የባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበር ከፍተኛ አመራር ታሰረ

ፍኖተ ነፃነት

በኢትዮጵያና በአዲስ አበባ ወጣቶች ስም በተመሰረቱ ማህበራቶችና ፎረሞች ውስጥ ተደራጅተው ከነበሩ ወጣቶች መካከል የተወሰኑት የሚገኙባቸው ማህበራት ‹‹ነጻነት››የማይጨበጥ ሲሆንባቸው ‹‹የባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበርን››መሰረቱ፡፡ከመስራቾቹ አንዱም ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ነው፡፡ብርሃኑ ማህበሩን በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዘዳንትነትና በህዝብ ግኑኝነት በማገልገል ላይ የሚገኝ ከመሆኑም በላይ በተለያዮ የህትመት ውጤቶች አማካኝነት ሀሳብን የመግለጽ መብቱን ይጠቀማል፡፡

ማህበሩ በየጊዜው የሚያነሳቸው የመብት ጥያቄዎችና አገራዊ አጀንዳዎች ያላስደሰተው አካል የእነ ብርሃኑን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በአይነ ቁራኛ ሲከታተል ቆይቷል፡፡ወጣቱ የመብት ታጋይ ዛሬ ማለዳ ከሚኖርበት ወረዳ 11 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ከሰዓት በኋላ ለደቂቃዎች በቤተሰቦቹ እንዲጎበኝ የተደረገው ብርሃኑ ‹‹ያሰሩኝ በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት አስባችኋል ብለውኛል ፡፡ ነገር ግን እኛ (ባለ ራዕይ ማህበር)ሰላማዊ ሰልፍ አልጠራንም ሰልፉን የጠሩት ሰማያዊ ፓርቲዎች ናቸው ስላቸው ይህንን ወረቀት ታዲያ ለምን በተንክ ብለው ከዚህ በፊት ተመልክቼው የማላውቀውን ወረቀት አሳዮኝ እኛ ሰልፍ ብንጠራ በህቡዕ ሳይሆን በአደባባይ እንደምናደርገው ነግሬያቸዋለሁ፡፡››በማለት የእስሩን ምክንያት ተናግሯል፡፡ የመኖሪያ ቤቱ መፈተሹን የጠቆሙት የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ፖሊሶች ግንቦት 7/2005 ተበትኗል ያሉትን ወረቀት ‹‹ የኤርትራ ጉዳይ ›› በተሰኘ የዘውዴ ረታ መጽኀፍ ውስጥ አገኘን ማለታቸውንና ብርሃኑም ተገኘ የተባለው ወረቀት ቤት ፈታሾቹ ሆን ብለው ያስቀመጡት ካልሆነ በቀር እርሱ እንዳላስቀመጠው በመግለጽ ፖሊሶች ‹‹የእኔ ነው ብለህ ፈርም ሲሉት›› እምቢ ማለቱን በኋላም አሁን ፈርምና ፍርድ ቤት በምትቀርብበት ወቅት የአንተ አለመሆኑን ትናገራለህ በሚል ማግባቢያ ቤተሰቦቹን ማስጨነቅ ባለመፈለጉ መፈረሙን ምንጮቻችን ፡፡ብርሃኑ በአሁኑ ሰዓት ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣብያ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኣብራሃ ደስታ - ከቅሊንጦ...!
Share