June 11, 2013
10 mins read

የዶ/ር መሠረት ቸኮል አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ

edom
በአሁኑ ወቅት የጋዜጠኝነት ትምህርቷን እየተከታተለች የምትገኘው የዶ/ር መሠረት ቸኮል ልጅ ኤዶም የአባቷን መጽሐፍ ይዛ

(ዘ-ሐበሻ) በቅርቡ ያረፉት ዶ/ር መሠረት ቸኮል ላለፉት 8 ዓመታት ሲለፉባት የነበረውና የኢትዮጵያን የ100 የፕሬስ ታሪክ የሚያሳይ መጽሐፍ ለገበያ መቅረቡን ቤተሰቦቹ ገለጹ። ጥልቀት ባላቸው ትንታኔዎቹና ቀላል አቀራረቡ የሚታቀው ጋዜጠኛና መምህር ዶ/ር መሠረት ቸኮል የጻፈው ታሪካዊው መጽሐፍ “The Quest for Press Freedom: One Hundred Years of History of the Media in Ethiopia” የሚሰኝ ሲሆን በamazon.com እንዲሁም በባርነስ ኤንድ ኖብል የመጽሐፍት መሸጫ መደብሮች እንደሚገኙ ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።
ይህ መጽሐፍ ለማስተማሪያነት ሁሉ ታስቦ እንደተጻፈ የገለጹት የዶ/ር መሠረት ባለቤት ወ/ሮ በልዩ ወደፊት መጽሐፉን በአማርኛ ለማሳተም እንደተዘጋጁም ገልጸዋል። “ዶ/ር መሠረት ይህን መጽሐፍ በአማርኛም ጀምሮት ነበር። ሆኖም ግን በድንገት ሳጨርሰው በማረፉ ወደፊት አስተርጉመን ለማቅረብ እንሞክራለን” ያሉት ወ/ሮ በልዩ ይህን መጽሐፍ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲያነቡት ጋብዘዋል።
የዶ/ር መሠረት ቸኮልን መጽሐፍ ከኢንተርኔት ላይ ለመግዛት እዚህ ይጫኑ
በመጽሐፉ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለምትፈልጉ ወ/ሮ በልዩን በስልክ ቁጥር 651-983-2052 በመደወል ማነጋገር ትችላላችሁ።
The Quest for Press Freedom is a book about press development and freedom in Ethiopia, with a focus on the state media. It examines the building of a modern media institution over the last one hundred years of its existence, and the restrictions against its freedoms. The significance of this work lies in its originality and that it addresses these two issues across three distinct epochs: the monarchy era, the Marxist military regime, and the current ethnic federalist regime. The book examines the political and social situations in each of these periods, and analyzes the effects they had on the media. The book also provides examples of how journalists working for the government-run media have a strong desire to exercise their constitutional right to press freedom. In the final chapter, Reta offers recommendations for a more viable media system in Ethiopia.

በአሁኑ ወቅት የጋዜጠኝነት ትምህርቷን እየተከታተለች የምትገኘው የዶ/ር መሠረት ቸኮል ልጅ ኤዶም የአባቷን መጽሐፍ ይዛ
የዶ/ር መሠረት ቸኮል አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ 1

ዶ/ር መሠረት ቸኮል ማን ነበር?
ከአባቱ ከአቶ ቸኮል ረታ እና ከ እናቱ ወ/ሮ የእናት ፋንታ አስረስ በ1950 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ ተወለደ። በአምስተኛው ዓመቱ በፈንጣጣ በሽታ ተጠቂ በመሆኑ በተደረገለት ህክምና ሕይወቱን ለማትረፍ ቢቻልም የዓይን ብርሃኑን የማጣት አደጋ በስምንት ዓመት ዕድሜው ደረሰበት። በሰበታ የዓይነ ስውራን ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተከታትሏል። በተማሪነት ዘመኑ ለመዝሙርና ለሙዚቃ እንዲሁም ለመጽሐፍ የነበረው ፍቅር ከፍተኛ ነበር። በዕድገት በህብረት ዘመቻ በባህር ዳር ከተማ በመምህርነት ተመድቦ ግዴታውን ለመውጣት ችሏል። በ1971 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ጥናት ኢንስቲቱት በ እንግሊሽ ዲፓርትመንት ገብቶ በ1974 ዓ.ም ከጠቅላላው ተማሪ በላቀ ውጤት የዓመቱ ኮከብ ተማሪ ሆኖ ከወቅቱ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት እጅ የወርቅ ተሸላሚ በሆን የመጀመሪያውን ዲግሪ አገኘ።
ከዚያም Ethiopian Extrnal Service ተብሎ በሚታወቀው መስሪያ ቤት በጋዜጠኝነት ተቀጥሮ በሪድዮ ጣቢያው በየሳምንቱ የሚደረገውን የባህልና የሙዚቃ እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች የሚጋበዙበት የውይይት ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን ያገለገለ ሲሆን ማዘር ትሬዛን በፕሮግራሙ ላይ ለማቅረብ የቻለ፤ በአነባበቡ፣ በፕሮግራሙ ጥልቀት፣ ታማናዊ በሆነ አቀራቡ የብዙ አድማጮችን ቀልብ የሳበ ነበር። በተለያዩ ሃጉሮች የተለያዩ ስልጠናዎችን ያገኘ ሲሆን ከቀይ ጨረቃ አፍሪካ አቀፍ የሬድዮ ፕሮግራም አምስት ጊዜ እውቅና አግኝቷል።
በ1982 ዓ.ም ከባለቤቱ ወ/ሮ በልዩ በላይ ጋር ህጋዊ ጋብቻ በመፈጸም በ1983 ዓ.ም የትምህርት ዕድል በማግኘቱ ወደ ሜኔሶታ በማቅናት የማስትሬት ዲግሪውን ጀምሮ በ1986ና በ1989 ዓ.ም የኮምዩኒከሽንና በፖለቲካል ሳይንስ የማስተርስ ዲግሪውን፣ በ1991 እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪውን (PHD) በመገናኛ ብዙሃን ትምህርት ከዩኒቨሪሲቲ ሚኒሶታ አግኝቷል።
ትምህርቱን ከጨረሰ በኋላ በከፍተኛ ተምህርት ተቋሞች በማስተማር ሥራ ተሰማርቶ በዩኒቨርሲቲ ሚኒሶታ፣ በዊስካንሰን ሪቨል ፎል ዩኒቨርሲቲ፣ በኦሃዮ በሚገኘው አሽላንድ ዩኒቨርስቲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚቺጋን ከመምህርነት እስከ ተባባሪ ፕሮፌሰርነት አገልግሏል።
ከማስተማሩና ከምርምሩ ተጨማሪ የተለያየ ኮሚቴዎች አባልና ስብሳቢ በመሆን ሙያዊ ግልጋሎት ሰጥቷል። በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፊችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች አቅርቧል። እንዲሁም ከአካዳሚ ጋር ያልተያያዙ ሁለት መፅፎችን ለአንባብያን አበርክቷል።
The quest for press freedom በኢትዮጵያ የ100 ዓመታት ሜዲያ ታሪክ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ሰጥቷል። ይህ መጽሐፉ በቅርብ ጊዜ በገበያ ላይ እንደሚውል ሕይወቱ ከማለፉ በፉት ለጓደኞቹና ለዘመድ አዝማድ አብስሯል። እንዲሁም ሁለት ለመጨረስ ያልታደላቸው ያሬድ ገብረሚካኤልና የዛሪኤይቱ ኢትዮጵያ ጽሁፎችን ለ Encyclopedia Aethiopica Vol.5 አዘጋጅቶ እንደነበር ይታወቃል።
ዶክተር መሠረት ከመምህርነትና ከምርምር ሥራዎቹ ባልተናነሰ መልኩ የሚታወቀው በሰባዊ መብት ተሟጋችነቱ፤ ለሃገሩ ባለው ቅናቂ አስተሳሰብና በተለይም ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በሚሰጠው ትንታኔ ነበር። በዚህ በሚኒሶታ የሚገኘው የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ የ እንግሊዘኛ ዜና በማዘጋጀት፤ በአሜሪካ ሬድዮ ጣቢአ የዘወትር ተባባሪ በመሆን፤ በ1995 ምርጫ ዘመን ድምጽ ላጡ ድምጽ በመሆን ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ ዕውቀቱን በመለገስ፣በተለይዩ ከተሞች በተናጋሪነት በመጋበዝ አስተዋጽሆ አድርጓል።
በ2007 በሜሪላንድ ተቀማጭ የሆነ የታዋቂ ግልሰቦችን ታሪክ የሚያጠናቅር ድርጅት በማቁቋምና የድርጅቱም ሊቀመንበር በመሆን አገልግሏል። በሕይወት ዘመኑ ብዙ ልጆችን የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ አድርጓል።
መሠረት በሥራው ላይ የማይኩራራ፣ ይህን አደረኩ ብሎ የማይናገር፣ እራሱን ዝቅ አድርጎ ከማንኛውም ሰው ጋር ተግባብቶ የሚኖር፣ ለ እውነት ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ እንደነበር በቅርብ የሚያውቁት ጓደኞቹ ይናገራሉ።
ባለፉት ሁለት ወራት የጉበት ካንሰር በሽተኛ መሆኑን ካወቀ በኋላ ከእራሱ ይቅል ለወገኖቹ በማሰብ ሌሎች ተገቢውን ምርመራ እንዲያከናውኑ ያሳስብ ነበር። ዶ/ር መሠረት ቸኮል በተወለደ 55 ዓመቱ ቅዳሜ ሕዳር ስምንት ቀን 2005 ከጠዋቱ 5am ላይ ህክምና ሲደረግለት በነበረው በፓርክ ኒክለት ሜተዲስት ሆስፒታል ባለቤቱን ወ/ሮ በልዩ በላይን፣ ልጁን ኤደን መሠረትን፣ ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን በመለየት ከዚህ ዓለም አልፏል።

 

Previous Story

የሰማያዊ ፓርቲ ተስፋ

ሸንቁጤ
Next Story

ዛሬም እዚያው ነሽ ወይ – (ሸንቁጤ ከአዲስ አበባ)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop