የኛ ነገር፡ የአባይ ችግር፡ የአያልሰው ምክር፡ ከልጅ ተክሌ፤ ተረንቶ

ከልጅ ተክሌ፤ ከተረንቶ

ክፍል 4 (ክፍል ሁለትና ሶስት ይመጣሉ)

  1. ብዜ ግዜ የአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፎች ረዣዥሞች ስለሆኑ፤ እንዲሁም ክፍል ስለሚበዛቸው (1፣ 2፣ 3፣ 4፣ … )፤ ርእሳቸውን ብቻ እያየሁ አልፋቸው ነበር። በዚህ በአባይ ጉዳይ ግን የጻፉት አነበብኩት። ጽሁፉ በርስ በርስ ቅራኔ የሚንተከተክና በኢህአዴግ የአባይ ግድብ ማጭበርበሪያ ዘመቻ ዙሪያ ያለውን ተቃውሞ በቅጡ ያልዳሰሰ፡ ይልቅስ ሌሎችን ተቺዎች በሚከስበት ደዌ ክፉኛ የታመመ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በተጨማሪም ጽሁፉ የአካባቢውን ፖለቲካ በቅጡ የቃኘ ቢሆንም፤ የደረሰባቸው ድምዳሜዎች ግን የተሳሳቱ ናቸው።
  2. እንደምንም በርትቶ እዚያ ለደረሰ ሰው፤ የአቶ አያልሰው ደሱ ጽሁፍ ዋና ሀሳብ በክፍል ሁለት፤ በአምስተኛው ገጽ፤ በሁለተኛ አንቀጽ ላይ ይገኛል።

“እንደ አንድ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ በሚከተሉት ምክንያቶች ይሄ የህዳሴ ግድብ መደገፍ እንደሚኖርበት እምነቴ ነው። በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ውስጥ በአባይ ላይ ግድብ ለመስራት ለኢትዮጵያ ከዚህ ጊዜ የተሻለ የአካባቢና የአለም አቀፍ ሁኔታ ኖሮ አያውቅም ማለት ይቻላል። … ኢትዮጵያ አባይ ላይ ትርጉም ያለው ግድብ መስራት ከፈለገች፡ …ወቅቱ አሁን ነው።”

  1. እንደተረዳሁት ከሆነ፤ አቶ አያልሰው የሚሉት፡ የአባይን ግድብ ሊያሳኩ የሚችሉ ሶስቱም ነገሮች፤ አለማቀፋዊ፤ አካባቢያዊ (ምስራቅ አፍሪካን ማለታቸው ይመስለኛል) እንዲሁም በግልጽ ባይሉትም አገር አቀፋዊ ሁኔታዎች (አገር ወዳድ መንግስት ማለታቸው መሰለኝ) ገጥመዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደኢህአዴግ ያለ የኢትዮጵያን ራእይ ሊያሳካ የሚችል መንግስት ከአለማቀፋዊ ሁኔታዎች ጋር ስለገጠመ፡ በሳቸው አነጋገር፤ እኛና እሳቸው እዚህ ምን እንደምንሰራም አልገባኝም። አንድ ሁለት ግሬደሮች ይዘን ጉምዝ ብንገባ ሳይሻል አይቀርም።
  2. የአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፍ የተገነባው ፈረንጆቹ “ስትሮው ማን ፋላሲ” በሚሉት፤ የሌላውን ሀሳብ አስቀድሞ በማኮሰስ፤ የኮሰሰውንም በሚተቸው አመንክዮ ላይ ነው። አቶ አያልሰው መጀመሪያ የአባይን የማጭበርበሪያ ግድብ የሚቃወሙ ሰዎችን ሀሳብ፡ ደህና ደህናው እየተዉ፡ በሁዋላ ለማጥቃት በሚመቻቸው መልኩ ደካማ ደካማውን መርጠው፡ እሱንም ፍንክትክት አድርገው አስቀመጡት። ከዚያ በሁዋላ ዋናውን የተቃውሞ ወይንም የጠያቂ ሀሳብ መሞገት ትተው፤ እሳቸው የፈጠሩትን የተፈነካከትና የተጋጋጠ የተቃዋሚዎች ሀሳብ መደብደብ ያዙ። እግዜር አይወደውም።
  3. የአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፍ፤ ከመነሻውም በአያሌ ህጸጾች የተከበበ ነው። መጀመሪያ በአሁኑ ግዜ የአባይን መገደብ የሚቃወሙ ወገኖች ለተቃውሟቸው የሚያቀርቧቸው የሚሏቸውን ደካማ ደካማ ምክንያቶች ብቻ መምረጣቸው ስህተት ነው። ክፍል ሁለት ገጽ አንድን ይመልከቱ። ከዚያ ሲደመድሙ አብዛኛዎቹ የተቃዋሚዎች ወይም ሁሉም ሀሳቦች ቀድሞ በኢህአዴግ ላይ ባለን ጥርጣሬና ጥላቻ የተጋረዱ፤ አብላጫዎቹ ደግሞ “በትክክለኛ መረጃና እውቀት ላይ ያልተመሰረቱ በግልብ ስሜት ላይ የተንጠለጠሉ በአጭሩ የአባይ ግድብ ለኢትዮጵያ ያለውን ፈርጀ-ብዙ ትርጉምና እርባና በቅጡ ካለመገንዘብ የመነጩ ናቸው፡” ሲሉ ፈረጇቸው።
  4. አንደኛ ነገር፤ ለግንዛቤ ይረዳን ዘንድ፤ አቶ አያልሰው ደሴ፡ የነማንን ሀሳብ የት ቦታ ተጽፈው አይተው ይሄንን አቋም እንደያዙ በጽሁፋቸው ላይ አልገለጡልንም። የሚተቹት ፓልቶክ ላይ ያደመጡትን ይሁን ፌስቡክ ላይ የታዘቡትን ሀሳብ አላሳወቁንም። ከሁሉም በላይ ግን የከነከነኝ፡ በግልብ ስሜት ላይ የተንጠለጠሉ ሀሳቦችን ይዘው ሙግት የመግባታቸው ብልሀት ነው። በመሰረቱ፡ በግልብ ስሜት ላይ የተመሰረቱ ተቃውሞዎች ሊታለፉ እንጂ፡ በአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፍ ሊያልፍላቸው አይገባም ነበር። የምናጠቃውን ሀሳብ መምረጥ አለብን።
  5. ሁለተኛ ነገር፡ የሌሎችን ሀሳብ በስሜታዊነት ላይ የተመሰረቱ ብሎ መፈረጅ፡ ተመሳሳይ ፍረጃን በራስ ላይ የመጋበዝ ያህል ነው። የአባይን ግድብ በተመለከተ ጥርጣሌ ያላቸው፤ ወይንም ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች ሀሳብ፤ አባይ ለኢትዮጵያ ያለውን ፈርጀ-ብዙ ትርጉም ካለመረዳት የመነጨ ከሆነ፤ የአቶ አያልሰው አይነት የአባይ ግድብ ድጋፍም፡ ምናልባት የኢህአዴግን ባህርይ ካለመረዳት ወይንም ከመርሳት የመነጨ ነው ወደሚል መደምደሚያ ይመራል። ይመስላልም። ጽሁፋቸው በርግጥም አቶ አያልሰው ደሴ ኢህአዴግን ረሱት እንዴ የሚል ጥያቄ ይፈጥራል። እመለስበታለሁ።
  6. ሶስተኛ ነገር፡ ሶስተኛውን ነገር ረሳሁት።
  7. አራተኛ ነገር፤ ከአባይ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ክርክሮች ላይ፤ አንዱን ቡድን የግድቡን ተቃዋሚ ሌላኛውን ጎራ የግድቡ ደጋፊ አድርጎ የመሳሉ አካሄድ ስህተት ነው። ይሄ ኢህአዴጎችና ደጋፊዎቻቸው ሆን ብለው እኛን ለመከፋፈልና ለማሳሳት የቀየሱት ቀሽም የክርክር መስመር ነው። የአባይን መገደብና ጥቅም ላይ መዋል የሚቃወም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብየ አላስብም። የአብዛኞቻችን ተቃውሞ፡ ገና ለገና ኢህአዴግ በስስ ብልታችን ስለመጣ፤ የ22 አመቱንና አሁንም የቀጠለውን ጭቆና ችላ ብለን፡ በስመ አባይ ግድብ ኢህአዴግን በጭፍን መርዳት የለብንም ነው።
  8. አቶ አያልሰው ደሴ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ የሚሉትን ቃላት ጽሁፋቸው ውስጥ ጣል ጣል ቢያደርጉም፡ ደግመው ደጋግመው የሚያነሱት፤ “ግድቡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መደገፍ አለበት” የሚለውን ሀሳብ ነው። በሌላ አነጋገር አቶ አያልሰው ደሴ ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ህዝብ ለአመታት እዳ ውስጥ ሊከት የሚችል፤ ወደአለማቀፋዊ ህጋዊ ግዴታ የሚዶል ውል መግባት የሚችል የህዝብ ውክልና ያለው ህጋዊ መንግስት ነው እያሉ ነው። ኤልያስ ክፍሌ ያስቀመጠውን፡ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለዚህ ኢትዮጵያዊያንን ለደፈረ፡ ለገደለ፡ ላሰረ፡ ላዋረደ መንግስት የምንሰጠው እርዳታ፤ በተዘዋዋሪ ኢህአዴግን ህጋዊነት የሚያላብስ፡ ኢህአዴግ የሚፈጽውንም አፋናና የመብት ጥሰት የሚደጉም ነው የሚለውን ስጋት ወይም ክርክር አልዳሰሱትም።
  9. ከዚያ አቶ አያልሰው የግድቡን ተቃዋሚዎች የሚሏቸው ሰዎች የሚያነሷቸውን መከራከሪያ አሳቦቦች በጥልቀት ለመዳሰስና ለመመለስ ይሞክራሉ። ለምሳሌ አቶ አያልሰው  ደሴ “የአባይ ጉዳይ ከባድና ውስብስብ ነው” ይላሉ።
ተጨማሪ ያንብቡ:  ዕርቅ እና የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር - አንዱ ዓለም ተፈራ፤

አባይ የኢትዮጵያ ስስ ብልት ነው ማለት ይቻላል። በጣም ጥንቃቄና በእንክብካቤ የሚያዝ ጠቃሚ የአገር አካል ነው። በመሆኑም በእሱ ላይ የሚወሰድ ውሰኔ በተራ የፖለቲካ ስሌት ላይ ተመርኩዞም ሆነ ብድግ ብሎ በዘፈቀደና በስሜታዊነት አዋጅ በማስነገር የሚደረግ አይደለም።

ከዚያ በሁዋላ፤ አቶ አያልሰው፤ አሁንም ለነማን እንደሆነ እንጃ፤ የኢህአዴግ ፕሮጀክቶች ላይ ተቃውሞ ሲደረግ እንዴት መደረግ እንዳለበት ትምህርት ይሰጣሉ። አቶ አያልሰው ደሴ፤ በስም ባይጠቅሷቸውም፤ እሳቸው “ግድቡን የሚቃወሙ” የሚሏቸውን በተራ ፖለቲካ ላይ ተመርኩዘው የሚቃወሙ አድርገው ይስሏቸውና፤ ኢህአዴግ ግን የአባይን ግድብ ከማወጁ በፊት ቢያንስ ለአስር አመታት ያደረገውን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይ የሰለቸንን የኢህአዴግ የዲፕሎማሲ ትግል ያወሳሉ።

  1. በመሰረቱ የአባይ ጉዳይ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነው ካሉ፤ ጥንቃቄው ለመቃወም ብቻ ሳይሆን ለመደገፍም ጭምር ነው። “አባይ አባይ” እየተባለ ሲዘመርልን ስለኖርን ብቻ ኢህአዴግ ማጣፊያው ሲያጥርበት ድንገት ተነስቶ አባይን ልገድብ ነው ሲል፤ “ከቀበሌ ጥይት ፈጥነን” ከኢህአዴግ ጎን መሰለፍ አለብን ማለት አይደለም። ጥንቃቄው ባለሁለት ዘርፍ ነው። አቶ አያልሰው እንደመከሩት ለመቃወምም። እሳቸውን ለማስታወስም ያህል ለመደገፍም ጭምር ጥንቃቄ ያስፈልጋል። አባይን ገነባን ብለን ለኢህአዴግ ገንዘብና ቁስ ወደማቅረብ መሮጥ የለብንም። ቀድሞ ነገር መቼ የአገራችን ባለቤት ሆንነና ነው የአባይን ግድብ ስለመርዳት የምናነሳው? አገርስ አለን እንዴ? አገራችንን ተነጥቀን አባይን ስለመገንባት ስናወራ ትንሽ ግራ ያጋባል።
  2. አቶ አያልሰው፤ የተቃዋሚውን አተያይ በጣም አድርገው ተችተዋል። እሳቸውንም የምናቀውቃቸው በተቃዋሚነት እንደመሆኑ መጠን፤ ራሳቸውን ከየትኛው ወገን አስቀምጠው ተቃዋሚውን እንደተቹ ከጽሁፋቸው ለማወቅ አልቻልኩም። “ከተቃዋሚው በኩል ምንም ይሁን ምን ነገሮችን አገዛዙን ከሚያዩበት መነጽር አኳያ” ነው ማለት ምን ማለት ነው አሁን?
  3. አቶ አያልሰው ደሴ አባይን ስለመገድብ ስልጣን ያስቀመጡትም ሀሳብ ምንጩና መሰረቱ ምን እንደሆነ አልተረዳኝም። አቶ አያልሰው እንዲህ ይላሉ፤
ተጨማሪ ያንብቡ:  በርግጥ ጠላቶቻችን በዝተዋል ሆዳም አማራውን ጨምሮ ቢሆንም ግን እናቸንፋቸዋለን!!    (አንተነህ ገብርየ)

ዞሮ ዞሮ ለማንም በተገቢ ግልጥ መሆን ያለበት ጉዳይ ዓባይን በኢትዮጵያ ምድር ላይ የመገደብና ያለመገደብ ውሳኔ የኢትዮጵያዊያን ብቻ እንጂ በምንም መንገድ ለሱዳን፡ ለግብጽም ሆነ ለሌላ የውጭ ሀይል አሳልፎ የሚሰጥ አለመሆኑን ነው።

ይሄ ሀሳብ አንደኛ ከኮመን ሴንስም ከህግም አንጻር ስህተት የበዛበት ነው። ሁለተኛ አቶ አያልሰው ደሴ ከሚያራምዱት የጥንቃቄ ጉዞና የዲፕሎማሲ ትግል ጋር ይቃረናል።

  1. ጋሼ፤ ኢትዮጵያ ደሴት አይደለችም። አባይም ድንበር ዘለል ወንዝ ነው። ደርግም፤ አጼ ሀይለስላሴም አባይን በእኩልነትና በፍትሀዊነት ሰለመጠቀም ሲናገሩ እንጂ፤ ለብቻችን እንዳሻን የመገደብም ያለመገደብም መብት የኛ ነው ብለው ሲናገሩ የተጻፈበት ቦታ አላያሁም። አባይ ከኢትዮጵያ ይመነጫል እንጂ የኢትዮጵያ ብቻ አይደለም። ልክ ኮሎራዶ ወንዝ ከአሜሪካ ቢነሳም የአሜሪካ ብቻ እንዳልሆነው። ኢትዮጵያ የአባይ ብቸኛ ባለቤት ተደርጋ አልተፈጠረችም። ስለዚህም፤ የአባይን እጣ ፈንታ ለብቻዋ ልትወስን አትችልም። ያለበለዚያ ሰላማችን ይደፈርሳል። በውሀ ጥም ከመሞት ሲታገሉ መሞትን የሚመርጡ ይወሩናል። ተያይዘን እንጠፋለን። ለዚህም ነው ዲፕሎማሲው ያስፈለገው። አቶ አያልሰው ሌሎቻችንን ስሜታዊ እንዳንሆን እየመከሩ እሳቸው ራሳቸው ስሜታዊ ሆነው፤ የተሳሳተ ሀሳብ ነው ያራመዱት። አባይን መገደብ አለመገደብ የኢትዮጵያ ብቻ ጉዳይ አይደለም። አገር ወዳድነት አንድ ነገር ነው። ብሄራዊ ስሜትም አንድ ነገር ነው። ህግና አለማቀፍ ጉዳይ ደግሞ ሌላ ነገር ነው።
  2. በገጽ አምስት ላይ አቶ አያልሰው ደሴ የኢህአዴግ የዲፕሎማሲ ትግል ስላስገኘው ትርፍ ይተነትናሉ። በመሰረቱ እሳቸው እንዳሉት አባይን የመገንባት ጉዳይ የኢትዮጵያ ብቻ ከሆነ፤ የሌሎች አገሮችን ድጋፍ ማግኘት አስፈላጊነቱ አይታየኝም። ይሄ 9 የምስራቅ አፍሪካ አገሮችን ማሰለፍ መቻል ባንድ በኩል የዲፕሎማሲ ትርፍና ድል ቢመስልም፤ በሌላ በኩል አደጋም አለው። አቶ አያልሰው ደሴ ከሚሉት በተቃራኒ፤ 85 ከመቶ የአባይን ውሀ የምታመርት ኢትዮጵያ፤ ይሄንን የአባይ ጉዳይ በዚህ የአባይ ተፋሰስ አገሮች ማእቀፍ ማህበር ስር ለዘጠኝ አገሮች አሳልፋ መስጠቷ፤ ኢትዮጵያን ለነዚህ ዘጠኝ አገሮች ድምጽ እስረኛ ያደርጋታል። ለምሳሌ፡ የአስሩ አገሮች ስምምነት ተፈሳሱን የሚያስተዳዳር ኮሚሽን እንደሚቋቋም ይደነግጋል። ኢትዮጵያ በቀጣይነት በአባይ ላይ ልትገነባ የምታስባቸውን ግንባታዎች ሁሉ ለነዚህ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ድምጽ አሳልፋ ልትሰጥ ነው ማለት ነው። ከድጡ ወደማጡ ነው ብሎ መከራከርም ይቻልል።
  3. የአቶ አያልሰው አስገራሚ መከራከሪያ ነጥቦች አያልቁም። ከሁሉም የገረመኝ ግን፡ በገጽ ስድስት ላይ፤ ግብጽና ሱዳን የኢትዮጵያን ሰላም ለማሳጣት ስለተጫወቱት ሚናና አሁን ያ ሚናቸው ስለመቀነሱ የተናገሩት ነው። የነሱ ሚና የቀነሰው አሁን ሳይሆን፡ ያኔ የዛሬ 22 አመት አሁን አራት ኪሎ ያሉትን ሰዎች አስታጥቀው ስንቅ ቋጥረው ስልጣን ላይ ካወጧቸው በሁዋላ ነው። ዛሬ እነሱዳንና ግብጽ ያስታጠቋቸው ቅጥረኞች አራት ኪሎ ቁጭ ብለው፤ አቶ አያልሰው በሱዳንና ግብጽ የጡት ልጆች ላይ ተማምነው ስለነሱዳን ሚና መመንመን ሲሰብኩና ስለ አባይ ግድብ ግንባታ ሲያወሱ እንቆቅልሽ ሆኖብኛል። እንዴት ያለው ሀሳብ ነው ባካችሁ?
  4. ከላይ የዘረዘርኳቸው አይነት ትንታኔዎች ላይ ተመስረተው ነው “ኢትዮጵያዊያን እንደ ህዝብ ይሄንን መሰል የሌለው ሁኔታ” እንዳገኘንና በወቅቱ ካልተጠቀምንበት፡ የመጪው ዘመን ኢትዮጵያዊያንን ምህረትና ይቅርታ የለሽ ምሬት እናተርፋለን ሲሉ የጻፉት። መቼም እውነተኛ ስሜቴን ለመደበቅ ብሞክርም፡ ይሄ ከአያ አያልሰው አምባ ሲመጣ ትንሽ ግራ እንደገባኝ ሳልናገር አላልፍም። አቶ አያልሰው ደሴ ክርክራቸው አንዳንድ ቦታ ላይ ለአንባቢያን ሀሁን የማስተማር ያህል ሆኖ ነው ያገኘሁት። አሁን በማዬ ሞት የአባይ ግድብ ተገንብቶ ሲያልቅ መብራት እንደሚያመነጭ፡ መብራቱ ለአገሬው ህዝብ እንደሚጠቅም፤ መብራቱም ከተሸጠ የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስገኝ፡ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለንን ግንኙነትና ትስስር እንደሚያጠናክረው የማያውቅ አለ? አበሳጭተውኛል።
  5. እዚህ ጋር ካላቆምኩ፡ የኔም ጽሁፍ ሊንዛዛ ነው። ተንዛዛ እንጂ። ተንቀዋለለ።
  6. ባጠቃላይ የአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፍ አርቆ አሳቢ፡ ስትራቴጂካዊ፡ ሳይንሳዊና የበሰለ ለመምሰል ጥረት አድርጓል። በርግጥም አንዳንድ ጠቃሚ ሀሳቦችን ለመፈንጠቅ ሞክሯል። ነግር ግን፡ በአብዛኛው፡ ጽሁፉ በርስ በርስ ቅራኔ የሚሰቃይ፤ በኢህአዴግ የአባይ ግድብ ማጭበርበሪያ ዘመቻ ዙሪያ ያለውን ተቃውሞ  በቅጡ ያልዳሰሰ፤ ይልቅስ ሌሎችን በሚከስበት የስሜታዊነት ደዌ ክፉኛ የታመመ ሆኖ አግንቼዋለሁ። በመሰረቱ የአባይን የማጭበርበሪያ ግድብ የምንቃወመው ሰዎች ካለን፤ ተቃውሟችን አቶ አያልሰው ደሴ እንዳሉት ሳይሆን ….
ተጨማሪ ያንብቡ:  የፕሬዝዳንት ሙላቱ ሪፖርት እና የፋና ውይይት…. ግርማ ሠይፉ ማሩ

ይቀጥላል …..

እኛው ነን። አያ ተክሌ፤ ከተረንቶ። ሰኔ፡ 2005/2013

በዚህ ይመይሉልን፡ lijtekle@gmail.com

7 Comments

  1. Tekle You have nailed it !! ayalsew seem to have bored being immigrant for such long time .Thus has taken the opportunity of the Abay crisis as a means to budge w woyane . I hope will declare soon as ardent supporter of woyane .Good luck corporal Ayalsew to be welcomed and in joining those big time opportunists like solomon ,Neway and many others.

  2. I think, Mr, Ayalesew is another Ledetu Ayalew. He is going to plan to walk the first lader of woyane. you can support TPLF with out writing this non sense fiction.I read all . it is boring. all point are the same. I am sure you do not understand what are peaple saying. no one oppose the Hitlor Melese dam. We are asking the basic question which are bread ,freedom and democracy before the dam.did you understand gashe Ayalesew. please be silent and you can start to go as you know your plan.

  3. sewyew absho biTie sayaqemsut ayQerm d..ro dro geTer eyale. I am not sure if Tekle was stashed with some “firfari” from the leftover from Egypt’s grant to Ginbot 7, although big portion of it is planned to train 1 “ganta” of Ginbot 7 army who could tople the TPLF government.

  4. Ayalsew Dese , le Hagerachew yeseru talaq Ethiopiawe nachwe!!!

    Tekle yehe nankuwan bante ayamerem !!!

    Jegnoch Abatochachen yesatatu marem enji zelefna men aletaw ?

  5. Liji Tekle

    Mr.Ayalsew Dessie put his argument based on evidence but yours look like to insult him.instead of arguing based on the fact. this is a childish behaviour.Last time you criticise ESAT like that.

  6. Lij Tekle really you are a kid. Your knowledge and experience is very low when compared to gallant Ethiopian Ayalsew Dessie. If you understand his writing, Ayalsew doesn’t invite Ethiopians to support Weyane for purpose of building the Nile Dam. But he said, still our opposition is continued, by any means the building of the dam is also important to Ethiopia if practiced which it can bring to dismiss the colonial agreement that honors Egypt and Sudan for century and would brought a new era to Ethiopia’s right of ownership of the Nile. Your article is simply based on antagonistic ideas and biased which can’t be supported by tangible evidences. Please, don’t continue your boring article, no one will read it may be some Weyane idiots use it for their usual degrading and insulting our known scholars and heroes like Ayalesew Dessie.

Comments are closed.

Share