June 25, 2013
2 mins read

እኔ እማልሰጣችሁ ፣ እናንተ እማትወስዱት….

 

ያለስም፣ ስም – ስጡኝ

ቅጡኝ፣ አስቀጡኝ፤

አግዙኝ፣ ወርውሩኝ፣…… በማጎሪያችሁ

እሰሩት…. እጀን፣…… በካቴናችሁ

‘ጠንዙት’…..እግሪን፣  …. በእግር ብረታችሁ

ቸንክሩት፣ ገንዙት፣ ….. ይደንዝዝላችሁ

ሽባ ሆኘ ልቅር፣ ‘’ልሰንከልላችሁ’’::…….

እንካችሁ …. ጀርባዬን

መጫሚያ፣  መዳፌን፤

ግረፉት፣ አቃጥሉት፣ …. በኮረንቲ ገመድ

የሰራ አከላቴ፣ ይክሰል፣ ይሁን ዓመድ::…….

ዝረፉት ……. ሀብቴን

ቤትና ንብረቴን፣ በምድር ያለኝን፤

ሰብስቡ፣ አከማቹት፣ ለዓለም ይሁናችሁ

ለማይጠረቃው፣ ለከርስ ዓላማችሁ

ለማፍረስ፣ ለመናድ፣ ለጥፋት ግባችሁ ::……….

እንካችሁ…… ደረቴን

እንካችሁ…… ግ’ባሪን፤

ለታንክ፣ ለመትረጊስ፣ ለጥይታችሁ

አፍስሱት ደሜን፣……. እስኪከረፋችሁ

አድቅቁት አጥንቴን፣……. እስኪወጋችሁ::…………

እንካችሁ……… እንካችሁ

ሥጋ – ሰውነቴን፣ ለጉድጓዳችሁ

ለመቃብራችሁ::…….

እንካችሁ………  እንካችሁ

ሁሉንም ………  እንካችሁ፤…….

…….. ግን “የእፍኝት ልጆች”…….

………. የሀገር እስስቶች ………….

………… እናንተ እኩያኖች፤……….

ምድር ሰማይ ሆኖ፣ ሰማይ ቢሆን ምድር፣ ቢፋለስ ተፈጥሮ

በጨረቃ ቦታ፣ ብትወጣ ጸሀይ፣ ዘመን ተቀይሮ፤

ቢተባበራችሁ፣ የዓለም ኃይል በአንድነት

እኔ እማልሰጣችሁ፣ እናንተ እማትወስዱት፤……

የሰው ልጅነቴን፣ ኢትዮጵያዊነቴን!

አረንጓዴ – ቢጫ – ቀይ፣ ሰንደቅ ዓላማዬን!

ከዓምላክ ያገኘሁት፣ ፍጹም ነጻነቴን!

—–//—-

ፊልጶስ/ ግንቦት 2005

 

Previous Story

አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር በሰሜን አሜሪካ ሕዝባዊ ስብሰባ – በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 30ኛው አመት የበዓል ላይ

Next Story

በዝዋይ እስር ቤት ለወራት የተሰቃየው ወጣት “ቤተሰቦቼን እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል” ይላል

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop