Hiber Radio:ዶ/ር ኑሩ ደደፎ የኦነግ ሊቀመንበር ሆነው ጄኔራል ከማል ገልቹን ተኩ; ቻይና በሕገ ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ የገባ ጫት ሕዝቤን እያወከ ነው አለች

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ጥቅምት 16 ቀን 2007 ፕሮግራም !

<... ገዢው ፓርቲ ሰሞኑን አንድነትን ለማዳከም ብሎ የሚአደርገውን ድራማ ተከትለን እሱን ስናስተባብል አንኖርም። ትግላችንን እንቀትላለን አንድነት ስብሰባ ሊጠራ ሲል የትኛውም ሆቴል እሺ እንዳይል ይከለከላል የአገዛዙ ቴሌቪዥን አይመጣም አሁን ግን ሶስት ሰዎች በእጅ ጽፈው ሄቴል ስብሰባ ተፈቀደ፣አባላት ያልሆኑን ጭምር በገዢው ፓርቲ በገንዘብ ተገዝተው የተሳተፉበት ስብሰባ ተደረገ ይሄ አንድነትን አያዳክመውም ይልቅ አሁን በአንድነት ውስጥ ስልጣን የያዘው ሀይል ለመንግስት ምን ያህል እንዳስፈራው የሚያሳይ ነው...>

አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ሀላፊ በአንድነት ላይ ሰሞኑን በገዢው ፓርቲ የተከፈተውን ዘመቻ አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

የኡበር አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎትና በቬጋስ የገጠመው ግብ ግብ ውይይት ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በታክሲና ኡበር በአገልግሎት ላይ ካሉ ጋር የተደረገ ቆይታ (ውይይት ክፍል አንድ)

በፈረንሳይ የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ስደተኞች ግጭትና የፖሊስ ሀይል እንቅስቃሴ

(ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የአቶ ሀይለማርያምና የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ አንዳርጋቸውን በተመለከተ የዲፕሎማሲ ጨዋታ ላይ መሆናቸው ተገለጸ

ዶ/ር ኑሩ ደደፎ የኦነግ ሊቀመንበር ሆነው ጄኔራል ከማል ገልቹን ተኩ

ጄ/ል ከማል አሁንም የኦነግ ሊቀመንበር ናቸው የሚሉ አሉ

አንድነት ፓርቲ በኢህአዴግ የተለመደ ፓርቲውን ማዳከም ሴራ ከትግሉ ወደሁዋላ እንደማይል ገለጸ

የአገዛዙ ድጋፍ ያላቸው ሶስት ግለሰቦች ለፓርቲው የተከለከለው የሆቴል ኪራይና የመንግስት መገናኛ ብዙሃን አብሮ መሰለፍ የተለመደ የኢህአዴግ ስትራቴጂ ነው ተባለ

በቬጋስ ኡበር ተፈቀደ ኡበር ተከለከለ ተባለ

የኡበር ሀላፊዎች አልታገድንም ብለዋል

ቻይና በሕገ ወጥ መንገድ ከኢትዮጵያ የገባ ጫት ሕዝቤን እያወከ ነው አለች

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በሲዲኒ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ

የአክብሮት ሽልማት ተበረከተላቸው

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  “የሰንደቅ ዓላማና አርማ ጉዳይ ለህዝብ ውይይት አልቀረበም” - ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (አዲስ አድማስ)
Share