April 5, 2017
4 mins read

ሦስት የሰማያዊ ፓርቲ የአማራ ክልል አመራሮች ታሰሩ

የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን የማሳደዱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)
የሰማያዊ ፓርቲ የአማራ ክልል አመራሮችን እያሳደዱ ማሰሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል።በአሳለፍነው ሳምንት ብቻ ሦሥት አመራሮች
*አቶ አዳነ አለሙ የወንበርማ ወረዳ የፓርቲው ሰብሣቢና የ2007 ዓ.ም ምርጫ የክልል ም/ቤት ተወዳዳሪ
*አቶ አዱኛ ካሳው የም/ጎጃም ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ አባል
*አቶ ይስማው ዳኘው የእሥቴ ወረዳ የፓርቲው ሰብሳቢና የ2009 ዓ.ም ምርጫ የህ/ተ/ም/ቤት ተወዳዳሪ በማዕከላዊ ታሥረዋል።

1.አዱኛ ካሳው፡­ተወልዶ ያደገው ደቡብ ጎንደር አስቴ ሲሆን ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ይህንን አስከፊ ስርዓት ለመለወጥ በቆራጥነት ታገሏል፡፡
በተደጋጋሚ ጊዜ ታስሯል፣ተደብደቧል እንዲሁም ከስራው ተፈነቅሏል፡፡በ2002 ዓ.ም የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)ን ወክሎ
በእስቴ ወረዳ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተወዳዳሪ የነበረ ሲሆን ምርጫ ቦርድ የመኢአድን አመራርነት ቦታ ለህገ ወጦች ሲሰጥ በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ መታገሉን ቀጠለ፡፡ይህ አይበገሬነትና ቆራጥነት ያሳሰበው ኢህአዴግ ይኖርበት ከነበረው ባህር ዳር ከተማ አፍኖ በማምጣት በማዕከላዊ ለእስር ዳርጎታል፡፡
2.አዳነ አለሙ፡­ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ3 ጊዜ በላይ ታሰሯል፡፡በ2008 ዓ.ም ህዳር ወር ላይ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሽብር ክስ ተመስርቶበት ከ7 ወራት በላይ በግፍ እስር ላይ ቆይቶ ምንም ማስረጃ ስላልተገኘበት በነፃ ተሰናበተ፡፡በነሐሴ ወር 2008 ዓ.ም በክልሉ ተከስቶ የነበረውን የህዝብ ተቃውሞ ተከትሎ በምዕ/ጎጃም ዞን በወንበርማ ወረዳ ሽንዲ ከተማ ተቃውሞውን አስተባብረሃል በሚል ታስሮ ህዝቡ ፖሊስ ጣቢያ ድረስ በመሄድ ሊያስፈታው ችሏል፡፡ይህንን ሲቃይና መከራ ተቋቁሞ ለህዝብ ነፃነት የሚታገለው አዳነ ለስራ ጉዳይ ከሚኖርበት አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ በመሄዱ አምጡት በሚል ባለቤቱ አና መነኩሴ እናቱ ለእስር ተዳርገዋል፡፡በመጨረሻም ከስራ ቦታው ይዘው በማዕከላዊ አስረውታል፡፡
3.ይስማው ወንድሙ፡በደቡብ ጎንደር ዞን አስቴ ወረዳ የሰማያዊ ፓርቲ የወረዳው ሰብሳቢ ነው፡፡ በ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ለክልል ምክር ቤት ተወዳዳሪ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በማዕከላዊ በግፍ እስር ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ ሰላማዊ ታጋዮች ከተያዙ ጀምሮ በቤተሰቦቻቸውና በጠበቃ እዳይጎበኙ የተከለከሉ ሲሆን ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸውና ጨለማ ቤት ታስረው
እንደሚገኙ የማዕከላዊ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

1 Comment

  1. Overweight Ethiopian swimmer nicknamed ‘Robel the Whale’ makes dramatic U-turn setting up the ‘Robel the Whale Foundation’ to collect money donation from interested Ethiopians and other nationalities to help the ‘Robel the Whale Foundation’ vowing to compete at Tokyo Olympics not as a whale but as a human being.

    Robel Habte, 24, was body-shamed after he appeared at the Rio Olympics sporting an unathletic paunch
    He was the target of much online criticism and dubbed ‘Robel the Whale’
    After his lackluster performance, he famously retired from the pools
    But now Habte has made a U-turn, vowing to better his performance and return for the Tokyo Games
    He also set up the ‘Robel the Whale Foundation’

    http://www.robelthewhalefoundation.com/

Comments are closed.

Previous Story

My entrance exam was on a book of matches

Next Story

ሆነና ነገሩ የተገላቢጦሽ ፣ አህያ ወደ ቤት ውሻ ወደ ግጦሽ | ይገረም አለሙ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop