January 21, 2015
20 mins read

ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ – 4

የጎንደር ሕብረት

ዛሬም እንደ ጥንቱ ፤ ህዝባችን በፈለገው ቦታ መብቱ እና ክብሩ ተጠብቆለት፤ እንደ ከብቶች ቦታ ሳይከለልለት፤ እንደሰው በነፃነት በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ የመኖር መብቱ እስከሚረጋገጥለት ድረስ፤ ለህሊናችን ግድ የሚለውን፤ ሁኔታው የፈቀደውን፤ አቅማችን የቻለውን ለህዝባችን እና ለአገራችን የሚጠቅመውን ሁሉ ከማድረግ ጭራሽ አንቆጠብም። ሕዝቡን እና ኢትዮጵያ አገሩን የሚወድ ሁሉ የነፃነትን ቀን በአጭር ጊዜ ያይ ዘንድ የዚህ ተግባር ማዕድ ተካፋይ መሆን የዜግነት ገዴታው ነው።
በተደጋጋሚ የምናወጣቸው መግለጫዎች ጎንደር እና አካባቢዋን በዋናነት የሚመለከት ቢሆንም፤ በመላዋ ኢትዮጵያ አገራችን ከሚደርሰው የአስተዳር ግፍ እና ሥቃይ አካል የሆነውን፤ በአካባቢው በመወለዳችን ለመላው ኢትዮጵያዊ ወገናችን በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ይረዳል ብለን ስላሰብን እና ለትግሉም አጋዥ ይሆን ዘንድ አንደኛዋን ጫፍ ለእይታ ማብቃታችን ዋጋ ይኖረዋል በሚል ዓላማ ነው።

(ጎንደር ፋሲል ግምብ – ፎቶ ፋይል)
ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ - 4 1

እናም ለዛሬዋ መልክታችን ሕዝባችን ያለበትን ሁኔታ የሚያሳይ የታሪክ ማነፃፀሪያ ይሆነን ዘንድ፤ የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ በመጥቀስ መጀመሩን ወደድን። በአንድ ወቅት ግብጽን ለረዥም ጊዜ በጭካኔ ይገዛ የነበረው ፈርዖን ራምሲስ በግብፅ ውሥጥ በባርነት ሲኖሩ በነብሩት እሥራኤላውያን ላይ ግፍ እና መከራውን ሲያበዛ ያዬ እግዚአብሔር፤ ሊታደጋቸው ሲያሥብ፤ ፈርዖን ወደ ህሊናው ይመለሥ ከሆነ በሚል ታምራቱንም ያሳዬው ዘንድ “ሙሴን ለፈሮኦን አምላክ (ገዥ)፤ አሮንን ነብይ” አድፍጎ አዘጋጀ (ዘጸአት 7፡1)። በመጀመርያ፤ ሙሴ የእሥራኤላውያን የነፃነት ቀን አሁን መሆኑን ለፈርዖን በነገረው እና ፈርዖን ‘’አሻፈረኝ’’ ባለ ጊዜ፤ መልዕክታቸው ከእግዚአብሔር መሆኑን ይረዳ ዘንድ እዲያሳዩት ከተሰጣቸው የመጀመሪያዋ ተአምር፤ የአሮንን በትር በፈርዖን እና በሹማምንቶቹ ፊት እባብ ማድረግ ነበር። ትቢተኛው ፈርዖንም ምትሀተኞችን አስጠርቶ እባብ እንዲሰሩ እና ከአሮን የማይተናነሥ ኃይል እንዳለው እና ታምራትን እንደሚያደርግ ለማሳዬት ሞከረ። ሆኖም የአሮን እባብ የፈፈርዖን ምትሀተኞችን እባቦች በሙሉ ዋጠቻቸው። ይህም ቢሆን ፈርዖንን አላሥደነገጠም። የእግዚአብሔር ታምርም በሙሴ አማካኝነት ለፈርዖን ምን እንደሚያመጣ እያሥነገረ ቀጠለ። ውሃ ወደ ደም ተለወጠ፤ የግብፅ ምድር በእንቁራሪቶች ተሞላች፤ ሰውና እንሰሳቱን በቅማል አሥወረረ፤ እንሰሳትን ጨረሰ፤ ሰውና እንሰሳትን በቁሥል አመረቀዘ፤ ሰውን እና እንሰሳትን እንዲሁም አዝዕርትን በበረዶ መታ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ፍርዖን ልቡ ደነደነ እንጅ አልራራም፤ ከትቢቱም አልወረደም። ወደ ሰባአዊ ህሊናውም አልተመለሰም። በመጨረሻም፤ እግዚአብሔር የፈርዖን ኃይል ይሰበር ዘንድ ተጨማሪ መቅስፍት በቤቱ ውሥጥ ማወጅ ነበር። ይኽውም፤ የግብፃውያንን የበኩር ልጆች መግደል። በዚህም ጊዜ በተደረገው ተአምር ሁሉ ጫፉ ያልተነካው ፈርዖን ራምሲስ የበኩር ልጁን በሞት ተነጠቀ። ሃዘን እና ዋይታ በቤቱ ነገሠ። የሞት መከራን በግፈኛ ወታደሮቹ እና አሽከሮቱ አማካኝነት ለዘመናት በእሥራኤላውያን ላይ የፈፀመው ፈርዖን ራምሲስ ፤ ብድራቱን ይከፍል ዘንድ የመጨረሻው ጊዜ መድረሱን የራሱ የራምሲስ በኩር ልጁ በሞት ሲነጠቅ አዬ። በዚህ ጊዜ ነበር፤ ለዘመናት በባርነት ቀንበር የያዛቸውን እሥራኤላውያን ከግብጽ ባርነት ነፃ ወጥተው ወደ ቅድስት አገራቸው ይሄዱ ዘንድ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1270 ለመፍቀድ የተገደደው።

የኛም ዘመኑ ያሥነሳቸው የአገራችን ፈርዖኖች፤ ተመሳሳይ ታምር እይተዋል። ከላይ ከሰሜን አንዱ ቡድን፤ ከመሃከል ሌላው ሰይጣን ሆነው አገር ሊያተራምሱ አቅደው የገቡት ሁለቱ ሰይጣናዊ ቡድኖች ባልታሰበ ጊዜ እርስበርሳቸው በጠላትነት ተሰልፈው እንዲቆሙ አድርጓል። ከበርሃ ጀምረው አብሯቸው ከተሰለፈውም ጋር ሳይቀር በሃሳብ ያልተግባባቸውን እየገደሉ ምኒልክ ቤተ መንግሥት የገቡት በተለያዬ ጊዜ እየተፈረካከሱ፤ በእሥራት፤ በሥደት እንዲበተኑ አድርጓል። የወያኔው ዋና ‘’የፖለቲካው እና የሃይማኖት መሪዎች’’ ነን ብለው በጉልበት ሥልጣን ጨብጠው ፈላጭ ቆራጭ የነበሩት በአንድ ሰሞን አፈር ለብሰዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን ማዬትና ማሥተዋል የተሳናቸው ቀሪ ገዥዎች ልብ ማለት ይገባቸው ነበር፥ ግን አላደረጉም። አሁንም ለዘላለማዊ የሥልጣን ዘመናቸው መመኪያ የነበረው የአዬር ኃይል አባሎቻቸው እሥከ ተዋጊ ጀቶቻቸው ከአይናቸው እዬተሰወሩ እጃቸውን ለጎረቤት አገር እያሥረከቡ ነው።

ይህ ሁሉም ሆኖ የኢትዮጵያችን ዘመነኛ ፈርዖኖች፤ ዛሬ እንደለመዱት የሕዝባችንን ሥቃይ እና መከራ አጠናክረው በመቀጠል፤ የጎሳ ሽንሸናቸውን ባላዳረሱበት የአገራችን መልካዓ ምድር ለማድረስ፤ በቀሩት የአገራችን አካባቢዎች ዘልቀው በመግባት ለዘመናት ተዋሕዶ የኖረውን የጎንደርን ሕዝብ “ቅማንት፤ እና አማራ” በሚል እርሥ በርሥ በማጋጫት የማቱሳላን እድሜ የማግኘት ከንቱ ምኞት እየተመኙ የግፍ አገዛዛቸውን ቀጥለዋል።

ስለዚህም፤ አሁንም ደግመን እንላለን፦ የዘመኑ ግፈኛ የአካባቢ የመንግሥት አሥተዳዳሪ አካላት ሆይ! ከላይ ካስቀመጥናቸው የፈርዖን ራምሲስ አምሳያዎች ጥቂት ግፈኞች የመጨቆኛ መሳሪያዎች ሁናችሁ የምትቀጥሉት እሰከመቸ ድረስ ነው? በእድሚያችሁ እና በጊዜያችሁ ብዙ ተለዋዋጭ ታሪኮችን አይታችኋል። ማንም ይሁን! ምን! ጭራሽ ዘላለማዊ ነገር ከእግዚአብሔር መንግሥት በቀር ምንም አይነት ዘላለማዊ የሆነ ሰው ሠራሺ መንግሥት የለም። በእጃችን ላይ ያለ የቅርብ ጊዜ ትውሥታችን እንደሚያሥረዳን፤ ማንም ሊነካቸው የማይችል ‘’ስዩመ እግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔር ሹም” እየተባሉ ይሰገድላቸው የነበሩት፤ የንጉስ ነገሥት ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት፤ ምድርን እና ሰማይን የሚያንቀጠቅጥ ወታደራዊ ኃይል አለው ይባል የነበረው ወታደራዊው የደርግ መንግሥት፤ ባልተጠበቀ ጊዜ እና ሁኔታ እንዳልነበሩ ሲሆኑ አይተናል። በደቂቃ ስድሳዎቹ ”የቡርዧ ርዝራዦች” ተብለው በጅምላ ሲረሸኑ፤ ‘’የአረመኔው ደርግ ወታደሮች እና ደህንነቶች’’ ተብለው ግማሹ በእሥር፤ ሌላው የጎዳና ለማኝ ሲሆን ዐይናችን ያዬው፤ ህሊናችን የሚዘክረው የቅርብ ጊዜ ትውሥታ ነው። እናንተም እንደነሱ፤ ማለፋችሁ አይቀሬ ነው እና፤ የግፍ ዘመናችሁ ማብቃቱን ከምታይዋቸው ምልክቶች ተረዱ። ዛሬ በጎንደር እና አካባቢዋ በቅማንት ብሔረሰቦች የመብት እና ራሥን በራሥ የማሥተዳደር ጥያቄ ምክንያት እየተሰራ ያለው ግፍ ጭራሽ ታሪክ የማይረሳው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ እሳት እየጫራችሁ መሆኑን፤ ገና በጥዋቱ ለማመላከት ሞክረናል። አሁንም የምታገለግሉት ሥርአት ወገንን ከወገን በመለያየት በቋራ እና በአለፋ ጣቁሳ ከአማራው ወገናቸው ጋር ተግባብተውና ተጋብተው በመዋሐድ በፍቅርና በአንድነት ይኖሩ በነበሩ እና አሁንም ባሉ የቅማንት ምሁራን እና አርሶ አደሮች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የጥፋት አላማ አስፈፃሚዎች ሁናችሁ መቆማችሁ ታሪክ የማይረሳው በደል መሆኑን ተረድታችሁታልን?

በጎንደር ታሪክ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ በራሷ ተወላጆች፤ ክብሯ እና ወሰኗ ተሸራርፎ ለባዕዳን እና ኢትዮጵያን እንደ አገራቸው ለማያዩና ታሪኳን ለማያከብሩ ግፈኛ ተሥፋፊዎች እንደ ቲማቲም ሲቸረቸር ማየት ደግሞ ልብ ያደማል። በዚህ ምክንያት፤ የናንተን የመምራት ብቃት እና እምነት ያጡት የታች አርማጭሆ እና ወልቃይት ጠገዴ ወገኖቻችን ወሰናቸውን ለማስከበር እየከፈሉ ያለውን መሥዋዕትነት፤ የዛሬ ሥልጣናችሁን እና ኃይላችሁን ተጠቅማችሁ ከተሥፋፊዎች ጋር ወግናችሁ ለመጨፍለቅ የምታደርጉት ሙከራ በራሱ በአገር ክህደት ያሥከሥሳል፤ ያስፈርዳል። የማይገባን ነገር! ሰላም እና መረጋጋት፤ ታሪክ እና ክብረ-ወሰን የሌላትን አገር እንዴት ነው ልታሥተዳድሯት የምትመኙት? ልብ ይሥጣችሁ።

በጎንደር እና በመላ አካባቢዋ የምትኖሩ የአማራ ተወላጆች ሆይ! ለዘመናት ሳይናቅ ተክብሮ በታሪክ ማህደር ሲጠቀሥ የኖረው የአብሮነት መኖር ታሪክህ፤ ዛሬ መሰሪ ከፋፋይ መሪዎች ባመጡብህ የቅማንት እና አማራ ጣጣ ፈተና ላይ መውደቁን ከተረዳን ቆይተናል። በፈተና ከሚጸና ህብረተሰብ መወለዳችንንም እናምናለን። እናም፤ የዛሬ ግፈኛ ገዥዎች፤ እንደ አለፉት ገዥዎች፤ በህዝብዊ ኃይል መንኮታኮታቸው አይቀሬው ሰዓት መድረሱን በዐይናችን በምናያቸው ክሥተቶች መረዳት ብዙም አይዳግተም እና፤ በመጨረሻዋ ሰዓት የመጣብህን የመከፋፈል እሳት፤ ውሃ ይዘህ እንድታጠፋው ከወዲሁ አደራ እንላለን። እሳት የሚጠፋው በውሃ እንጂ፤ በቤንዚን አይደለም እና። መሰሪዎች፤ ከጎረቤቶችህ፤ ከወንድሞችህ፤ ጋር በሰላም መኖርህ፤ ለነሱ ሥልጣን አደጋ ልትሆን ሥለምትችል፤ አንድ ላይ እንዳትቆም የክፋፍለህ ግዛው እሳት ለኩሰዋል። ይህን የተለኮሰ እሳት ወደ ለኳሾቹ ልቀቅ እንጅ፤ እርስ በርሥህ እንዳትቃጠልበት ከአብራክህ የወጣን የቅማንት እና አማራ ልጆች “ጎንደር ሕብረት” ብለን በመደራጅ በሆነው ሁሉ ከጎንህ ለመቆም ቆርጠን ተነሥተናል። እናንተም ወገኖቻችን በመጨረሻው የሥራዓቱ መውደቂያ ሰዓት እንዳትሳሳቱ ደራ እንላለን።

የቅማንት ብሔረሰብ ወገኖቻችን ሆይ! አንድ እግሩን ጅብ የሚቆረጥመው ግለሰብ፤ ባለቤቱ ጅብ ቤታችን ገባ ሥትለው፤ ዝም በይ የኔን እግር ነው የሚቆረጥም አለ እንደሚባለው፤ የመብትን ጥሰት ለማሥመለስ ሲባል ይዛችሁ የተነሳችሁት የመብት ጥያቄ በህገመንግሥት ሥም ተለጥጦ የት ሊደርሥ እንደሚችል ማሳሰብ ከጀመርን ጊዚያቶች አለፉ። ከላይ መጀመሪያው ላይ ያሥቀመጥነው የፈርዖን ምሳሌ እዬታዬ ያለው በናንተም ላይ ጭምር ነው። ዛሬ የአምናው ሥጋታችን እውን ሆኖአል። ምሆሮች ከመሥሪያ ቤቶቻቸው፤ ገበሬዎች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ ነው። ሰባአዊ መብት፤ በገመድ የሚለካ የእርሻ መሬትን ያክል ተቆርሶ የሚሰጥ ጠባብ መብት አይደለም። ሰባአዊ መብት ለአንድ ጎሳ ብቻ የሚቸር ችሮታም አይደለም። ለዘመናት በኩራት ሲጠራበት የኖረውን የቅማንት ብሔረሰብ ሥም የነፈገ፤ ከፎርም/ቅጽ ላይ የሰረዘ እና ከሌላው ወንድሞቻችን ጋር በጥላቻ ጎራ እንድንለያይ ያደረገ መሰሪው መንግሥት እንጅ፤ ለዘመናት በክፉ እና በበጎ አብሮህ የኖረው ወገናቻን አማራው አይደለም።

በመሆኑም፤ ሁሉም የቅማንት ተወላጆች የሰው ልጅ መሰረታዊ የዲሞክራሲ መብት ከቡድን መብት የራቀ፤ ሰውን በሰባዊነቱ የሚያስከብር መሆኑን ተረድታችሁ፤ የጀመራችሁትን ትግል ከጠበበ የጎሳ ኩሬ አውጥታችሁ፤ ሰፊ ባህር ወደሆነው ሕዝባዊ ትግል በመቀላቀል ለመሰረታዊ ለውጥ አጋዥ ትሆኑ ዘንድ በድጋሚ እናሳስባለን። ይህ ባይሆን እና ካፈርኩ አይመልሰኝ አይነት የማይቻለውን እንደሚቻል አድርጎ በመወጠር ለሚመጣው የህይወት ጥፋት እጅግ በታሪክ እና በህግ ፊት ያሥጠይቃል።
በመጨረሻም፤ ጎንደር በቅማንት ብሔረሰቦች የመብት ጥያቄ ምክንያትም ይሁን፤ በመሬት ቅርምት ምክንያት ሥትታመሥ እያያችሁ፤ ዝምታን የመረጣችሁ ምሁራን፤ የኃይማኖት መሪዎች እና ታዋቂ የአገር ሺማግሌዎች ጉዳዩን ለማረጋጋት አቅሙ እና ችሎታው ያልችሁ ዜጎች፤ በወገናችሁ ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር እያያችሁ እንዳላያችሁ፣ እየሰማችሁ እንዳልሰማችሁ ሁናችሁ መቀመጣችሁ ጥፋቱን ከሚያራምዱት እኩል በሃላፊነት የሚያሥጠይቅ ባይሆንም፤ ቀን ሲያልፍ ራሥን ቀና አድርጎ በህ/ሰቡ መካከል በኩራት የማያራምድ መሆኑን ተረድታችሁ፤ ጉድዩን በባለቤትነት እንድትቀላቀሉት እና የመፍትሄው አካል እንድትሆኑ በአጽንዖት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የጎንደር ከፍለ ሀገራዊ ስሜት: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስሜት ዋና መገለጫ ነው !!!
የጎንደር ሕብረት ።

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop