September 22, 2016
5 mins read

ኢትዮጵያ ሽምግልና ለምኔ?ዶ/ ር ዘላለም እሸቴ

ኢትዮጵያ ካለችበት ወቅታዊ ችግሮች ለመውጣት ሽምግልናን እንደ መፍትሄ አድርጋ መውሰድ ትችላለች ወይ? እስቲ ይህንን ሀሳብ በተመለከተ ጉዳዩን ከሁሉም አቅጣጫ ረጋ ብለን እንመልከት። ከኢአዴግ አንዳንዶች አንድ ምርጫ ብቻ እንዳለ ሊያስቀምጡ የፈለጉ ይመስላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲሆን ፀጥ ለጥ አሰኝቶ መግዛት አሊያም በሃይልም ቢሆን መግዛት እንችላለን ብለው የሚያምኑ እስኪመስል ድረስ ሃይልንም ሲጠቀሙ ይታያል። በተቃዋሚ ጎራ ያሉ አንዳንዶች ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ምርጫ ብቻ እንዳለ አድርገው ያስቀምጣሉ። ያም የሚያስከትለውን ዋጋ ከፍሎና በአመፅ አብዮት አካሄዶ መንግስትን መገልበጥ ነው እንጂ መነጋገር የትም አያደርስም ብለው ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ። እና ምን ይሻላል? ተያይዞ ገደል መግባት ወይስ አውጥቶ አውርዶ፥ ከሁለቱም ተቃራኒ አስተሳስብ ይልቅ ሌላኛ ሶስተኛ አስተሳሰብ አለ ብለን መንግስትንና የተቃዋሚ አካላትንመሞገት? የኢትዮጵያ ሕዝብ በመቻቻልና በመተሳስብ አብሮ የኖረ ሕዝብ ነው። ያልታደለው እኩልነትን አንግሶ በፍቅር የሚያያይዘውና አንድ የሚያደርገው አስተዳደር እስካሁን አለመገኘቱ ነው። ፈሪሃ ፈጣሪን የተላበሰው ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በእውነት ላይ የተመሰረተ ጥል ሆነ ጥላቻ አንዱ በሌላው ላይ የለውም። መሪዎች እንደ ሕዝቡ ቅን ሆነው እኩልነትና ፍቅርን ቢዘሩ የሚታጨደው የፍቅር አዝመራ የሚያስጎመጅ በሆነ ነበር።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ህብረ ብሔር በሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማንነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በመሪዎች የስህተት አካሄድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። ስለሆነም መንግስት በተቀዳሚነት ለዚህ ስጋት ሃላፊነትን ራሱ መውሰድ ይገባዋል። ራሱንም ተጠያቂ ካደረገ በውኋ ላ፥ ወደዚያ ጥፋት ከሚመራው የሃይል እርምጃ ታቅቦ ኢትዮጵያን ለማዳን ውይይትና መግባባትን እንደ ብቸኛ አማራጭ በመውሰድ አማራጭ ሃይሎችን ለሰላሙ ጉዞ መጋበዝ ይኖርበታል። አብዮት ላለፉት አራት አስርተ አመታት ያተረፈልንን እያየነው ነው። ችግርን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ለዛሬና ለወደፊቱ ፍቱን መድሃኒት ነው። አብዮት የዛሬን ችግር ፈቶ ሲያበቃ የነገውን ችግር ይወልዳል። መንግስት ጊዜ ሊገዛ ፈልጎ የውሸት ሽምግልና ቢመርጥ ያንን ውድቅ ማድረግ ያባት ነው። አለበለዚያ ግን በጭፍን ሽምግልና ዋጋ የለውም ማለት ከማስተዋል ሃላፊነት መጉደል ይሆንብናል። ሽምግልና ይሰራል አይሰራም ሳይሆን ጥያቄው፥ የትኛው ሽምግልና ይሰራል ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል። ሁለት አይነት የሽምግልና አካሄድ ሊኖር ይችላል። አንድም አድሏዊ የሆነ ከሃይለኛው ጋር የወገነ የይስሙላ ሽምግልና ሲሆን ሌላኛው ደግሞ፥ አድሏዊ ያልሆነ ከማንም ያልወገነና እውነተኛ ሽምግልና ነው። በርግጥ የይስሙላ ሽምግልና ምንም ፋይዳ ላይሰጥ ይችላል። ነገር ግን ለእውነተኛው ሽምግልና እድል ተሰጥቶት ኢትዮጵያ ካለችበት አጣብቂኝ እንድትወጣ ድልድይ ቢሰራ ሀገራችን ዘላቂ ሰላም ይሰፍንባታል። የዚህ እውነተኛ ሽምግልና ግብና ዓላማ የሚያዛልቀው ሶስተኛው (ሌላኛው) መንገድ፥ በውይይትና በመግባባት አገሪቱን በሰላማዊ መንገድ ወደ ዘላቂ ዲሞክራሲ ፍትህ እኩልነትና ዕድገት የሚያመራውን ሂደት ለመፍጠር ሁኔታዎችን የሚያመቻች ነው። ዞሮ ዞሮ ይህን ዓላማና ግብ ሁላችንም የምንፈልገው ነው። እግዚብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

spy file
Previous Story

የመተማው “የዘር-ፍጅት” ትርክት በደህንነት ተቋሙ የተቀናበረ ነበር (ዋዜማ ራዲዮ)

Next Story

ከስልጣንዎ ሲባረሩ እውነቱን ይነግሩናል (ከይገርማል)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop