የሽራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች የስር ተላላኪዎቻቸውን ሕዝቡ ኢሕአዴግን እንዲመርጥ አልቀሰቀሳችሁም በሚል ከሃላፊነታቸው ማውረዳቸው ተዘገበ

የሽራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች በነሱ ስር ሆነው ሲያገለገሏቸው የቆዩትን ሰዎች; ህዝቡን ኢህአዴግን እንዲመርጥ በሚያስችል መንገድ አልቀሰቀሳችሁትም በማለት ከሃላፊነታቸው እያወረዷቸው እንደሆኑ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ገለፀ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ::

በሸራሮ ከተማ የሚገኙት አስተዳዳሪዎች በነሱ ስር የሚገኙትን በሃላፊነት የተቀመጡ አባላት ላይ እምነት ስላጡባቸው ነዋሪው ህዝብ ህ.ወ.ሃ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን እንዲመርጥ የሚያስችል አስፈላጊውን ቅስቀሳ አላደረጋችሁለትም በሚል ምክንያት ከሃላፊነታቸው እያወረዷቸው መሆኑን የገለጸው መረጃው ከስልጣናቸው ከተወገዱት መካከልም የወረዳው ፕሮፖጋንዳ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሃፍቲና የወረዳው የሴቶች ሃላፊ ወ/ሮ ደስታ ማሙ እንደሚገኙባቸው ለማወቅ ተችሏል።

እነዚህ በሃላፊነት ደረጃ ሲሰሩ ቆይተው ባሁኑ ሰአት ከስልጣናቸው የታገዱት የህወሃት ኢህአዴግ አመራሮች ስርአቱ በህዝቡ ላይ ያለው ተቀባይነት ስላጣ የስርዓቱ ሃላፊዎች በነሱ ስር ለሚገኙ አመራሮች ከሃላፊነታቸው እያወረዷቸውና እየሾሟቸው አንደሆኑና; ይህ ድርጊትም በሸራሮ ከተማ ብቻ ሳይሆን; በመላው ያገራችን አካባቢዎች እየተሰራበት እንደሆነ መረጃው አክሎ አስረድቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  " ሽርፍራፊ ስልጣን ለግለሰብ ኢጎ እና ጥቅማጥቅም እንደሆነ እንጂ ለህዝብ የተለየ አማራጭ ሃሳብ እንዲያገኝ አያደርግም ! " ተክሌ በቀለ
Share