ውጥረት በሰሜን ሸዋ መርሃቤቴ በርትቷል

በሰሜን ሸዋ የመርሃቤቴ ወረዳ ህዝብ ከወያኔ የፀጥታ ሃይሎችና ፌደራል ጋር ከባድ ውጊያ እያካሄደ ነው፣

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ለወረዳው አለም ከተማና አካባቢዋ አገልግሎት ይውላል ተብሎ ከብዙ ጊዜ በሁአላ የገባውን መብራት የወያኔ መንግስት ህዝቡ የሚገለገልበትን መብራት አቁሞ ትራንስፎርሜሽኖቹን ነቅሎ ለአስቸኩአይ ጉዳይ ይፈለጋል ብሎ ወደ ትግራይ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የወረዳው 27ቱም ቀበሌ ተጠራርቶ ትራንፈርመሩን በቁጥጥር ስር በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት የወያኔ የፀጥታ ሃይሎች ጋር ኣሁን ድረስ ውጊኣ እያደረገ ሲሆን እስካሁን 7 የወያኔ ወታደሮች የሞቱ ሲሆን ከህዝብ ታጣቂ በኩል 1 ሞቷል።

ባሁኑ ሰዓት ወረዳውን መሉ በሙሉ የህዝቡ ታጣቂ ተቆጣጥሮት ይገኛል። ወያኔ ከአዲስ አበባና ከተለያዩ አካባቢወች ተጨማሪ ሃይል ወደ አካባቢው እያንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቁኣል።ሁኔታው የሚመለከታችሁ ወገኖች ሁሉ እየሆነ ያለውን ሁሉ በመከታተልና አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉ ያስፈልጋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በእነሀብታሙ አያሌው ጉዳይ ማረሚያ ቤት ላይ ክስ ቀረበ

3 Comments

  1. **************************************
    “አትድረሱብኝ ቢል አትንኩኝ እንቢኝ! በቤቴ
    ኢህአዴግ ምን እግር ጣለው መራ ቤቴ!?
    ሕዝቡ ተከልሎ ግድቡ ተሰርቶ መብራቱ ሲጠበቅ
    እንደአማረው ቀረ ሸዋ በሻማ ብቅ
    ገንዘብ አስወድዶ ይህ ሰው መናቅ
    ዘንድሮ አለ ነገር!
    እኛ በጭለማ ሰጡ ሸጡ አሉ መብራት ለጎረቤት
    የእኛንም ወደብ ደግሞም የእኛን መሬት
    እነሱ ምን ያርጉ ገዢ አጡ ከእኛ ቤት
    ***
    እኩል ተጨቁኖ በጋራ የጣለ አምባገነንን
    እንግዲህ ይነሳ ይጠይቅ የነጻነት ድርሻውን
    ወኔ ያለው ትውልድ ያስከብር መብቱን
    ያስመስክር የዜግነት ተዋረድ አለመኖሩን
    ሃይማኖት የግል ሀገር የጋራ
    ማን ፈቀደለት አንዱ ሊጠፋ ሌላው ሊበራ
    *******
    እንቢኝ በል!
    ከትናንት ዛሬ ተሽሎ ካላገኘኸው
    ትዕግስት ፍራቻ ከመሰለው
    እንቢኝ ባለ ነው መይሳው
    ታፍረን ተከብረን የኖርነው
    ምነው ሸዋ በለው!

    አልበዛም ወይ?
    ወይ ንቀት! አለማወቅ የሰው ልክ
    እንቢኝ ባለ ነው ምንይልክ
    በኅብሪተኖች ላይ ስንነሳ የኢትዮጵያዊያን ልክ
    ጠላት ይመስክር፣ ሹምባሽም ያውራ፣ ይናገር ታሪክ!።
    ሀገር ሠላም ይሁን በመፈቃቀር በመከባባር
    ዘንድሮ፣ ነገም፣ ተነገ ወዲያ፣ አ’ለ ነገር
    ኢትዮጵያ የሁላችንም በሁላችንም ለዘለዓለም ትኑር።!
    ****************************

Comments are closed.

Share