ አስተዋዮች ጋር ተባብረን ስለጋራ መፃኢ ዕድላችን ጨለማው ከዚህም ይበልጥ ሳይበረታ አሁኑኑ አንዳች ነገር ለማድረግ እንሞክር፡፡ በተለይ ደግሞ የአማራን ሰቆቃ እንስማለት፤ እንረዳለትም፡፡ የሀገር ባለውለታ መሆኑንና ከምሰሦዎቹ አንዱ መሆኑን እንገንዘብ፡፡ ምሰሦ ተነቅሎ ቤት ቤት አይሆንም፤ ቤት ያለምሰሦ ይዘብጣል፤ በሂደትም ይወድቃል፡፡ አማራን ያልጨመረች ኢትዮጵያን ማሰብ ደግሞ ከሁሉም የከፋ ጉዳት አለው፡፡ አማራ ያልገባበት ቤት የለም፡፡ አፍንጫ ሲመታ ዐይን ያለቅሳል፡፡ ለምሣሌ በጃዋር መሀመድና በኢሣይስ አፈወርቂ ውስጥ የአማራ ደም እንደመኖሩ የነዚህ ሰዎች የተመሰቃቀለ ስብዕና በሚፈጥረው ቅራኔ ምክንያት አማራ ላይ አዲስ ዕልቂት ቢታወጅ ተጎጂው አንድ ወገን ብቻ ሣይሆን ሁሉም ነው፡፡ ስለዚህም ነው አማራነት ከኢትዮጵዊነት ጋር የሞክሼነት ጠባይ ያለው እስኪመስል ድረስ በታሪክም በትርክትም የሚጠቀስ፡፡
እናም አማራ ላይ የተነሣችሁ ሁሉ እጃችሁን ከዚህ ምሥኪን ሕዝብ ላይ አንሱ!
ከይቅርታ ጋር ለዛሬ ግንቦት ሰባትን በሚመለከት ጥቂት ሃሳብ እሰነዝራለሁ፡፡
ይህን “ግንባር” በተመለከተ ብዙውን ጊዜ ብዙዎች ብዙ ነገር ብለዋል፡፡ እኔም ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ተናግሬያለሁ፡፡ የሰማኝ ይኑር አይኑር አላውቅም፡፡ ስለዚህ “ድርጅት” ብዙዎች የሚሰማቸውን ለመናገር ፈልገው በተለያዬ ምክንያት በዝምታና በይሉኝታ የሚያልፉ እንዳሉ እንዲሁ በግምት መረዳት ይቻላል፡፡ የነፃነት ትግሉን የጎዳን እየመሰለን አፋችንን በይሉኝታ በመሸበብ ስለግንቦት ሰባት ምንም ሳንተነፍስ የተቀመጥን ወገኖች በርካቶች ነን፡፡ በተለይ ካለፈው ሐምሌ ወር 2008ዓ.ም ወዲህ ይህ ድርጅት ከወረቀት ነብርነት ባለፈ ሌላም አጀንዳ እንዳለው የምንጠራጠር ዜጎች በዝተናል፡፡ ሙሽሪት “ካልታዘልኩ አላምንም” ያለችው እውነቷን ነበር፡፡ አንዳንዶች ተናግረው ይወጣላቸዋል፡፡ ከነዚህ አንዳንዶች መካከል ጥቂቶቹ ምናልባትም ሆድ እየባሳቸው ሳይሆን አይቀርም ይህን ይበልጡን ምናባዊነት የሚጠናወተው የጦር ግምባር በዱላ ቀረሽ ስድብ ሲወርዱበት በየራዲዮው ይደመጣሉ፤ በየድረገፁም ይነበባሉ፡፡ ብሶት ሲበዛ ምክንያታዊነትን ማደብዘዙ አይቀርምና በነዚህ ዓይነቶቹ ስሜታውያን ብዙም አንፈርድባቸውም ይሆናል፡፡ እውነቱን መናገር ግን ይገባናልና አሁንም ሆነ ወደፊት እንናገራለን፡፡ እውነት ይመራል ወይም ትመራለች፡፡ ይመራል ወይ ትመራለች ተብሎ ግን ሀገር እንጦርጦስ ስትወርድ፣ አንድ ሕዝብ በሥልት ሲያልቅ ዝም ማለት ቢያንስ ለኅሊና ወቀሣ ያጋልጣል፡፡ ዝም ማለት ደግሞ ዝም ባይን ብቻ ሣይሆን ሀገርንም እንደሚጎዳ የተረጋገጠ ነው፡፡
ግንቦት ሰባት ከአማራው ራስ ውረድ!
አማራን እያስፈጁ ካሉ ወገኖች መካከል አንደኛው ይህ ከአየር ወርዶ መሬት ላይ መቀመጥ ያልቻለ ድርጅት ነው፡፡ በተያያዘው ሁለገብ የተባለ የትግል ሥልት በእስካሁኑ አካሄድ ከአራት ኪሎ ቤተ መንግሥት በ1080 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ እንዳለ ነው፤ አንዲት ጋትም ፈቀቅ አላለም፡፡ ወያኔና ሻዕቢያ እስካሉ ድረስ ደግሞ ወደፊትም ቢሆን ከዚህ ርቀት ስንዝር ውልፊት የሚል አይመስልም – የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል፡፡ ይህ እውነት ፀሐይ በምሥራቅ ወጥታ በምዕራብ የመግባቷን ያህል ገሃድ ወጥቶ የፈጠጠ ነባራዊ እውነት ነው፡፡ የማይሆነውን? በ“ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” ብዙ ተጓዝን፡፡ አሁን ግን በቃ፡፡ ሌሎች ወገኖች ሌላ ሁነኛ የትግል ሥልት ይፈልጉ – ተባብረን እንፈልግ፡፡ ታዲያ ከእግዚአብሔር ጋር፡፡ ፈጣሪ የሌለበትና በርሱ ያልተባረከ የነፃነት ትግል ታጥቦ ጭቃ ነው፡፡ በእስካሁኑ መንገድ ከተጓዝን ዓሣማ ጅብን፣ ጅብም ዓሣማን በየጊዜው እየገለበጠ የእስስት ቀለም በሚቀባ ቤተ መንግሥት ውስጥ በሚገሸሩ የእፉኝት ልጆች ከመሰቃየት በስተቀር አንድም ለውጥ አይመጣም፤ ስቃይ በፈረቃ ይብቃን፡፡
ግንቦት ሰባት – ሌላው ቀርቶ የመታገያ ሥፍራ ሳይጠፋ አሉኝ የሚላቸውን ታጋዮች የአማራው ትግል በተፋፋመባቸው ወደ ጎንደርና ከፊል ጎጃም መላኩ ድርጅቱን በርግጥም ሌላ ተልእኮ እንዳነገበ ጥርጣሬ ውስጥ ይከተዋል፡፡ በዚህ ድርጅት ሰበብ የሚገደለውና ታፍኖ ደብዛው የሚጠፋው ወገን የመቃብር ሥፍራዎችን፣ የሚታሰረውና ሰይጣን ራሱ እንኳን በማያውቃቸው ነውረኛና ግፈኛ የማሰቃያ ዘዴዎች እዬዬ የሚለው ወገን ደግሞ እሥር ቤቶችን እያጣበበ ነው፡፡ ሰዎችን ማሳሰር ደግሞ የመጨረሻ የትግል ግብ ሊሆን አይችልም፤ አይገባምም፡፡ “የግንቦት ሰባት የነፃነት ፋኖዎች በበተኑት የትግል ጥሪ ማስታወቂያ ወረቀቶች ምክንያት ይህን ያህል ወጣትና ጎልማሣ በዚህ አካባቢ በወያ ታፍሶ ታሰረ” የሚል ዜና አሣፋሪም አስቂኝም ነው፡፡ የግንቦት ሰባት ብቸኛ ግብ በርሱ እንቅስቃሴ ምክንያት የሰዎች መታፈንና ደብዛ መጥፋት እስኪመስል ድረስ ብዙ አስገራሚ ዜናዎችን እየተከታተልን ነው፡፡ ይህ ድርጅት ነፃነታችንን ማምጣት ቢያቅተው የወያኔን ማነቆ በማጠባበቅ ረገድ ትልቅ አስተዋፅዖ እያበረከተ ለስቃያችን መራዘም ምክንያት ከመሆን መታቀብ አልቻለም፡፡ ባለቤቱ የሌለበትን ባዶ መኖሪያ ቤት በጠፍ ጨረቃ በርቀት ቦምብ በመወርወር ለማቃጠል መሞከርና ወንዝ ለማያሻግር ልቅላቂ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲባል ብዙ ሰዎች አለአበሳቸው እንዲታሰሩ ማድረግ አዋጪ የትግል ሥልት አይደለም፡፡ “በመካከላችሁ ነን፤ እኛ እንዲህ ነን – ዕወቁን!” በሚል ከንቱ ውዳሤን ለማግኘት በታለመለት ፕሮፓጋንዳ ንጹሓን ዜጎችን ማሳፈስና ለወያኔ ኦሽትዊዝ መዳረግ በክትትል ሥርም ማዋል ብልህነት አይደለም – “ሙያ በልብ” እየተባለ ምሥጢራዊነት በሥነ ቃል በሚወሳበት በኛዋ ሀገር ቀርቶ በየትም ሀገር የነፃነት ትግል ወቅት ይህ ዓይነቱ አስተዋይነት ከጎደለው ድፍን ልብ የሚወጣ ዘዴ ጥቅም ላይ ስለመዋሉ እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ ደግሞም ትምክህት ባይኖር የሚመረጥ መሆኑ እንዳለ ሆኖ እንደ ዐመል ቢሆንና ሊከሰት የግድ ሊሆን ቢችል ግን ከውጤት ጋር ቢሆን ብዙም ባላጣላ፡፡ በፈረንጅ አገርና በጠላት አገር አንቀልባ ውስጥ ሆኖ ግና አያምርም፡፡ ለትዝብትም ይዳርጋል፡፡
“አማራ አካባቢ ጥቃቅን ጥቃቶችን በአሳቻ ቦታና ጊዜ በመሰንዘር ሕዝብ መሀል መደበቅ ግንቦት 7 ሆን ብሎ አማራን ለማጥቃትና ለማስጠቃት ማቀዱን ያሳያል፡፡” የሚል ወቃሽና ከሳሽ ቢነሳ አሳማኝ መልስ ለመስጠት እንዳይቸግር ድርጅቱ በቅጡ ሊያስብበት በተገባ ነበር፡፡ ኢሣይያስ በምድር ከሚጠላቸው ነገሮች አንዱ አማራ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በርግጥ ሰሞኑን OMN ከተባለና ኢትዮጵያን እጅግ ከሚጠየፍ አንድ “የውጭ ሀገር” የዜና አውታር ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ለአማራው ያዘነለነት የሚመስል ድምጸት ከንግግሩ ታዝበናል፡፡ መልካም ጅማሮ ነው፡፡ ነገር ግን ዕብድ ቢጨምት እስከኩለ ቀን በመሆኑ የተጣባው የአማራና የኢትዮጵያ ጥላቻ በምንም መንገድ ይለቀዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡ እንኳን ለኢትዮጵያ “የገዛ ሀገሩን”ም በፈርዖናዊ ዐረመኔያዊ አገዛዝ እንደሰም አቅልጦና እንደብረት ቀጥቅጦ እየገዛ መሆኑን ለመገንዘብ፣ በሚደርስባቸው ስቃይና እንግልት ሳቢያ የርሀብ ዐድማ መትተው ሕይወታቸውን በገዛ ራሳቸው እንዳሳለፉ ሰሞኑን የተዘገበላቸውን የሁለት ሴቶች ታሪክ ማጤን ብቻውን በቂ ነው፡፡ ለርሱ አስተሳሰብና ፍልስፍና ሩቅ የሆንነውን እኛን ይቅርና አምባገነን ሲባል ለወንበሩ ሲል የራሴ ናቸው በሚላቸው ምሥኪን ዜጎች ላይ ሳይቀር የማይፈጽመው ግፍ የለም፡፡ እናም ከርሱ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ከማጥፋት ወይ ከማውደም ውጪ ትንሣዔዋን ማብሰር ይቻላል ብሎ ማመን ሲዖል ውስጥ በሚገኝ የሊቀ ሣጥናኤል አደባባይ መሀል የመንግሥተ ሰማይን ሠገነት ለመገንባት እንደመሞከር ያለ ቂልነት የተሞላበት ድፍረት ነው፡፡ ይህን ዕብድ ሰው ለማስደሰት ደግሞ አማራን በአሽሙርና በነገር መወረፍ፣ በተገኘ መድረክ ሁሉ መዝለፍ፣ መናቅና ማግለል፣ ታሪኩን ማጠልሽትና እስከተቻለም ከያለበት እየሰበሰቡ ማውደም ብቻውን አይበቃም፤ በዋናነት ዘሩን ከምድረ ገጽ ማጥፋትም ጭምር እንጂ! ለዚህም ነው እጅግ በርካታ የአማራ ተወላጆች ኤርትራ ውስጥ በየዋህነት በመግባት በኢሣይያስ ሠይፍ አሁንም ድረስ እየታረዱ የኤርትራን አበሳ ሲያበዙና የኢትዮጵያን የማይቀር ነፃነት ሲያዘገዩ የሚስተዋሉት፤ የጠማማ ቀንና የዕዝ ጉዳይ ሆኖበት እንጂ ሕዝቡ ይህንን ሁሉ በሚገባ ያውቃል፡፡ ይህም ሁሉ ሊሆን የቻለው በአንድ በኩል በግንቦት ሰባት ቅስቀሳ መሆኑን መካድ አይገባም፡፡ ስለዚህ ግንቦት ሰባት ከሻዕቢያ የመወዳጀት መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ባልጠፋ ቦታ ግን ይህን ሞትና ስደት የታወጀበትን የአማራ አካባቢ ለትግል ማዕከልነት መምረጡ ለተልእኮ ነው ቢባል ከፈጠጠው እውነት አኳያ ስህተቱ ለክፉ የሚሰጥ አይሆንም፡፡ እናም ግንቦት ሰባት በሚያምነው ይሁንበት የአማራን አካባቢዎች በቶሎ ይልቀቅና አማራውን ከዘርፈ ብዙ ትግል ይገላግለው፡፡ የሚጠሉትን ኃይል በደጀንነት ማሰለፍ ደግሞ ቃላት ቢደብቁት ዐይነ ውኃ ያወጣዋል፡፡
መላ ትግራይ፣ ከፊል ባሌ፣ ሲዳሞ፣ አርሲ፣ ጋምጎፋ፣ ከፊል ወሎ፣ ከፊል ሸዋ፣ ወለጋ፣ አፋር፣ ኢሉባቦር፣ ጂማ፣ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ ዐርባ ምንጭ፣ ዐርባጉጉ፣ በደኖ፣ ጉራፈርዳ፣ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ወዘተ. አንድ ብቻ ሣይሆን በመቶዎች የሚቆጠሩ ግንቦት ሰባቶችና ከተገኙም ጳጉሜ ሰባቶች ያስፈልጓቸዋል፡፡ ለነገር ካልሆነ ታዲያ የነፃነት ትግል እየተካሄደበት በሚገኝ ሥፍራ ላይ ተደራቢ ደባደቦ ለምን አስፈለገ? ይህ ጊዜስ እንዴትና ለምን ተመረጠ? ለምንስ ትግሉ ቀዘቀዘ? በርግጥ ለአማራው ታዝኖለት ነው ወይንስ የነፃነት ትግሉን በእጅ አዙር ለመቆጣጠርና ለማኮላሸት? በወያኔ ቋንቋ መሬት ላይ በግልጽ የሚታዩ ሁኔታዎችን ስናይ አንዳች ነገር እናሸታለን – ፈረንጆች እንዲህ ዓይነት የተወሳሰበና ለፍርድ የሚያስቸግር ነገር ሲገጥማቸው “it is fishy.” ይላሉ፤ የኛ ግን ከ”fishy”ም በላይ ነው፡፡ አማራው እንደሕወሓት፣ እንደዴምሕት፣ እንደኦነግ፣ እንደኦብነግ፣ወዘተ. ያለ የነፃነት ፋኖ ስለሌለው ታዝኖለት እንደሆነም አላውቅም፡፡ እንዲህም ከሆነ ግዴለም ይቅርበት፣ በአፍንጫው ይውጣ፡፡ ግንቦትም ሆነ ለካቲት ወይም መስከረም በእስካሁኑ ሁኔታ አስጠቁት እንጂ የፈየዱለት ነገር የለም፡፡ በ”ሳቢውን ግረፈው” የተጀመረ ትግል ላይ ከጠላት የተላከ ቀዝቃዛ ውኃ ከመከልበስና ትግልን ከማጓተት ብርታትና ጥንካሬው አቅሙም ካለ በሌላም አቅጣጫ ተጉዞ አራት ኪሎ ላይ መገናኘትም እኮ ይቻላል ነበር፡፡ የሥልጣን ሽሚያ እንዳይባል ደግሞ “ሳይከካ ተቦካ” እንዲሉ ይሆናል፡፡ ገና ምኑ ተይዞ?
“አመራሮቹ በአብዛኛው የደቡብ ሰዎች ናቸው፤ አማራ የለባቸውም” መባሉ እንደኔ ምንም ማለት አይደለም፡፡ “የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው” እንደሚባለው ዋናው የእውነተኛ ነፃነታችን መገኘት እንጂ በማንና በየት በኩል መምጣቱ ብዙም አያስጨንቅምና ለእውነተኛዋ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ነፃነት ከቆመ ትግሉን ማንም ይምራው፡፡ ከየትም አቅጣጫም ይምጣ፡፡ “ግንቦት ሰባቶች ምንም የረባ ነገር ሳይሠሩ የሞኝ ዲያስፖራዎችን ገንዘብ እየሞጨለፉ ይኖራሉ” የሚባለውም ለኔ ውኃ አያነሳም፤ ከምቀኝነትና ከተራ አሉቧልታነትም ለይቼ አላየውም፡፡ ተከራክሮ ለማሣመን መሞከር ሚዛን በሚደፋ የሃሳብ ልዩነት እንጂ ይህን በመሰለ መብልና መጠጥን ያማከለ ተራ ነገር መሆን የለበትም፡፡ እውነቱን ለመናገር ከአመራሮቹ ብዙዎቹ እኮ ምንም የማይጎድላቸው ናቸው፡፡ በገንዘብም፣ በዕውቀትም፣ በዝናም ከነሱ አልፎ ለሌላም የሚበቃ ትሩፋት አላቸው – ለምሣሌ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ምን ጎደለበት? እንዲህ መከራ እያዩ፣ በሰው አፍ እየተቦጨቁ ሆዳቸውን በእንጀራ ሊሞሉ የሚሹ የግንቦት ሰባት አባላት ሊኖሩ ይችላሉ ተብሎ ቢገመት እንኳን ቁጥራቸው እዚህ(ም ሆነ እዚያ) ግባ የማይባል አነስተኛ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እናም በዚህ ልጠረጥራቸው አልፈልግም፡፡ የሆነ ነገር ዞሮባቸው ወይም የሆነ ፈተና ውስጥ ገብተው በ“ካፈርኩ አይመልሰኝ” ዓላማቸውን እንደሳቱ ቢነገር ይበልጥ ያሳምነኛል፡፡ አንዳንዴ አንዳንድ ነገር ትጀምርና አንዳንድ የማይሆን ቅርቃር ውስጥ ትገባለህ፤ አይፍረድ ነው፡፡ “እነዚህ ሰዎች የኛ ናቸው፡፡ ግን ኢሣይያስ በሆነ ትብታብ ቀይዶ ለሆነ ሰይጣናዊ ተንኮሉ ሊጠቀምባቸው ‹ጃዝ‹ እያላቸው እንዳይሆን፡፡” ብዬ የምሰጋባቸው ጊዜያት ይበዛሉ፡፡ የትሮይን ፈረስ ታሪክ ያነበበና ፊልሙን ያዬ ድንጉጥ ነው፡፡
ከዚህ በተረፈ “አመራሮቹ አማራን ይጠላሉ፤ ከዛም ባለፈ አማራን ይሳደባሉ፤ ያንቋሽሻሉ፤…” መባሉ ግን ከሀሜት አልፎ እውነት ከሆነ መሠረታዊና የማይታረቅ፣ ራሱንም በየዘመናቱ የሚደጋግም ችግር ውስጥ እነሱም የተዘፈቁ መሆናቸውን ጠቋሚ ነው፡፡ አማራን እየጠሉ በአማራ አካባቢ መንቀሳቀስ ደግሞ ትልቅ አያዎ(paradox) ነው፡፡ ለጠላት ለጠላትማ እነወያኔንና ሻቢዕቢያን እንዲሁም ኢትዮጵያና አማራ ሲወሱ ደማቸው የሚንተከተከው ቀናተኞቹን ምዕራባውያን የመሳሰሉ ግንዲላ ግንዲላ ታሪካዊ ጠላቶች ስላሉት ከነዚህ በተደራቢ ግንቦት ሰባት የሚባል በተለይ የኢሣይያስ አፈወርቂ የመቶ ዓመት የቤት ሥራ አስፈጻሚ ለአማራው አያስፈልገውም፡፡ አማራውን ጠላት አታብዙበት፡፡ የአማራው ችግር በሚገባ ይታወቃል፡፡ እውነቴን ነው የምለው – ከመቶ በመቶ ባለፈ እርግጠኝነት ችግሩንና የችግሩን መባቀያ ብዙ ዜጎች ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡
የአማራው ችግር ዋናው ኢትዮጵያዊነቱ ነው፡፡ ሌላው ችግሩ ተፈጥሯዊ አስተዋይነቱ ነው – አይቸኩልም ወይም አይጣደፍም፡፡ ሌላው ችግሩ ዘረኛ አለመሆኑ ነው፡፡ ሌላው ችግሩ ሆደ ሰፊነቱና ታጋሽነቱ ነው፡፡ “ሌላው ችግሩ” በቀልን ለፈጣሪው እርግፍ አድርጎ መተውና ከቅርብ አሠርት ዓመታት ወዲህ ደግሞ የሚፈጸምበትን ግፍና በደል ሁሉ ከገዛ ወገኖቹ እንደተሰነዘረበት አምኖ ለመቀበል መቸገሩ ነው (Truly speaking, the Amharas have really been in disbelief for the past good number of decades to logically accept that these crooked Woyannes would inflict such a horrendous act upon them, upon their brethren, indeed, mainly for the sake of winning their daily bread, in fact. …) ከዋናነት ችግር ባልተናነሰ ደግሞ በወንዝና በጎጥ አምኖ በአማራነት ሊያሰባስበው የሚችል ማዕከላዊ አደራጅ ኃይል መፍጠር አለመቻሉ ነው፡፡ ሳይማር የተማረ፣ ፍትሃዊ ብይንን በተፈጥሮው ያወቀ፣ ከሌሎች ነገድና ጎሣዎች ጋር በፍቅርና በመተሳሰብ ለዘመናት የተዋሃደና የተሳሰረ፣ ትግስቱ ከሰማየ ሰማት የዘለቀ፣ የመጣበት እንደሆነ ጀግንነቱ በዝናብ ውኃ የሚያስጠማ … መሆኑ አማራን ክፉኛ ጎድቶታል፤ እየጎዳውም ነው፡፡ እነዚህ ችግሮች ቢወገዱ (በርግጠኝነትም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሲወገዱ) ጠላቶቹም እንደሚፈሩት ሁሉ አማራ ለአፍሪካ ቀርቶ ለሌላም የሚበቃ ኃይልም ዕውቀትም የደም-መላሽነት ወኔና ብቃትም አለው፡፡ ይህን ጠባዩን የሚረዱ ጠላቶቹ እስካሁን እግር ከወርች አሥረው ይዘውት ነበር፡፡ አሁንና ከአሁን በኋላ ግን ይህ ዓይነቱ ሞኝነት አይኖርም፡፡ እናም አማራን ለማጥፋት ከጠላት ጋር ተሰልፈህ በደም ጥማት ስትወራጭ የነበርክ ሁሉ ዕርምህን አውጣ፡፡ ከእንግዲህ አማራው የገደል ላይ ወይን ሊሆን የቀረው ጊዜ በጣም ኢምንት ነው፡፡
ማንም ይሁን ማን በዘርም ይደራጅ በሃይማኖት፣ በቀበሌም ይቧደን በአውራጃ አማራው ከሰፈረው በላይ ዕጥፍ ድርብ በሚያስከነዳ ቁና ዕዳውን ከፍሎ እየጨረሰ ስለሆነ ከእንግዲህ ውዝፍ ዕዳን የማወራረዱ ጣጣ ለግፈኞቹ ጭራቆች እንጂ ሒሳቡን አወራርዶ ላገባደደው ለአማራው አይሆንም፡፡ አማራው ከቀደምት አባቶቹ መካከል ጥቂቶቹ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ – ያኔ በኋላ ቀር ዘመን – እንደፈጸሙት የሚነገረው የቀድሞ ዘመን በደልና ወያኔዎች በዚህ የሥልጣኔና የዕውቀት ዘመን እየፈጸሙት የሚገኙት ሊነገር የሚዘገንን ግፍና ስቃይ ቢወዳደር የቀደመው የአማሮች ጥፋት ከቁንጥጫ እንኳን የማይቆጠር ግን በመጥፎነቱ ይቅርታ ሊጠየቅበት የሚገባው የታሪክ ጠባሳ ትውስታ ነው – የዕዳ ትንሽ ትልቅ የለውምና ይህ ታሪካዊ ዕዳ ደግሞ ከሚገባው በላይ ተለጥጦ ተከፍሎ አልቋል፤ ፈራጁ እርግጥ ነው እኔ ኃጢኣተኛው ግርማ ሳልሆን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ግን ይብላኝ የከመሩትን ዕዳ ገፍግፈው ለመጨረስ ሥፍር ቁጥር የሌላቸውን ምሥኪን ትውልዶችን ለሚፈጅባቸው ወያኔዎች፡፡ የሠሩት ግፍ በአንድና በሁለት ትውልድ ተክፍሎ የሚዘለቅ አለመሆኑን አሁንም ድረስ በየዕሥር ቤቱ የሚፈጽሙት ዘግናኝ ሰቆቃ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ በአስተሳሰብ ከከብት የማይሻት እነዚህ ጅላጅል ወያኔዎች ዛሬን እንጂ ትናንትንና ነገን ማየት ተስኗቸዋል፡፡ ዛሬን ብቻ የሚመለከት ሰው ደግሞ የታሪክ ሰው ሳይሆን ከእንስሳት ያነሰ የዛሬ ብቻ ሰው ነው፡፡ የአሁኑን አያድርገውና አህያም እኮ ከጠገበች ታናፋለች፤ አሁንም የዛሬውን አያድርገውና መጨረሻዋ ግን የጅብ ነው፡፡ ተረቱም “ካልጠገቡ አይዘሉ፣ ካልዘለሉ አይሰበሩ” ነው፡፡ እናም የአነጋገር መስመሬ እንዴቱንም ያህል ይወለጋገድ ዋናው መልእክቴ ግን በጥጋብም ሆነ በጠላት ሥውር ተልእኮ ሀገርንና ሕዝብን መካድ በመጨረሻው ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን መጠቆም ነው፡፡
አማራ አሁን ከፈጣሪው ጋር ይታረቃል፤ አሁን ከፈጣሪው ጋር ብቻ ይመካከራል፤ አሁን የተዳፈነች እውነተኛ ሃይማኖቱን የበግ ለምድ ከለበሱ ተኩላዎች ይረከባል፤ እግዚአብሔርም እውነተኞቹን እረኞች ሳይውል ሳድር ይልካል፡፡ አሁን ከተበዳደለው ጋር ይቅር ለእግዜር ይባባልና ታሪካዊ ጠላቶቹን መቀመቅ በማውረድ የግዛት አንድነቷ የፀና፣ የሕዝቧ ፍቅርና መተዛዘን የጠነከረ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ከወገኖቹ ጋር ይመሠርታል፡፡ ህልም ብቻ አይደለም፡፡ ምኞትና ፍላጎት ብቻም አይደለም፡፡ ከድቅድቅ ጨለማ ማኅፀን ውስጥ ፍንትው ያለ ብርሃን መረገዙንና ጊዜውን ጠብቆ መወለዱን ከማወቅ የሚመነጭ ግልጽ “ራዕይ” ነው፡፡ ምኞትም ቢሆን ለማንም የተከለከለ አይደለም፡፡
ኢሣይያስ አፈወርቂ አማራን ለማጥፋት የማይቀይሰውና የማይተገብረው ሥልት የለም፡፡ አሁን ባለን የስሜትና የእውነት መረጃ ደግሞ ግንቦት ሰባት ትልቁ የሻዕቢያ መሣሪያ እንደሆነ በሚያስጠረጥር ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ እንዲህ ስል ደግሞ ምንም ላደርገው ባልተቻለኝ ድፍረቴ አዝናለሁ፤ ይቅርታም መጠየቅ ይዳዳኛል – በውስጡ ብዙ ቅን ሰዎች እንዳሉ እረዳለሁና፡፡ እውነት መስሏቸው በየዋህነትና በሀገር ፍቅር ስሜት ምክንያት እዲሁም በሚዲያዎች ጫና አማካይነት በዚህ ድርጅት ውስጥ ገብተው የሚዳክሩ ጥቂት የማይባሉ ወገኖች ይህን ወረቀት ሲያነቡ ምን ሊሰማቸው እንደሚችል እገነዘባለሁና ከአንጀቴ እንደማዝንላቸው በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡
“የጨነቀው እርጉዝ ያገባል፤ ስትወልድበት ገደል ይገባል” እንላለን፡፡ ግንቦት ሰባት ጨንቆት ሻዕቢያን ተወዳጀ፡፡ የሻዕቢያን መርዝ ከተወጋና ከዓላማው መናጠብ ሲጀምር ግን ስህተቱንም እያወቀ በመጣው ይምጣ ዓይነት የማያስፈልግ እልኽና ድፍረት በስህተት ጎዳናው ቀጠለ፤ እንደገበሬ ግና ገደል መግባቱን አልደፈረም፡፡ ገደል መግባቱን በበኩሌ ስለማልመኝ ጥሩ ነው፡፡ ነገር ግን መቶ ሚሊዮን ሕዝብ እውን የማይሆን የተስፋ ዳቦ እያስገመጠ ሌላ አቅጣጫ ሊይዝ ይችል የነበረውን የነፃነት ትግል ማጓተትና የወያኔ ዱላ ሕዝቡ ላይ በርትቶ እንዲቀጥል መፍቀድ አልነበረበትም፤ በዚህ ረገድ ታሪክ ይቅር ሊለው የሚቸግረው ትልቅ ስህተት ሠርቷል ብዬ እገምታለሁ፡፡ ብዙ እውነቶች አሉ፡፡ አንዱ ይህ ነው፡- ተስፋ እንደማንም ፍጡር ተፀንሶ ይወለዳል፡፡ ዕድሉን ካገኘም ያድጋል፡፡ የሚወለድና የሚያድግ ነገር ደግሞ አርጅቶ እንደሚሞት ሁሉ ተስፋም ዕድሜው ሲደርስ ወይም ከዚያ በፊት ይሞታል፡፡ በወቅቱ እውን የማይደረግ ተስፋ ዕድሜው ስለተንዘላዘለና በፕሮፓጋንዳ ውሻል ተደግፎ ስለቆመ ብቻ ሕይወት እንዳለው ሊቆጠር አይገባም፡፡ አንድ ተስፋ ሲጨልም በጨለመ ተስፋ ውስጥ መንገዳገድ በትንሹ ሞኝነት ወይም ግንቦት ሰባትና አባቱ ኢሕአፓ እንደሚሉት “ተጨፈኑ ላሞኛችሁ” ዓይነት የ“ሞኝ እንዴት ያሸንፋል” ቢሉ “እምቢ ብሎ” መሰል የሌባ ዐይነደረቅነት ነው፡፡ በመሠረቱ ደረቅ ሰው ሲገጥመን ለማሳመን መሞከሩ ልፋት ነው፡፡ አውቆ የተደበቀን መቀስቀስም እንዲሁ፡፡ እኛም የተቸገርነው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ እዚህም እዚያም ድርቅና፡፡ እዚህም እዚያም የተያዘው “ማን ምናባቱ ምን ያመጣል?” ዓይነት ትዕቢትና ዕብሪት ነው፡፡ ቤት ውስጥ ያለውም፣ እደጅ የቆመውም፣ በር ዘግቶ የተቀመጠውም በሩቅ ሆኖ በህልሙ በሩን የሚያንኳኳውም ሁሉም ተያይዞ በትምክህትና በትዕቢት ጋጣ ውስጥ ይንቦራጨቃል፡፡ ወ/ሪት ትኅትና ወዴት ጠፋች? አያ ይሉኝታ ወዴት ተደበቀ? ሁሉም ራሱን በሃቅ ቢፈትሽ ሩቅ ሳይሄድ መፍትሔውን በቅርብ ያገኝ ነበር፡፡
ተረት አበዛሁባችሁ፡፡ ግን ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ እንዲያውም ልጨምርባችሁ ነው – የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም፡፡ ጦር ቢሰላና ቢረዝም ካልወረወሩት ጠላትን አይገድልም፡፡ ወሬ ቢበዛም በአህያ አይጫንም፡፡ በትልቅ ሚዲያ ወሬ ቢጠረቅ ዓመታት እየነጎዱ ዓመታት ይመጣሉ እንጂ ግመሎቹም ከመራመድ ፍየሎቹም እየጮኹ ከመከተል የሚያግዳቸው የለም፡፡ ከጧቱ አለመለከፍ ነው፡፡ እኛን ያጋጠመን ልክፍት ደግሞ መሥፈሪያ የለውም፡፡ ከ1966ዓ.ም ወዲህ ራሱ ያረሩ ዳቦዎች ቢከማቹ ሰሞኑን ወያኔ በድማሚት ካፈረሰውና ብዙ ምሥኪን ዜጎችን ከጨረሰው የቆሻሻ ክምር ይበልጣሉ፡፡ ልጆቿ በዘረኝነት ፈንጣጣና በማይምነት ኩፍኝ እየሞቱ እንግዴ ልጆቿ በሚያድጉባት ኢትዮጵያ በተስፋ ብቻ መኖር ከጀመርን ብዙ አሠርት ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ክፉ ዕድል ነው፡፡ የትልቅ መረገም ውጤት መሆን አለበት፡፡ ከተቆለሉት የተስፋ ዳቦዎች ውስጥ አንዱም እንኳን አንጀት ጠብ ሊል ያልቻለው እኛ ኢትዮጵያውያን በተለያዬ ግላዊ ፍላጎትና ዓላማ በተቀነበቡ ትንንሽ ዓለማት ውስጥ ስለምንኖር ነው፡፡
“እገሌ ይጠጣል፤ ከእገሌ ጋር እንዲህ ያደርጋል፤ እንዲህ እንዲያ ይዝናናል” የሚለው ለኔ በጣም የወረደ ተራ ወሬ ነው፤ ይህንን ማንም ያደርገዋል – ሰው ነውና፡፡ ለኔ ዋናው መለኪያ ጊዜ ነው፡፡ ለኔ ትልቁ መመዘኛ አንደበትና የገቡትን ቃል በገቡት ጊዜ ውስጥ ማከናወን ነው፡፡ ለኔ ትልቁ ሰውን የመለኪያ መሣሪያ ከጉራና ትዕቢት በጸዳ ንጹሕ ኅሊና ሕዝብን ማገልገል ነው፡፡ ትልቁ ሰውን መመዘኛየ በዱባ ጥጋብ ኅሊናን ያለማሣወርና ሀገርንና ሕዝብን ከልብ መውደድ፤ እስከቀራንዮም ተጉዞ ነፃነትን ለግፉኣን መዋጀት ነው፡፡ ይህን የሚያደርግ ብፁዕ ነው፡፡ (በነገራችን ላይ ሰሞኑን ሰሙነ ህማማት ነው፤ ትንሣኤ ክርስቶስ ይለጥቃል፤ ስለሆነም ክርስቲያን ወንድሞችና እህቶችን “እንኳን ለብርሃነ ትንሣዔው አደረሳችሁ” እላለሁ በዚህ አጋጣሚ፡፡) በዚህና ከፍስ ሲል በጠቀስኩት የግንቦት ሰባት ሙከራ መካከል ግን ቦግ ብሎ የሚታይ ልዩነት አለ፡፡ ይህ ነገር ካልታሰበበትና መፍትሔ ካልተገኘለት – ማሰብ ከተቻለና ጊዜው ካለን – አደጋው ቀላል አይደለም፤ትግሉ ከመጠን በላይ እየተጓተተ ነው፡፡ ሲጓተት ኪሣራው ይበዛል፡፡ ኪሣራው ሲበዛ አብሮነታችን ክፉኛ እየተጎዳ ይመጣል፡፡ እየሞተ መኖርን የሚሰለች ትውልድ ሲያቆጠቁጥ መዘዙ አይጣል ነው – እየገደለ መፈንጠዝን የሚጠላ ትውልድ ቢፈጠርም ያው ነው – የሁለቱ ተቃራኒ እውነቶች መጋጠሚያ ደግሞ ሊያስቡት የሚከብድ አደጋን የሚያስከትል መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ማስተዋልን አድሎን ቆም ብለን ራሳችንን ካልመረመርንና የኮምፓሳችንን አቅጣጫ በአፋጣኝ ካልቀየርን የገባንበት አረንቋ ርዝማኔው የታችኛውንም ዓለም እሳተ ገሞራዊ የወለል ንጣፍ አልፎ ይነጉዳል፡፡
ሲናገሩት የማይቀል ነገር የለም – ፈርንጆ better said than done የሚሉትም ለዚህ ነው፡፡ እዚህ ያገናኘን ደግሞ የዚሁ ውጤት የሆነው የንግግርና የተግባር መለያየት ነው፡፡ ከንግግርና ፉከራ በፊት አቅምን ማወቅ ጥሩ ነው፡፡ የማድረግ ፍላጎትንና አቅምን ማገናዘብም ጥሩ ነው፡፡ ሰውን እንዴትና እስከምን ድረስ ማስደሰት እንደሚቻል መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ሁሉንም ማስደሰት እንደማይቻል መገንዘብ ደግሞ ብልኅነት ነው፡፡ ሁሉንም ለማስደሰት መሞከር ሁሉንም ለማስከፋት ከመሞከር ብዙም አይተናነስም፡፡ የማመስገንን/የማወደስንና የመንቀፍን ስሜቶች መቆጣጠር አስተዋይነት ነው፡፡ ከብረት ድስት ይልቅ የሸክላ ድስት ይሻላል፡፡ ብረት ድስት ግልብ ነው፡፡ በቀላሉ ይቆጣል፤ በቀላሉ ይቀዘቅዛል፡፡ በትንሽ በትልቁ መፎግላት የአመዛዛኝ አእምሮ ባለቤት አለመሆንን ይጠቁማልና ከዚህም መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ ይህ በሂደት ያገኘሁት ግንዛቤ በተለይ ለግ7 አባላት እንደሚጠቅም አስባለሁ፡፡ እንዳስተዋልኩት ደርሶ ቱግ ማለትና አልፎ አልፎ አስፀያፊ ስድብ መሳደብ የአንዳንድ አባላት ባሕርይ ሳይሆን አልቀረም፡፡ የስሜት ፈረስ ወደጦር ሜዳ ይወስድ እንደሆነ እንጂ በራሱ ጦርነትን አይዋጋም፡፡ ሰከን ብሎ ማሰብ ግን ከራስ ጋርም ያስታርቃልና መልካም ነው፡፡ ብዙ የተማረ ኃይል ያለበት ድርጅት ከሚጠበቅበት ነገሮች ዋንኞቹ ሆደ ሰፊነትና ዴሞክራሲያዊነት ነው፡፡ የዝና ስካርም ይበርዳል፤ የአካል ውበትም ይጠወልጋል፤ የመልክ ቁንጅናም ይረግፋል፤ ለሁሉም ጊዜ አለውና፡፡ ጊዜውን ጠብቆ ያልበቀለ እህል እንደዐረም ተቆጥሮ ይነቀላል፡፡ ከመነቀል እንድንድን የጊዜን ጥቅምና የተስፋን ምንነት ከተግባራዊ እንቅስቃሴያችን ጋር በተጎዳኘ መረዳት ይገባናል፡፡
ለማንኛውም ከጠላት ጋር ወግኖ ሠልፍን በማበላሸት በሕዝብና በሀገር ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት መፈጸም ነውር ብቻ ሣይሆን ለነገ የሸንጎ ፍርድ የሚዳርግ መሆኑን ሁላችንም እንረዳ፡፡ በግልጽነት ለመናገር የሞኝ ሙርጥ ደግሞ ዘላለሙን አይበልጥም፡፡ ሚናን በቶሎ መለየት ከታሪካዊ ተጠያቂነት ይሠውራል፡፡ ከፍ ሲል እንደተገለጸው ሕዝብ ሁሉንም ያውቃል፡፡ የሕዝብ ዱላ ደግሞ በግድ ታንክ ወይም መትረየስ እንዲሆን አይጠበቅበትም፡፡ ሕዝብ ሲበደል ወደፈጣሪው አምርሮ ያለቅሳል፡፡ በዕንባውም አይቀጡ ቅጣት ይቀጣል፡፡ የሕዝብ ችግር ሊሆን የሚችለው ከኃጢኣትና ከዐመፃ ተግባራት ርቆና የፈጣሪውን ትዕዛዛት አክብሮ፤ በዘርና በነገድ ሳይከፋፈል እርስ በርስ ተሳስቦና ተዛዝኖ በአንድ መንፈስ ፈጣሪን ማስደሰት የሚያቅተው ከሆነና በአግባቡ በመጸለይ የአምላኩን ቀልብ መግዛት ካልቻለ ነው፡፡ እንጂ በሰቆቃ ዕንባ የታጀበች “ኤ!” የመጀመሪያዋ ትልቅ ሕዝባዊ የኒኩሌር ጦር ናት፡፡ በሕዝብ መቀለድ ይቻላል፤ በሕዝብ ሀብት አንቱ የተባለ ቱጃር መሆን ይቻላል፤ በሕዝብ ደም በመነገድ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ መገንባት ይቻላል፡፡ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ተጋድሞ እንደወያኔ ለበርካታ ዓመታት ዜጎች ላይ መጸዳዳት ይቻላል፡፡ ማጣፊያውን ግን የሚችለው የለም፡፡ በትምህርት ቤት አንድ “ኤ” ከአራት የሚታሰብ ሙሉ ነጥብ አለው – ኮርስን አኩርቶ ያሳልፋል፡፡ በእርግማን ግን ደም ያስለቅሳል – ደም! መለስ ዜናዊ በሚሊዮኖች “ኤ!” ምክንያት በመንደር ውስጥ ውርጃ እንደተበጣጠስ ሽል ለሥርዓታዊ ቀብር እንኳን መብቃት አቅቶት በስብሶ ሞተ – እንደሰው ያሳዝናል፡፡ መንግሥቱም፣ አፄ ኃ/ሥላሤም ሕዝባዊ “ኤ!”ዎችን አፍሰው የሆኑትን ሲሆኑ አይተናል – ምናልባት ከመንግሥቱ በስተቀር ሌሎቹ ዘር እንኳን የወጣላቸው አይመስለኝም – የብዙ “ኤ!” ባለቤት መሆን ትልቅ ዕዳ ያስከፍላላ! ስለዚህ ሕዝብና ሀገር ላይ ግፍና በደል ፈጽሞ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝ የንስሃና የቀኖና ሂደት ካላለፉ – በስፖርታዊ አገላለጽ የግብ ዕዳ ክፍያን በቅጡ ሳያወራረዱ – በቀላሉ ሸርተት ማለት አይቻልም፡፡ ወደኅሊና በመመለስ ብዙ ተጨማሪ ጥፋት ሳያደርሱ ትክክለኛ መስመርን መያዝ ከቅሌትና ከውርደት ከቅጣትም ያድናል፡፡ ይህን ምክር ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡
“ስለዚህ” ብዬ ልሰናበት ነው፡፡ “ስለዚህ አማራን አምርረው እየጠሉና ጠላትን ለማስደሰት ሲባል ብቻ ይህን ገር ሕዝብ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ አድርገው በየመድረኩ በስድብ እየሞለጩ፣ ‹አማራ ከተገኘ እኛ አንገኝም› ከሚሉ የቤተ ሙከራ ሥሪት ጠላቶቹ ጋርም በማበር ‹ለሀገርና ሕዝብ ነፃነት ቆሜያለሁ› ማለት እንደማይቻል፣ እንዲህ እየተሙለጨለጩም በሃሳብ ደረጃም ቢሆን ወያኔን መፋለም የቀልዶች ሁሉ ቁንጮ እንደሆነ መረዳት እንደሚገባ ማስታወስ ይገባናል፡፡…” በማለት ሃቁን መመስከርና በአማራ ላይ እጁን ያነሳ ሁሉ – እንደማስፈራራት አይቆጠርብኝና – ለራሱ ሲል በአፋጣኝ እንዲሰበስብ የተሰማኝን ብቻ ሳይሆን “የታየኝን” ማስገንዘብ እፈልጋለሁ፡፡ ቀና አስተሳሰብ ላለው – gb5214@gmail.com
mejemeria meche GO ETHIOPIA midir gebana….belelebet bewushet…be newuregnaw esat yasiworal enji…gondar endederesu menager kejemeru eko koyitewal…enam g0 malet kentu newuregna..amharan lemaschefichef balwalebet alehu yemil zelalemawi ye amhara telat new
ከላይ እስከ ታች ጽሑፉን አነበብኩት:: ፀሀፊው ለግንቦት 7 ካለው ጭፍን ጥላቻ በስተቀር ለአማራው አንድ ፍሬ ነገር አልቆጠረም:: ግንቦት 7 በማውገዝ አማራ ነፃነቱን አይቀናጅም:: ነፃነት በፀሎት ከሰማይ አይወርድም:: ለአማራ ህዝብ ቆሚያለሁ የምትል ከሆነ ጨርቄን ማቄን ሳትል በጎበዝ አለቃ የተደራጅትን ተቀላቀል:: አማራው ለነፃነቱ በአንድ ላይ ቆሞ በጋራ እንዲታገል አደራጅ:: አማራ እየታሰረ እየተገደለ እየተሰደደ ከነባር ይዞታው እየተፈናቀለ ያለው ከግንቦት ሰባት መመስረት 30 ቀድሞ በህወሓት የሽፍትነት ዘመን ነው:: አማራውን ከመጥፋት መታደግ ያለመቻላችን ን ለመሸፈን ግንቦት ሰባትን በምክንያትነት ማቅረቡ ሊቆም ይገባናል:: አማራውን ከመጥፋት መታደግ ባለመቻላችን አማራ ነን የምንል ሁሉ ተጠያቂዎች ነን::
ከላይ እስከ ታች ጽሑፉን አነበብኩት:: ፀሀፊው ለግንቦት 7 ካለው ጭፍን ጥላቻ በስተቀር ለአማራው አንድ ፍሬ ነገር አልቆጠረም:: ግንቦት 7ትን በማውገዝ አማራ ነፃነቱን አይቀናጅም:: ነፃነት በፀሎት ከሰማይ አይወርድም:: ለአማራ ህዝብ ቆሚያለሁ የምትል ከሆነ ጨርቄን ማቄን ሳትል በጎበዝ አለቃ የተደራጅትን ተቀላቀል:: አማራው ለነፃነቱ በአንድ ላይ ቆሞ በጋራ እንዲታገል አደራጅ:: አማራ እየታሰረ እየተገደለ እየተሰደደ ከነባር ይዞታው እየተፈናቀለ ያለው ከግንቦት ሰባት መመስረት 30 አመት ቀድሞ በህወሓት የሽፍትነት ዘመን ነው:: አማራውን ከመጥፋት መታደግ ያለመቻላችንን ለመሸፈን ግንቦት ሰባትን በምክንያትነት ማቅረቡ ሊቆም ይገባዋል:: አማራውን ከመጥፋት መታደግ ባለመቻላችንም አማራ ነን የምንል ሁሉ ተጠያቂዎች ነን::
Fighting against g7 will never bring freedom for the amharan people. The suffering of amhara people existed before g7 and it will continue after g7. From this article i can only understand that the writer accept the ethnic politic in ethiopia. Like aksum or lalibela is nothing for the welaytan, fasdiledes is also nothing for the gurage. So logicaly g7 should go out from amhara. The writer tell us Amhara belongs to Amhara….
Although i do not support the stratagy of g7 it is totally unacceptable to portrait g7 as enemy of amara.
በጣም የተዋጣለትና ጥሩ መልዕክት የይዘ ጽሁፍ ነው። እናመሰግናለን ወገናችን።
በነገራችን ላይ ከአንድ ከፍተኛ የግንቦት 7 አመራር እንደሰማሁት ግንቦት 7 ቁጥራቸው ከ70 እስከ 100 የሚሆኑ ካድሬዎችሁን አሰልጥኖ በፌስቡክ፣ በቲዊተርና በየፎረሙ እየዞሩ የአማራውን ወጣት እያደረገ ያለውን ትግል ለማስጠላት ከፍተኛ ስራ እየሰሩ እንደሆነ ላማወቅ ችያለሁ። እንም ይኸው ከፍተኛ የሆነ የንግንቦት 7 አባል ቁጥራቸው ከ70 እስከ 100 የሚሆኑ የግንቦት 7 ካድሬዎችን አስልጥነን ወደ ፌስቡክ ልንልክ ነው ሲለኝ እኔም እንደ አንደ አማራ ግንቦት 7 በአማራ ላይ ያለውን ጥላቻ ለመረዳት በመቻሌ በምችለው አቅም ሁሉ ይህንን ፀረ አማራ የሆነ ድርጅት ለመፋለም ቆርጨ እንድነሳ አድርጎኛል።
አቶ ግርማ በላይ፣ ግንቦት7 የሚባል ድርጅት የለም በእንቅስቃሴ ላይ ያለው “አርበኞች ግንቦት7 የነፃነት,የፍትህና የዲሞክራሲ ንቅናቄ”የሚባል ነው ሌላው በዚህ ጹሑፍህ ውስጥ አርበኞች ላለማት የፋለክው ክስድብህ ለማዳን ከሆነ ተሞኝተሀል እነሱ ዘንድ ዘረኝነት የለም።
ለአቶ አለማየሁ— ተራ ውሸታም ነህ! !!! አንተና መሰሎችህ ከያዛችሁ የውሸት ቫይረሰ የህክምና ያስፈልጋችኋል።
አቶ ግርማ በላይ፣
ጹህፍህን አንብቤ ስጭርስ ፍሬክርስኪ ሆኖ አገኘሁት ድከም ብሎህ፣ የእነ ተክሌ ይሻው ምድብ መሆንህን ያረጋግጥብሀል ስለዚህ የምጦቆምህ ነገር በሞረሽ ሬዲዮ ላይ ለደምስ ቃለመጠይቅ ሰጥና በመጨረሻ የሚያስተላልፉት መልእክት ካለ እድሉ ልስጦት ሲልህ”ኢሳት የሚባል ሬዲዮና ቴሌቬዥን አለ እኔ እንኳን ሰምቼውም አላውቅም ለሱ ማዋጣት አቁማችሁ ሞረሽ ሬዲዮን እርዱ”ብለህ እርፍ በለው።
Oh my God! From this article, the comments above, and other media opinions, one can conclude AG7 is in trouble. That makes me sick. “እውነቱን ለመናገር ከአመራሮቹ ብዙዎቹ እኮ ምንም የማይጎድላቸው ናቸው፡፡ በገንዘብም፣ በዕውቀትም፣ በዝናም ከነሱ አልፎ ለሌላም የሚበቃ ትሩፋት አላቸው – ለምሣሌ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ምን ጎደለበት? እንዲህ መከራ እያዩ፣ በሰው አፍ እየተቦጨቁ ሆዳቸውን በእንጀራ ሊሞሉ የሚሹ የግንቦት ሰባት አባላት ሊኖሩ ይችላሉ ተብሎ ቢገመት እንኳን ቁጥራቸው እዚህ(ም ሆነ እዚያ) ግባ የማይባል አነስተኛ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ እናም በዚህ ልጠረጥራቸው አልፈልግም፡፡ የሆነ ነገር ዞሮባቸው ወይም የሆነ ፈተና ውስጥ ገብተው በ“ካፈርኩ አይመልሰኝ” ዓላማቸውን እንደሳቱ ቢነገር ይበልጥ ያሳምነኛል፡፡ አንዳንዴ አንዳንድ ነገር ትጀምርና አንዳንድ የማይሆን ቅርቃር ውስጥ ትገባለህ፤ አይፍረድ ነው፡፡ “እነዚህ ሰዎች የኛ ናቸው…”
I think the above statements represent to express the concern and feeling of many AG7 devoted supporters. I urge AG 7 leadership to address this issue of mistrusts before it is too late.
In many instances I have tried to point out that AG7 and ESAT are heading towards the cliff. I commented that I did not like Efrem Madebo”s interview content regarding the Amhara issues. I noticed his rhetoric sounded like that between MEISON and EPRP cadres way back in the 70s. He said, “tiqit enqifatoch”. I also heard Prof Birhan, in one of his video speeches, saying ” tiqit amekelawoch”, obviously referring to the budding Amhara organizations. I feel we are going back to square one and repeat the dirty and nihilistic history of that generation whose ghost is still haunting us through the remnants, TPLF and EPLF.
Some serious questions deserve answers and clarifications by AG7 if it wants to flourish as popular as it has been:
1. What is the secret behind AG 7’s reluctance to recognize
the sufferings of the Amharas, as it does note that
of the Oromos and other “gossas”?
2. Why are ESAT and AG7 leadership fiercely fighting against
and undermining the attempt of Amhras to organize themselves
for self defense?
3. How does AG7’s political narrative, “Equality, justice
and democracy for all Ethiopians, based on citizenship only”
work without the inclusion of the Amharas?
4. Wide spread rumors have it that Prof Birhanu said,
“woyanen tiye Amaran lemanges aydelem Eritrea chaka yegebahut”.
Did he say that? If so in what context?
5. AG7 has gone a great length to approach and talk to people
like Lencho Leta, a man with deep and bitter hatred against
Amharas and Ethiopiawinet, and bring them to form ENM. Why not to
Moresh and/or other coming up Amhara organizations?
6. Why doesn’t AG7 give Zemene Kasse a chance to appear on skype and
say about his condition, instead of shunning the issue by saying,
“what is special about him” (Abebe Bogale)?
7. How do Moresh Wogene and other Amhara organizations,
including those with extreme views, become obstacles to the
struggle that AG7 wages on TPLF?
I believe that AG7 has to come out in earnest disposition and give explanations to the above questions. AG7 and ESAT have been the first borne beloved children of diaspora Ethiopians, and the hope of millions at home. The leaders have the respect of the people, but they need to shape and adjust their management in accordance with what situations demand for the betterment of the two complementary organizations. I guess the only issue you dare not tell us is how much pressure, and to what end Isayas Afeworki puts on you.
ግንቦት 7-ትን ጨምሮ ሕብረ-ብሔራዊ ድርጅቶችና ደጋፊ የሆናችሁ ሰዎች ትንሽ የግንዛቤ ችግር ያለባችሁ ይመስለኛል። የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ጎሳዎች ወይም ብሔር ብሔረሰብ ሲባል እኮ የአማራውን ህዝብ ጨምሮ መሆኑን ትዘነጉታላችሁ መሰለኝ። ያውም ለዚህች ሃገር ነጻነት ደሙን አፍሶ አጥንቱን ከስክሶ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን ነጻነቷን ያስጠበቀውን ህዝብ። የአማራው ህዝብ በጽንፈኞች ቢገደልም ሆነ ቢፈናቀል፣ ቢዘረፍም ሆነ ዘሩ ቢመክን ምንም ያህል ተቆርቁራችሁ ድምጻችሁን አታሰሙም። እንኳን ደግ አደረጋቸውም ብላችሁ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም። የእናንተ ፍላጎት የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው ዓይነት ስለሆነ የሃገር ፍቅር ከሚያቃጥለውም ሆነ ከፀረ-አማራና ከፀረ – ኢትዮጵያ ቡድኖች ጋር ህብረት ፈጥራችሁ በባሌም በቦሌም አተራምሳችሁ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ማስቀጠል ላይ ነው ትኩረት ያደረጋችሁት።
ግንቦት 7-ቶችን ግምት ውስጥ ከከተታችሁ ነገሮች ውስጥ አንድልና አሳዛኙ ነገር ጽንፈኛ ድርጅቶች በጠራራ ፀሃይ በአማራ ህዝብ ላይ በዘመቻ ወንጀል መፈጸማቸውን እያወቃችሁ አለማውገዛችሁ ብቻ ሳይሆን፣ እነዚህ የንጹሃን ዜጎች ደም በእጃቸው ካለባቸው ሰዎች ወይም ድርጅቶች ጋር ህዝብን ይቅርታ ሳይጠይቁ የጋራ ህብረት መፍጠራችሁ ነው። ጽንፈኞቹ ይቅርታ አለመጠየቃቸው በድርጊታቸው አለመጸጸታቸውን ከማመላከቱም በተጨማሪ ወደፊት ዳግም በአማራው ህዝብ ላይ ተመሳሳይ ወንጀል ላለመፈጸማቸው እርግጠኛ መሆን አይቻልም።
እንደ ኦነግ ዓይነት ፀረ አማራ ድርጅቶች ጋር ህብረት የምትፈጥሩት እውነቱ ጠፍቷችሁ ሳይሆን እንዳያኮርፉ ለማባበል መሆኑ ግልጽ ነው። የእውነት መንገድ ቀጥተኛ ናት እንጂ በመሽመድመድ እንደማትገኝ እወቁ። እነሱም ቢሆኑ የፈጸሙትን ወንጀል እና የተናገሩትን ውሸት ያውቃሉና ይታዘቧችኋል።
በተረፈ ለአማራ ክብር ስጡ። በአማራው ህዝብ (ጎሳ) ላይ የተፈጸመውን ወንጀል ወደ ጎን በመተው፣ በአማራው በደል ላይ በመደራደር (compromise በማድረግ) ከነኦነግና ከሌሎች ልባቸው በፀረ-አማራና በፀረ – ኢትዮጵያ ከተመረዘ ድርጅቶች ጋር የፈጠራችሁት ህብረት ሰዎቹ ነገ ሸርተት ሲሉ እንደ እንቧይ ካብ መናዱ አይቀርም፣ እናንተ እንዳሰባችሁትም ዘላቂ ሰላምና የኢትዮጵያን አንድነት አያመጣምና ካሁኑ ብታስቡበት ጥሩ ይመስለኛል። —-//—-
Le ethiopyawi keber tesete malet le amarawem endihum lehulum mirt kiber keber tesete malet new. Aleqe de qeqe!!!!
Hi,i Samma from Nashville, how are you people down there in the Elvis city. My thoughts go to the king when I see Nashville. I guess it was there the legend started his carried.
Samma, you response was very interesting. it shows your concern for your people and country. you have raised some questions as you ut down bellow.
Me am just ordinary Ethiopian, representing nobody. I ve nothing to do with AG7. except that I am a sympathizer so my answers are solely mine, as your questions are hopefully yours…..
—————- here we go!
Some serious questions deserve answers and clarifications by AG7 if it wants to flourish as popular as it has been:
1. What is the secret behind AG 7’s reluctance to recognize
the sufferings of the Amharas, as it does note that
of the Oromos and other “gossas”?
I am not sure if AG 7, would pay attention to such media medium, nor do I believe that they would respond to individuals on such forum. What they use to do is, as you certainly know, Call a public gathering and answer questions.
I believe your question has been asked before and dealt with properly. AG 7 leaders response to your questions, as far as I recollect, was as follows. AG 7 believes that all the people of Ethiopia are victims of the Woyenne repression. This being said, its also acknowledges that The Amara people had been solely singled out and mistreated harshly. Hate propaganda against Amara had been spread through out the country and has resulted to mass deportation, and death. Fertile Amhara land has been annexed by the Woyanne and given to Tigreans. All these injustice will end only if the regime is removed. Liberating only the Amhara kilil, which is impossible under the existing reality, can not achieve this goal.
2. Why are ESAT and AG7 leadership fiercely fighting against
and undermining the attempt of Amhras to organize themselves
for self defense?
This one is false allegation. No where have I heard Esat and AG 7 undermining Amhara Organizations. What I rather observe is some people who may or may not be Amharas doing exactly the same thing the other way round.
3. How does AG7’s political narrative, “Equality, justice
and democracy for all Ethiopians, based on citizenship only”
work without the inclusion of the Amharas?
it’s simple. What you need to be is an Ethiopian citizen. But you still retain your Amaranet, which is your culturally identity. you can also organize as an Amhara to defend yourself as any other ethnic organization, like the OLF or TPLF. The problem arises when you cross AG 7 road, the road to eradicate Woyanne from the face of earth.
4. Wide spread rumors have it that Prof Birhanu said,
“woyanen tiye Amaran lemanges aydelem Eritrea chaka yegebahut”.
Did he say that? If so in what context?
Rumors are rumors, just dont give much attention to them. I have geard worse rumours. He might have said like “የትግሬ ዘረኞችን አውርጄ፥ የአማራን ለማንገስ አይደለም ጫካ የገባሁት “። Look once Malcolm X said, ” if I say I don’t believe Marry was a Virgin.” NEXT day my enemies would say “Malcolm x disvirgined Marry.”
5. AG7 has gone a great length to approach and talk to people
like Lencho Leta, a man with deep and bitter hatred against
Amharas and Ethiopiawinet, and bring them to form ENM. Why not to
Moresh and/or other coming up Amhara organizations?
My information on this issue is that Moresh had been contacted. I believe the Moresh leadership has reservation to join in a coalition with the Lenchos, who are still regarded as accountable to the Arbagugu Massacre. For any Amhara organization this remains to be a very difficult challenge to overcome. You can’t just jump over your peoples dead body and continue business as usual. Here the Woyanne has succeeded by putting a barrier between the two huge population. I believe the Amharas have to bypass this predicament some how and join the united force, for the current enemy is far greater a danger to ignore. Woyanne is determined to wipe out the two people by all means. Woyanne might not kill all physically , but in the long run, it can put them in inferior position in almost every aspect of life, education, health, wealth even in physic and psych.
6. Why doesn’t AG7 give Zemene Kasse a chance to appear on skype and
say about his condition, instead of shunning the issue by saying,
“what is special about him” (Abebe Bogale)?
Abebe Bogale’s answer was wise, adiquate and proper. He gave you his words , that’s all. It has to end there. As a matter of fact, People should not ask about personalities in the front line duty. In such places reigns military rule. A fighter can be punished , banished or even executed for a serious misbehavior, like treason etc.
7. How do Moresh Wogene and other Amhara organizations,
including those with extreme views, become obstacles to the
struggle that AG7 wages on TPLF?
Good question! It’s very is important.
Hopefully those organization won’t become obstacles to the struggle that AG 7 wage. Nevertheless I have observed few campaigning for the closure of ESAT, others name calling Dr. Birhanu, and defaming AG 7, further more, some, probably Woyanne paid agents, striving to spread lies about AG 7s achievements. others were even persuading people not to contribute to the freedom effort. such action can be quite annoying if not decisively hampering the progress to the final goal.
ግርማ በላይ
እጃችሁን ከአማራው ላይ አንሱ! –ለማለት እርስዎ ማን ነዎት ፥ መጀመሪያ
ቁምነገር የጻፉ መስሎኝ ዘፈንዎን አነበብኩት። መልዕክትዎ በግልጽና በድብቅ ወያኔን እትንኩብኝ ነው። ያን ለማለት ይህን ያህል ምን አደከማቸው ብዬ ነበር ግን ምናልባት በቃላት ብዛት ይሆን የሚከፈላቸው አልኩ። በኣንድ ቃል ስንት ነው፥ ግርምሽ? ስማችሁ ሲያምር . . . በላይ፥ አባይ፥ አንተነህ ወዘተ
ኦሮሞ መምስል ስትፈልጉ ደግሞ ጉርማሳ፥ ቶሎሳ፣ ዳመሳ
ቅጫማም! አስተሳስባችሁን ማለቴ ነው! እንጂ እሱንማ ካራገፋችሁ ሩብ ሚሊኒየም አለፈ!
Oh, Girma!! First, thank you for giving attention to my queries. I also notice you are a concerned Ethiopian. However, from the way you tackled some of my questions, especially question one and six, you seem to be more of an insider of AG7 rather than a sympathizer. Which ever way you go I don’t care. But your answer to the case on Zebene made my blood run cold. Are you telling me the Marxist politics of elimination of the 1960s still persists in AG7? If you and AG7 leadership are mean and merciless to this degree, then again AG7 is on a slippery slope.
In general, your point of views based on my questions have incited me to use my forefathers very relevant saying,”woten agegnehut kenemamseyaw”
The other thing about you is: You seem to be not from ordinary caliber. If I were you I wouldn’t quote Malcom X’s spit about Marry, however it may help strengthen your point. It is rude, low esteemed and insane example from a lunatic person like him.
Quote you Samma, “But your answer to the case on Zebene made my blood run cold. Are you telling me the Marxist politics of elimination of the 1960s still persists in AG7? If you and AG7 leadership are mean and merciless to this degree, then again AG7 is on a slippery slope.’
How can you jumped to such conclussion. I was simply giving you the picture of the enviroment in the field where armed stuggle is waged. Ahis carrier s I told you previously, I know nothing of the AF 7 rules and regulations. As a matter fact I do not know who Zemmene is, nor do I know where he is now. First time i heard his name was when ABEBE was asked about him. I am not an insider. What I know about AG 7 is based on information I gather from the cyber world.
You have reacted like the people Malcom X mentioned, adding untold stories of your own, on the told told ones. Not good.
By the way, elvis started his carrier not in nashville but in Menphis….
have it nice..