እሁድ ሰማያዊ ፓርቲና ኢሕአዴግ በመስቀል አደባባይ የጠሩት ሰልፍ እያወዛገበ ነው

‘‘ቀድመን ሰልፍ የጠራነው እኛ ነን’’

 ሰማያዊ ፓርቲ

‘‘የቀደምነው እኛ ነን’’

– የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

‘‘ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ የሚያካሂደው ሰልፍ ህገ-ወጥ ነው’’

– የአ.አ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ የስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት

 

በዘሪሁን ሙሉጌታ

በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው። ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።
ይህንን ተከትሎ በፓርቲው እና በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መካከል የቀደምኩት እኔ ነኝ በማለት በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት በበኩሉ፤ ሰልፍ እንደሚካሄድ ቀድመው ያሳወቁት የሃይማኖት ተቋማቱ በመሆኑ በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚካሄድ ከሆነ ህገወጥ ነው ብሏል።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጉዳዩን በማስመልከት ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገሩት ፓርቲው ከወር በፊት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ማድረጉን በማስታወስ ፓርቲያቸው ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ በቅድሚያ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል።
እንደ ፓርቲው ሊቀመንበር ገለፃ ፓርቲው አስቀድሞ ቀን መቁረጡንና በተባለውም ቀን ሰልፉን ለማካሄድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ ስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ጭምር የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ተናግረዋል። በወቅቱ ጽ/ቤቱ ደብዳቤውን ለመቀበል ፍላጎት ባያሳይም በህጉ መሠረት ማሳወቅ ብቻ በቂ በመሆኑ ደብዳቤውን በጽ/ቤቱ አስቀምጠው መመለሳቸውንና በኋላም ጽ/ቤቱ በፖስታ ቤት በኩል በሬኮማንዴ ለፓርቲው ሰልፍ የት እንደሚያካሂድ፣ ምን ያህል ሰው እንደሚሳተፍ ማብራሪያ በመጠየቁ ፓርቲው በበኩሉ ለጽ/ቤቱ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል። ሆኖም ጽ/ቤቱ በህጉ መሠረት በ48 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ መስጠት ሲገባው ዝምታን በመምረጡ፣ ዝምታው ደግሞ ሰልፉ እንደተፈቀደ የሚጠቁም በመሆኑ በሰልፉ ዙሪያ ፓርቲው ዝግጅት ማድረግ መቀጠሉን አስታውቀዋል።
ከጽ/ቤቱ እስካሁን (ነሐሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም) ምላሽ ባለመገኘቱም ፓርቲው በዕለቱ የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ከማካሄድ ወደኋላ የሚመልሰው የህግ መሠረት ባለመኖሩ ሰልፉን እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል። ፓርቲው ከነገ ሐሙስ ጀምሮ በአምስት ተሽከርካሪዎች በአስሩም ክፍለ ከተማ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። በመላ ከተማዋና በአካባቢዋም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ወረቀት እንደሚበተንና ሰልፉም ካለፈው ሰልፍ ልምድ በማግኘት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ ባለፈው ሰኞ (ነሐሴ 20 ቀን 2005) በዋና ጽ/ቤቱ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ያስታወቀው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን እንደማያውቁና ጽ/ቤታቸውም ቀደም ብሎ ሰልፉን ሲያዘጋጅ መቆየቱን ተናግረዋል።
ምንም እንኳ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ የሃይማኖት ጽ/ቤቱ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያሳወቀበትን ቀን ለመናገር ባይፈልጉም በዕለቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በሰጡበት ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በ10ሩም ክፍለ ከተሞች እና በ116 ወረዳዎች በተካሄደ ሕዝባዊ የሰላም ኮንፈረንስ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር በከተማ ደረጃ ነሐሴ 15 እና 16 ቀን 2005 ዓ.ም በተዘጋጀው ማጠቃለያ የሰላም ኮንፈረንስ የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎችና ተከታዮቻቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማችን እየታየ ያለው የአክራሪነትና የፅንፈኝነት እንቅስቃሴ የሀገራችንን ልማት የሚያውክ፣ በሰላም አብሮ የመኖር እሴቶቻችንን የሚያናጋ እና የሃይማኖት መልክ የሌለው የጥፋት እንቅስቃሴ ከመሆኑም በላይ በሕገ-መንግስታችን የተደነገገውን የኃይማኖት እኩልነትና የእምነት ነፃነት የሚፃረር ስለሆነ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞአችንን እንግለፅ በማለት የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች መንግስት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች፣ የኃይማኖት ተቋማት የጋራ ጉባኤም እንዲያስተባብር መወሰኑን ተናግረዋል።
ከዚህ መግለጫ መረዳት የሚቻለው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ሰልፉን ለማካሄድ ጥያቄ ያቀረበው ነሐሴ 15 እና 16 በኋላ መሆኑን መረዳት ይቻላል። በአንፃሩ ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 16 ቀን 2005 ዓ.ም የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባቱን አመልክቷል።
የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ ጉዳዩን በተመለከተ የእውቅና ጥያቄ በማቅረብ ቀዳሚ የነበሩት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በመሆናቸው ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንዲያካሂድ አልተፈቀደለትም ብለዋል። ሰልፉ የሚካሄድ ከሆነም ህገወጥ ነው ከማለት ውጪ ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰልፍ ያሳወቁበትን ቀን እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ከመናገር ተቆጥበዋል።n

ተጨማሪ ያንብቡ:  መራሹ ኦነግ አማራወችን በወለጋ እርደዋል

(ምንጭ ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ)

 

4 Comments

    • Are you trying to refuse to admit the truth what has been already happened? Or are you gonna try to convince people in one small sentence? What I see in you is dark. I see that you are covered with a folded black sheet of cloth. The truth is that EPRDF calls the demonstration to make truble or mess the situation up. EPRDF is calling the the genocide what it has been dreaming to realize in Ethiopia like it was in Ruanda and Brundi. It has been speeding but the people has been refusing. What I tell the truth for the people like you is that, the EPRDF dream will be vanish like a white cloud that can be taken away by a small and easy breath of wind. Never to be happened in Ethiopia. What I am telling you the truth also is that you and the whole TPLF members will be in put before Justice. You will see that; believe me or believe the truth.

    • What a kind of name that you have, ayalew? Do you think you can touch anybody with your nasty words psychologically or physicaly? You learn that and you have such a kind of habbit those you are from the member of narrow minded group. Learn more to reach on that and to be called Engineer to write the exact spell of the word “engineer” , but not to write the word, Enginieur, which has not an exat meaning in any human language. You are the master of wicked anmal that you do not have a feeling that humans have. If you had you would never say “…go to hell..” or else. You are little. Really, you are little. Watch your mind and spirit, body.

Comments are closed.

Share