አንድነት ፓርቲ በፀረ -ሽብር ሕጉ ላይ ሕዝባዊ ንቅናቄ ሊጀምር ነው

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከአራት ዓመት በፊት የፀደቀውን የፀረ-ሽብር ሕጉን ለማሰረዝና ይሄንኑ ሕግ ተላልፈዋል ተብለው በእስር ላይ የሚገኙ የፓርቲውን አመራሮችንና ጋዜጠኞችን ለማስፈታት በአይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ ሕዝባዊ ንቅናቄ እንደሚጀምር አስታወቀ።
የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ አባልና የሕዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዳንኤል ተፈራ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት የአንድነት ፓርቲ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ሰለባ ከሆኑ ፓርቲዎች አንዱና ግንባር ቀደሙ መሆኑን በመጥቀስ አዋጁን ለማሰረዝ በሚሊዮን የሚቆጠር የሕዝብ የድጋፍ ፊርማ በማሰባሰብ አዋጁ ሕገ-መንግስቱን በግልፅ የሚጥስ መሆኑን ማስረጃ በማቅረብ ጭምር ክስ ለመመስረት መታቀዱን ተናግረዋል።
የህዝባዊ ንቅናቄ አተገባበሩን በተመለከተም በነገው ዕለት በፓርቲው ጽ/ቤት የፖለቲካ እስረኞች ቤተሰቦች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ወኪሎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ጋዜጠኞች በተገኙበት ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ንቅናቄው መጀመሩ በይፋ እንደሚበሰር አመልክተዋል።
ሕዝባዊ ንቅናቄው “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” በሚል መሪ ቃል የሚጀመር ሲሆን ለቀጣዮች ሶስት ወራትም በተከታታይነት እንደሚቀጥል ከአቶ ዳንኤል ገለፃ መረዳት ተችሏል።
ፓርቲው ባስቀመጠው የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት በአዲስ አበባና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች መዋቅሮቹን ሲያደራጅ መቆየቱን ያስታወሱት አቶ ዳንኤል ሕዝባዊ ንቅናቄውን ትርጉም ባለው ደረጃ ማንቀሳቀስ የሚያስችል በአዲስ አበባ በ23ቱም ወረዳዎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውጪ በዋና ዋና ከተሞች መዋቅር መመስረቱንም አረጋግጠዋል። የሕዝባዊ ንቅናቄውን ዓላማ ከዳር ሊያደርስ የሚችል ግብረኃይል መደራጀቱን አያይዘው አመልክተዋል።
ሕዝባዊ ንቅናቄው የሚካሄደው የድጋፍ ፊርማ በማዘጋጀት፣ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍና የአደባባይ ላይ ሕዝባዊ ስብሰባዎች በማካሄድ እንደሆነም አቶ ዳንኤል ገልፀዋል።

፦ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያዊቷ ወጣት በአትላንታ 25 ዓመት እስር ተፈረደባት

6 Comments

  1. unless united with all other parties and be ONE. It won’t work it will be a good advantage for these cruel juntas to single you out and put you in jail.please be UNITE before you do any struggle path.

  2. Go a head !!! let you not give respite for woyane .keep the struggle alive by raising issues that over boil the woyane thugs. Go andnet !!!! go andnet.

  3. This is just another empt talk with no substance. Bravada and boasting is no use for the people. Action is what matters most. Any political party claiming to represent the people has a responsibility and it is better keep quiet instead of simply talking and doing nothing.

  4. ዛሬ፡አንድነት፡በፅ!ቤቱ፡ዉስጥ፡ያነሳቸዉ፡ነጥቦች፡ወቅታዊ፡ናቸዉ፡የዜጎችን፣መፈናቀል፣የፀረሽብር፡ህግ፡እንዲሻር፣የኑሮዉድነት፣የመሬትሽሚያ፡ንግዱ፡ፍትሀዊእንዲሆን፡ይላል፡ጥያቋዉአጠር፡ሲልፓርቲዉ፡ህገመንግስቱ፡በግልፅ፡ተንዶመንግስት፡በሀይማኖት፡ጣልቃመግባቱን፡በመቃወም፡ከአንድ፡አመት፡በላይ፡የወሰደዉ፡የሙስሊሙማህበረሰብ፡ጥያቋ፡መፍትሄ፣ሳያገኝ፡እስርናስደቱ፡ተጠናክሮ፡በቀጠለበት፣በአጀንዳ፡አለመያዙ፡ለምንድነዉ?

  5. አንድነትያነሳቸዉነጥቦችህዝባዊናቸዉ፡ነገርግን፡በሚሊዮንየሚቆጠሩሙስሊሞችከአመትበላይለሆነጊዜየሀይማኖትጣልቃገብነትንበመቃወማቸዉበመላዉሀገሪቱእየደረሰባቸዉ፡ያለዉ፡በደልስ፡ግድያዉእስራቱስደቱ፡_ህዝባዊነት፡ለማነ?ቀደም፡ሲልአንድነትሙስሊሙንበሚመለከትያወጣዉመግለጫ”አገምጠገም”እንደነበርምይታወሳል፡ምናልባትምፓርቲዉ”በናፋቂነት”ይቸገራልከመድረክምጋርያላግባባዉጉዳይአንዱናፋቂነትመንፈስመሆኑእየተነገረነዉ።እስቲ፡እናያለን

Comments are closed.

Share