በአርባ ጉጉ እና አካባቢው በዐማራው ህዝብ ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መካድ አይቻልም

ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን

moweswe@gmail.com

ፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማሪያም ከሸገር ራዴዮ ጣቢያ ጋር በነሐሴ ፫ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. (Aug 08, 2014) ያደረጉት ቃለ መጠይቅ ምንም እንኳዐማራውን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ እርስ በራሱ የተምታታ ቢሆንም፣ ዐማራውን ሕዝብ «የለም» ከማለት አልፈው በአርባ ጉጉ በዐማራው ህዝብ ላይየተፈጸውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ክደዋል። የፕሮፌሠር መሥፍን ክህደት ‘እስላም ኦሮሞዎች ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ነበር የገደሉት’ ለማለት ከሆነ፣ ሀቁና መረጃዎቹከፕሮፌሠር መሥፍን ክህደት ጋር እንደማይጠጣሙ በተከታታይ መረጃዎችን እየመዘዝን የአርባ ጉጉን እልቂት ለማቅረብ እንሞክራለን። ወይም ጉልበታቸውለፈረጠመ ወንጀለኞች መውጫ ቀዳዳ በመፈብረክ የተለመደው የፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማሪያም “የወንድ በር እንስጥ” ፍልስፍናም ከሆነ በዐማራው ህዝብ ላይየተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ያልተፈጸመና ያልተደረገ አያደርገውም ልንላቸው እንገደዳለን። ከአባሎቻችን እና ከደጋፊዎቻችን ጋር ለመወያየት የግብዣወረቀት ከላክን በኋላ፣ ከስብሰባው በፊት በዐማራው ህዝብ ላይ በአርባ ጉጉ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፕሮፌሠሩ መካዳቸው ብዙዎችን እንዳስቆጣቸውመልክት ሲደርሰን፣ እኛም አንድን ሰው «ከሃዲ» ከማለታችን በፊት መረጃዎችን አቅርቦ ፍርዱን ለአንባቢ ለመተው በማሰብ፣ በጊዜው የመላው ዐማራ ህዝብ ድርጅትለኢህአዴግ፣ ለውጭ መንግስታት ዲፕሎማቶች እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲደርስ ያወጣውን የአቋም መግለጫ ከሞላ ጎደል አቅርበነዋል።

የመላው ዐማራ ህዝብ ድርጅት ‘መዐህድ’ ኢህአዴግ በካድሬዎቹ አማካኝነት በዐማራው ላይ የሚያካሂደውን የእልቂት እና የሽብር ዘመቻ እያፋፋመው፣የዐማራ ሕዝብም ከፋሽስቶች ዘመን በባሰ ሁኔታ እያለቀ መሆኑን ባወጣው የአቋም መግለጫ አብራርቷል። የመአህድ ፕሬዜዳንት ለሽግግር መንግስቱ ምክር ቤት እናለልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ባቀረቡት መግለጫ ላይ እንዳብራሩት፣ በዐማራው ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ እና በደል፦

ተጨማሪ ያንብቡ:  በርካታ‬ መምህራን የስራ መልቀቂያ አቀረቡ ተባለ | የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ አጫጭር ዜናዎች

ሰብአዊ አዕምሮ ሊሸከመው የማይችል ነው በተለይ ከግንቦት ፳፮ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. ጀምሮ ጭፍጨፋው በከፋ መልኩ እንዲቀጥል ተደርጎየጭፍጨፋው ሰለባ የሆነው ዐማራ ሬሳው በገደል ውስጥ እንዲጣልና በቤት ውስጥ እንዲቃጠል እየተደረገ ነው።”

ይላል። በማስከተልም፦

ከግንቦት ፳፮ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም.  ጀምሮ በዐማራው ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ የተካሄደው በአርሲ ክፍለ ሀገር በአቦምሣ ከተማና በአካባቢው ነው።ኢህአዴግ በዚህ ስፍራ የሚኖሩ ተወላጆችን ሰብስቦ «በነዚህ መንደሮች የሚኖሩ ዐማሮች ይገደሉ ብላችሁ ፈርሙ» በማለት ትእዛዝ ሰጠ። በማግስቱግንቦት ፳፯ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. «አቡሌ» የተባለውን መንደር በኦህዴድ (የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራቲክ ድርጅት) የታጠቀ ወታደር ተከቦ ተኩስ ከተከፈተበኋላ መንደሩ በላውንቸር መደብደብና ማቃጠል ሲጀመር ሕዝቡ ህይወቱን ለማዳን ሕዝቡ በየአቅጧጫው መሸሽ ጀመረ። ከሚሸሹት መካከል፴(ሰላሳ) ሕጻናት ቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ እንደተጠጉ ከቤተክርስቲያኑና ከካህናቱ ጋር ተቃጥለዋል። አከታትሎም ፻፶(መቶ ሃምሣ) የዐማራ ነዋሪቤቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓል።

የአውራጃው የኢህአዴግ ተወካይ አቶ ዲማ ጎርሜሳ ለወራሪው ሠራዊት «አማራን መጨረስ ዛሬ ነው» የሚል መፈክር በማሰማት «አበሳ»የሚባለው የዐማሮች መንደር እንዲከበብ አስደርገው ሕዝብ ከቤቱ ሳይወጣ መንደሩ እንዲቃጠል ተደረገ። በመንደሩ ከነህይዎታቸው በቤት ውስጥእንዳሉ የሞቱት ቁጥር የማይታወቅ ሲሆን የቤቶቹ ጠቅላላ ብዛት ፻፶(መቶ ሃምሣ) ነው። ከቃጠሎው የተረፉት ፶(ሃምሣ) ሰዎች ተይዘው በጥይትተረሽነዋል።

በሌላም «አሼ» በተባለ መንደር በዐማራ ተወላጆች በአካባቢው የሚፈጸመውን ሰቆቃ እየተመለከቱ የመንግሥት ኃይል ያድነናል ብለው ሲጠብቁ፳፭(ሃያ አምሥት) ሰዎች የኢህአዴግ ሰራዊት ፈጅቷቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከድምጻዊነት ያለፈው የያለምወርቅ ጀምበሩ ችሎታ

በጉና ወረዳ «አዲስ አለም» በተባለ ቦታም ፻፶(መቶ ሃምሣ) ቤቶችን ከነነዋሪዎቹ ከማቃጠላቸውም ሌላ ሁለት የአገር ሽማግሌዎች እጅ እግራቸውንአስረው አቃጥለዋቸዋል።

«ዋቄንትራ» ከተባለው መንደር ፻(መቶ) ቤቶችን ከእነነዋሪዎቹ አቃጥለዋቸዋል።

«መሶ» የተባለውን መንደር በጦር እንዲከበቡና ፻(መቶ) ቤቶች እንዲቃጠሉ ተደርጓል። ከቃጠሎው የዳኑት ፹(ሰማንያ) ሰዎች እጃቸው ታስሮበኦህዴድ (የኢህአዴግ አንዱ ክፍል) ተረሽነው ሬሳቸው «ቆሬ» ከሚባል ገደል ውስጥ እንዲጣል ተደርጓል። አንድ ሰው በተአምር ከዚህ መአት ተርፏል።

«እንደሴ ባዩ» የሚባለው መንደር ነዋሪ የሆኑ ዐማሮች በተመሳሳይ ሁኔታ በኦህዴድ ሰራዊት እንዲከበቡ ከተደረገ በኋላ ከመንደሩ ነዋሪዎች መካከል፹(ሰማንያ) የሚሆኑት እጅ እግራቸውን ታስረው ተወስደዋል። ወደ ገደል እንደተወረወሩም ይወራል።

ስድስት ቤተክርሲቲያናት በዚህ አካባቢ ተቃጥለዋል። ይህ ሁሉ የተፈጸመው ግንቦት ፳፯ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. በአንድ ቀን ነው።”

ሲል የመአህድ

2 Comments

  1. ምነው: ሞረሽ?አሁን አሉባልታና ስለ ግለሰብ ማውራት የሞረሽ ስራ ሊሆን ይገባል?ትልቁ ህዝብ የሚጠብቀው ይህን
    አልነበረም::

  2. Henok why u decided to unpublished my comment I wrote in support of MORESH and criticized the failure of AMHARA elites to help their people from the planned Genocide by TPLF OLF and SHABIA
    Yet u publish this guy criticizes MORESH who is the only organization working to defend Amharas
    Organizations like OLF TPLF including SHABIA and some good for nothing AMHARA elites are busy attacking and mocking MORESH in order to silence the organization serving as a voice for the ethnic Amharas being killed, prosecuted and displaced by TPLF and OLF

Comments are closed.

Share