ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እና ዶር ታዬ ወ/ሰማያት ወዴት ገቡ?

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ እና ዶር ታዬ ወ/ሰማያት ወዴት ገቡ?

ዛሬ ካልወጡሰ መቼ?        

ከሎሚ ተራ 

ዝነኛውና የማይጠገበው ድምጻዊ (ዶ/ር) ጥላሁን ገሠሠ፤ ሲያንጎራጉር፤ እንዲህ ብሎ ነበር፤

“ጩኸቴን ብትሰሙኝ ፤ ይኸው አቤት አቤት እላለሁ በደል ደርሦብኝ እጮሃለሁ ብያለሁ”

 

ኮለኔል ጎሹ ወልዴ

እያለ ያንጎራጎረውን  እኔም አቤት አቤት የ ( የመሪ ያለህ!!! ) በዪ እኔም እጮሀለሁ። ምንም እንኳን ሰለኮነሬል ጎሹም ሆነ ሰለ ዶክተር ታዬ ታላቅ ሰራና አገር ወዳድነታቸው አገር የሚያወቀው ያደባባይ ሚሰጥር ቢሆንም  ቅሉ፤ ሰሞኑን ግን የተለያዩ የሀገርኛ ጉዳይን የሚያሳዩ ቪዲዩዎችን ሰመለከት ድንገት የኮነሬል ጎሹን ብዙዎችን ያሰደነቀና ያኮራ ሃገር አቀፍ የጥብቅና ንግግር (On the fate of Ethiopia and Eritrea’s Referendum) አየሁና  በቁጭት ምን ተብሎ፤ ማን አሰከፍቶት ይሆን ኮነሬሉ ጥግ የያዙት ? ዶክተር ታዬ ወልደሰማያትሰ ? የት ገቡ ? በማለት በቁጭት ለመጠየቅ ብዕሬን አነሳሁ።

መቼም እንዲህ ያለውን አንገብጋቢ ሃገራዊ ጥያቄ የሚጠይቁ በርካታዎች እንደሚሆኑ ባምንም ጥቂቶች ደግሞ  የ ምርጫ 97 ቱን ምሳሌ በማድረግ የሞተ ዘመድ የለውም ወይ?  ይኸ ሰው ምን ነካው የሚሉ እንደማይጠፉም አምናለሁ። መልሴ ግን የሞቱ ዘመዶች በርካቷች አሉኛ፤ ተሰፋዪ ግን አይሞትም።ተሰፋ ላንድም ሰከንድ አጥቼ አላውቅም ነው ።

 

እንዲህ አይነቱ ጥያቄ አገራችን የምትገኝበትን የፖሎቲካ ሂደትና ቀውሰ በሰፊው እንድንጠይቅና ከሰኸተታችንም ታርመን ይቅርም ተባብለን፤ በሃገር ጉዳይ እኔ ማን ነኝ ? ምንሰ ማድረግ ይጠበቅብኛል ? የሚለውን ጥያቄ በቅንነት በመጠየቅ አንተ ትብሰ፤ አንቺ ትብሸ በመባባል እንደገና እጅ ለእጅ ተያይዝን አገራችን እንድትገባበት ከተቆፈረላት ጥልቁ ጉድጓድ የማውጣት አገራዊ ግዴታ አለብን በዬ አምናለሁ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ፍቅራችን የት ገባ? - ከተማ ዋቅጅራ

 

ከገጠመን እና ከተጋረጠብን የፖሎቲካ ውጥንቅጥ አኳያሰ እባክህ፤ እባክሽ ያሰፈልጋል ወይ ? ብቃት ያላቸው የፖሎቲካ መሪዎችሰ እባካችሁ እሰኪባሉ መጠበቅ አለባችው ወይ ? በሚል የተለያዩ እሣት የሚተፉ እንጉርጉሮዎች ከየጎራው ሊነሱ እንደሚችሉ የሚጠበቅ ቢሆንም ከተጋረጠብን ከፍተኛ አደጋ ባሻገር ምንሰ ብናደርግ አገር ትዳን እንጂ ነው መልሴ።

ሥለዚህ  ሰለጠንካራ የፖሎቲካ አመራር ብቃታቸውና፤  ሰራቸው በርካታ አገር ወዳዶች የሚመሰክሩላቸውን ጠንካራ መሪዎች ዳግም ወደ ፈጠጠው የትግል ጎዳና እንዲመጡ የማይደረግበት ምክነያት ምንም ሊኖር አይችልም።  እነ ኮነሬል ጎሹንም እነ ዶክተር ታዬ ወ/ሰማያትንም ሌሎችም አሉ የሚባሉትን ከየ አካባቢያችን ውጡ፤ አገራችን ኢትዮጲያ ትጮሃለች፣ የመሪ የለኸ እያለችም ትጣራለች ብለን የማውጣት ሃገራዊ ግዴታ አለበን። እከሌ ከከሌ ሳንል ጩኸታችንን እናሰማና አገራችንን ተባብረን ከውድቀት እናድን።

 

“ይሄ – መሪ ትግሉ ይወልዳል የሚለውም ባዶ ጩኸታችን ለ 22 አመት ወልዶ አላሳየንም እና ሁላችንም ቆም ብለን እናስብ፡

የሚዲያ ክፍሎችም በሙሉ፤-  እነ ቪ. ኦ. ኤም፣ ዶቼ ቬሌም ፤ እሣትም፣ ሌሎች ሚዲያዎች ሁሉ ካሜራችሁን ወደ አራቱም ማዕዘናት አዟዙሩት ፤ምክነያታቸውንም አሰሙን እያልኩ ጩኸቴን ብትሰሙኛ እላለሁ። በቸር ይግጠመን!!

 

ሎሚ ተራ፦Tuesday, May-28-13

7 Comments

  1. አዎን ወቅታዊ፣መሠረታዊ፣ ሀገራዊ፣ሐሳብ ነው። አኛም የምንጠይቅበት ድምፅ የምንሠጥበት ቦታ አጥተናል ። በአመራሩ መቀጠል ባይችሉ አማራር አሰልጥኖ የማብቃተ ጊዜው አሁን ነበር። በሚስጠር ከሰሩትም እየሠሩም ካሉ ያስመሰግናቸዋል በመሰልቸት፣በንዴት ፣ተስፋ በመቀረጥ የሚቆም ትግል ግን… የባሰ የአዕምሮ ዕረፍትን ይነሳል፣ ምሁርንትን ዝቅ ያደርጋል፣ ዜግነትን ያስረሳል ፣ ሀገርን በድሎ፣ ሕዝብና ቤተሰብን ጨምሮ ያሳዛናል፣ ያሳፍራል፣ ለትውልድ መምከንም ላለው የጋጠ-ወጥ ሥርዓት ተባባሪነትን ያሳያል። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለሚሞላፈጡ ለሚዘልፉና ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ላልተላበሱ የማናቸውም የፓርቲ አባላትና ጎሠኖች ዘረኞች ሁሉ ቅድሚያ ሀገር እንጂ የግለሰብ ሥም ማግነን በራዕይ በመለከፍ የፖለቲካ ሥርዓት የመብሊያ ገበታ መሆኑን ተረድተው በሀገራዊ ጉዳይ ላይ ሁሉም ዜጋ የመናገር፣ የመጠየቅ፣ መሥራት፣ መብቱ የተጠበቀ ነው። ግለሰቦች የግል ጥፋት አለባቸው ቢባል እንኳ ሥድብ የሕግ አካል አደለም ጉዳዩ በህግ አካል ይታያል ከትግል የሚያርቅ ዛቻ ማስፈራራት አያስፈልጋቸውም።

    ለማናቸውም ይህ በሳል ጥያቄ ሁሉንም ሀገር ወዳድ ዜጎችን ይመለከታል። ሀገር በተወሰነ ቤተሰባዊ ሥርዓት መዳፍ ልዩ የጦር ሠራዊትና የገንዘብ ምንጭ ከተጠበቀ… ብዙ ህዘብ ግን አንድ አገዛዝ ትውልድ ተሻጋሪ የሚለው ለትውልዳችን የምናስተላልፈው የግላችን ሀብት ማለታቸው እንደሆነ መረዳት ያሻል በለው!! ለመሆኑ የብሔር ብሔረሰቦች የቻይና ዕቃ ናቸውን ?የግንቦት ሃያ ዕለት የተፈለፈሉ ጫጩቶች ይጠየቅ! ይጠና !ይታወቅ ! በለው!!

  2. Dear Lomi Tera,

    Thank you for your article. when I browse the computer last week I came across the historical speech of Colonel Goshu wolde on the fate of Ethiopian and Ertrea’s Refrendum speech made by him. I asked my self where is he now?when I saw your article I was very suprised you asked the same question as mine.what I undersood from his speech he has a great love for his mother land Ethiopia his inside burning like a fire.He is an eloquent and fluent English speaker. where is he ?

  3. if not them, how about their kids or proteges who are very few men away from the ethiopian public? Yonas Berhane Mewa has taken the lead. Who is next? Even Semehal Meles’s recent protest is a case in point.

  4. ty Lome Tera !

    enem yehe neger yegermegnal ! Ethiopia letwedq setengedaged

    sew betefabet weqt sew honew yewetalu yalnachew Hager wedadoch

    yet Gebu ????????????

  5. In other words, where are those who were given best schooling at the expense of the Ethiopian masses in all directions, at the time of their need?

    The answer is simple they were educated for their own sake and they did not and do not care for the Ethiopian people, but their ego!

    I admire you good intention, but you have to be naive to think these are model Ethiopians. Rather they are the best examples of who not to emulate. I am sure they have found comfort some where in their old age, a motive they lived with!

  6. one additional person that has disappeared from the political scene….Ato Assefa Chabo.
    Where is he?
    Why doesn’t he write?

  7. ወዳጄ ጥሩ ጠይቀኸል ቀደም ባለዉ ጊዜ እኔም እንዚህን ሁለት መሪዎች ስለ ጀግኖች ምሁራን ስዘግብ በዚሁ አምድ አዉጥቸዉ ነበር አንዳንድ የማይሞቱ ጽሁፎች አልፎ አልፎ ተደግሞም ቢሆን ቢወጡ ክፋት አልነበረዉም። ለማንኛዉም መልሱ ኢትዮጵያዉያን መስለዉ ኢትዮጵያዉያን ያልሆኑ የሻቢያ እና ወያኔ ተላላኪዎች ሁለቱንም ግዙፍ ምሁራን በእሩምታ ተኩስ ጣሉዋቸዉ ለዚህም ከረንት አፌየርስ የተባለዉ የፓልቶክ ክፍል ተቀዳሚ ቦታዉን ይይዛል። የሚያሳዝነዉ እነዚህ በሁለት እጂ የማይነሱ ምርጥ ኢትዮጵያዉያንን የት ጠፉ ብለን እንዳንተ ኡኡ ያለማለታችን ነዉ። ወይ አገሬ የሞተለሺ ቀርቶ የገደለሺ በላ ብሎ ጨርሶታል ነገሩ የገባዉ የሀገሬ አዋቂ። ለነገሩ ደናቁርት ሲበዙ አዋቂዎች የነሱ ጊዜ እስኪመጣ ጥግ ይዘዉ ይቆያሉ እንጂ በዱርዬ መንጋ ተገኝተዉ እሰጥ አገባ አይሉም። ለማንኛዉም ድንቅ ስራቸዉን ማሰታወስህ ልትመሰገን ይገባል።

Comments are closed.

Share