ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ በሚጠራው ሰልፍ ላይ 100ሺህ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል

May 29, 2013
በመስከረም አያሌው
የፊታችን ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም በሚካሄደው እና ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት፤ ፓርቲው ባለፈው ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያራዝም መንግስት በጠየቀው መሰረት የፊታችን እሁድ ያካሂዳል። መንግስት በፀጥታ እና ሰላም ማስከበር ሂደት ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥመው ሰልፉን ለሌላ ጊዜ እንዲዛወር መጠየቅ ይችላል የሚል ህግ በመኖሩ ሰልፉ ከአንድ ሳምንት በኋላ እንዲደረግ መወሰኑን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
ሰላማዊ ሰልፉን በአፍሪካ ህብረት በዓል ወቅት ማካሄድ የተፈለገው ኢትዮጵያ በአሉን ስለምታዘጋጅ እና መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው ስራ በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብና ሚዲያው እንዲሁም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስለሚሰሙት ጥያቄው ከፍ ብሎ ይሰማል ከሚል አስተሳሰብ መሆኑን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ የሰላማዊ ሰልፉ ቀን መራዘም ምንም የተለየ ነገር እንደማይፈጥር ገልፀዋል። “የችግሩ ባለቤትም ሆነ መፍትሔ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። የሚጨቁነንም መንግስት እዚህ ነው ያለው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ሰልፉ በታሰበለት ቀን ቢካሄድ ጥሩ እንደነበር ገልፀው ቀኑ መቀየሩም ያን ያህል ለውጥ እንደሌለው ተናግረዋል።
የሰላማዊ ሰልፉ በመራዘሙ በፊት ይሳተፋል ተብሎ ከታሰበው በላይ ሰው ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ሰላማዊ ሰልፉን በህጉ መሰረት ማስፈቀዱ እና ህዝቡም ጊዜ ወስዶ እንዲወያይበት በመደረጉ ከ100ሺ በላይ ሰዎች በሰልፉ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሰልፉ የሚነሱት አራት ጥያቄዎች በመሆናቸው ህዝቡ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እና የተነሱ ጥያቄዎችን የተመለከተ ብቻ እንዲሆንም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል። በሰላማዊ ሰልፉ ወቅትም የታሰሩ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ፣ የእስልምናን እምነት ነፃነት በመጠየቃቸው የታሰሩት የሙስሊም የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ፣ የተፈናቀሉ ሰዎች ወደሚኖሩበት አካባቢ በሰላም ተመልሰው ካሳ እና ድጎማ ተደርጎላቸው ህይወታቸውን እንዲቀጥሉ እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱ እና በስራ አጥነት እና በሙስና ላይ መንግስት አፋጣኝ መፍትሔ እንዲፈልግ የሚሉ ጥያቄዎችን አንግበው ሰላማዊ ሰልፉን እንደሚያካሂዱም ተገልጿል።
ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፉ መነሻውን ግንፍሌ አካባቢ ከሚገኘው የፓርቲው ጽ/ቤት በማድረግ በአራት ኪሎ፣ ፒያሳ እና ቸርቸል ጎዳና አልፎ እስከ ድላችን አደባባይ ወይም ኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት አደባባይ የሚደረግ ሲሆን፤ በእለቱም አጠቃላይ የሀገሪቱን ሁኔታ የሚገልፁ ንግግሮች እና መፈክሮች ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።¾
(ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የረቡዕ ሜይ 29 ዕትም)

4 Comments

  1. Woyane Wodeke….Blu party seltan Yaze and after Yekal Getnet become the
    President of Ethiopia..and then….put in prison woyane and then tell me the result

Comments are closed.

Previous Story

ትግሉ ጥራት እንዲኖረው -በቶኩማ አሸናፊ

321589 109993089111063 1484315227 a
Next Story

ከሙስና ተጠርጣሪዎች እሥር በኋላ የጥቆማ ቁጥር በእጥፍ ጨመረ፤ ሕጉ ይሻሻላል ተባለ

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop