እኔ ስለአንድነት/መድረክ እከራከራለሁ

በፍቃዱ ዘ ኃይሉ
BefeQadu Z Hailu

ሰሞኑን በአንድነት እና አቃፊው መድረክ መካከል የተከሰተውን አለመግባባት የተጋነነ ቨርዥን ጋዜጦች ላይ ያላነበበ ወይም ካነበበ ሰው ያልሰማ አይኖርም ብዬ በመገመት ልጀምር። ባለፈው ሰሞን የማከብራቸው አቶ ቡልቻ አንድነት (በመድረክ) ሕወሓት (በኢሕአዴግ) ማለት ነው የሚል ጽሑፍ (የአማራ ፓርቲ ነው ከሚመስል ነገርጋ) መጻፋቸው አነጋጋሪ ኹኖ ሰንብቶ ነበር አሁን ደግሞ አንድነት መድረክን ገምግሞ ድክመቱን በማሳወቁና ወደውኅደት በፍጥነት እንዲሸጋገር በመጠቆሙ የቃላት ልውውጡ ተበራክቷል። በዚህ መሐል ያስተዋልኩት:–

ሀ)。አንድነት ፓርቲ የመድረክ ትልቁና የበለጠ ተቀባይነት ያለው ፓርቲ መሆኑ አይካድም። ይህ ግን ከሕወሓትጋ አያመሳስለውም። ምክንያቱም አንድነትነ ኅብረብሔራዊ ፓርቲ በመሆኑ ሁሉንም ሕዝብ የሚወክል እንጂ እንደሕወሓት ለአንድ ወገን የቆመ አይደለም።

ለ)。አሁን የተፈጠረውን አለመግባባት ብዙዎች “አይ የተቃዋሚዎች ነገር” ሲሉት ስሰማ ተቃዋሚዎቹ የምንተቸውን ኢሕአዴግን እንዲሆኑ ነውንዴ የምንፈልገው የሚል ጥያቄ ይመጣብኛል። ሕወሓት የበላይነቱን፣ ቀሪዎቹም ደካማነታቸውን እያወቁ ሳይበርዳቸው ሳይሞቃቸው ገዢና ተገዢ ሆነው አሉ። የመድረክ ትንንሽ ፓርቲዎች ጥያቄ ማንሳታቸው የሚያሳየው ትንሹ ትልቁን በጥያቄ መገዳደር እንደሚችል ነው። የአንድነትም መድረክን መገምገምም የሚያሳየው እንደሕወሓት የሌሎቹን አቅመቢስነት ሳይጠናከር እንዳይቀጥል መፈለግ ነው።

ሐ)。አንዳንዶች የሰነዘሩት አስተያየት ደግሞ ሌሎቹ እንደአንድነት መጠናከር አለባቸው የሚል ሳይሆን አንድነት እንደሌሎቹ መድከም አለበት የሚል ይመስላል። አንድ ፓርቲ የበለጠ ጠንካራ በመሆኑ ሲተች አስቂኝና አሳዛኝ ነው። ጥንካሬውን ከጨቋኝነት ቀላቅሎ መረዳትም እንደዚያው።

መ)。ለአንዳንድ የመድረክ አባል ፓርቲዎች አባላት (በተለይ) ወጣቶቹ አባልነታቸውን የአንድነት ፓርቲ የማድረግ ዝንባሌ እየታየባቸው እንደሆነ ሰምቻለሁ። ይህ በፊዚክስ የስበት ማዕከሉ (the center pod gravity) የሚፈጥረው ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ዓይነት የማየቀር እውነት ነው – የስበት ማዕከሉ ትልቁ ሲሆን፣ ትንንሾቹ ወደትልቁ ይሳባሉ። የአንድነት ጥንካሬ የሳባቸው ወጣቶች ወደአንድነት መግባታቸው የሚያሳየው የአንድነትን ጥንካሬ እንጂ ሌላ አይደለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  (የሊቢያው እልቂት ጉዳይ) እኛ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ነን!!

አንድን ፓርቲ በጥንካሬው ምክንያት መተቸት አሳማኝ አይደለም።

1 Comment

  1. ቡልቻ ደመቅሳ የሚባል ሰዉ በጣም ያስቀኛል፡ በጣም ዘረኛ እና በኢትዮጵያዊነቱ የማያምን የኦነግን ሀሳብ የሚያቀነቅን ነዉ፡ በአፄ ሀይለስላሴ ዘመን ትልቅ ባለስልጣን ነበር፡ አሁን ዘረኛዉ ስርአት ሲመጣ አማራ እያለ በጭቁኑ የአማራ ህዝብ ላይ ያላግጣል፡ የሚገርመዉ ኦሮሞ ነኝ እያለ አንድም ነገር አለመስራቱ ነዉ፡ ካወቀዉ አማራም፡ ኦሮሞም፡ ጉራጌም ሌላዉም ወንድማማች ኢትዮጲያ ነን ደስ አይበልህ።

Comments are closed.

Share