ኢህአፓ ዴሞክራሲያዊና የኢህአፓ እርምት እንቅስቃሴ በአንድ ኢሕአፓ ጥላ ሥር   ሆነው ለመታገል የሚያስችል ጉባኤ ለመጥራት ተስማሙ።

12/21/14
ከዚህ በፊት ባወጣናቸው የጋራ መግለጫዎች ኢህአፓ ዴሞክራሲያዊና የኢህአፓ እርምት እንቅስቃሴ የጋራ ኮሚቴ አቋቁመን ውይይት እያደረግን መሆናችንን ገልጸን ነበር። አሁን ደግሞ ሁለታችንም ኢህአፓን አንድ አድርገን ከመታገል ውጭ ሌላ አመራጭ እንደሌለ ተማምነናል። ከዚህ ስምምነት እንድንደርስ ከአደረጉን ዋና ዋና ምክንያቶችም

1ኛ ገና ትግሉን ስንጀምር ይዘነው የተነሳነው ዕራይ አሁንም ሁኔታው የሚጠይቀው በመሆኑ

2ኛ. እንዲሁም ድሮ ለሕዝባችን የጠየቅነው የዴሞክራሲና የሰብዓዊነት ጥያቄ አሁንም ድረስ ያለተመለሰ

በመሆኑ

3ኛ የአገራችን ሁኔታ ከምን ጊዜውም በበለጠ በከፋ ሁኔታ ላይ በመገኘቱና ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚቻለው ተጠናክሮ በመታገል እንጅ በመከፋፈል አለመሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው።

እየከፋ ለመጣውን የአገራችን የፖሊቲካ፤ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ቀውስ መፍትሄ ማግኘት የሚቻለው

ተባብሮና ተጠናክሮ መታገል ታሪካዊ ሁኔታው የግድ ይላል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ሕብረተሰባችን በመሬቱና በንብረቱ ላይ የባለቤትነት መብት ተነፍጎት፤ የዴሞክራሲ ጥያቂ አንስተው በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባሎች፤ የነጻ ጋዜጣ አዘጋጆችና ብሎገሮች ወደ እስርቤት የሚወረወሩባት አገር ናት። አያት ቅድማያቶቻችን በደምና በአጥንታቸው አስከበረውት የኖሩትን የአገራችን መሬት ለሱዳን ዳርንጎት ተቆርሶ የተሰጠበት ሁኔታ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ እንደ እግር እሳት የሚያንገበግብበት ወቅት ላይ ነን። በልማት ስም ያለምንም ቁጥጥር የውጭ ከበርቴዎች የአገራችን ለም መሬት በመቀራመት በቦታው ላይ የሚኖሩትን አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች እያፈናቀሉ ቤት የለሽ እያደረጓቸው ነው። የድህነት ደረጃ ጣራውን ነክቶ ከገጠር ከቀያቸው የተፈናቀሉ፤ በከተማ ከሥራ የተባረሩት እና ትምህርታቸውን ጨርሰው ስራ ያጡ ወጣቶች በአገሪቱ ዋና ዋና ከተማዎች በረንዳ አዳሪ ሆነዋል። “ምርት ተትረፍርፋል፤ 11% አድጓል፤ ከአፍሪቃ አገሮች በኢኮኖሚ ዕድገት በአንደኝነት እየመራን ነው” ሲል የከረመው አሁን ሰሞኑን በአገራችን ርሃብ ገብቷልና የዓለም እርዳታ ሰጭ ድርጅቶች ድረሱልን ማለቱን ስንሰማ ድሮንስ ከአምባ ገነን መንግሥት ሽፍጥ እንጅ ሀቅ አይጠበቅም ብለናል። በዚህ ሁኔታ ላይ ባለች አገር ውስጥ የሕዝብ መብት እንዲከበር በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ እየታገሉ ባሉት ወይም ጥያቄ ባቀረቡ ድርጅቶች ላይ እየደረሰ ያለው አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ እስራት፣ አፈናና እንግልት እያወገዝን የትግል አጋርነታችንም ጭምር ለመግለጽ እንወዳለን። ያለው ተጨባጭ ሁኔታ የሚያስቆጭና ተጠናክሮ መታገልን የሚጠይቅ ፈታኝ ወቅት ነው። በመሆኑም በአገራችን ውስጥ ያለውን አሳሳቢ ሁኔታ በመገንዘብ ኢህአፓን አንድ አድርጎና አጠናክሮ ትግሉን መቀጠል አማርጭ የሌለው ግዴታ ነው በሚለው መሪ ሃሳብ መሰረት ነው ኢሕአፓ ዴሞክራሲያዊና የኢሕአፓ እርምት እንቅስቃሴ ከአንድ ዓመት በላይ ውይይት ካደረጉ በኋላ የነበራቸዉን ልዩነቶች ዓርቀውና ተቻችለው በአንድ ኢሕአፓ ሥር ተሰባስበው ትግሉን ለማስቀጠል ስምምነት ላይ የደረሱት። ስምምነቱ ያተኮረባቸው ዋና ዋና ጥቦች፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፋኖ አንድነት ም/ቤት ተመሰረተ | ጥብቅ መልዕክት! | "ወልቃይትና ራያ ቀይ መስመሮቻችን"

 

ሀ. በጥቂት ወራት ውስጥ አንድ ሁሉን አቀፍ የሆነ ጉባኤ ማዘጋጀት

ለ. ለጉባኤው ዝግጅት እንዲረዳ በየከተሞች የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም አብሮ መሥራት

ሐ. ኢህአፓን አንድ አድርጎና አጠናክሮ ትግሉን ለመቀጠል እንዲቻል በኢሕአፓ/ኢሕአሠና ኢሕአወሊ

ትግል ውስጥ ያለፉ፣ ሆኖም ግን በተለያዩ መክንያቶች ራሳቸውን ከድርጅቱ አግልለውና አርቀው፣ የነበሩ የዛ ጀግና ትውልድ ጓዶች/ጓዲቶች በሙሉ የታሪኩ አካል በመሆናቸው በጥቂት ወራቶች ውስጥ ለምናደርገው ሁሉን አቀፍ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ አብረን የጀመርነውን ትግል አብረን ለመጨረስ ይቻል ዘንድ የሚቻለውን ያህል ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል። እነዚህና ሌሎችንም በጎ ሀሳቦች በማጠቃለል የጋራ ስምምነት ላይ መድረሳችን ለአባሎቻችን፤ ለደጋፊዎቻችን፤ እንዲሁም አምባገነኑን የወያኔ ዘረኛ ቡድን ለሚታገሉ ድርጅቶች ሁሉ ሥናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

 

ኢህአፓ ዴሞክራሲያዊና የኢህአፓ እርምት እንቅስቃሴ

አንድነት ኃይል ነው

ትግሉ ይቀጥላል

 

የጋራ ኮሚቴ

taskforce@gmail.com

 

 

 

3 Comments

  1. Time is changed and it belongs to younger generation. Let Andenet/ Semayawe try there best.

  2. ወያኔን ከመታገል ውጭ ከእናንተ የሚገኝ ጥቅም የለም በዚህ እንስማማለን።ከዚያ ውጭ ግን እጃችሁ ከደም አልፀዳም አይፀዳምም ለዚያ ሁሉ ወጣት ማለቅ ምክንያት ማን ሆነ እና አሁንስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስማችሁን የረሳው ይመስላችኋል ?ኢሕአፓ የሚባል ድርጅት መጣ ከተባለ ሕዝቡ ወደ ወያኔ እንደሚወግን አትጠራጠሩ ።ሌላ እውከት ከማስከተላችሁ በፊት ስማችሁን አስተካክሉ ከኢሕአፓ አንድ የሚወሰድለት ዲሲፕሊኑ ብቻ ነው ከዚያ ውጭ ግን በመጀመሪያ ነጭ ሽብር ብላችሁ በደርግ ባለስልጣናት እርምጃ መውሰድ የመጀመሪያው ተዋናኝ በመሆን ለዚያ ሁሉ ትውልድ ማለቅ ተጠያቂው ደርግ ሳይሆን እናንተ ነበራችሁ የእናንተን መሰሪነት የኢትዮጵያ ሕዝብ እስከ ዛሬ አላወቀም ። ለማነኛውል 40 ዓመት የነበረ ድርጅት ስም ይዞ ከመንገታገት ስማችሁን ቀይሩ ወያኔ መጠቀሚያ ያደርጋችኋል አስቡበት ።8

  3. እንዲያዉ በእዉነት ለኢትዮጵያ ካሰባቹህ ለምን ሌላ ስም አዉጥታቹህ አትታገሉም: ዋናዉ ኢሓአፓ እኮ ጽህፈት ቤት, ሬድዮ ጣቢያ, ድሕረ ገጸ እና አባሎች አሉት እኮ, እናንተ ምኑም የላቹህም ናዳ!! ናዳ!! እረ ሕዝቡን አታወናብዱ ትግሉንም አትጎትቱ እባካቹህ;;

Comments are closed.

Share