የአማራ ጉዳይ፤ አለ? ወይስ የለም?

መስፍን ወልደ ማርያም

ግንቦት 2006

ተናግሬ ነበር ማለት ዋጋ የሌለው የወሬ ማጌጫ ነው፤ እስቲ ፍቀዱልኝና ልጠቀምበት፤ ከወያኔ ዋና ምሁር፣ ከመለስ ጋር ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ፊት-ለፊት በቴሌቪዥን በተገኛኘን ጊዜ ‹‹አማራ የሚባል ጎሣ የለም፡›› በማለቴ መለስ ዜናዊና ጭፍሮቹ ብቻ ሳይሆኑ ‹‹አማራ-ነን ባዮች›› በቃልም፣ በጽሑፍም፣ በቴሌፎንም ልክ-ልኬን እየነገሩኝ አንጀታቸውን ቅቤ አጠጥተው ነበር፤ ‹አንዲት ሴት ደውለው እብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል፤› ብለውኛል፤ አንድ ሰው የተናገረው ስሕተት ከሆነ ስሕተቱን በማስረጃ ማጋለጥና የራስን ሀሳብ በማስረጃ መትከል ነው፤ እውቀት የሚዳብረው፣ ሰዎች የሚማሩትና በእድገት ጎዳና የሚጓዙት በተጨባጭ ማስረጃ መነጋገር ሲችሉ ብቻ ነው፤ እኔ አማራ የለም፣ ዜሮ (0) ነው፤ አልሁ፤ አማራ አለ፣ አንድ አለ፤ (1) ነው ያለ ሰው የአንድን ዋጋ ማሳየት አለበት፤ አማራ የለም የሚል ዜሮ ነው ማለቱ ስለሆነ ከሌለ ነገር ምንም አይጠብቅም፤ ከአለ ነገር (ከ1) ብዙ ነገሮችን መጠበቅ ይቻላል።

ዱሮ በልጅነታችን ጭራቅ የሚሉት ማስፈራሪያ ነበረ፤ በአለፉት ሃያ ሦስት ዓመታት አማራ የሚባል ጭራቅ ማስፈራሪያ፣ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ ቋት እንደሆነ ሲነገር ቆየ፤ መለስ ዜናዊም እየደጋገመ ‹አከርካሪቱን ሰብረን ሁለተኛ እንዳያንሰራራ› እናደርገዋለን እያለ እንደዛተ የተሰበረውን አከርካሪት ሳያይ ሞተ፤ በሕይወትም እያለ ቢሆን መለስ ዜናዊ አከርካሪቱን እሰብረዋለሁ የሚለውን አማራ የተባለ ስያሜ እንደሹመት ለነበረከት ስምዖንና ለነተፈራ ዋልዋ ይሰጥ ነበር፤ የክብር ጎሣ እንበለው! ራሱም ቢሆን ከዚህ የክብር ጎሣ ቤተሰብነት አልራቀም፤ አከርካሪቱ እንኳን ሊሰበር አልተገኘም!

ስንት ሺህ ሰዎች አማራ ናችሁ እየተባሉ ከስንት ስፍራ ተፈናቀሉ? አማራ ማለት እነዚሁ የተፈናቀሉት፣ በየጫካው የተገደሉትና የተሰደዱት ብቻ ናቸው? ሌሎችም ካሉ የጎሣ ዝምድና ሳይስባቸውና ከተፈናቀሉት ጋር አብሮ ለመቆም ለምን አልቻሉም? በጋምቤላ በደረገው ጭፍጨፋ የተጨፈጨፉት ጎሣዎች በጣም ትንሽም ቢሆኑ ከካናዳ እስከ አውስትራልያ ዓለምን ያዳራሱት የጎሣ ዝምድና ስሜት ለምን ለእነዚህ አማራ ለተባሉት ተፈናቃዮች አልሠራም? እንግዲህ አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉትና የሚሰቃዩት ዘመድና ደጋፊ የሌላቸው ሰዎች ናቸው ማለት ነው፤ ሰውነታቸውም ቢሆን በሕግ ያልተረጋገጠላቸው፣ ሕግ የማይመክትላቸው ናቸው ማለት ነው፤ ይህንን ክርክር ከገፋንበት ዜግነታቸውንም የምንጠራጠርበት ደረጃ ላይ እንደርሳለን፤ ደርግ በጎሣ ላይ የተመሠረተ የውትድርና ሥልጠና ያደረገ ይመስለኛልና በዚህ ጉዳይ ላይ የደርግ ባለሥልጣኖች፣ በተለይም ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አንድ ቀን የሚነግሩን ይኖራል የሚል ግምት አለኝ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መላኩ ፈንታ መታመማቸውን ጠበቃቸው ፍ/ቤት ተናገሩ፤ ኦ! ኦ! ርዕዮት ዓለሙ ጡቷን ታማ የጮኸ የለም!

አጥቂና ጨቋኝ ነፍጠኛ የሚባለው ሕዝብ ሲጠቃና ሲበደል ከኡኡታ በቀር ድምጹ የማይሰማው ትርጉሙ የህልውና ነው? ወይስ የወኔ? በሌላ አነጋገር አማራ የሚባል ጎሣ በእርግጥ አለ? ወይስ የለም? ከአለ የሚወራለትን ነፍጠኛነትና ወኔ ምን ዓይነት ብል በላው? ይህ ክርክር ከሃያ ሦስት ዓመታት በፊት አማራ የሚባል ጎሣ አለ ብለው የሞገቱኝን ሰዎች (የሞተውን መለስንና ያሉትን ጓደኞቹን ጭምር)፣ የመላው አማራ ይባል የነበረውን ድርጅት፣ ብአዴን የሚባለውን የወያኔ ድርጅት መሠረተ-አልባነት ለማሳየት እንጂ የሌለውንና ከዚህ በፊት ተቆስቁሶ ያልተነሣውን ጎሣ ለማነሣሣት አይደለም፤ የሌለ ነገር ቢቆሰቁሱት አይነሣም,

በአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ውስጥ እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን፣ የሚገደሉትን፣ የሚሰቃዩትን ሁሉ ‹‹ሰዎች›› ብናደርጋቸውና ሰዎች ብንላቸውስ? ሰው መሆን የተፈጥሮ ነው፤ ልለውጥህ ቢሉት አይለወጥም፤ ሰው ሆኖ ተወልዶ ሰው ሆኖ ይሞታል፤ ሰው መሆናቸውን ወንጀል የማድረግ ዝንባሌ የሚኖረው ሰይጣን ብቻ ይመስለኛል።

ወይም አማራ የክርስቲያን ሃይማኖትን ተከታይነት የሚገልጽ ስያሜ አድርገን ብንወስደው የእነዚህ ሰዎች መፈናቀል፣ መገደል፣ መሰቃየትና መሰደድ ክርስቲያኖች እንዲጠፉ ለማድረግ ነው? ይህ ከሆነ አንድ ጸረ-ክርስቲያን ኃይል አለ ማለት ይመስለኛል፤ ይህ መደምደሚያ ችግር አለበት፤ ፓትርያርክና ሊቃነ ጳጳሳት ሰይሞ ጸረ-ክርስቲያን ተግባር ነጋ-ጠባ ማከሄድ አታላዩንና ተታላዩን ለመለየት ያስቸግራል።

እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን ‹‹ኢትዮጵያውያን›› ብንላቸውስ? ኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ ዜግነት ነው፤ ዜግነት አንድ ሕዝብ በደሙና በአጥንቱ የሚገነባው ነው፤ ዜግነት የሕግ ከለላ አለው፤ ይህንን የሕግ ከላላ ተነፍገው በኢትዮጵያ ምድር ከያለበት የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉት፣ የሚሰቃዩትና የሚሰደዱት ኢትዮጵያዊ ዜግነትን ለማጥፋት የተደራጀ ኃይል አለ ማለት ነው።

አንግዲህ አማራ የሚባሉት ነፍጥ የሌላቸው ነፍጠኞች በምድረ ኢትዮጵያ ሰዎችም ሆነው፣ ክርስቲያኖችም ሆነው፣ ኢትዮጵያውያንም ሆነው መኖር አይፈቀድላቸውም ማለት ነው ወደሚል መደምደሚያ በግድ መድረሳችን ነው፤ ያዋጣል ወይ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ በታሪኳን እንደ ዐቢይ አሕመድ አይነት እቡይና ፍጹም አምባገነን አጋጥሟት አያውቅም! - አቻምየለህ ታምሩ

ግራም ነፈሰ ቀኝ አማራ የሚባል ጎሣ እንደሌላ በስያሜው ላይ የሚደርስበትን ጥቃት ለመመከት እንኳን ባለመቻሉ አስመስክሯል፤ በሕይወት ላለ በህልውና ላይ የሚደርስበትን ጥቃት መመከትና መከላከል የተፈጥሮ ነው፤ ይህ ሳይሆን ሲቀር ህልውና የለም።

36 Comments

    • ለአኔ ያልገባኝ የፕሮፌሰሩ ክርክር ነው ::
      ምንም ስም ይኑራቸው አነዛ አጋር የሌላቸው ህዝቦች ተገለዋል : ቤት ተዘግቶባቸው አንድቃጠሉ ተደርጎል በገደል ተወርውረዋል ተፈናቅለዋል !
      ፕሮፌሰሩ ክርስቲያኖች ይበሏቸው ሸዌዎች: ወሎዎች ይሁኑ ጎጃሞች : ጎንደሪ ይባሉ ኢትዮጵያኖች : በነዚህ ህዝቦች ላይ አሁን በዚች ሰዓት የሚደረገው አየተደረገ ያለው አስከፊ ወንጀል ነው::
      ምንድነው ችግሩ በነዚህ ወገኖቻችን ላይ አየተደረገ ያለውን ወንጀል ለዓለም ማሳወቁ አንደ ሀጥያት ያስቆጠረብን ?

  1. “በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ” ተምሮ እንዳልተማረ በታሪክ ተመራማሪዎች ፕሮፌሰሩ ስለካደው የአማራ ማንነት በጥንታዊ ግሪክና አረብ ታሪክ ጸሀፊዎች አማራ ተብሎ የተሰሩ በርካታ ካርታዎች አማራ ከሌለ ሌላው ቢቀር እንደ ጂኦግራፊ ባለሙያነቱ መመልከት የተሳነው ምክንያቱ ችላ ሳይባል መመርመር ይኖርበታል:: የኢትዮጵያን ታሪክ አውቃለሁ የሚል ሰው አክሱሞች በቤጃ ጋር በነበራቸው ውግያና ሌሎች ምክንያቶች ተዳክመው ወደ ስሜን ተራሮችከዛም ወደ ጎንደር ሀይቅና ሸዋ አካባቢ ዘልቀው መግባት ሲጀምሩ ያገኙትን ሕዝብ በቕቕንቁዋውና በባህሉ ከነርሱ የተለየ ምሆኑን ከ18 ትውልድ በሁዋላ አቡነ ተክለሀይማኖት በገድላቸው ስለ አማራ ማንነት የገለጹትን ማስታወስ እንዴት ይሳነዋል? በ linguistics ጥናት አንድ ቕንቕ መሰረቱ ሕዝብ እንደሆነ በምርምርና ጥናቶች ተረጋግጡዋል:: አማርኛ አማራ ከሌለ ከየት መጣ? እንደ ፕሮፌሰሩ ከሆነ ኦሮም የለም ሲዳማ የለም ትግሬ የለም እንግሊዝ የለም ያሉት ማን እንደፈጠራቸው የማይታወቁት ኦሮምኛ ሲዳምኛ ተግርኛ እንግሊዝኛ ብቻ ናቸው:: ከሁሉም የሚደንቀው ይሄው አቕሙ አማራ ላይ ብቻ ያነጣጠረ መሆኑና አንድም ቀን ኦሮሞ የለም ትግሬየለም ወዘተ. ብሎ በድፍረት ሲናገር ተሰምቶ አለመታወቁ ነው:: ታሪክ ቕንቕ ባህልና ልምድ ሲወርድ ሲዋረድ የግዛት ጉልት መለያ ከስሜን ተራራዎች ከተከዜ ወዲህ ከቕራና መተማ አባይ ሸለቆ በሺሎና ሚሌ እስከ አዋሽ በተዘረጋ መሬት ጥንታዊ አገሩ እንደሆነ በበርካታ ታሪክ ተመራማሪዎች ሪቻርድ ፓንክረስትን ጨምሮ የተመስከረለትን ሕዝብ የለም ብሎ መካድ ከጄኖሳይድና የዘር ማጥፋት ወንጀል ተለይቶ መታየት የለበትም:: 23 አመት ሙሉ “አማራ የለም ብሎ ማላዘን” አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል ወደሚባለው አነጋገር ያሸጋግረዋል::

  2. ፕሮፌሰር መስፍን ተምታቶበት ለማምታታት የምጥር የፈለገውን ያመነበትን ይናገራል እንዲባል ብቻ የምጽፍ ሰው ነው:: ፕሮፌሰር አስራት የዛሬ 23 አመት መአአድ ሲያቃቁሙ መኖሩን አረጋግጠው ነው እወክለዋለሁ ብሎ ፓርቲውን መመስረታቸው :: ተወደደም ተጠላ በዛች ሃገር ውስጥ ለተፈጸሙት መልካምም ሆነ መጥፎ ስራዎች አሻራቸውን ጥለው ያለፉት አማራዎች በታሪክ ይታወሳሉ:: የአማራውን የፖለቲካ የበላይነት መካድ መሞከር እውቀት ሳይሆን ድድብና ነው:: ፕሮፌሰር መስፍን ከደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል ስለተፈናቀሉት የአማራው ህዝብ ሲጽፉ ትዝም ያማይላቸው በግፍ በዚያች የጥቁር እምፓየር ሀገር ውስጥ ኦሮሞ በመሆናቸው ብቻ የሚታሰሩ የሚገደሉ ከትምህርታቸው ላይ የሚፈናቀሉ ለዘመናት ከኖሩበት እትብታቸው ከተቀበረበት ከአባት ሀገራቸው የሚፈናቀሉና ለዘመኑ ሹሞች መሬታቸው እየተሰጠ እነርሱ ግን ጉልበት ያለው የሃብታሙ ሰው ዘበኛና ተላላኪ ሆኖ እንዲኖር ደካማው ደግሞ ለልመና የሚወጣባት ኦሮሚያን እያዩ እንዳላዩ ሲሆኑ እኝህ ሰው የተማሩትና ያስተማሩት ዩኒቨርሲቲ ቀስ ት/ቤት ነበር ወይ ያስብላል
    የዚህ ድህረ ገጽ አስተዳዳሪዎች ቢያንስ እናንተ ሲለምታነቡት ባታወጡትም አይገደኝም ግን ቢቻል ፌር ለመሆን ጣሩ

  3. ፐሮፌሰር መስፍን
    እርስዎ ምንጊዜም ትክክል ነዎት።
    አማራ ነኝ፣ወረሞ ነኝ፣ትግሬ ነኝ አያለ ሁሉም ራሱን ያሳሻል። ሰው ተው ሲለው የማይገባው ጀነሬሽን ነው ያለው።
    ለአቶ መለስ ዜናዊም ትክክል መልሰውለታል።

  4. u were the one who said there is no people called “Amhara”. “amhara emibal yelem” this was your word u said during your meeting with Meles Zenawi, every one remember the time and the word u say. but one day we will show u as there is amhara people in Ethiopia. really after that time i don’t consider u as a professor. how can a professor think like that? whether u know or not u are enemy for the amhara people like meles Zenaw who want to see the destruction of the amhara people and amhara land. we will not forget u and meles Zenawi (Devil) for ever and one day we will show u as we are alive.

    • Mr anmanuel. 50 cent we know your intention you try to be smart
      Huh ,,,,,you TPLF cadres are so funny .how much you get paid to to this divisive job ,neka. Belenal!!!

  5. ፕሮፈሰር መስፍን!
    ጥቃትን መመከት የማንነት መግለጫ ከሆነ እነዚህን ሰዎች በኢትዮጵያውያንነታቸውም ሆነ በከርስቲያንነታቸው ልናድናቸው አልቻልንም:: እርሶም እንደሚያምኑት የክርስቲያንነትም ሆነ የኢትዮጵያውነት ህልውና ግን እንደ አምሃራነት የሚጠራጠሩት አይደለም:: ያለፉት ሃያ ሶስት አመታት የሚያሳዩት ኢትዮጵያውያኖች የገባንበትን ችግር ጥልቀት ምንነት ወይ አልተረዳንውም ወይም ለመረዳትና ለመፍትሄው ሃላፊነትን ለመውሰድ እጅግ በጣም እንፈራለን:: ችግሩ ግን የጥፋት አድማሱን ጨምሮ ዛሬ አምቦ ደርሶል:: አዲስ አበባንም እየተፈታተናት ይገኛል:: ወያኔ የሌለ አማሃራ ጎሳ በፕሮግራሙ ፈጥሮ ጥፋት ለማድረስ ቢሞክርም ጉም የመጨበጥ ያህል ነው ውጤቱ ብሎ ማሰብ ትልቅ ስህተት ነው:: ይልቁንስ የጥቃቱ ዋና ሰለባ የሆነው የአምሃራ ጎሳ አባላት መጀመሪያ እራሳቸውን ከአጠቃላይ ጥፋት የማዳን ከዛም ከሌሎች ጎሳዎች ጋር በጋራ ስለምንኖርባት ሃገር አብረን መስራት እንችላለን:: ይህ ሆኖ ሳይቀር ግን የስካሁኑ በገደል መወርወርና በጅምላ መቃጠል ሳይበቃ የርዋንዳ አይነት እልቂት የአምሃራን ህዝብ ቢያጋጥመው ፕሮፌሰር እርሶን ጨምሮ የዚህ ትውልድ የጎሳው ተወላጆች የታሪክ ተጠያቂ ከመሆን አናልፍም:: ምንም እንኮን መአህድ በማፍረስ ታሪክ የማይረሳው ስህተት ብንፈጽምም ሞረስን በመደገፍ በጋራ መቆም የግድ ይለናል::

  6. አይ ሰው አሁንስ ለየልህ:: ድሮ ድሮ ማስረጃ ምናምን ስትል ጎበዝ ነው እኮ እያልኩ ያንተን ጉብዝና ለማስረዳት ያልሆነ ማስረጃ እደረድር ነበር:; ለካ ማስረጃ የማላገኝ የነበረው ማስረጃ ስላልነበረህ ነው::
    ወደድንም ጠላንም አማራ አለመሆኑን ማስረጃ እስላቀረብን ድረስ አማራ አለ;; ያለ ነገር ለምን አይኖርም? ነው ወይስ አንተም አንዱ አሳዳጃችን ነህ? ነገሩ አሁን እኮ ጨዋታው ሁሉ የወደቀን ዛፍ ምሳር…. አይደል የሚባልው!

    ለማንኛውም ኣለ የለም ለማለት ወይም አለሁ የለሁም ለማለት ባለበይቱ እንጅ አልፎ ሂያጁ ሁሉ ማውራት ያለበት አይመስለኝም:: I am Amhara. ያንተን አላቅም:: ስለራስህ የለሁም ጠፍቻልሁ እንደ ዳይኖሰር ማለት ትችላለህ::

  7. “እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን ‹‹ኢትዮጵያውያን›› ብንላቸውስ? ” Amhara & Eth are two sides of a coin and that where the problem lies. I wish we had ALL inclusive Ethiopia.

  8. Min aynet sidb new! Yih sidb betawaki sewochna balesltanat minew tedegageme? Amara melewetin yemifelgna let ke ken yilefa yenebere gin yalew eshokna kurnchit menfesun atfitot tikit blot yale bher enji bebekel woym bezer yemimeka ena yetekefafele chinklat yalew bher aydelem. Amhara lik endetintu Ethiopian enji amaran netlo ayaym malete andn gosa lematfat yemiruaruat ena yetebabe aimro balebet aydelem. Minm enkua zeregna balemehonu bezeregnoch baiywodedm, minm enkua tekula endadenew beg beyechakaw bikerm, minim enkua kehedebet endetechanech ahya badowun teragfo bimelsm, amara zarem gosawinet yemibal koshasha aynekakawum hulem yemiyayew Ethiopia yemtbal hagerun new. Yetintun asbu neftegnanetu le amara sayhon le abysinia neber enji legosa alneberem. Teddyn asbu sheshto mekemet yichl neber gin yetayew ye hageru lualawinet medefer neberna rasun lemot asalfo sete. Minilikn astawusu minim enkua yezihn tarik record mesber yakatachew kifilfayoch tarikun metfo kefen biyakenanbutm, lehageru sihon koratnetun manim yemikdew aydelem! Drom bihon amara amarawi saihon Ethiopiawi new. Yemanim simyelesh eyetenesa yemsalkbet weradana tebab aydelem. Ewunet lalebet sew amara malet sebawinet yemisemaw, lehageru muach, lelimat wedehuala yemail, astewayna libe sefi hizb new. Beteleyayu univesity wust sekay temariwochn eiyu abzagnochu amaroch nachew. Beyetekuamatu yemimesu bitbtochn eyu amara yasnesaw amets yelem. Bizu malet yichalal. Slezih yemanim kiflfay ena kurtrach chinklat balebet hulu eyetenesa afun aykfetbet. Respect amhara bcoz it is not racist but who gave it’s soul for Ethiopians soverignity!

  9. Well there were about 60 learnt, noble, and experienced Amharas to whom you and the notoriously anti Amhara Bereket Habteselassie know what exactly happened.
    The psychological warfare waged against Amhara by the Tegries and the likes of you for too long is costing my people time to organize and rise up. Your denial of my people’s existence is part of the warfare.

    We Will Not Forget

    • T. Goshu, “That is a very challenging and deeply powerful argument !” Hahahahahaha!!!!

    • ፕሮፈሰር በታም ተክክል ናችው ራሱን መከላከል ያቃተው የተጠቃ ብሐር ኣማራ ብቻ ነው ሰለዚህ ህልውናው ያጠራጥራል አማሮች አስቡበት

    • To Prof. Mesfin!

      Question to Prof. Mesfin— Are you Amhara or not? If you are not an Amhara, then leave us alone. Great Amhara will come with Great Ethiopia in the near future!

      God bless The Great Amharawian !!!

  10. you reminded me Mengistu Haile mariam saying there is no Amhara and said AMA means terara and hara means hisbe so AMHARA meanse yeterara hisbi.

    I am guessing you been working for him so you might gave him the speech

  11. Prof may be trying to tell as the amhara people
    Stands to ethiopianisem then its better to call
    Them ethiopians

  12. amara ye leme Eyalaheu amarane atasFegu………ye amara lije wegenh zirh EyalQhe new Tense Atakelfa !!!

  13. ናዚዝም በጀርመን ፣ ፋሽዝም በጣሊያን ቢቀበሩም በኢትዮጵያ ትንሣኤ አግኝተዋል!!!!
    የትግሬ-ናዚዎች አዋጅ፦ «ዐማራን ከምድረ-ገፅ እናጠፋለን!
    ወያኔ የተመሠረተበት ዓላማ እና ተልዕኮ በድርጅቱ ማኒፌስቶ በግልፅ የሠፈረው አቋሙ ነው። ወያኔዎች ተዋጊዎቻቸውን ከሚቀሰቅሱባቸው መፈክሮች «ገረብ ገረብ ትግራይ፣ መቃብር ኣምሓራይ» የሚል ይገኝበታል፤ ትርጉሙም «የትግራይ ተራሮች የዐማራ መቀበሪያ ይሆናሉ» ማለት ነው። ስለዚህ ዛሬም ዐማሮችን በነገዳቸው ለይቶ መፍጀት ከዚህ የትግሬ-ወያኔዎች የትግል መግለጫ የመነጨ፣ ግቡም የዐማራን ነገድ ከምድረ-ገፅ ማጥፋት እንደሆነ ምንጊዜም ሊዘነጋ አይገባም።
    ናዚዝም እና ፋሽዝም በሁለት የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች ተፈጥረው በሁለት የተለያዩ ሥያሜዎች ቢጠሩም መገለጫ ባህርይዎቻቸው ተመሣሣዮች ነው። ናዚዝምም ሆነ ፋሽዝም የፓርላማ ዲሞክራሲን አይቀበሉም። ለእነርሱ ብሔረተኝነት የሚገለፀው በዘር (በጎሣ ወይም በነገድ) ላይ በተመሠረተ መሥፈርት ላይ ስለሆነ የርዕዮታቸው መሠረት ሁሉ ዘረኝነት ነው። ለናዚዎች እና ለፋሽስቶች የቡድን ማለትም «የጎሣ ወይም የነገድ» መብት ከሁሉም መብቶች በላይ ስለሆነ የግለሰብ መብት ሥፍራ የለውም። በተለይ ደግሞ ናዚዎች «ምርጥ የሆነው የአርያን ዘር ነን» ብለው ስለሚያምኑ ዘራቸውን ከሌላው ዘር ሣያቀላቅሉ ማራባት መርሆዋቸው ነበር፣ ነውም። ናዚዎች ለፖለቲካ ግባቸው መቀስቀሻ ፀረ-አይሁዳዊነት ዋና መፈክራቸው ስለነበረ ከ6 ሚሊዮን የማያንሱ አይሁዶችን በአሠቃቂ ሁኔታ በግፍ ጨፍጭፈዋል። ለፋሽስት ጣሊያኖች ዋና ጠላታቸው «ኢትዮጵያዊ» በተለይም ደግሞ «ዐማራ» የሚባለው ዘር ስለነበረ ኢትዮጵያን በወረራ በያዙበት 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን የማያንሱ ኢትዮጵያውያንን በመርዝ ጋዝ፤ በቦንብ፣ በመጥረቢያ፣ በእሣት በማጋዬት እና በሌሎችም አሠቃቂ መንገዶች ጨፍጭፈዋል። በታሪክ ተመዝግቦ እንደሚገኘው በፋሽስት ጣሊያኖች በብዛት የተጨፈጨፉት ዐማራዎች ነበሩ። ናዚዎች እና ፋሽዝቶች በነፃ ገበያ መርሆ የሚመራ የኢኮኖሚ ሥርዓት አይቀበሉም። ስለዚህ የመሠረቱት የኢኮኖሚ ሥርዓት በዘር ትሥሥር እና በሥውር ሤራ ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ካፒታሊዝምን የጀርባ አጥንት አድርጎ የሚንቀሣቀስ የማፍያ ካፒታሊዝም ነበር። በፖለቲካ አመለካከታቸውም ዜጎቻቸውን ለፍፁም አምባገነናዊ አመራር ታዛዥ የሚያደርግ ሥርዓትን ያራምዳሉ። ስለሆነም የሊበራል ዲሞክራሲንም ሆነ በተፃራሪ የቆመው የግራ ርዕዮተ-ዓለም «ኮሚኒዝምን» አምርረው የሚጠሉ እና የሚታገሉ ነበሩ፣ ናቸውም። ሁለቱም እኒህን የርዕዮተ-ዓለማቸውን ምሦሦዎች ያቆሙት «ውሽት ሲደጋገም ወደ እውነቱ ይጠጋል» በሚሉት የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ መሠረት ላይ ነበር። ከላይ የተዘረዘሩትን ለሚመለከት የትግሬ-ወያኔዎች ቀዳሚውን የርዕዮተ-ዓለም መሠረታቸውን ያገኙት ከጀርመን ናዚዎች እና ከጣሊያን ፋሽስቶች መሆኑን ለመገንዘብ ይችላል። ለትግሬ-ወያኔዎች ሁለተኛው የርዕዮተ-ዓለማቸው መሠረት ደግሞ የኮሚኒዝም አመለካከት ነው። አንድ ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው «እንዴት ተደርጎ እኒህን ሁለት ፍፁም ተፃራሪ የሚመስሉ ርዕዮቶች አንድን የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለመምራት በተጣመረ ሁኔታ መርሆ አድርጎ መቀበል ይቻላል?» ብሎ ሊጠይቅ ይችላል፣ ተገቢ ጥያቄም ይሆናል። መልሱ ደግሞ «የትግሬ-ወያኔዎች በሚሄዱበት አቅጣጫ ከተሄደ ይቻላል፤» ነው። ለዚህ እንዲረዳ የትግሬ-ወያኔዎችን የመጀመሪያውን የ1968 ዓ.ም. ማኒፌስቶ በከፊል መመልከቱ ይጠቅማል።

  14. ወያኔ የተመሠረተበት ዓላማ እና ተልዕኮ በድርጅቱ ማኒፌስቶ በግልፅ የሠፈረው አቋሙ ነው። ወያኔዎች ተዋጊዎቻቸውን ከሚቀሰቅሱባቸው መፈክሮች «ገረብ ገረብ ትግራይ፣ መቃብር ኣምሓራይ» የሚል ይገኝበታል፤ ትርጉሙም «የትግራይ ተራሮች የዐማራ መቀበሪያ ይሆናሉ» ማለት ነው። ስለዚህ ዛሬም ዐማሮችን በነገዳቸው ለይቶ መፍጀት ከዚህ የትግሬ-ወያኔዎች የትግል መግለጫ የመነጨ፣ ግቡም የዐማራን ነገድ ከምድረ-ገፅ ማጥፋት እንደሆነ ምንጊዜም ሊዘነጋ አይገባም።

  15. የስለት ገንዘብ የበላ ለፍልፍ-ለፍልፍ ይለዋል እንዲሉ ሽማግለው አገር ከሚያምሱት አንዱ መሆኑን እየመሰክረ ነውጎበዝ ተረባረብ ራስህን አድን=

    • ዉድ ጌታቸዉ!
      ምስጋና ይድረስህ::
      ቀጥሎም ፕሮፌ. መስፊን የተባለዉ የከሰረ ሰዉ ነዉ::
      ዝም ብሎ ይቀባጥራል:: ትልቁ ባንዳ ነዉ::
      ትንሽ ማሰብ ቢችል ኖሮ እንዲህ ባለ ቅሌት አይከስርም ነበር::
      ያማራ ሕዝብ የለም ማለት እብደት ነዉ:: ያማራ ሕዝብ ከሌለ ታዳይ ማን ነዉ የሚፈናቀለዉ?
      ለምን ወያኔዎችና ተለጣፊዎቻቸዉ ጸረ አማራ ዘመቻ ያደርጋሉ?
      መስፍን የመጣበት አይታወቅም:: ወፍ አራሽ ነዉ::
      በመሆኑም ነዉ አማራ የለም እያለ የሚያወናብደዉ::
      የተከበሩ አቶ ተክሌ የሻዉ ጥሩ አድርገዉ የመስፍንን ማንነት አቅርበዋል:: እስከ አንገቱ ድረስ ልክ አድርገዉ ነግረዉታል:: ምንጭሩ ስለበገነ ነዉ አማራ የለም እያለ የሚወሻክተዉ::

      ያማራዉ ባላገር ሕዝብ ለጠላት አኢላማ የሆነዉ በልሂቃኑ ሆዳምነትና ከሃዲነት ነዉ::
      መስፍን ወልደ ማርያም አንዱ ነዉ::
      አማራዉ ተደራጅቶ ጠላቱን እንዳይመክት ያስደረጉት ዋና አሳማዎች እንደ መስፍን ወልደማርያም: ኤንድርያስ ኤሸቴ: ወዘተረፈ የመሳሰሉት ናቸዉ:

  16. Feb12,2o14 አውራምባ ታይምስ ደረ-ገፅ የአቶ መለስንና ሊቀጠበብት መስፍን መልደማርያምን የቆየ ውይይት ለጥፎ ነበር *** ”አሁን የምናደርገው ውይይት አቶ መለስ የግዜያዊ መንግስት ፕ/ት… ምንም እንኳ አሁን በዚያው ወንበር ሆነው ባይሆንም የሚሳደቡት በኢህአዴግ ሊ/መንበርነት ሆነው ይህ ውይይት መደረጉ መልካም መሻሻል ነው”ብለው ነው ሊ/ጠ መስፍን ወልደማርያም የጀመሩት የተቆረጠና የተቀጠለ ስለሆነ ለሟች ሻማ ይዘው ለቋሚ ችቦ ይዘው ለሚያለቅሱ ጥሩ ነው አልገባቸውም። ****ግን ይህ በሻቢያ ኦነግና ኦብነግ ህወአት ያለውን የተቀነባበረ ሸፍጥ የሚያሳብቅ ሀቅ አለው በጥቂቱ… የቀድሞው ፕ/ኮ/ል መንግስቱ ኅይለማርያም ሰለአማራ የሰጡትን ሊ/ጠ መስፍንና መለስ ዜናዊን አስደምሟል ነገር ግን ታዛቢውን ታማኝ ካድሬ ሊ/ጠ እንድሪያስ እሸቴ ሲደግፉም ሲቃወሙም አልተደመጡም ለምን? የመለስ የብሔር ብረሰቦች ጥናት የፈተና ሰጪና የግል አራሚ ስለሆነ ይሆን? ኮ/ል መንግስቱ “አማራ ማለት በተራራ ላይ የሚኖር ደጋኛው ማለት ነው ከአሉ በኋላ በደጋ የሚኖሩትን ሁሉ ዘረዘሩ (ኤርትራዊው፣ ከንባታው፣ ሃዲያው አፋሩ…) እነኛ ሁሉ አማራዎች ናቸው ማለት አደለምን!?።ግን አማራ ደጋ፣ ወይና ደጋና ቆላ መኖር አይፈቀላለትም ማለት ነውን? አማራ አለ!..ለመሆኑ የኤርትራ ግማሽ የአማራ የወታደር ልጅ አደለምን? ሀገሩን ህዝቡን ዳርድንበሩን ለማስጠበቅ በሄደበት ሁሉ ኖረ አገባ ወለደ ችግሩ ምንድነው? ይህ ሁሉ መሞት አለበትን? ይህ አልቅሶ፣ ለምኖ፣ ተስሎ፣ አሜሪካና ካናዳ የሚጎርፈው ሳይሳካለት በጫካ በዱር በገደሉ ከአውሬ ተርፎ በውጭ የሚኖር ሁሉ ማንነቱ ይሰረዝ ያለው ማነው? ይህ አሁን በቋንቋ በዘር በቀለም ያልተመሳሳላችሁን ሁሉ የራሱ ባህል፣ ቋንቋ፣ሃይማኖትያለው አማራ ነውና አፈላልጋችሁ ለመግደል፣ ለማምከን፤ ለማፈናቀል፣ለማሰር ጭራሽም ተጨቋኞችን አሳድመው፣ አሰልጥነው፣ ለማስጨፍጨፍ፣ለማጥፋት ቁጥሩን ለማወቅ የት እንዳለ ይለይ አሉ ።ያለ ፍላጎቱ ኢትዮጵያዊነቱን አስከድተው ባንዲራና መታወቂያ ቀረጹለት እያንዳንዱን ብሄር አቧድነው፣በክልል እንደቁም ከብት መለያ አንገት ልብስ፣ ከኒቴራ፣ ባርኔጣ፣ አስለብሰው ከከተማ ከተማ በመኪና እየጫኑ እንደቀድሞው የባሪያ ንግድ በሜዳ ላይ እያስጨፍሩ እያስለቀሱ መሳቂያ መሳለቂያ አድርግውታል።
    **አማራን ማን ይወክለው? አቶ መለስ ሲመልሱ ሊወክል የሚገባውን ድርጅት ግምታችንም የተሳሳተ ቢሆን ጦርነት ያወጀ ስለሆነ በሚል ‘ኢአኀቅ’ወንጅለን ከጨዋታው ከወጣ… በክቡር መለስ አብዮታዊ ዶሞክራሲያዊ ፍልስፍና “በአመለካከት” ይወከል አሉ።(በትውልደ ኤርትራ ከንባታ ተወከለ ይላሉ.. ሲያብራሩ ግን ገደል ገቡ ‘ሊቁ ይናገራሉ እንጂ አይጠየቁም!” ያለው ማን ነበር? **አማራን የሚወክለው ስላጣን ምንም እንኳ ግለሰቦቹ የግድ የዚያ ብሔር ባይሆኑም አመለካከቱን ስለሚያንፀባርቁ ከኢህአዴግ ክንፍ መልምለን (በብአዴን) አደራጀነው አሉ። አማራን የወከሉት’በአመለካከት’ እኛ እናውቅልሃለን ብለው እያስፈጁት እንደሆነ ባለዕራዩ በሰጡት ቃል አመኑ?..አሁን አማራ ሁሉም ቦታ ያለ ከሁሉም የተጋባ፣ የወለደ፣አብሮ የኖረ ያልመሰላቸው የወከሉት ዲቃሎች እነማን ናቸው? ታምራት ላይኔ፣በረከት ስምኦን፣ አያሌው ጎበዜና ግልገሎቹ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ደመቀ መኮንን ሁሴን እና ሌሎችም ምን ይላሉ? በጥቂት ትምክተኞች ሥም ተወክሎ የተበደለና የተጨቆነ ድሃ፣ የዋህ፣ ህዝብ መሆኑን ያወቁት አራት ኪሎ ተመልሰው በሥልጣን በአጀብ ሲመጡ ሲጨበጨብላቸው ሁሉም በባዶ አግሩና በባዶ ሆዱ ሜዳ ላይ ስላገኙት እንጂ ተማሪ ሆነው የአማራን ንብረትና የተንደላቀቀ ኑሮ ይህ ነበር ብለው የሚያሳዩት ያው የፈረደበትን የደብረብርሃን ብርድ ልብስ ፋብሪካ ይሆናል፡ ምንአልባት ሸዋ ዳቦ ቤት? በተረፈ ተገንጣይ ወቃሽ አያድርገኝ እንጂ ቡና ቤቱ፣ትላልቅ የዕቃ መጫኛ መኪናዎች፣ ጋራዦች፣ ንግድ ቤቱ፣አትገንጠሉብን ብሎ አማራው የወጋቸው መለስ ከኦነግና ኦብነግ ተመሳጥረው ሂዱ ብለው ገርፈውና ዘርፈው ያበረሯቸው የኤርትራውያን ንብረት ነበር። የሌላው ብሔር ብሔረሰብ ጭቆና ከአማራ ይበልጣል ብለው አልተናገሩም፡ቀድሞውንም የዘርን ካርታ የመረጡት ሞኝ በረት የገባ ቀበሮ ሆነው ብሔር ብሔረሰቦች ኦነግና አብነግን ሰብስበው ጫት እየቃሙ ወሬ ሲያቅሟቸው ስለነበር ብቻ ነው። ግን ያልተወራረደ ዕዳ ነው!ደገኞች ከቆለኞች ከወይና ደጋ ነዋሪዎች ከተቀላቀሉስ!?
    *ሊ/ጠበብት መስፍን ወልደማርያም…ጣሊያን በአምስት ዓመት ቤጌምድር፣ወሎን፣ ጎጃም፣ሰሜን ሸዋን አማራ አደረገው አሉ። አቶ መለስ የየጁ ወሎ ኦሮሞ ነበር ብለው መርዝ ከረጩ በኋላ።ትግራይ ውስጥ ሸዋ፣ሽሬ፤እንደርታ፣አክሱም፣ዓጋሜ፤ዐዲግራት፣ መኖራቸውን ሸፍነው ሥነ-አዕምሮ፣ ቋንቋ፣ ባህል፣ግን የትግሬነት መለያቸው ነው ብለው። ጎጃም፣ ጎንደር፣ ሸዋና ወሎ አንድ ባይሆኑም ለአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ልማታዊ መንግስት ፈጠራ ብቻ ሲባል አማራም እራሱን ያጋልጥ ብለው አለቀሱ። እግዚኦ የመሃይማን ጥርቅም ያለህ!”አድዋን አንኳን ሰውን ድንጋዩን አውቀዋለሁ” ያሉትን ክቡር አቶ ገብረመድክን ዓርያን ጥሩልኝ!!አቶ መለስ በሰጡት ምሳሌቸው ላይ ይፈራሉ ያፍራሉ..ትግራይን ከአገው ጋር ለያይቶ ማየት ሊያስቸግር ይችላል ይላሉ!’በአመለካከት’ታሪክ ሳያውቁ መዘባረቅ አደጋ አለው በለው! የጎንደር ሕዝብ ከሸዋ አማራ ከሚጋባ የሚቀለው ከትግሬ ቢጋባ ነው ይላሉ። ሌ/ኮ መንግስቱም ያሉት የትኛው ‘ደገኛ!’የሚለው ሊቁ መለሱት። አቶ መለስ “በአመለካካት” የአማራ ብሄር መወከል አለበትና ትውልደ ኤርትራውያንም አገውም ጥሩ አማርኛ የሚችል ኦሮሞም ቢሆን ጫነው ሲሉ በእራሳቸው ማንነትና ውክልና ላይ ጉድ መኖሩን ይሸፍናሉ። ለመሆኑ ህወአት ትግራይን በሙሉ ይወክላል? አቶ መለስ ሙሉ ትግራይ ናቸው? ወይንስ ትግራይን ‘በአመለካካት’ ብቻ ወክለው ነበር? “እንኳንም የእናንተ ሆኜ ተፈጠርኩ! እንኳንም ከእናንተ ወርቅ አብራክ ወጣሁ!እኮራለሁ አሉ” እልል!…እልል! ተባለ ግን አልነበርኩም። እሳቸው ይህንን ምን አስቀባጠራቸው የባንዳ ዘርነቴን እርሱት? ሹማባሽ አደለንም! መንግስት ሆነናልና የአያቴንና አባቴን አክሳለሁ/እበቀላላሁ ለማለት ነበር? ከኤርትራዊነቴ ይልቅ በፌደራል የምወክላችሁ የትግሬን አመለካካት እኔ ብቻ ስለማውቀው ነው ብለው ማላገጣቸው ነበር? እወይ!
    **”የጭቁን ብሔሮችና ብሔረሰብ መብት ማስከበር የአማራን ጥቅም መጉዳት አደለም ብለው አዛኝ የመሰሉት አድመው አማራው አልተጠቀመም ሲሉ ከደነፉ በኋላ ነው። ሐቁ ግን ሌለውን አለ የማይወክለውን ይወክለው ሲሉ ባንዲራና ቀርጸው ክልል ፈጥረው ሂድ ፍጀው አሉ…
    (ሀ)የቋንቋና የብሄር ተኮር ግደል…ደቡብ ኦሮሚያ ቤንሻንጉል ሲያፈናቅሉ በምን ነበር ትግርኛ ስላልተናገሩ ይሆን?ቦታው ወይና ደጋና ቆላ ከሆነ አማርኛ ተናጋሪ መኖር የለበትም የሚል ሕገ አራዊት አለ?
    (ለ)አሁን አቶ መለስ ዋናው ያማራ ህዘብ ማለት ‘ ከርስቲያንም’ ኢሁን ደገኛ ወይንም ኢትኦጳያዊ የተወከለው ” በሊ/ጠ መስፍን ወልደማርያም አገላለፅ “ውክልና ለውክልና “መስጠት አግባብ አደለም ከኢትዮጵያ መሠረት ብንፈልግ ኖሮ ሀገር እንጂ የዘርን አመለካካትን መለስ ባልወከሉ ነበር”የሚለው አጅግ በጣም ትክክል ነው።
    (ሐ)መለስ አለ ብለው ት እነደሆነ የጠፋቸው አማራ!ሰንደቅ፣ባህል ሃይማኖት፣ሉዓላዊነት ሲላቸው ይናደዳሉ ሊአጠፉት መጡበት ነውና፡
    (መ)አዩ የእኛ ብሄር ብሔረሰብአባት አቶ መለስ…ይህ የዘሩት ዘረኝነትና አማራነት አንድ ዘር እንጂ ሁሉም ቦታ መታየት የለበትም ያሉት ራዕይ ..በአርባ ጉጉ፣በበደኖ፣በሜንጫ ያስጨረሱት የጫት ላይ ፍልስፍናዎ ነው።ዛሬም ራዕይዎን ለማስቀጠል የጀዋርያን የሜንጫ አብዮተኞች መፈክር ድንፋታና የፅንፈንነት ሽብር፤ የቡልቻ ደመቅሳ፣ ነጋሶ ጊዳዳ፣ መራራ ጉዲና፣ሊ/ጠ በየነ ጴጥሮስ የተስፋዬ ግብረእባብ በመፅሐፋቸውና በጋዜጣዊ መግለጫዎቻቸውና ቃለመጠይቆቻቸው በድረገፆች የሚሰጡት ዛቻ ዝልፊና የአመፅ ማስፈራራት ሁሉ “አንድነት ህብረት’ ማለት ኢትዮጵያዊነት ማለት ሆኖ አማራ ማንሰራራቱ ነውና ኢህአዴግ አባላቱን ይሰር ፓርቲውን ያጥፋልን ይበተኑልን ይታሰሩ ሲሉ መግለጫቸውን ይዘው ብቅ ሲሉ አዳዲስ ራዕይ አስፈጻሚ በአጭርና ደቃቅ የታቀፉ ግን መርዛማ ድርጅቶችን በመፍጠር ከፖሊቲካም ከገሀርም ከቤታችንም ውጭ ሆነናል እያሉ ታላቅና በሀገርና በሕዝብ እንዲያውም ኢህአዴግን ከውስጥ በደጋፊ ተቃዋሚ ገልባጭ የጥፋት ኀይልን አደራጅተው እንደሆነ በዚህ ድረገጽ የሚሰነዘረውን የመለስ ደጋፊ መሳይ ሐሳብ መረዳት ለሁሉም በጣም ጠቃሚ ነው!!። የራዕይ አስቀጣይ አማራና ትግሬን መሰል”የአመለካከት ወካዮችን” ከወዲሁ በጥብቅ ሊያስቡበትና ሊጠነቀቁ ይገባል!።በሬ ከአራጁ በላቸው!
    (ሠ)እንግዲህ ‘በአመለካከት’የተወከለው አማራ ሰሞኑን መሰደቡ ብዙዎች እዚህ ተደስተዋል፡ አቶ መለስም ራዕያቸው ይኸው ነበር።ግን ከሊቀ/ጠበብት ብዙ ቁምነገር ተምረው አልፈዋል ችግሩ አስተዳዳጋቸው ተጣሟል ደጋፊዎቻቸውም እንዲሁ!እናንተም ሞታችሁ ድጋፋችሁንና ራዕያቸውን አስቀጥሉ !! መለስ ትግሬና ትግራይን ሳያውቁ እዚያ ክልል በመወለዳቸው ብቻ ‘በአመለካከት’ብቻ ትግሬን ወክለው መሞታቸውን ለቋሚው አዘንኩ!!ኦሮሞዎችም ብሄር ብሄረሰቦችም እራሳችሁን ፈትሹ ጆግራፊ ሳታውቁ ማን? እና የት?እንዳላችሁ ታውቃላችሁን!?እናንተስ የማንና የምን መሆናችሁን በማን? ለምን?እንደተወከላችሁ ማረጋጋጫችሁ ምንድነው? ሰዎች የሚወከሉት በፍቃደኝነት በእውቅና ወይንስ አደባልቀህ ውቃው ዘመናዊ የቅንጦት ባርነት!ብሔር ብሔረሰቦች ነጻ ውጡ በለው! እራሳችሁን በራሳችሁ ወክሉ ተናገሩ ጠይቁ መልስ ይገባኛል፣ ነጻነቴ፣ ሀገሬ ኢትዮጵያ በል! “ውክልና ለውክልና” ዘመናዊ ባርነት! የቁም ተናጋሪ ከብት! እንቢኝ በል! ጀግኖቻችን እንቢኝ ባሉ ነው ታፍረን ተከብረን የኖርነው! በቸር ይግጠመን (ካለፈ መሐደር ለትውስታ)ይጥላል በለው!

  17. ይድረስ ለፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ይቅርታ ከዛሬ ጀምሮ በሀገሬ ህዝብ ገንዘብ ተምረው እንዲህ እንዳንተ አንድን አንጋፋ ነገድ የለም ኖሮም አያውቅ ብለው ለሚክዱ ምሁራን ከልቤ እያዘንኩ ታሪክ ይፋረዳችሁ እላለሁ::በሌላ በኩል ግን ሰፊው የአማራ ነገድ ሕዝብ ነበረ አሁንም ይኖራል:: ወደፊትም ይኖራል:: ተደራጅቶ ራሱን ከጥቃት በመከላከልና ለሌሎችም እንዳይጠቁ ከዚህ በፊት ያደርግ እንደነበረው <> አስከብሮ ይኖራል::የማዝነው ግን ለአንተ ቤተሰቦች ነው ምክንያቱም አንተ እንዲህ በዘባተልክ ቁጥር ቤተሰቦችህ ምን ያህል እንደሚሸማቀቁ ስለማስብ ነው:: በአንድ ጋዘጠኛ ጋባዥነት ያንተንና የመለስን ስለአማራ ትንተና የመንግሥቱን ንግግር አንድ ላይ ተመልክቸዋለሁ::እንዲያ ነው ምሁርነት; እንዲያ ነው በህዝብ ላይ ማላገጥ እንዲያ ነው ኢትዮጵያዊነት ለካስ ለዚህ ነበር ድርጅቶችን አንድነት እንዳይፈጥሩ ስታባላቸው የኖርከው? ለመሆኑ ህወሃት ስንት ነበር የሚከፍልህ?አሁንስ ምን ያህል ሀብት አካብተሃል? የሰው ልጅ እድሜ ሲጠግብ ረጋ ብሎ የሚያስብበትና ትክክለኛ ሚዛናዊ ፍርድ የሚሰጥበት እንጅ እንዲህ የአንድ አንጋፋ ነገድ ሕዝብን የረገጠ የወረደ ንግግር ወይም ጹሑፍ እንዴት ይታሰባል? ፕሮፌሰር የመለስ መምህር እንደነበርክ ሰምቻለሁ ከቶ አንተ ትሆን መለስን እንዲያ ጣሊያን እንዲሆን አገሩን እንዲክድና አማራውን እንዲጨርስ ያስተማርከው? መሆን አለበት:: ደስ አይበል አማራው በሰፊው መደራጀት ከጀመረ ቆይትዋል::ይህ ያንተው አባባል ደግሞ የበለጠ እንድንደራጅ ያደርገናል እንጅ አንድ የጃጃ ሰው ህዝብን ስለአዋረደ አንገታችን አንደፋም::አንድ ጥያቄ ላንሳና ልጠይቅህ ለመሆኑ ያንተው ነገድ የቱ ነው?ምክር ስለ ነገደ አማራ የሚገልጽ ክቡር አቶ ተከለጻዲቅ መኩርያ ከጻፉት “የግራኝ መሐመድ ወረራ” ከሚለው መጽሐፍ ስለሚገኝ እንደማንም ብለህ ፈላልገህ አንብብና ሌላ ነገር ደግሞ ይዘህ ብቅ በል::ሕዝባችሁንና አገራችሁን የምትወዱ ምሁራን በዚህ ሰው ላይ ያላችሁን አስተያየት ለህዝብ እንድታሳውቁ አደራ እላለሁ:: ምክንያቱም ከህወሃት በከፋ መልክ ሌሎች በአማራው ላይ ያላቸውንና የነበራቸውን ጥላቻ የሚያባብስ ቅስቀሳ ነው በእጅ አዙር እየተናገረ ያለው::

    • የዚህ ጽሑፍ ምንጩ ፋክት መፅሔትና http://mesfinwoldemariam.wordpress.com/ናቸው። ማንኛውም ጽሑፍ ለአስተያየት ክፍት ቦታ የሚኖረው ደራሲው ለቀረበለት ሂስም ሆነ ጥያቄ መልስ በመስጠት ሌሎችንም ጨምሮ ውይይቱን ማስፋት፣ ማዳበር እንዲችል መሆኑን getachewም ሆነ የዚህ ድረገጽ አዘጋጆች አያጡትም። የዚህ ጽሑፍ ደራሲ የሚኖረው አዲስ አበባ እንደመሆኑ መጠን ተሯሩጦ በየድረ ገጹ የተጻፉትን ሂሶች የመፈለግ አቅምም ችሎታም እንደማይኖረው ሁሉም ያውቃሉ። ስለዚህ በወፍ ዘራሽ የሚሰጡት ሂሶችም ሆኑ የሚቀርቡት ጥያቄዎች የራስን መድረክ በሰው አርእስትና ጽሑፍ ከማድመቅና ሰውን ከማንቋሸሽ የተለየ ውጤት ተፈልጎላቸው ሊሆን አይችልም። ያሳዝናል!

  18. It would have been appropriate for the Professor to call the Amhara people cowards and useless neftegnas because the Amharas have not been able to even attempt to defend themselves from the onslaught of Tigre Weyane. In that respect, it is fair to say that Amharas should not be considered to even be existing in the land called Ethiopia. If the so-called Amhara exists, why wouldn’t it be able to defend itself from the genocide and ethnic cleansing being committed against it?

    As for me, I will accept the existence of Amhara only after it successfully dislodges weyane from power and defends itself from its enemies. Again, I agree with the professor that an Amhara that cannot self-defend itself from Tigre-Weyane onslaught cannot be considered to have existence.

  19. ancient ethiopia
    January 25, 2014 at 12:09 pm
    The ethiopia’s people have un limited right to know who are the most canncerious enemies of ethiopia who have directly and indirectly involved in the genocide of Amhara.. reliable sources confirmed these Eritreans the fake weyanes ] have killed over 8.9 million ethiopians , 5 million out of 8.9 million are from Amhara ethnice group. If you know any eritreans who are working as TPLF members in the army, police, security, please forward their lists.
    ****እነዚህን አማራ እየተባሉ የሚፈናቀሉትን ‹‹ኢትዮጵያውያን›› ብንላቸውስ? ኢትዮጵያዊነት ታሪካዊ ዜግነት ነው፤ ዜግነት አንድ ሕዝብ በደሙና በአጥንቱ የሚገነባው ነው፤ ዜግነት የሕግ ከለላ አለው፤ ይህንን የሕግ ከላላ ተነፍገው በኢትዮጵያ ምድር ከያለበት የሚፈናቀሉት፣ የሚገደሉት፣ የሚሰቃዩትና የሚሰደዱት ኢትዮጵያዊ ዜግነትን ለማጥፋት የተደራጀ ኃይል አለ ማለት ነው።”
    Eritreans who have been working day and night to eliminate Amhara from the face of this planet and who are responsible for the killing of over 5 million Amharas are as follow]. የአማራውን የዘር ማጥፋት (Genocide)የረጅም ጊዜ እቅድና ፖሊሲ በማውጣትና በመተግበር በዋናነት
    የሚጠየቁት፤ ከነዘር ሃረጋቸው፤ እነማን ናቸው የሚለውን እንመልከት፤
    1. Melese Zenawi. Eritrean.
    2.Sebhat Nega Eritrean.
    3. Abbay woldu m eritrean
    4. Seyum Mesfin , Eritrean.
    5, Tsadikan gebertensae , Eritrean.
    6. Samora yunus , Eritrean
    7. workeneh gebeyehu , Eritrean
    8’ Neway Geberab, Eritrean.
    9. Berkete simon, Eritrean.
    10. berhane G. kistos, Eritrean.
    11, Yosef Hilawi , Eritrean
    12,DR, Fasil Nahom, Eritrean.
    13. Debertsion G. Michael , Eritrean
    14. Tewdros adhanom. Eritrean
    15. tewodros hagos , Eritrean
    16. Dr Solomon enkuae , Eritrean
    17,Tsegaye berhe , Eritrean
    18. Roman hailemariam , wife of the fake PM,,Eritrean.
    19. Tesfaye gebereab., eritrean
    20., Ejigayehu beyene, Eritrean,[ killed so many religious fathers by poisioning their food who were against her boy friend]
    21. G/Michael belai [ tegeray on line moderator] Eritrean.
    22.. Issayas abay berhe [ ayga form moderator], eritrean
    23 yemane kidane , Eritrean
    24. pastor daniele Almaz, Eritrean
    25. Geberkidane desta, Eritrean
    26 Daniel Birhane , eritrean
    ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም ወላጆቻቸው የጣልያን ወራሪን በባንዳነት አሽከር ሆነው እያገለገሉ፣ ኢትዮጵያን የወጉና ሕዝቧን ያስፈጁ
    የጠላት ልጆች ናቸው። የወላጆቻቸውን ፈለግ በመከተል ወላጆቻቸው የሰጧቸውን አደራ በመከተል አሁንም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ
    ጥቃትና በደል እየፈጸሙ ነው። ኢትዮጵያን በማፍረስ፣ ሃብትና ንብረቷን በመመዝበርና በዘር ማጥፋት ወንጀል በመሰማራት በሕግ
    የሚያስጠይቃቸውን ድርጊት እየፈጸሙ ናቸው።
    *************************
    (እንደ መለስ ዜናዊ ትንታኔ “አማራን የሚወክለው አልነበረም…የግድ የዚያ ብሔር ባይሆንም ‘በአመለካካት የሚወክለው ብአዴን’ ተመሰረተ…ታምራት ላይኔ(ደቡብ) ተፈራ ዋልዋ(ከንባታ) አዲሱ ለገሠ (ሀረሪ)ደመቀ መኮንን ሁሴን (አገው) በረከት ስምኦን (ኤርትራዊ) ሌላው ማሟያ (ባለ ሁለት ነገድ) ተጨመረ። አማራ ነን አላችሁ ውጡ እንያችሁ!…’ከደቡብ ክልል አማርኛ ተናጋሪዎች ተፈናቀሉ(የኢሳት ቱሪናፋ በለው!) እነ ዶ/ር ጌታቸው ረዳ (ከኢትዮጵያ ሰማይ ድረ ገፅ) ሰሞኑን በፃፉት አስተያት አማራ ነን ባዮች የወያኔን ቃልና ሥራ ከማራገብ በቀር ስለክልላቸው ሰዎች በቂ ግንዛቤ የላቸው ሲሉ ይሞግታሉ።አንግዲህ አማራ የሚባሉት ነፍጥ የሌላቸው ነፍጠኞች በምድረ ኢትዮጵያ ሰዎችም ሆነው፣ ክርስቲያኖችም ሆነው፣ ኢትዮጵያውያንም ሆነው መኖር አይፈቀድላቸውም ማለት ነው።ግራም ነፈሰ ቀኝ አማራ የሚባል ጎሣ እንደሌላ በስያሜው ላይ የሚደርስበትን ጥቃት ለመመከት እንኳን ባለመቻሉ አስመስክሯል፤ በሕይወት ላለ በህልውና ላይ የሚደርስበትን ጥቃት መመከትና መከላከል የተፈጥሮ ነው፤ ይህ ሳይሆን ሲቀር ህልውና የለም።(ይህ ፅሑፍ ካልገባቸው አማሮቹ አዕምሮም አማርኛም የላቸውም ይቀጥላል በለው!)።

  20. ይሄ ሁሉ ውርጅብኝ ለምንድነው ? እስቲ ደጋግማችሁ የፕሮፌሰሩን ጹሁፍ አንቡት። መልሱን ታገኙታላችሁ። እሳቸው እኮ እያሉ ያሉት ይሄ ሁሉ በደል ሲደርስበት የማይጮህ የማይቆጭ ተደራጅቶም የአማራን ብሄር ለማዳን የተነሳ ሀይል ስለሌለ አማራ የለም አሰኝታቸዋል። እንዲያውም ለተፈናቀሉት አማራዎች ለተገደሉና ሜዳ ለወደቁ አማራዎች ዘመድና ወገን የላቸውም ማለት ነውን እያሉም ይጠይቃሉ ። እውነት ባለፉት ሁለት አመታት በአማራ ብሄር ላይ ብሚደርስበት በደል መፈናቀል እንዲሁም መገደል አማራ ነን የምንል ምን ያደረግነው ነገር አለ? አንዳንዴ ዝም ያለን ነገር ለማናገር የሚያናግር ነገር መፍጠር የሚኖርብን ይመስለኛል። በአማራ መፈናቀል መገደል ሲዘገብ ምንም አስተያየት ሳይሰጥ የለህም ሲባል ግን አስተያየት ጎረፈ።
    ፕሮፌሰር እንዳሉት መለስ ዜናዊ እኮ አማራነትን ለነ በረከት ስሞን ለነ ተፈራ ዋልዋ ሰጥታል ሲሉም ይሞግታሉ እውነተኛ አማራ ቢኖር ኖሮ አማራ ባልሆኑ የአማራ ጠላቶች አልገዛም ይል ነበር። እናም አማራነት መኖሩ እንዲታወቅ አማራነቱንም ያስከብር ያዛን ጊዜ የአማራ መኖርና ለአማራውም ተከላካይ ስለሚኖረው መፈናቀሉም መገደሉም ያቆማል ነው መ ል እክቱ። ካለተሳሳትኩ ወያኔ እንደገባ ሰሞን የሁሉም ብሄረስብ ተወካይ ኖሮት የአማራ ባለመኖሩ አማራ የለም በምለታቸው ብዙ ትችት እንደደረሰባቸውና መአህድ ሲመሰረት የአማራን መኖር ያረጋገጡ ይመስለኛል። አሁንም አማራ የምትባል ተነስ ወገንህ በአማራነቱ ብቻ ሲጠቃ አለሁልህ በለው እያሉ ነው። እኔ የምረዳው እንደዛ ነው።

  21. ይድረስ ለመስፍን ያረጀና ወደ ሞት እየሄደ ያለ ውሻ
    አገቱኒ ብለህ የጻፍከውን መጽሃፍ ላነበበ ሰው ለምን ጸረ አማራ እንደሆንክ መልስ ያገኛል። ንጉሱ በዘመኑ የነበሩትን የስልጣን ቢሮዎች ሳይሰጡህ ወደ ጊምቢ ወለጋ ስለላኩህና ስለተከፋህ ወሎ ላይ ድርቅ ሲከሰት ከሃገርህ ከሚመለከታቸውና የተራቡትን መርዳት ከሚችሉት ጋር መነጋገር ሲኖርብህ ለውጭ ጋዜጠኞች አቃጥረህ ሃገርህን በአለም ዙሪያ አዋረድካት።

    ሁለተኛው ምክኒያት ያገባሃት ሴት ትግሬ ስለነበረችና የወለደችልህ ዲቃሎች ከወያኔ ጋር ሆነው ስለሚጠቀሙብህ ነው።

    ሶስተኛው ምክንያት ድብቅ የስልጣን ፍላጎት ስላለህ ወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣን ያደርገኛል ብለህ ነው።

    ያም ሆነ ይህ አንተም ጥላቻን ይዘህ ከመለስ ጎን መቀበሪያህ ደርሷል ሻቢያም ሞቷል እኛም አማራነታችንን ይዘን በእግዚአብሔር ጥበቃ እንኖራለን።

    አንተ የተረገምክ ቆሻሻ ልትሞት የደረስክ ውሻ፣ ማወቅ ያለብህ ነገር አማራ ኢትዮጵያውያን ስለማንነታችን እንድትዘባርቅ አልወከልንህም አንተኮ በልጅነትሕ የተሰጠህን ክህነት ክደህ በስተርጅና እንኳን ባንተ እድሜ ያሉ ሰዎች ወደ ንሰሃና ወደ ስጋወደሙ ይሄዳሉ። ፕሮፌሰር መሆንኮ እግዚአብሄርን መተው አይደለም ያስተማሩህን የህንድ ፕሮፌሰሮች ተመልከታቸው የሃይማኖታቸውን መለያ ጸጉራቸው ላይ አርገው ሃገራቸውን በዐለም ታላቅ ሃገር አርገዋታል።

    አፍህን መዝጋት ባትችልም ፈጣሪ የጋሃል

  22. መስፍን ሊሞት የደረሰ ከሃዲ የጃጀ የአይምሮ ህመምተኛ ሲሆን በብዙ ሚልዮን የምንቆጠር አማራ ኢትዮጵያውያን በእግዚአብሔር ጥበቃ አለን

  23. ******የአማራ ጉዳይ አማራ አለ? ወይስ የለም? ብአዴን አማራ ነው?
    >>>በመለስ ዜናዊ ሊቀመንበርነት አባይ ፀሃየ፣ ከህወሃት፣ ህላዊ ዮሰፍ፣ ብአዴን ተብሎ ተወሰነ።የኢህዴን ጉባኤ ተጀመረ። ለአንድ ቀን በተለያዩ ጉዳዮች ከተወያዩ በኋላ በሁለተኛው ቀን ፩ኛ) የብአዴን አማራውን የሚወክል (አርማና ባንዲራ) ማጽደቅ፣ ፪ኛ) የብአዴን አመራር መምረጥ ሲሆን በአንደኝነት የተጠበቀው አልተዘጋጀም ተብሎ ለ፪ኛ ጉባኤው ሲተላለፍ፣ መረጣው ግን ቀጠለ። ከዚህ በታች የሚታየው ስም ዝርዝር የአማራ ህዝብ አመራር ናቸው። ከአማራው ህዝብ አብራክ የተወለዱት አማሮች እንደመሆናቸው አማራውን ይመሩታል በማለት በህወሓት የማጭበርበር ዘዴ መለስና አባይ እየተቀባበሉ ተናግረው ምርጫው ቀጠለ።(የግድ የዚያ ነገድ ባይሆኑም በአመለካከት ይወክሉት)ተጠፍጥፈው የተሰሩ!
    ተ.ቁ- ስም- ከነ አባት -የትውልድ ቦታ – ሃላፊነቱ
    1) ታምራት ላይኔ (ጌታቸው ማሞ) -ከንባታ -የብአዴን ሊቀመንበር
    2) በረከት ስምኦን -ኤርትራ -ም/ሊቀመንበር
    3) አዲሱ ለገሰ -ሂርና-ሐረሪ(አደሬ)
    4) ተፈራ ዋለዋ -ሲዳማ -ፕሮፓጋንዳ ቢሮ
    5) ዮሴፍ ረታ -ኤርትራ
    6 መለሰ ጥላሁን- አማራ- ትግሬ
    7 ህላዊ ዮሴፍ -ኤርትራ -የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ
    ተ.ቁ -ተለዋጭ -ማ/ኮሚቴ- ስም ከነአባት- የትውልድ ቦታ
    1 ታደሰ ካሳ -ትግራይ
    2 ሙሉአለም አበበ -አማራ
    እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት በጉባኤው ተመረጡ። ኢህዴን የሚለው ስም ተለውጦ ብአዴን (ብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ተብሎ ተሰየመ። የአማራ መሪ ድርጅት ሆነ። ቀደም ብለው የተነሱ ጥያቄዎች ብአዴን ማን ነው? ከየትስ መጡ? እነማንስ ናቸው? ወዘተ ለሚሉትጥያቄዎች መልሱ ይህ ነው። እውነተስ ብአዴን የአማራውን ሕዝብ ይወክላል? መልሱ ፈጽሞ አማራውን የሚወክል ድርጅት አይደለም ነው።
    **መስከረም 1982 እንደርታ አውራጃ ሰምረ ወረዳ ባኽላ ቁሽት ግዞተኛ የነበረው ብአዴን አመራሩ በሙሉ ተጠርተው መቀሌ ገቡ። የመጡበት ምክንያት ለስብሰባ መሆኑ ተነገራችው። ስብሰባው ሁሉም የህወሓት የፖሊት ቢሮ አባላት፣ መለስ ዜናዊ፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየ፣ ሥዩም መስፍን፣ ስየ አብርሃ፣ ገብሩ አስራት፣ አለምሰገድ ገ/አምላክ፣ አበበ ተ/ሃይማኖት፣ አርከበ እቁባይ፣ አረጋሽ አዳነ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ክንፈ ገ/መድህን እና ጻድቃን ገ/ተንሳይ ሲሆኑ፤ በብአዴን በኩል ታምራት ላይኔ፣ በረከት ስምኦን፣ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋለዋ፣ ዮሴፍ ረታ፣ መለሰ ጥላሁን፣ ህላዌ ዮሴፍና ተደሰ ካሳ ናቸው። በዋናው አጀንዳ ከተነጋገሩ በኋላ በመጨረሻ ብአዴን የህወሓት አጋር ደርጅት መሆኑ ተገለጸላቸው። በዚህ መሰረትም ህወሓትና ብአዴን በመሆን ኢህአዴግ (የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር) ተብለው እንደሚጠሩ ተወሰነ። የቀኑ ውሎ ሁኔታ እንደመግቢያ ተደርጎ “ድምፂ ወያነ” ልክ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በይፋ ታወጀ፣ በጽሑም ተበተነ።አዲሱ ለገሰ በተወለደበት አካባቢ ይኖሩ የነበሩትን አማሮች በአሰቃቂ ግደያ አጥፍቷቸዋል። ከንብረታቸው አፈናቅሎ ለመከራና ችግር የዳረጋቸው የብአዴን መሪ ነው።መለሰ ጥላሁን ባደገበት የአማራው ቦታ በህወሓት የታጠቁ ሃይሎችን በመምራት በአማራው ላይ አሰቃቂ ግፍ የፈጸመ የብአዴን መሪ ነው። በረከት ስምኦን የብአዴን ሥራ አስፈጻሚና መሪ ባደገበት ወሎ አካባቢ በሱ የሚመራው የህወሓት ታጣቂ ገዳዮች በመያዝ በአማራው ህዝብ ላይ ከፍተኛ ግድያ የፈጸመው የብአዴን መሪ ቅጥረኛ ኤርትራዊ ነው።የዚህ ወጀል ፈጻሚዎች ቅጥረኛ ባንዳዎች ኦህዴድ፣ ደህዴን በሌላ ቦታዎች፣ ራሱ ህወሓት በቀጥታ በመግባት ግድያ፣ ዘር ማጥፋት፣ ማፈናቀል ከግብረአበሮቹ ጋር ሆኖ እየፈጸመው ይገኛል። “የአማራ ሕዝብ ተነስ ስንለው ይነሳል፣ ተኛ ስንለው ይተኛል፣ አድርግ ስንለው ያደርጋል በማለት የተናገረው የአማራው ህዝብ ለ፳፫ ዓመታት እንደ ባርያ እየገዙት፣ መብቱ እየተረገጠ፣ እንዴት በእነዚህ የብአዴን ቅጥረኞች ዘሩ እየጠፋ፣ ከየቦታው እየተፈናቀለ፣ እየተገደለ ሊኖር ነው? መልስ የሚሰጠው የነፃነት ግዴታው የሆነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። (አማራ አለ? ወይንስ የለም?) ህወሓት ለራሱ ትግል የተነሳው ኤርትራን አስገንጥሎ የትግራይ መንግሥት እናቋቁማለን ብሎ ነው ፕሮግራሙን አዘጋጅቶ የካቲት/1967 ደደቢት በረሃ የወረደው። በምን መልኩ ነው ደመኛ ጠላቴ ለሚለው አማራ ድርጅት ብአዴንን ሊፈጠርለት የቻለው? ህወሓት ምን መብትና ሃላፊነት አለው? ማንስ ሰጠው? ህወሓት ይህን ሁሉ የፈጠረው የአማራውን ህዝብ ከዘር ማንዘሩ ሊያጠፋልኝ ይችላል ብሎ ነው የብአዴንን ቅጥረኞች “mercenary” የፈጠረው። ሌላውም ህወሓት ለአማራ ድርጅት መፈጠር ቅንጣት የምታክል መብት ፈጽሞ የለውም። ስለዚህ ብአዴን ፀረ- አማራ ቅጥረኛ ድርጅት ነው።
    (ክቡር ገብረመድክን አርዓያ ብአዴን ማነው? ከአውስትራሊያ ሚያዚያ 2006ዓ.ም ከፃፉት ተወሰደ)

  24. ይህ ይህውሃት ውሽማ ተውት; ድሮስ ከአዳሪ ልጅ ምን ይጠበቃል:: እሱ የማንነት ጥያቅይ ስለሚያቃዠው ነው:: ከንቱ

Comments are closed.

Share