December 26, 2016
2 mins read

አዲስ አበባ በ24 ሰዓታት ውስጥ 3 የእሳት ቃጠሎዎችን አስተናገደች

ዘርይሁን ሹመቴ

አዲስ አበባ ከወትሮ ለየት ባለ ሁኔታ በሶስት (3) በተለያዩ ስፍራዎች 24ሰአት በልሞላ ሰአት ውስጥ አስተናግዳለች። የእሳት አደጋው በንብረት ላይ ከፍተኛ ጎዳት አድርሷል። ከመረጃዎች መረዳት እንደሚቻለው በአብዛኛው የንግድ ሱቆች በእሳት አደጋው ወድመዋል።

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለስልጣን የኮምንኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ እንደገለጹት አደጋው የተከሰተው በዋናው ፖስታ ቤት በአራዳና በጉለሊ ክፍለ ከተማ እንደሆነ መረዳት ተችሏል።

የዋናው ፖስታ ቤት ንብረት የሆኑት አራት (4) ሱቆች በእሳት በመንደዳቸው በግምት ከ500 ሺህ ብር በላይ ንብረት ጠፍቷል። ይህም በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከሌሊቱ 8 ሰአት እንደሆነ ከኮምንኬሽኑ ገለጻ መረዳት ተችሏል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ አከባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ ስምንት (8) መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለው ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከመድሃኒአለም ቤተክርስትያን አጥር ጥግ የሚገኙ ሁለት (2) የንግድ ሱቆች ላይ በደረሰው ቃጠሎም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰ ታውቋል።

በአጠቃላይ በ24 ሰአታት ውስጥ በመዲናችን ሶስት (3) የተለያዩ ቦታዎች በተከሰቱት የእሳት አደጋዎች በግምት ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሞል። በህይወት ላይ የደረሰ አደጋ እንዳልተከሰተ አቶ ንጋቱ ሞሞ ገልጸዋል። የኮምንኬሽን ባለሙያው ህዝቡ የእሳት አደጋ መንስኤ የሚሆኑ ነገሮችን መጠንቀቅ እንዳለበትም አሳስበዋል።

Previous Story

ለኦርቶዶክስ ስኖዶስ

70494
Next Story

“ከወያኔ ጋር ወግነው አማራውን የገደሉትን ለፍርድ እናቀርባለን” – የሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት መግለጫ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop