የእነ መላኩ ፈንታ ጉዳይ… ከተመስገን ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ከተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝከአንድ ወዳጄ ጋር ሃያ ሁለት አካባቢ ምሳ በልተን ስናበቃ እንደሌላው ቀን ሹፌሬ ስላልነበር በኮንትራት ታክሲ ወደቤቴ (አሲምባ) አመራሁ፡፡ ታክሲው በውለታችን መሰረት የቀበናን አደባባይ ዞሮ ሲቆም፣ እኔም ሂሳቤን አወራርጄ ወረድኩ፡፡ ሆኖም ጥቂት እርምጃ እንደተራመድኩ ያላስተዋልኳቸው ሁለት ሰዎች አጠገቤ ደርሰዋል፡፡ በዕድሜ እኩዮቼ ይመስላሉ፡፡ አንዱ ቀጭንና ቀውላላ ነገር ነው፤ ሌላኛው ደግሞ ቁመቱ መካከለኛ ሆኖ፣ ደልደል ያለ ሰውነት አለው፤ ሁለቱም ‹‹ጠይም›› የሚባሉ ናቸው፡፡ ቀውላላው፡-
‹‹ሰላም ተመስገን!›› አለኝ፣
‹‹ሰላም!›› መለስኩኝ፡፡
‹‹ልናናግርህ ፈልግን ነበር?››
‹‹ይቅርታ አላወኳችሁም፡፡››
‹‹አንተ አታውቀንም! እኛ ነን የምናውቅህ››
‹‹የት ነው የምታውቁኝ? ማለቴ በምን መልኩ…››
‹‹እሱን ተወው! የእኛ ማንነትንም እንድንነግርህ አትጠብቅ፣ ይገባሃል ብለን እናስባለን!›› አለ እስከአሁን ዝም ብሎ የነበረው ደልዳላው ሰው፡፡ ሆኖም ቀውላላው ጓደኛው አቋርጦት ቀጠለ፡-
‹‹ ምን መሰለህ? ሰሞኑን እነ መላኩ ፈንታ እንደታሰሩ ታውቃለህ፤ እናም የእነርሱ ጉዳይ የእኛ ብቻ ነው፤ አንተን አይመለከትህም፡፡››
‹‹አልገባኝም! ይህ ምን ማለት ነው?››
‹‹በቃ! በዚህ ጉዳይ ላይ ትንተና፣ ማብራሪያ እፅፋለሁ ምናምን እያልክ አትድከም ለማለት ነው!›› ቆጣ ባለ መልኩ መለሰልኝ-ደልዳላው ሰው፡፡
ከትከት ብሎ መሳቅ አማረኝ፤ በጣም መሳቅ! ሆኖም ለምን እንደሆነ አልውቅም-አልሳቅኩም፡፡ በግልባጩ ድንገተኛ ንዴት በመላ ሰውነቴ ሲሰርፅ ታወቀኝ፡፡ ከሰከንዶች በኋላም እስከአሁን ሲናገር ትህትና ያልተለየው ቀውላላው ሰው እንዲህ ሲል አግባባኝ፡-
‹‹እየውልህ፣ መንግስት ሰዎቹን ያሰረው በወንጀል ላይ በመሰማራታቸው ከመሆኑ በተጨማሪ ለህዝብና ለሀገር ጥቅም ነው፤ ስለዚህም ገና ፍርድቤት ስለሚቀርቡ፣ ምርመራውም ስላላለቀ አንተ በፅሁፍህ ተሳስተህ፣ ለሌሎችም የተሳሳተ መረጃ እንዳታስተላልፍ ለመምከር ነው፡፡››
‹‹ስለምክራችሁ በጣም አመሰግናለሁ! ነገር ግን እኔ የምሰራውን አውቃለሁና ለስራዬ መካሪ አያስፈልገኝም›› ስል ባለመካከለኛ ሰውነቱ አቋረጠኝና፤ ከቅድሙ በባሰ የቁጣ ቃል መናገሩን ቀጠለ፡-
‹‹ስማ! ልንመክርህ ወይም ልናባብልህ አይደለም የመጣናው፤ በቃ በማያገባህ ጉዳይ መግባት እንደሌለብህ ልንነግርህ ነው!››
ይህን ጊዜም አነጋገሩ በስሱ አስቆጣኝና፡-
‹‹እየወልህ! እናንተ ማንም ብትሆኑ ግድ አይሰጠኝም፤ ኋላ ኪሳችሁ ያለው መታወቂያም አያሳስበኝም፡፡ እስከዛሬ ድረስ የማደርጋትን እያንዳንዷ ነገር አስቤበትና አምኜበት ነው፤ ማስፈራሪያችሁ እኔ ጋ ቦታ የለውም፡፡ ምናልባት ‹ይህንን ጻፍ፤ ይህንን አትጻፍ› ስትሏቸው ትዕዛዛችሁን በመፈፀም ያስለመዷችሁ ጋዜጠኞች ካሉ ወደእነርሱ ልትሄዱ ትችላላችሁ›› ብዬ መንገዴን ልቀጥል ስል፣ ትሁቱና ቀውላላው ሰው፡-
‹‹ተመስገን ብታስብበት መልካም ነው!›› አለ፣
መላኩ ፈንታ እኚህ ናቸው።‹‹ምንም የማስብበት ነገር የለም፤ ይልቅ አለቃችሁን ንገሩት፣ ሰሞኑን እንደናንተ አይነት ፀጉረ ልውጦች በቤቴ አካባቢ በዝተዋልና ሰብስብልኝ፣ ይሄ አንድም ስራ መፍታት ነው፤ ሁለትም የሀገር ሃብት ማባከን ነውና! ብሎሀል በሉት››
…ከዚህ በኋላ ቤቴ ገብቼ ስለገጠመኜ ማሰብ ስጀምር መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች በአእምሮዬ ተመላለሱ፡- በዚህች ሀገር ላይ ምን እየተደረገ ነው? እነማን፣ በእነማን ላይ እያሴሩ ነው? መላኩ ፈንታ የታሰረው እውነት በሙስና ብቻ ነውን? ኢህአዴግስ ዕውን ሙስናን ለመከላከል ቆረጦ ተነስቷል?አሁን ማ ይሙት በሙስና መጠየቅ ከተጀመረ መላኩ ነው የመጀመሪያ የሚሆነው? ወይስ…
አቶ ገብረዋህድ ወ/ጊዮርጊስ(የሆነ ሆኖ ይህችን የሞነጫጨርኩት ‹‹አይመለከትህም!›› ያሉኝ ሰዎች እንደሚመለከተኝ ይረዱ ዘንድ ነውና፣ በቅርቡ በስፋት የምመለስባቸውን የመነሻ ሃሳቦች አስቀምጬ ልሰናበት)
1. መላኩ ፈንታ በባህርዳሩ ስብሰባ ላይ ‹‹የህወሓት ስውር እጆች›› እንደሚደግፋቸው የሚነገርላቸውን ሁለት መቶ ነጋዴዎች በስም ጠቅሶ ‹‹አላሰራ አሉኝ፤ አስቸገሩኝ!›› ብሎ ሪፖርት ማቅረቡ ያስቆጣው አካል በእስሩ ላይ መኖር አለመኖሩን፤ አዜብ መስፍን በዛው ጉባኤ ላይ ‹‹መለስ ብቻ ነው በደሞዝ የኖረው›› የሚል ጥቆማ ከማቅረቧ ጋር ተያያዥነት አለው ወይስ የለውም?
(ስለሰውየው ብቃትና ከሙስና የፀዳ ስለመሆኑ በስፋት ይነገር እንደነበር አውቃለሁ፤ በአናቱም የኢህአዴግ አመራር ሆኖ ከሙስና የራቀ ይኖራል ብሎ ማሰብ በእጅጉ ይከብዳል፡፡ በእርግጥ ‹‹የመላኩ ችግር›› ተብሎ ሲነገር እስማ የነበረው ከመልከ መልካምነቱ ጋር ተያይዛ የምትነሳ ጉዳይ ነች-ቶሎ በፍቅር መሸነፍ፡፡ በነገራችን ላይ መላኩ ከሆኑ ጊዜያት በፊት ዱባይ ውስጥ የመኪና አደጋ ደርሶበት እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ለስራ ጉዳይ ሄዶ ግን አልመሰለኝም)
2. መቼም የማይካደው ሀቅ መላኩ ፈንታ ለፓርቲው ባለውለታ መሆኑ ነው፡፡ ይኸውም በተለይ ከምርጫ 97 በኋላ ኢህአዴግ ‹‹አይደግፉኝም›› ያላቸውን ነጋዴዎች የተለያየ ምክንያት እየለጠፈ እንደአኮሰመናቸው ይታወሳል፡፡ ይህንን የስራ ሂደት ካሳኩት ‹‹ዋነኞቹ አስፈፃሚዎች›› መካከል ደግሞ እርሱ ይመራው የነበረው መስሪያ ቤት ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ እናም እዚህ ጋር የሚነሳው ጥያቄ ዛሬ መላኩ ፊቱን ከጠላት ወደወዳጅ (የስርዓቱ አውራ ጣት ወደሆኑ ነጋዴዎች) ማዞሩ የመዘዘው ጦስ በድርጅቱ ውስጥ ለተፈጠረው ልዩነት ‹‹መያዣ›› (የአብርሃም በግ) አድርጎት ይሆናል ብሎ መከራከር ይቻል ይሆን? መላኩስ ይህንን ጥያቄ ያቀረበው በራሱ ተነሳሽነት ነው? ወይስ ‹‹አይዞህ›› ብሎ አደፋፍሮት ሲያበቃ የከዳው ቡድን አለ?
3. በኢህአዴግ ውስጥ የእስክንድር ነጋ ጉዳይ ልዩነት ፈጥሯል፡፡ እነ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ እንዲፈታ ይፈልጋሉ፡፡ ብአዴንም ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ይህንን ሃሳብ ይደግፋል፡፡ እናም እነዚህ ልዩነቶች መስፋታቸው ይሆናል ሁለት የብአዴን አመራር አባል የሆኑ ሚንስትሮችን በአንድ ሳምንት ውስጥ ‹‹የነቀላ››ው ሰላባ አድርጓቸው ይሆን?
4. እንዲህ አይነቱ እስር እና ድንገት ከሃላፊነት መባረር በመላኩና በብርሃን ብቻ ይቆማል? ወይስ ይቀጥላል? ከቀጠለስ ወደ እነማን ያመራል?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምርኮኛ - አገሬ አዲስ

ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን ለማስከበር ማንኛውንም መስዋዕትነት መክፈል የሁላችንም ግዴታ ነው!

16 Comments

  1. በወያኔወች ቤት ደግሞ ከመቸ ጀምሮ ነው ሙስና ሀጥያት ሆኖ የሚያውቀው?በወያኔ ዘንድ በዝነኛውና ታዋቂው በኢትዮዽያዊዩ ጎንታናሙ በቅፅል ስሙ ቃሊቲ የሚያስወረውረው=1 አማራ መሆን 2 እውነት መናገር 3 ወያኔን መቃወም 4 አማራን ለማጥፋ(ለማዳከ:ለማሰቃየት) በሚደረገው እንቅስቃሴ ተባባሪ አለመሆን___ወዘተ::እነዚህ ወያኔ ሰራሽ ወንጀሎች ይቅርታ የላቸውም::ተሜ ለዘላለም ኑር::”ሊነጋ ሲል ይጨል

    • ንብረት ቃሊቲ የሚያስወረውረው አማራ መሆን ያልከው አልተመቸኝም። የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሥራ ቋንቋ ኦሮምኛ ነው እስኪባል ድረስ ኦሮሞዎች ናቸው እኮ የሚበዙት።

  2. Nice perspective. it is crystal clear that weyane have no intention of fighting corruption without dismantling itself. Now the question is what is going on behind the scine?? I think a sizeable mebers of non-weyane parties in EPRDF are tired of lies and being dictated by weyane. Some might have started working with the opposition and some fighting back weyane. We know what Meles said about Amaharas in benishangul and what Hailemariam said about them. The new word, ‘aderbaynet’, have a lot to do with the recent moves. They are hunting down ‘aderbayoch’, who are working with weyane and still pass confidential information to ESAT and oppositions. And there are some ‘aderbayoch’ who are challenging the control freak tplf. I believe weterners are incouraging and backing non-tplf mebers(likes of protestant Hailemariam D), to take the right path. Any hows lets try to find really going on inside EPRDF and help those who have the gut to stand up against tplf to save Ethiopia and use it to our own advantage, unseating tplf. At the end of the day it is coming clearer more than ever the tplf way is detroying Ethiopia even to some EPRDF members.

  3. Ech ahuns ye3Ethiopia neger hulu astelagn. Lemin Ethiopia tebetina hulum yeyemenderu aleka ayihonim? Yih bicha yekeren. so lets try it!

  4. ተመስገን ማለት ውሽታም ማለት እንደሆነ የማያውቅ ይኖር ይሆን?…አሁን ግን ትንሽ እውነት ለማስመስል ማክሮዋል፡ውሽታምነቱን የሚጠራጣር ካለ ከዚህ በፊት እሱ የጻፈውን ይመለከት። ያልታስረውም ለዚህ ነው…የሱን መዋሽት መንግስት ይፈልገዋል…kkkkkkkkkkk

  5. የህወሀት አዛዦች ስለተመስገን ባህሪ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ለዚች ቀላል ማስፈራሪያ እጅ ሰጥቶ ስለመለኩ ፈንታ ለመፀፍ የፈለገውን ከመፀፍ ይታቀባል ብለው ሊያስቡ አይችሉም። ይልቁንስ እልኸኛነቱን ስለሚያውቁ በርዕሰጉዳዩ ላይ እንዲፅፍ ለማነሳሳት የፈለጉ ነው የሚመስሉት። ይህ ማለት ደግሞ የአቶ መላኩ ፈንታ መታሰር አነጋጋሪ ሆኖ የህዝቡን ትኩረት እንዲስብላቸው መፈለጋቸውን ሊያሳይ ይችላል። ህዝቡ ትኩረቱን ከሌላ አንገብጋቢ ጉዳይ ወደዚህ እንዲያዞርላቸው የፈለጉ ይመስላል። ይህ አሳሳቢ ጉዳይ ምን ይሆን? እንጃ፣ ምናልባት ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ይሆን?

  6. እንደልቡ ልብ ያለህ አልመሰለኝም::እከሌ ያልታሰረው የመንግስት ደጋፊ ስለሆነ ነው::ብሎ መናገር ይከብዳል::ልብ ቢኖርህ ይህንይህንም ልታስብ ትችል ነበር::ተሜ ምርጥ የአቢሲንያ ልጅ ነው::አንተ ልብ የለለህ እተሜ አድናቂወቹ ልብ ውስጥ ድንጋይ ለመቸመር አትሞክር::”ማንም አያምንህም::ሊነጋ ሲል ይጨልማል”

  7. I agree with the therory that Mr. Mussie ( above ) gives.
    The manner in which the 2 persons approach and speak with Temesgen seems
    just a simple provocation and indirectly pushing him to write. Temesgen has written much sensitive issues than this one. If weyanes wanted to prohibit him from writing now, they would have done anything to stop him.
    It seems, as always, weyanes wanted to give indirect warning to everybody who comes on their way, and at the same time leaving the matter as a pure speculation and rumour. Anyway they are also dismanteling themselves, be it ANDM or TPLF or whatever. Just a matter of time for weyanes until the base makes an uprising.

  8. ሙሴ፣

    ነገሮቹን ለማሰናሰልና ለማሰላሰል የተጠቀምክበት መነጽር በጣመ አስገርሞኛል፡፡ የሚገርም አስደናቂ እይታ ነው፡፡ ሃሳብህን ሙሉ በሙሉ እጋራለሁ፡፡ በአናቱም ለመጨመር መላኩ ፈንታ በሙስና ብዙም የሌለበት መሆኑን ደጋግሜ ሰምቻለሁ፡፡ በማስፈጸም ብቃቱም ሆነ በሞያ ቅርበቱ ለባለሥልጣኑ መሥሪያ ቤት የተሻለ ሰው መሆኑ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ይህ ያልታሰበ ርምጃ የሚከተለትም ሃልዮቶችን መሠረት ያደረገ ይመስልኛል፣

    አንደኛ፣
    አውራምባ ታይምስ ስለጉዳዩ ሲዘግብ በመጨረሻው አንቀጽ ላይ “ቆራጡ” ጠ/ሚ ኃይለማርያም በፓርላማ ንግግራቸው ሕዝቡን በሙስና ላይ እንዲነሳና እንዲረዳቸው በጠየቀው መሠረት የሚል ነገር ጨምሯል፡፡ ለመሆኑ እንዲህ ዓይነት በሚሊዮን ብር ከየጓዳውና ከየሥርቻው የሚለቀምበትና የብሔራዊ መረጃና ደኀንነት መ/ቤቱን ንቁ ተሳትፎ የተጠቀ ምርመራ በኃይለማርያም ጠያቂነት በሕዝቡ ንቁ ተሣትፎ በሦስት ሳምት ጊዜ ውስጥ የተደረገ ነው ለማለት ይቻላል? አይመስልም ታዲያ አውራም ታይምስ ኃይለማርያምን አጉልቶ ለመሣል ለምን ፈለገ? በኃይለማርያም መጉላት ምክንያት የመንግሥት የማሽከርከሪያው ማርሽ ህወሃት እጅ ሳይሆን በኃይለማርያም እጅ መሆኑን ለሚያውቀው ኢትዮጵያዊ “ለማሳወቅ” ይሆን?

    ሁለተኛ፣
    ሰሞኑን በሶማሌ ክልል አፈትልኮ የወጣውና የክልሉ ፕሬዚዳንት ተዋናይ የሆኑበት የቪዲዮ ማስረጃ የዚህ ዓመት ታላቁ “የዊክሊክስ” መረጃ ይመስለኛል፡፡ ይህ መረጃ በሶማሌ ምሑራንና የመብት ታጋዮች ሳይቀር ተጨማሪ ማብራሪያ እየተሰጠበት የህወሃት ሥውር እጅ በሕዝቦች እንድነትና በኢትዮጵያ ቀጣይ ሉዓላዊነት ላይ ያደረሰውን ወደር የለሽ ጥፋት በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ ቪዲዮ በሂደት የሚለቀቅ መሆኑን ኢሳት ከገለጸውም በላይ ስዊድን ውስጥ ፊልም እየተሰራበትም የሚገኝ ክፍል ሁሉ አለው፤ በዚያውም የስዊድን መንግሥት በእርሱም በኩል የአውሮፓ ኀብረት በክልሉና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ላይ ያለው ጥፋትና ኢሰብአዊነት ምን ያህል ቅጥ ያጣ መሆኑን የሚረዱበት አጋጣሚ ተፈጥሮአል፡፡

    እነዚህን መሠረታዊ ነጥቦች ጨምሮ የአማራ ተወላጆችን ከቤኒሻንጉል ጉምዝና ከጉራፈርዳ ማፈናቀሉ የፈጠረውን ዓለማቀፋዊ የቁጣ ማዕበል ረገብ ለማድረግና ጊዜ ለመግዛት የጦስ ዶሮው መላኩ ፈንታ ለእርድ መቅረቡ በህወሃት ውስጥ ያለው መደናገጥና መረበሽ የሚይዘውን የሚጨብጠውን እንዳሳጣው በግልጽ የሚያሰረዳ ነው፡፡

  9. ተሜ ደሳለኝ እንዚህ በደም የተነክሩ የባንዳ ልጆች አይናቸውን ጥለውብሃል ያ መለስ የሚባል የሂትለር የልጅ ልጅ እነ እስክንድርን በልቶ ሰው ሲሰድበው በፍርሃት ተልፈስፍሶ ከስቶ ሞተ አሁን ደሞ አንድ ያለሀው አንተ አንተንም የሱ አሸፍሻፊዎች እየተከታተሉ መከራህን እያበሉህ ነው በርታ መንድም አለም ቀኑ ደርስዋል

  10. ምነው ከጫወታ ውጭ አረጋችሁት ፅሁፌን?::ሳንሱር ማድረግ ጀመራችሁ እንደ?

  11. what Temesgen trying to tell us about his conversation with the Gov’t “agent” looks rubish and non-sense.By the way what did he tell us in his story about the corruption arrest???It seems that there is something btn hima nd weyane.
    If weyane is not happy and think that Temesgen is a critics of the government,it is easy for them to throw him to jail like the other journalists,like Eskinder Nega and the other journalists.Temesgen is doing a drama,which will soon be revaled itself….Readers.watch up,and read carefully what Temesgen is writing…

Comments are closed.

Share