የጥንታዌት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አጭር ታሪክና ሥርዓት -bታሪኩ ዉነህ ጌታነህ

 

ክፍል ሶወስት

ክርስትና እንዴት ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ

ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ የመጣው በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው። እንዴት እንደመጣም የተጻፉ መጻሕፍት በጣም ብዙ ናቸው። አንባቢ ይህንን ታሪክ በትኩረት መመልከት አለበት፤ ታሪኩ የሚመለከተው  በኢትዮጵያ የተዋህዶ እምነት ተከታዮች ብቻ ሳይሆን  በዓለም ላይ ያሉ አፍርቃዉያንን በሙሉ ይሆናል። በመጀመሪያ በኢትዮጵያዉያን ታሪክ ጸሐፊዎች የተጻፈዉን አስፈላጊዉን ትኩረት ሰጥቶ መመልከት አስፈላጊ ነው። ሶወስት መምሕራን በሶወስት  በተከፈለ ክፍለ ዘመናት የነበረዉን የኢትዮጵያን ታሪክ ጽፈዋል። ፕሮፌሰር ስርጉ ሐብለ ሥላሴ “የጥንታዌት ኢትዮጵያ ታሪክ አስከ 1270” ያለዉን         [ Ancient and Medieval Ethiopian History to 1270, Addis Ababa : Haile Sellassie I University Press, 1972] ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት  “ቤተ ክርስቲያንና የአገር አገዛዝ እስከ 1527” በቤተ ክርስቲያኑና በአገዛዝ የነበረዉን ግንኙነት [Church and State in Ethiopia; London: Oxford University Press, 1972] ፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴ “የኢትዮጵያ ዘመናዌ ታሪክ ከ1855 አሰከ 1974” [A History of Modern Ethiopia: 1855-1974]. እነዚህ መምሕራን የጻፉት ታሪክ እጅግ ጠቃሚ ነው፤ በተቻላቸው አቅም አሉ ከተባሉት አገር ቅርስ ጋር እያመሳከሩ በጽሑፍና በቃል ከትውልድ ወትውልድ የተላለፈዉን ታሪክ አባሪ በማድረግ ጽፈዋል፤ ይህም ሆኖ በአስተማሪዎቻቸውና ጽሑፋቸው በመጽሐፍ እንዴወጣ የሚፈቅደው አካል ገደብ ስለአስቀመጠባቸው ሙሉ በሙሉ በነፃነት ሆነው ሊጽፉ አልቻሉም። እንግዲህ ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ በተረጋጋ መንፈስ መወያየቱ ብዙ እማናቃቸዉን ነገሮች እንድናውቅ ይረዳናል። ከአለማወቅ ማወቅ ይሻላል፤ አውቆ ደግሞ ለማያውቀው ወገን ማሳወቅ ለግለሰቡም ለሕበረተሰቡም እድገት ነው።

ታሪክ በሥነ ልቦና ተጸንሶ በአይን ሳይታይና በእጅ ሳይዳሰስ የሚጻፍና የሚነገር ወሬ አይደለም፤ ሁኔታዎች በተመቻቹ ግዜ የሚፈጠር ሕዝበ ትዕይንት ነው። ታሪክ እንደዚሁ በራሱ ሃይል የሚፈጠር ትዕይንት አይደለም። ፈጣሪ ሃይል ያስፈልገዋል፤ ያ ሃይል የተባለው ደግሞ “ሁኔታ” የሚፈጥረው ነው፤ “ሁኔታን” የሚፈጥር ደግሞ ሰው ነው፤ አንድ ሰው ከላይ እታች ብሎ “ሁኔታን” ያመቻቻል፤ እነዚህ ንጥረ ነገሮች ከተመቻቹ በኋላ የታሪኩ ሂደት ይጀምራል፤ ከተጀመረ በኋላ ግን ለማስቆም አይቻልም፤ ታሪካዌ ሂደቱን ይፈጽማል። እዚህ ላይ ውይይታችን እንዲዳብር በተባለው ንጥረ ነገር ላይ በተመሳሳይ “ሁኒታ” የተፈጠረ ታሪክ በምሳሌነት እንደመረጃ መቅረብ አለበት፤ ታሪክ በሂደት እያለ እንደታሪክ ሊቀርብ አይችልም፤ ከላይ እንደተጠቀሰው ሂደቱን መፈጸም አለበት፤ ነገር ግን እዚህ ላይ ሊጠቀስ የተፈለገው ምሳሌ ታሪካዌ ሂደቱን ስለፈጸመ ታሪክ ሆኗል፤ የአድዋ ጦርነት በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ አራተኛ ትውልድን [120 ዓመት] ይጨርሳል፤ የአውሮፓውያን ሃይል የአፍሪቃን አህጉር በቅኝ ስር ለማዋል ያመቻቹት ፡”ሁኔታ” አፍሪቃዌያንን በጎሳ በመከፋፈል ነበር፤ ነገር ግን ታላቁ መሪ ዳግማዌ ምኒልክ እና ጅግነዋ ጣይቱ በቆራጥነት ከታላቁ ሕዝባቸው ጋር በመቆም ያ ሊፈጥር ያሰበው “ሁኔታ” ሳይመቻች ስለቀረ ኢትዮጵያ በድል አድራጊነት አንድነቷን ጠብቃለች፤ ነገር ግን የከፋፍለህ ግዛው “ሁኔታ” በአገራችን ዉስጥ ስር ሰዶ ቀስ በቀስ ከሶወስት ትውልድ በኋላ አገርቱን እንዲት እንደከፋፈላት በትኩረት እንመልከት። ወሬ እንደታሪክ ተወርቶ እንዴት ታሪክ ሊሆን እንደቻለ እንመልከት፤ ኢትዮጵያ የምትባል አገር የተፈጠረችው በምኒልክ የዛሬ መቶ ዓመት ነው፤ ከዜያ በፌት የተለያዩ ብሔሮች በነፃነት ይኖሩባት የነበረች አገር ነበረች፤ አሁን ግን በአንድ ብሒር  በላይነት የምትገዛ የቅኝ ግዛት ሆናለች በማለት ለተደረገው በደል ሁሉ አንድን ብሒር በመክሰስ  እና ተጠያቂ በማድረግ ይህ ነው ሊባል የማይችል የሰው ልጅ እልቂት የተፈጸመበት አገር ሆናለች፤ እዚህ ላይ ትንሽ ግዜ ወስደን ይህ “ሁኔታ” እንዴት እንደተፈጠረ ማወቅ አስፈላጊ ነው፤ የዚህ “ሁኔታ” ፈጣሪዎች የዉጭ አገር ቅኝ ገዝዎችም ቢሆኑም ሁኔታው በስራ ላይ ዉሎ ፍጻሜ እንዴያገኝ ያደረጉ እገር ዉስጥ በተውለዱ ግለሰቦች መሆኑን ማወቅ ለተፈጠረው “ሁኔታ” መፍትሔ ሌያመጣ ስለሜችል ነው። አንድ ብሔርን ሌሎችን ብሔረሰቦችን ጨቋኝ ነው ማለት የዜያን ብሔረሰብ ዘር ማጥፋት መነሻ ምክናያት ነው፤ አፈወርቅ ኢሳእያስ እና መለስ ዜና የረጩት የዘር ማጥፋት መርዝ ነው፤ ይህንን ተመልከት፤  ካድሬ ታምራት ላይኔ እና ጓዶቹ አማራ ክልል ዉስጥ ገብተው ገበሬዉንና ቤተሰቡን በሙሉ ሕፃን ልጆች ሳይቀሩ እቤታቸው ላይ እሳት አንድደው በመትረየስ ሴያስደበድብ፤ ኢሰያስ አፈወርቅ በካድሬዎቹ አማራዎችን ከነ ነፈሳቸው በገደል ላይ ሴያስወረዉር፤ መለስ ዜና ወጣት ተማሬዎችን ጉጓድ አስቆፍሮ በጥይት ሴያስደበድብ፤ የወንቤዴው መንግሥት አራሷን እናት ከነሕፃኑ በቡል ዶዘር እቤቷ ውስጥ  እንዳለች ሴጨልቅ፤ የኦሮሞ ወጣቶች የአባትና የእናትችንን መሬት አትነጥቁም ስለአሉ በጅምላ በጥይት ሴደበደቡ ፤ የወጣቱ ኦሮሞ እናት በአጋዜ ጥይት ተደብድቦ በሞተው ልጇ ላይ ቁጭ እንድትል ስትገገደድ፤ የጋምቤላ ሕዝብ መሬቱን ተነጥቆና ተገድሎ ለዉጭ አገር ሃብታሞች በጅምላ ሴሽጥ ምክናያት የሆነው በዉነት ላይ ያልተመሰረተ ወሬ እንደታሪክ ተጽፎ መንግሥት  ለዴሞክራሴና ለልማት የቆመ ነው እየተባለ ነው፤ ድርጌቱንም የፈጸሙ ግለሰቦች በወሬ ተጠምደው ታላቅ ታሪክ የሰሩ መስሎአቸው ነው። እውነት አንድ ናት፤ ወሬ ግን ብዙ ነው፤ ቢያወሩት አያልቅም፤ አሁንም በወሬ የሚነዱ ብዙ ናቸው።  ለውይይታችን መዳበር እና ለም ናቀርበው መረጃ ሜዛናዌ አስተያየት እንዴነሮን የአገራችንን ታሪክ በምን ምክናያት በወሬ እንደተሳሰረ ማወቅ እውነተኛ ታሪኩንና ወሬዉን ለይተን ለማወቅ ይረዳናልል

እዜሁ አርዕስት ላይ እንዳለን አንባቢ መጠየቅ ያለበት ጥያቄ እንዴት ወሬ እንደታሪክ ሊነገር ቻለ? ብሎ ነው፤ አገራችን ከጥንት ጀምሮ የሚነገረው ታሪክ ወሬን ተደግፎ ነው፤ የዚህም ወሬ መዋቅር በሶወስት ክፍል ይከፈላል፤ ነጋሽ [የወሬው ምንጭ]፤ አንጋሽ [የወሬው አቀባባይ]፤ አወዳሽ [ ስለወሬው ትክክለኛነት የሚሰብክ]፤ እንግዴህ አንባቢ በአንክሮ ጠንክሮ ማወቅ ያለበት “አንጋሽ፤ ነጋሽ፤ አወዳሽ” እንዴት ተወሳስበው እንደተሳሰሩ ነው፤ ሰዎስቱም አንድ አካል ሆነው ስለተዋሃዱ መለየት አይቻልም፤ አገራችን ዉስጥ እውነት እና እውነት ያልሆነዉን  ነገር ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሬ ነው። ሂደቱን ደግሞ ተመልከት፤ ነጋሽ ስለራሱ ታላቅነት ሴያወራ ፤ አንጋሽ ደግሞ እንደፈረስ እና በቅሎ አፉን ተሽብቦ ዓይኑን ግራና ቀኙን እንዳያይ ታስሮ ነጋሹን ተሸክሞ ሲጋልብ ፤ ካህናቱ መቋሙያንና ጽናጽኑን ከበሮዉን ይዞ ሲጨፍር፤ የመንግሥቱንም የባላይነት የሚቃወመውን  ክርስቶስ ወንቤዴዎችን ከቤተክርስቲያኑ ገርፎ እንዳሶጣቸው እኔም እየገረፉክ አሶጣለህ እያለ ሴጮህ ዉዳሴው የሚቀጥለው በከረቦ በጭብጨባ በዕልልታና በጭፈራ ነው። ትልቅ ችግር ያለብን ሕብረተሰቦች ነን፤ ይህንን ችግር ለመፍታት ደግሞ ብዙ ዕዉቀትን አይጠይቅም፤ ነገር ግን ችግራችንን ስለማናውቅ ወይም ማወቅ ስለማንፈልግ ልንፈታው ፈጽሞ አልቻልንም፤ በአጭሩ ችግር እያለብን ችግራችንን ለማወቅ የማንፈልግ ሞጎደኞች ስለሆንን ከችግር የተለየንበት ዘመን ኖሮ አያውቅም፤ በእንደዜህ አይነት “ሁኔታ” ለዘላለም መኖር ይቻላል? እንዴት ሊዘለቅ ነው? በዚህ “ሁኔታ” መኖር ይሸለቻል፤ ይመራል፤ ከመኖር ወደ አለመኖር ይመረጣል፤ ታዳጊ ሕጻናት ለምን ተወለድን ይላሉ። ክፉ ትውልድ በቢልጥ የከፋዉን ትውልድ ይወልዳል፤ ታሪካዌ ሄደቱም ከክፉ ዘመን ወደ ከፋው ዘመን ይሆናል፤ ለዚህም አይነት ሄደት ፍጻሜ የለዉም፤ በተረጋጋ መንፈስ ሆነን  በመወያየትችግራችንን መፈታት አይሻለንም? ምርጫው የኛ ነው።

ስለ ታሪክ መነሻና መድረሻ ከመግባታችን በፌት ስለ አጻጻፉ ስነ ሥርዕትና ሕግ በአጭሩ ማቅረብ አስፈላጊ ነው፤ ታሪክ በተለምዶ የሚጻፍ አርዕስት አይደለም። ሁኔታ የሚፈጥረው ሕዝበ ትዕይንት ነው፤ በሄደት ላይ እያለ መነሻውም ሆነ መንደርደሪያው ወይም መድረሻው አይታውቅም። እንደ ማዕበል የሚወርድ ጎድፍ ነው፤ ቆሞ ከማየት በስተቀር የሚያቆመው ሃይል አይኖርም፤ ሂደቱ መድረሻው ነው። ከላይ የተጠቀሱቱን ሶወስት ኢትዮጵያዉያን ታሪክ ጸሐፊዎች  ብትመለከት የታሪክ አጻጻፍ ግድፈቱን ለመረዳት አያዳግትም፤ በመስቀልኛ ጥያቄ መጠየቅ ያለበት የኢትዮጵያ ታሪክ ከየት ው የሚጀምረው? መንደርድሪያው የት ነው? የትስ ደረሰ? የሚል ስለሆነ አጥጋቢ መልስ ያስፈልገዋል፤ ቀደም ስንል ታሪክ ጸሐፊዎቻችን ላይ የዉጭ ኃይል ገደብ ስለአደረጉባቸው በነፃነት ሆነው ስለአገራቸው ሊጺፉ አይችሉም ተብሏል፤ ይህም የሆነበት ምክናያት ታሪክ ሊጻፍ የሚቻለው ጸሐፊው “ታሪክ የሰው ልጅን ችግር የሚፈታ አንደኛው የሆነ የትምህርት ክፍል” መሆኑን አምኖ ሲቀበልና በተለያዩ ጥያቄዎች ለታሪኩ መነሻ የሆነውን “ሁኔታ” ሴመረምር ነው። ምርምሩም ግልጽ በሆነ ዘዴ የታሪኩን ሄደትና መድረሻ ማን ምን እንዳደረገ ድርጊቱ ያስከተለዉን ለውጥ በግልጽ ያሳያል። በገለፃ ግዜ መቅረብ ያለባቸው ትንታኔዎች ከዚህ የሚከተሉት መሆን አለበት፤ የሁኔታው መንስኢ በዝርዝር፤ “ሁኔታው” በቁጥጥር ስር መሆኑና ያለመሆኑን፤ በድርጊት ተጣናቆ የተለወጠ ለውጥ፤ አሉታዌ ለውጥ፤ አወንታዌ ለውጥ፤ ለውጡ ያመጣው ትርፍ ወይም ጥፋት፤ ሕብረሰቡ ስለለዉጡ ያለው ግንዛቤ፤ እነዚህ ሁሉ በአጠቃላይ ተቀነባብረው መቅረብ አለባቸው። በመጨረሻም “ሁኔታ” በፈጠረው “ታሪክ” ምን ዓይነት ትምህርት ተገኝ? ለሕብረተሰቡ ምን ዓይነት ግንዛቤ ሰጠ? ታሪክ የዚህ ሁሉ ዉጤት ስለሆነ ሕብረተሰቡ የሰራዉን ታሪክ ወደኋላ መለስ ብሎ የሚያይበት መስተዋት ነው፤ ቀደም ብሎ የነበረው ትውልድ የሰራዉን ስሕተት መልሶ አይሰራዉም። እንግዴህ አንባቢ ከላይ ከተጠቀሱት ታሪክ ጸሐፊዎች ምን እንደተማረ ምርምሩን ለሱ እተዋለሁ፤ ግን ለማስታወስ ያህል ወሬ “ታሪክ” አይሆንም፤ አውሮፓዉያን የራሳቸዉን “ታሪክ” ለማጋነን በተለይ “የጥቁርን ታሪክ” ለማሳነስ “ታሪኩን” በሁኔታ ሄደት መነሻዉን አውቆ መድረሻዉን ለማወቅ ሴሞክር እንዴያወቀው ተድርጎ በመላቢስነት ታግቶ እንዴቆም አድርጎቷል፤ ለዚህ ነው አንባቢ በትኩረት “ታሪክ” ነው ተብሎ የቀረበዉን መመርመር ያለብት።

እዚህ ላይ ቀንጠብ ተደርጎ መነገር ያለበት “የኢትዮጵያ ታሪክ” መቼ ነው የጀመረው? የሚለው ነው። በአጭሩ የዛሬ መቶ ዓመት አይደለም፤ መቶ ዓመት የሚሉ ባንዳዎችና የልጅ ልጆቻቸው ናቸው፤ ምኔልክ የዛሬ መቶ ሰላሳ ዓመት ትግሬን የኢጣልያን ቅኝ እንዳትሆን በድል አድራጊነት ነፃ አድርጓቷል፤ ኢርትራ የኢጣሊያን ቅኝ የሆነችው በአፂ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት ግዜ ነው። የአድዋ ጦርነት ትግራይን ነፃ ለማዉጣት ነው። የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃዉያን ድል ነው፤ ምኒልክ ጠብቶ ያደገበትን ጡት አልቆረጠም፤ የባንዳዎችና የልጅ ልጆቻቸው ወሬ ነው፤ እንግዴህ “ታሪክ” እንዴህ እያለ በጥራት የሚነገር ዝክረ ነገር እንጂ የተዘረከረከ መነሻና መድረሻ የሌለው የነበረው “ሁኔታ” የማይታወቅ በመላቢስነት ሳይሆን አይቀርም እየተባለ የሚጻፍ ትዕይንት አይደለም። አገራችን ወሬ በሰፊው የሚነገርባት የወረኛ አገር እንዳትሆን “ታሪክ” የሥነ ጽሑፉን አጻጻፍ ደንብ ተከትሎ መጻፍ ይኖርበታል። በአገራችን አባባል “ወሬ ቢበዛ ቋቱ ጠብ አይልም” እንደሚባለው የዘመኑ ትውልድ በወሬ ተደምጦ ቡና ቤት ቁጭ ብሎ ሴያወራ ነው የሚዉለው፤ ወሬዉም ተወርቶ ስለሚያልቅ እንደሚቀጥል ተስማምቶ ነው የሚለያየው። በአንፃሩ “ታሪክን” በአጻጻፉ ሥነ ስርዓት ተደግፎ በሚጻፍበት ሕብረተሰብ ዉስጥ ታላቅ ቦታ ተሰጥትቶት የሕብረተሰቡን ንቃተ ሕሊና እንዲሰጥ ይደረጋል፤ ለምሳሌ የአንድ አገር ፈላስፋ እንደጻፈው “አንድ ሕብረተሰብ ከአለፈው ስሕተት ከአልተማረ ሕብረተሳዌነቱ ሊቀጥል አይችልም  ሙታን ይሆናል“ ይላል። ወሬ እንደታሪክ ሆኖ የሚነገርበት አገር መነሻዉም መድረሻዉም ወሬ ስለሚሆን ትርፉ ወሬ ነው፤ ወሬ ያለዉን ችግር  ያባብሳል እንጄ አይፈታም። ይህ ለመግቢያ ያህል በቂ ስለሆነ ወደ ጥንታዌት ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ እናምራ።

 

ቤተ መቅደስ

ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት ቤተ መቅደስ ነበራት፤ እንግዲህ አስቀድመን ማወቅ የሚገባን ነገር ቤኖር የቤተ መቅደስን ትርጉም ነው፤ ቤተ መቅደስ ማለት የተባረክ ስፍራ፤ የማመልክያ ቤት ማለት ነው። በአፍሪቃ በዋናነት የሚታወቀው ግብፅ ዉስጥ  የሚገኝው ሎክሰር ቤተ መቅደስ ነው። በተለያዩ ዓለም ዉስጥ በዙ ቤተ መቅደስ ይገኛሉ፤ አገልግሎታቸውም ለተለያዩ እምነት ተከታዮች የማምለኬያ ቤት እንዲሆን ነው። የሎክሰር መቅደስ የተሰራው በምስራቅ በኩል በሜገኝው የአባይ ወንዝ አጠገብ ሎክሶር በሚባል ከተማ ነው፤ የተሰራዉም ክ3400 ዓመት በፊት ነው፤ ይኸዉም  ከክርስትና  በፊት 1400 ዓመተ ዓለም  መሆኑ ነው። የሎክሶር ቤተ መቅደስ እንደሌሎቹ የማምለኬያ ጣኦት መቀመጫ ሳይሆን የነገሥታቱ  የዘዉድ በዓል መናገሻ ሆኖ ለብዙ ዘመን አገልግሏል፤ በአገሬው ቋንቋ “አይ ፐት” ተብሎ ይጠራ እንደነበር በታሪክ ይነገርለታል፤ ከዚህ ሌላ ብዙ መቅደስ በሎክሰር አካባቢ ይገኛሉ፤ የነግሥት ሐትሺፑሰት መቅደስ በደር ኢል ባሕሬ፤ የዳግማዌና የሳልሳዌ ራመሰስ መቅደስ እንዲሁም በርከት ያሉ ጣኦት ማምለኬያ መቅደስ ይገኛሉ፤ በትልቅነቱ የታወቀው መቅደስ አቡ ሲምብል በተባለው የኑቤያን አገር ውስጥ ይገኛል። መቅደሱም የተሰራው በዳግምዌ ራመሰስ በ 1279 ዓመተ ዓለም መሆኑን ይነገርለታል፤ መቅደሱም ንጉሡ በዘመኑ የሚያመልከው ለፅሐይ አምላክ አሞር ረ ለተባለው ጣኦት እንደነበረ በታሪክ መዝገብ ተመዝግቧል። ከዚህ ሌላ ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የተያያዘ “የኦፔት በዓል” የሚባል ሶወስት ጣኦቶች የሚከበሩበት ዓመታዌ ንግሥ ነበር፤ ይህ በዓል ነገሥታቱ የሚያመልኩበት ጣኦቶች “አሙን” “ሙት” “ኮንሱ” ዓመታዌ በዓላቸው በሚከበርበት ግዜ ንጉሠ ነገሥቱ በመሳፍንቱና በቀሳዉስቱ ታጅቦ እነዚህን ጣኦቶች ጽላት በሚመስል ሳጥን ተከተው ወደ አባይ ወንዝ ለሶወስት ቀናት አዳር ይጓዛሉ፤ በጉዞአቸዉም ግዜ  በዜማ በከበሮ  በጽናጽን እየተዘመረ ወደወንዙ ይጓዛሉ፤ ይህ ትዕይንት ሎክሶር ዉስጥ በሚገኘው መቅደስ ዉስጥ እግድግዳው ላይ ተቀርጾ ይታያል። ከሶወስት ሼህ ዓመት በፊት የተቀረጸው ቅርጽ እስከአሁን ድረስ በመረጃነት ያለ ታሪክ ነው። በዚህም በሶወስት ቀናት አዳር ጸሎትና ምስጋና ይቀርባል፤ ምስጋናዉም አባይ ወንዝ ያመጣው ጥቁር አፈር ፍሬ እንዲያወጣ የተወለዱት ልጆች በጤና እንዲያድጉ አገራቸው በሰላምና በፍቅር እስከሚከትለው ዓመት ድረስ በደሕና እንዲደርስ ይጸልያሉ፤ በክበሮና በጽናጽን ታጅቦ ጣዕም ባለው መዝሙር ይዘመራል፤ በመቅደሳቸዉም ዉስጥ የተለያዩ መስዋዕትን ያቀርባሉ፤ ባሕላቸውና አምልኮታቸው የተሳሰረ ነው፤ የአገሩ መሪ የሚታየው እንደፈጣሪ ነው፤ አምላክ ስለሆነ ለሥልጣኑ ገደብ የለዉም፤ ከሱ በላይ ምንም ነገር የለም። ይህ ከተባለ በኋላ ስለ ኢትዮጵያ መቅደስ በአጭሩ እንወያያለን።

 

የኢትዮጵያ መቅደስ ከግብፅ ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ማለትም ሎክሶር ግድግዳ ላይ የተቀረጹት የቆሳቁስ መሰሪያዎች አንድ አይነት ናቸው፤ ጽናጽኑ፤ ከበሮው፤ ጽላቱና በአጠቃላይ ሥነ ስርዓቱ ተመሳሳይ ሳይሆን አንድ ነው። ይህ የሚያሳየው የአጋጣሜን ሁኔታ ሳይሆን የታሪክ ግንኙነትን ነው። ጥያቄው ግን እንዴት እውነተኛ “ታሪክ” ታሪክ ሳይሆን ቀረ? በዚህ አይነት ብዙ ታሪክ እንደታሪክ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ታሪካችንን እንዳናውቅ የተደረገብን እገታ ታላቅ ስለሆነ ዛሬ ኢትዮጵያ የምትባል አገር የተፈጠረችው ትላንት በምንልክ ዘመን ነው እያልን የምናወራ ወሬኞች ሆነን ቀርተናል። እንግዲህ አንባቢ በተረጋጋ መንፈስ ማጥናት ያለበት ከላይ የተጠቀሱት ኢትዮጵያዉያን ታሪክ ጸሐፊዎች ይህንን በመረጃ የተደገፈ ታሪክ ትተው ባሕር ማዶ ተሻግረው ታሪክ የሊለበት አገር  የኢትዮጵያን ታሪክ ሲፈልጉ ማየቱን ከተረዳ ሊላውን በቀላሉ ማየት ይችላል፤ በተጨማሪ አንባቢ የአገሩን ታሪክ በምን አይነት “ሁኔታ” እንደተጻፈ መመርመር ነው። አንባቤ ለዚህ የሚያበቃ ዕውቀት እንዲኖረው ያስፈልጋል፤ ይኸውም ለታሪኩ መነሻ የሆነዉን “ሁኔታ” በዝርዝር ማወቅ ነው፤ ለታሪኩ መንስኢ የሆነዉን “ሁኔታ”፤ በግዜው የነበረዉን ሕብረተሰብ ሕሊናዉነቱን፤ ንቃቱን፤ አስተሳሰቡን፤ ችግሩን፤ ፍትሕ መኖሩንና ያለመኖሩን፤ የፖለቲካ ሥራዓቱን፤ የኢኮነሚዉን እድገት፤ ጢንነቱንና ሰላሙን፤ ሃይማኖቱን፤ ከጎረቤት አገሮች ላይ ያለዉን ግንኙነት፤ በአጠቃላይ በአንድ ግለሰብ ላይ ያለው የሰዉነት መብት ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ማወቅ አስፈላጊ ነው፤ የአጠቃላይ ሕብረተሰብ መበት ሊረጋገጥ የሚችለው የግለሰቡ መብት ሲጠበቅ ብቻ ነው። በቅድሚያ ግን አስተዳደር በሕግ ስር መሆኑን ማረጋገጥ የታሪካዌ ሄደቱን  አቅጣጫ ያመልክታል።

የታሪክ ሂደትን በትክክል ለማወቅ እንዲረዳን እዚህ ውይይት ላይ ትንሽ መቆየት ይኖርብናል። እንግዲህ ለታሪካዌ ትንታኔ መስፈረት ወይም መለኪያ የሚሆነው በአገር ዉስጥ ያለው“ሁኔታ” በቁጥጥር ስር መሆኑንና ያለመሆኑን ማረጋገጥ ነው። የሕብረሰቡ ሊቃነ ሕሊና  ዝቅ ሲል፤ ሕግ የግለሰብ ታዛጅ ሲሆን፤ ሃይማኖት የፖለቲካ አካል ሆኖ ገዥዉን ሲያገለግል፤ የዘውግ አቀኝቃኞች በጅምላ አንድ ብሔር ሊላዉን ብሔር ጨቁናል በማለት የሃሰት ክስ መስርተው  “ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል” በማለት የዘር ማጥፋት እርምጃ ሲያካሂዱ፤ የግለሰብ መብት ሲገፈፍ፤ ግለስብና ሞገደኛ የአምባ ገነንቱ ኃይል ተቀባይነት ሲያግኝ በግዜው ያለው “ሁኔታ” ከቁጥጥር ዉጭ ሆኖአል ማለት ነው። በዚህ ግዜ ያልሆኑ ነገሮች ሆነዋል፤ ያልተሰሩ ነገሮች ተሰርተዋል፤ ያልተደረጉ ድርጊቶች ተደርገዋል እየተባለ የሚነገሩ ወሬዎች እንደታሪክ ተጽፈው የሚቀርቡበት “ሁኔታ” ነው። በተለምዶ ታሪክ እንጽፋለን እያሉ ታሪክን የሚያበላሹ አገር ሆናለች። ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት “ሁኔታ” ይህንን ይምስላል። የቤተ ክርስቲያኑ ታሪክ በሚቀጥለው ክፍል አራት ይቀርባል።

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  “Fly out of Ethiopia while you can.” ማለትስ አሁን ነው - አምባቸው ደጀኔ (ከወልዲያ)

6 Comments

  1. A total lie. Christianity was not improted to Ethiopia. Read about the Ethiopian Eu nich.

    Where is your reference? And what is the importance of writing this “DIRITO” at this time when the people are under marshal law? Why do not you writr about that, Mr. Deftera?

  2. Ewuntim Deftera,

    Ethiopia was one of the very few countries who started to believe in one GOD. Reading the books of prophets such as Eyssayas, Ethiopia accepted Christianity. Ethiopian never imported christiantiy. Do not lie and spread lie.

    It is not time to talk about false history. It is time to fight and reclaim ehtiopia.

    • ጽሑፉ በሚገባ ተጽፏል፤ ታሪኩም በቅደም ተከተል ቀካቷል፤ ከዚህ የበለጠ ምንድነው የሚፈለገው? ታላቅ ምስጋና ለጸሐፌው።

  3. zimbleh tikebatiraleh ethiopia wust yeneberut betemekdesoch ende egypt yetaot mamlekia alneberum yeayhud Emneth inji.
    2 ferenji yetsafelhen becha yezeh kerstina we’d ethiopia yegebaw be 4th century new telaleh mejemeria yagerhen tarikawi metshaft bedenb fetsh lelaw beker metshafkidusun sele Ethiopia ytetsafewn mefetesh tiru neber zemblo awaki lememsel menderder tiru aydelem yawum legnaw le ethiopiyaweyan. be 4th century official yehageritu haymanot yehonebet yihonal enji ethiopia yemejemria kirstna teqebay hager nat read the Bible about queen hindakey and janderebaw lelam bezu yekuskusna yetshufe tarikawi masrejawoch moltewal ethiopia wust.

  4. The problem is not with the writer it is with you; I have never seen such a shallow commentary on matters of historical importance; with no education in any field you are given an office to disrupt civic discourse on the role of the clergy and the tug; the warning against these clergy who were sent by the Woyane to disarm the uprising were given justice; no matter what you write on this the Church will be liberated from……….? You do not even understand between “reformation” and “liberation” …it is liberation from Woyane””””””””””””””””””””””””””””””””’

  5. Here we go again! Woyane is working day and night to disrupt civic discourse about the clergy and its collaboration with this tug; I do not think they even understand between “Reformation” and “Liberation.” The tug has assemble a large contingencies of cadres to write anything against any credible threat to its survival. Gojam and Gondar has already liberate its Church; any attempt to disarm the uprising will be dealt accordingly; those clergy who were sent by the Woyane to disarm was a disgrace for our Church; you are also a disgrace”””””””””””””””””””””””””””””””

Comments are closed.

Share