ግልጽ መልእክት ለአገራችን የታሪክ ፀሃፊዎችና ፖለቲከኞች !

የታሪክ ተወቃሽነቱን ከራሳችን እንጀምር !
በመንገሻ ሊበን
እኛ ኢትዮጵያዊያን የአኩሪ ታሪክ ባለቤቶች እንደሆን ከልጅነት እድሜያችን ጀምሮ እየተነገረን ያደግን ህዝቦች ነን ። የሰው ልጅ መገኛ ፤የቅዱሳን አገር ፤የጀግኖች መፍለቂያ ምድር ፤ መቅደላ ፤አድዋ፤ ማይጨው ወ..ተ የሚሉት ቃላት በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አእምሮ ውስጥ የሚያቃጭሉ የታሪክ ፀፊዎቻችን የብእር ትሩፋቶች ናቸው ። እጅግ የሚገርመው ግን ፣ የአፄ ቴድሮስ እጅና እግር ቆራጭነት ፤ የአፄ ዮሃንስ አንገት ቀንጣሽነት የአፄ ምኒልክ ጡት ዘልዛይነት እንደዚሁም የአፄ ኃይለስላሴ ፤ የኮሎኔል መንግስቱና የአቶ መለስ ዜናዊ አሰቃቂ ወንጀሎች የታሪካችን አንድ አካል መሆናቸው እየታወቀ በታሪክ ፀሃፊዎቻችን ዘንድ ግን ብዙም የሚዳሰሱ ነገሮች አለመሆናቸው ነው ።
እንደዚህ ፅሁፍ አቅራቢ እምነት ፣ መልካሙን ታሪካችን እንዴት አቅበን መጓዝ እንዳለብንና ከመጥፎ ታሪካችንም ምን ዓይነት ልምድ መቅሰም እንደሚገባን መማር የምንችለው ታሪክ ፀሃፊዎቻችን ትክክለኛውን ታሪካችንን ያለምንም መዛነፍና ወገንተኝነት በሃቀኛ ብእራቸው ሲከትቡልን ብቻ ነው ።መረረም ጣፈጠም የኛ ታሪክ የኛ የራሳችን ነውና ።
ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩ በቀጣይነት ላነሳው ወደፈለኩት ርዕሰ ጉዳይ ላምራ።
አውሮፓውያን ቅኝ ገዥዎች እንደ ቅርጫ በተከፋፈሏት የጥቁሮች ምድር፣ በጀግኖች አባቶቻቸን ከፍተኛ መስዋእትነት ብቸኛዋ የነፃነት ቀንዴል የሆነችው እናት አገራችን ኢትዮጵያ ካለፉት 50 እና 60 ዓመታት በተለይም ደግሞ ካለፉት 22 ዓመታት ወዲህ እያጋጠማት ያለው ህልውናዋን የሚፈታተን ኩነት የቱን ያህል ከባድና አሳሳቢ እንደሆነ ብዙዎቻችን የምንገነዘበው ነገር ይመስለኛል።
እንደ እኔ እምነት ለዚህ የአገርን ህልውና በቀጣይነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እየጣለ ለሚገኘው የተወሳሰበ ችግር ተጠያቂዎቹ፣ ከ1983 በኋላ መንበረ ስልጣኑን የተቆጣጠረው የወያኔ ስርዓትና ከእርሱ በፊት የነበሩት ሁለት መንግስታት ብቻ ሳይሆኑ፣ የሃገራችን ታሪክ ፀሃፊዎች፤ ሙሉ እድሜያቸውን በተቃዋሚነት ጎራ ተሰልፈናል የሚሉ ሃይሎችና የኢትዮጵያን ችግር እንደ እጃችን መዳፍ ጠንቅቀን እናውቀዋልን እያሉ በየአደባባዩ የሚመፃደቁት ፖለቲከኞቻችን ጭምር ናቸው።
በእርግጥም እነዚሁ ሃይሎችና ተመፃዳቂ ግለሰቦች ፣ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ፣ ያልነበረን ታሪክ የነበረ አስመስሎ በማቅረብና ፣ “ታሪክ እንደፀሃፊው ነው” እንዲሉ ፣ ከሞላ ጎደል ሁሉንም ታሪካችንን (መጥፎም ይሁን ጥሩ ታሪክ ለፀሃፊው ወይም ለገዥው አካል በሚመች መንገድ በማቅረብ ፣ አንዳንዴም ኢምንቱን ፍፃሜ እጅግ በተጋነኑ የማንህሎኝነት ቃላት በመጀቦን ወይም ደግሞ ትውልድ ሊማርበት የሚገባውን አንኳር ፍፃሜ ምንም እንዳልተፈፀመ በማስመሰል፣ አላስፈላጊ የህይወትና የጊዜ መስዋእትነት እንድንከፍል ከማድረጋቸውም በላይ … በአገራችን ኢትዮጵያ ላይም አሳፋሪ ውድቅት እንዲከተልና ትውልድም ያለፈ ታሪኩን በሚገባ እንዳይገነዘብ የየራሳቸውን ድርሻ አበርክተዋል ብቻ ሳይሆን እስከ ዛሬም እያበረከቱ ይገኛሉ ።
ስለሆነም ታሪክን በማፋለስ ረገድ ፣ የታሪክ ተወቃሽነቱ መጀምር ያለበት፣ ይህንን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተፈጸመ በደል ይፋ አውጥቶ በግልፅ በመወያየትና በመመካከር እንጅ፣ በተፋለሰ ታሪክ ላይ ተንተርሶ በጥፋት ላይ ጥፋት በመስራት አልያም ደግሞ የራስን ሌባ ጣት ወደ ሌላ በመቀሰርና ተጠያቂነቱን በሌሎች ላይ በመለደፍ መሆን የለበትም።
እንደሁሉም የአለም አገራት ፣ አገራችን ኢትዮጵያም በተለያዩ ፍፃሜዎች መጥፎና ደግ ኩነቶችን ያስተናገደች ምድር ናት ። ይህ ሁለት ተፃራሪ ኩነት በታሪክ መዝገብ ላይ በሚገባ ሊሰፍርና ትውልድም በጥልቀት ሊማርበት የሚገባው ነገር ይመስለኛል ። አስቀድሜ በፅሁፌ መግቢያ ላይ እንደጠቀስኩት ከመጥፎ ታሪካችን ምን ዓይነት ልምድ መቅሰም እንደሚገባንና መልካሙን ታሪካችን ደግሞ እንዴት አቅበን መጓዝ እንዳለብን መማር የምንችለው ታሪካችን ያለምንም መዛነፍና ወገንተኝነት በሃቀኛ ፀሃፊዎች ተከውኖ ሲቀርብልን ብቻ ነው። ከዚያ ውጭ ግን መነገር ያለበት ሃቀኛው ታሪካችን በግለሰቦችና የፖለቲካ ሃይሎች አስተሳሰብ ፤ ስሜትና ፍላጎት ላይ ብቻ ተመርኩዞ መፃፉን ከቀጠለ ፣ የታሪክ መፋለስ እንዳያስከትል በእጅጉ ሊያሰጋን የሚገባ ነገር ነው ።
ለመንደርደርያ ያህል አንድ አንኳር ነጥብ ላንሳ ። ይህ አንኳር ነጥብ ፣ ላለፉት 50 እና 60 ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ዓመታት ፣ የህዝባችንና የፖለቲካ ሃይሎቻችንን ቀልብ በከፍተኛ ደረጃ ከሳቡት የአገራችን የፖለቲካ አጀንዳዎች መካከል አንዱ ነው። ይህ አንኳር ጉዳይ በአገራችን የታሪክ መዝገብ ላይ ያለምንም መዛነፍና ወገንተኝነት በሚገባ ሰፍሯልን…ወይም ደግሞ ከእስካሁኑ ፍፃሜ በኋላስ ትውልድ ሊማርበት የሚገባው ሃቀኛ ታሪክ ያለወገንተኝነት እየተፃፈ ነውን…ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ይሰጥበት ዘንድ አንባቢን በአክብሮት እጋብዛለሁ ።
ሁሉም እንደሚያውቀው በአገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻን ከሚይዙት አንኳር ጉዳዮች መካከል አንዱ የኤርትራ ጉዳይ ነው። ፖለቲከኞቻችንና ፀሃፊዎቻችን ይህንኑ አንኳር ጉዳይ አስመልክተው ከደርዘን በላይ የሆኑ መጣጥፎችን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ነገር ቢሆንም “ታሪክ እንደፀሃፊው ነው” የተሰኘው ብሂል ግን በመጣጥፎቻቸው ላይ መንፀባረቁ አልቀረም ። ለምሳሌ ያህል በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ፤ በደርግና በወያኔ ዘመነመንግስታት የኤርትራን ጉዳይ በሚመለከት በፖለቲከኞቻችንና ፀሃፊዎቻችን አማካኝነት ለንባብ የበቁ መጣጥፎችን ብንመለከት ፣ ትውልድ ሊማርበት የሚገባው ታሪካችን የቱን ያህል እየተፋለሰና ያለጥልቅ ጥናት በፀፊው ፍላጎትና ስሜት ላይ ብቻ ተንተርሶ እየተፃፈ እንደሆነ ለመገነዘብ የግድ ተመራማሪነትን አይጠይቅም ። ያም ሆነ ይህ ነገር ከማንዛዛትና አንባቢን ከማሰልቸት በቀጥታ በቀዳሚነት ላነሳው ወደፈለግኩት ርእሰ ጉዳይ እናምራ ። በዚህ ጉዳይ ላይ ሶስቱን መንግስታት ጨምሮ ፖለቲከኞቻችንና ፀሃፊዎቻችን ሲከተሉት የነበረውን አቋም በመጠቃቀስም፣ ከእውነተኛው የታሪክ ፍፃሜ አኳያ የየራሳችንን ድምዳሜ ለመስጠት እንሞክር።
እስካሁን ድረስ በግብታዊነት ስንከተላቸው ከቆዩት የታሪክ ፀፊዎቻችንና ፖለቲከኖቻችን መጣጥፍ አንፃር ከዚህ በታች የሰፈሩት እውነታዎች ለመቀበል የሚያዳግቱና እንደ እሬት የመረሩ መሆናቸው አሌ ባይባልም ፣ የኛ ታሪክ የኛ የራሳችን ነውና ለትውልድ ይበጅ ዘንድ ያለምንም መሸፋፈን መነገርና መፃፍ አለበት የሚል ፅኑ እምነት አለኝ ። ይህ የኔ ብቻ ሳይሆን የብዙዎቻችንም እምነት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ።
በበርካታ የታሪክ ድርሳናት ላይ ከሰፈሩ መጣጥፎች መገንዘብ እንደሚቻለው ፣ የኤርትራ ጉዳይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንደከፍተኛ አገራዊ አጀንዳ በተደራጀ መልኩ ተጋግሎ መስተጋባት የጀመረው በአጼ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት ነው ። ከንጉስ ሃይለስላሴ በፊት የነበሩት የአገራችን ነገስታት (ንጉሰ ነገስታት ምኒልክን ሳይጨምርኢትዮጵያን አሁን በያዘችው የሉዓላዊነት ቅርፅ የማስተዳድር እድሉን ስላላገኙትና (የኢትዮጵያ ግዛት አንዴ ይጠብ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይሰፋ እንደነበረ ልብ ይሏልየግዛት ጠረፋቸውም በነበራቸው የሃይል ሚዛን ላይ የተመረኮዘ ስለነበረ፣ በማስገበርም ይሁን በሌላ ምክንያት (ለምሳሌ አፄ ዮሃንስ መጥቀስ ይቻላል አልፎ አልፎ ወደ ደጋማው የኤርትራ ግዛት ከመዝለቅ ባሻገር ኤርትራን እንደ ክፍለአገር ወይም እንደ ጠቅላይ ግዛት አሁን በያዘችው ቅርጽና ይዞታ የኔ ናት ብሎ የተነሳ አንድም የኢትዮጵያ ንጉስ በታሪክ አልተመዘገበም። ይህ ማለት ግን የባህር በር ጥያቄ አይነሳም ነበር ማለት አይደለም። የባህር በር ጥያቄው ግን አሰብና ምጽዋን ብቻ ሳይሆን ጁቡቲንና ሶማሊያንም ያካትት እንደነበር መዘንጋት ታሪክን ማፋለስ ነው ።
የግዛት ጅማሮውን አሰብና አካባቢዋን በማድረግና ወደተቀረው የኤርትራ ግዛት በፍጥነት በመዛመት ለ60 አመታት ያህል የቅኝ ግዛት ቀንበሩን በኤርትራ ህዝብ ላይ የጫነው የጣሊያው ፋሽስት ስርዓት፣ የመስፋፋት ህልሙን እውን ለማድረግ በኢትዮጵያም ላይ ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችንና የወረራ ሙከራዎችን ማድረጉ ይታወቃል ። ነገር ግን በተለያዩ የማደናገርያ ስልቶችም ሆነ በሃይል የኢትዮጵያን ህዝብ እንደሌሎች የአፍሪካ ህዝቦች አንበርክኮና ረግጦ መግዛት እንደማይቻል ፣ በጀግኖች አያቶቻችን ብልህነት ፤ አርቆ አስተዋይነትና ከፍተኛ መስዋእትነት በታሪካዊው የአድዋ ጦርነት ላይ ሲረጋገጥ ፣ ወራሪው የባእድ ሃይል ያለውድ በግዱ ኢትዮጵያን እንደ ሉዓአላዊት አገር ተቀብሎ ከአፄ ምኒልክ ጋር የተለያዩ ስምምነቶችን ለማድረግ ተገደደ ።
ከነዚህ ስምምነቶች መካከል ተጠቃሾቹ የጣልያን ቀኝ ግዛትንና (ኤርትራንየኢትዮጵያን ድንበር በተመለከተ በ1900 ፤ በ1902 እና በ1908 (..በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈረሙ የስምምነት ሰነዶች ናቸው ። በነዚህ የስምምነት ሰነዶች መሰረት ፋሽስት ጣሊያን የኢትዮጵያን ዳርድንበር በምንም አይነት መልኩ ላለመጣስና የአገሪቱንም ሉዓላዊነት ለመቀበል ስትገደድ፣ ኢትዮጵያ በፊናዋ ከጣልያን ጋር በምንም አይነት መንገድ በጠብ ላለመፈላለግ የውል ቃል ኪዳን አስራለች ።
በአድዋው ጦርነት የጣሊያውን ፋሽስት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወራሪ ሰራዊቱን ከአገራችን ሉዓላዊ ግዛቶች ጠራርጎ ያባረረው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት፣ በጀግኖች አያቶቻችን የማያዳግም ምት ተደናግጦ የተበታተነውንና የመዋጋትና የመከላከል አቅሙ ከዜሮ በታች የወረደውን የፋሽስት ሰራዊት እስከ አስመራ ድረስ ዘልቆ ከምንጩ የማድረቅ…ብቃትና ሞራል ቢኖረውም ፣ ያልነበረን ታሪክ እንደገና መፍጠርና የክብር ስሙን በወራሪነት መዝገብ ላይ ማስፈር አልፈለገም ። እንዲያውም ንጉሰ ነገስታት ምኒልክ አሸናፊ ሰራዊታቸው ድንበሩን ተሻግሮ እንዳይገሰግስ መመርያ ሲያስተላልፉ “ የአገሩ ዛፍ የለው ፤ የወንዱ ባት የለው ፤ የሴቱ ጡት የለው። ከዚህ በኋላ አገሬ አይደለምና ፣ ተመለስ !! ” በማለት እንደተናገሩ እስካሁን ድረስ በእድሜ ጠገብ አያቶቻችንና አባቶቻችን የሚነገርና የሚተረክ እውነታ ነው ። ይህ ታሪካዊ ፍፃሜ የጀግኖች አያቶቻችንን ህግ አክባሪነት የሌሎችን ግዛት ያለመመኘት ጨዋነት በተጨባጭ ያሳየ ተግባር ነው። ከታሪካዊው የአድዋ ጦርነት በኋላ የተፈረሙት ሶስቱ ታሪካዊ ስምምነቶች ደግሞ የኢትዮጵያዊያኑን የአልገዛም ባይነትና የአገርን ዳርድንበር አሳልፎ ያለመስጠት አኩሪ ታሪክ ያስመሰከረ አንኳር ፍፃሜ ነው ።
ነገር ግን ስለኤርትራ ጉዳይ ቀን ከሌት የሚሰብኩን የዘመናችን ፖለቲከኞች ይህንን እውነታ በትክክለኛ ታሪክነቱ ሲያስነብቡን አልታዩም ። እንዲያውን ይባስ ብለው በወቅቱ የነበሩ ሁኔታዎችን ሸፋፍነው በማለፍና የኢትዮጵያውን ንጉሰነገስት መንግስት ህግ አክባሪነት በማጣጣል ለጀግኖች አርበኞቻችን መረብን ተሻግሮ አለመሄድ የተለያዩ ምክንያቶችን ከመፍጠር ባለፈ የወቃሽነት ጣታቸውን በአፄ ምኒልክ ላይ ሲቀስሩ ይስተዋላሉ ። የታሪክ መዝጋቢዎች ወይም ነጋሪዎች ስራ እውነተኛውን ታሪክ በተገቢው መንገድ በመዝገብ ላይ ማስፈር ሆኖ እያለ ፣ የኛዎቹ ጸሃፊዎችና ፖለቲከኞች ግን፣ ባልነበሩበትና ባልተካፈሉበት ታሪክ ውስጥ ሆነው የታሪክ ፈጻሚዎችን ስራ በማጣመምና የየራሳቸውን ትርጉም በመስጠት ፣ የምኒልክን ወደ ኤርትራ ግዛት ዘልቆ አለመግባት፣ አንዴ ከሰራዊታቸው በረሃብና በውሃ ጥም መድከም ጋር፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከመሃል አገር የሰራዊት ሃይል መሳሳት ጋር እያዛመዱ በመግለፅ ፣ እስካሁን ድረስ መፍትሄ ላልተገኘለት ውስብስብ ችግራችንና የህይወት፤ የንብረትና የግዜ ኪሳራችን የበኩላቸውን አሉታዊ አስተዋፅዖ አበርክተዋል ።
እዚህ ላይ መጠቀስ ያለበት ሌላም ታሪክ አለ ። እርሱም፣– በታሪክ ፀሃፊዎቻችን ዘንድ ብዙም የማይወሳውና አፄ ምኒልክ በአድዋው ጦርነት ወቅት በተማረኩት የኤርትራ ተወላጅ የጣልያን ወታደሮች ላይ የፈፀሙት እጅግ አሰቃቂ በደል ነው ። አፄ ምኒልክ ድል የነሷቸውን የጣልያን ምርኮኞች ሰብአዊነት በተመላበት ሁኔታ ተንከባክብው በክብር እንደሸኟቸው በታሪክ ፀሃፊዎቻችን መጣጥፎች ላይ ተደጋግሞ የተነገረን ነገር ቢሆንም … በጦርነቱ ላይ የማረኳቸውን የኤርትራ ተወላጆች ግን እንዴት እጆቻችውን እየቆረጡና በአንገታቸው ላይ እንደሚዳሊያ እያንጠለጠሉ ወደ አገራቸው ኤርትራ እንደሸኟቸው በታሪክ ጸሃፊዎቻችን ብእር ብዙም የተነገረለትና የተወሳለት ጉዳይ አይደለም ። ለምን…?
እርግጥ ነው ይህ እውነታ ለብዙ አመታት ስንጋተው ከቆየነው የተፋለሰ ታሪክ አንፃር ለብዙዎቻችን የማይዋጥና እንደ ኮሶ የመረረም ሊሆን ይችላል ። ነገር ግን ጣፈጠም መረረም የኛ ታሪክ የኛ ነውና ሁሉም ይማርበት ዘንድ በሚገባ መፃፍ አለበት ። ያም ሆነ ይህ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ጊዜ ከማባከን አሁንም ወደ ዋናው ነጥቤ ልመለስ ።
ቅድም እንዳልኩት ካለፉት 50 ወይም 60 ወይም ደግሞ ከዚያ በላይ ከሆኑ ዓመታት ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የመላው ህዝባችንን ቀልብ በመሳብና በአገራችን የፖለቲካ አጀንዳ ውስጥም ጉልህ ድርሻ በመያዝ የሚታወቀው ርእሰ ጉዳይ ኤርትራን የሚመለከተው ክፍል ነው ።
ፋሽስቱ የጣልያን መንግስት በአድዋው ጦርነት ድል ተነስቶና በነጮች አለም አሳፋሪ የውርደት ሸማን ተከናንቦ ከድል ነሽዋ ኢትዮጵያ ጋር ሶስት የተለያዩ ስምምነቶችን ከተፈራረመ በኋላም ቢሆን የተስፋፊነት አባዜውን እርግፍ አድርጎ ለመተው አልፈለገም ። እንዲያውም ይባስ ብሎ በአድዋው ጦርነት የደረሰበትን አሳፋሪ ውርደት ለማካካስ ለረጅም አመታት የዘለቀ ሁለንተናዊ ዝግጅት ሲያደርግ ነበር የቆየው ። በዚህ የረጅም አመታት ዝግጅቱ ነው እንግዲያውስ ለሁለተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ መጠነሰፊ የሆነና በከፊልም ቢሆን ስኬታማ የሆነበትን ወረራ ያካሄደው ። (በዚህ ርእሰ ጉዳይ ዙርያ ብዙ ስለተባለና ስለተነገረ…ወደ ዝርዝሩ ገብቼ በመፃፍ የአንባቢዎችን ጊዜ ማባከን አስፈላጊ አይመስለኝም።)
ያም ሆነ ይህ በዚህ ጉዳይ ላይ መጠቀስ ያለበትና በታሪክ ፀሃፊዎቻችንና ፖለቲከኞቻችን አንደበት ብዙውን ጊዜ በግልፅ የማይነገረን አንድ ነጥብ አለ ። ይሄውም የጣልያን የአምስት አመታት የቅኝ ግዛት ዘመን በማንና በምን መልኩ እንደተቋጨ ተድበስብሶ የሚፃፈው ታሪካችን ነው ። እርግጥ ነው ጀግኖች አያቶቻችንና አባቶቻችን በፋሽስቱ ጣልያን የተደፈረውን የአገራቸንን ክብር ወደ ነበረበት ለመመለስ ለአምስት አመታት ያህል ያደረጉት አኩሪ ተጋድሎ ሁሌም ሊዘከር የሚገባው ነው። ነገር ግን በፋሽት ጣልያን የተደፈረው የኢትዮጵያ ክብር ዳግም ወደ ነበረበት የተመለሰው ያለማንም እርዳታና ድጋፍ በጀግኖች አባቶቻችን ቆራጥ ተጋድሎ ብቻ ነው ብሎ መፃፍ ታሪክን ማፋለስ ነው ።
የእንግሊዝን ወረራ ለመመከት በመቅደላ አፋፍ ላይ ህይወታቸውን እንደሰዉት አጼ ቴድሮስ (በእርግጥ አፄ ቴድሮስ በራሳቸው ሽጉጥ ወይስ በጠላት ጥይት ተገደሉ የሚለው ታሪክ አወዛጋቢ ቢሆንም፣ ስለ ኢትዮጵያ ክብር እስትንፋሳቸውን ይሰጣሉ ተብለው ሲጠበቁ ጭራቸውን ቆልፈው በመፈርጠጥ ለንደን ላይ የታዩት የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ አሳፋሪ ታሪክና ፣ የጣልያንን ፋሽስት ጦር ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርጎ ያወጣው የእንግሊዝ ሰራዊት ከፍተኛ ሚናም የታሪካችን አንዱ አካል በመሆኑ ፣ እንደ እሬት ቢመረንም የግድ መፃፍ አለበት። (ስለአዲስ አበባዎቹ የጄኔራል ዊንጌት ትምህርት ቤት ፤ የዊንስተን ቸርችልና የኮለኔል በርኒንግሃም መንገዶች ፣ የስም አወጣጥ መነሻ ታሪክ የሚያውቀው ኢትዮጵያዊ ወጣት ስንት ነው…..? )
ከፍጻሜ ማህደሮቻችን ውስጥ ምርጥ ምርጡን ብቻ እየለቃቀሙ በታሪክ ድርሳናት ውስጥ ማስፈር ፣ ትዝብት ብቻ ሳይሆን ትውልድንም ማሳሳት ነው ። የታሪክ ድርሳን ማለት አኩሪ ፍፃሜ ብቻ የታጨቀበት መዝገብ አይደለም። ጣፋጭና መራራውም በአንድ ላይ ተቀይጦ የሰፈረበት የእውነተኛ ፍፃሜዎች ሰነድ እንጅ ። ስለዚህ ለትውልድ ይበጅ ዘንድ ያላንዳች መሸፋፈን ሁሉም መፃፍ አለበት።
ወደ መነሻ ነጥቤ ልመለስ………
በሁለተኛው የአለም ጦርነት በአክሲስ ሃይሎች ላይ የደረሰውን ሽንፈት ተከትሎ ፣የጣሊያው ፋሽስት ጦር እንደ ሊቢያና ሶማሊያ ግዛቶቹ ሁሉ ለአምስት አመታት ከገዛት ኢትዮጵያና ለ 60 አመታት ከአስተዳደራት ኤርትራ ጠቅልሎ ለመውጣት ሲገደድ ፣ ኢትዮጵያ ከስደት በተመለሱት ንጉስ ገዥነት በነፃነት ፣ ኤርትራ ደግሞ ጣልያንን አሸንፈው በመጡት እንግሊዞች ስር በሞግዚትነት መመራት ጀመሩ ። ከዚህን ጊዜ በኋላ ነው እንግዲህ የኤርትራ ጉዳይ በአገራችን የፖለቲካ አጀንዳ ውስጥ በተደራጀ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ መራገብ የጀመረው ። ይህ ጉዳይ ከአገራችን ባሻገር አለማቀፋዊ ደረጃ እንዲይዝና ይበልጥ እንዲቀጣጠል ካደረጉት መካከል ደግሞ አፄ ኃይለስላሴና በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው የነበሩት አቶ አክሊሉ ሃብተወልድ በቀዳሚነት ቢጠቀሱም፣ ኤርትራን በሞግዚትነት ስም የተረከበው አዲሱ የእንግሊዝ አስተዳደርም ቢሆን ከራሱ የፖለቲካ ጥቅም አንፃር ጉዳዩን ይበልጥ በማቀጣጠልና አለማቀፋዊ ትኩረት በማሰጠት ረገድ የተጫወተው ሚናም በቀላሉ የሚገመት አይደለም ።ይህም የታሪካችን አንዱ አካል ነውና….ያለምንም መሸፋፈን አሁንም መፃፍ አለበት ።
ይቀጥላል…….
መንገሻ ሊበን
ማንኛውንም አስተያየት ለመቀበል የፀሃፊው የኢሜል አድራሻ ሁሌም ክፍት ነው ። mengeshalibenn@yahoo.com
ተጨማሪ ያንብቡ:  ዘመነ መሣፍንት እና ክልላዊ የስልጣን ሽኩቻው (በ ሙሉጌታ ገዛኸኝ)

19 Comments

  1. The habeshas,

    This is some sort of distraction. Now it is not time to deal with such issues. This is to divert us from our main struggle. Now we are engaged in saving Ethiopia and its people and woyane is getting confused and can do or write what ever they think distract us and to argue each other. No time should be allowed to talk on the title they are giving us. We have our own plan and program and we go ahead to implement it. Imagine he is trying to tell us Eritrea was not part of Ethiopia and all our leaders were totally wrong. even He could not understand the contemporary history. Can He tell us the world history without war? was not any regime or country formation in the world gone through some sort of war? Our Historian do not waste their time currently as there is a lot to write about the currently ongoing harsh situation in Ethiopia. After Ethiopia is liberated from woyane fascist organization they will have ample time to write, research about Ethiopian history that might not covered already.
    Hence please even if you have to, limit such shabia/woyane diversion on this site. There is aigaforum/Tigrayonline for them.

  2. Mengesha,

    Where are you living now? presumably, in Esayas Afewerki palace in Asmara.

  3. @Mengesha Liben
    How did you get all these garbage history, if it not written in Historical books?????
    You are accusing historians in one hand and you wrote garbage in the other hand without giving any references to it. Definitely you heard all these garbage from your Banda forefathers. It is the nature of Banda’s condemning patriots!!!
    Faggot weyane/shabia!!!!!

  4. ይሄን መልክትህን ከሓላ ኪስህ ክተተው::ሀቀኛ ተሁኖ ተሙትዋል::ኢሳያስ በሽንቱ አጠመቀህ እንደ?

  5. Beneka ejihe lemin ante atetsfewem tadeya sentena sent zemen sedekmubet yenorutin bemulu be 1 pege tsfehe lemtechet lematatal setnesa atafrem wey?

  6. በሀይለስላሴ ጊዜ ማነው በራሳችን ሀይል ነው ያስወጣነው ያለው?እርግጥ ነው አምስት አመት ስትቆይ ኢትዮዽያ ሙሉበሙሉ ይዛለች ብሎ ለመናገር አያስደፍርም::እንግሊዝ እረድታ እንዳስወጣና ማንም ኢትዮዽያዊ ያውቃል::ዊንጌት ኢትዮዽያዊ ነው::ያለም የለ::አቦ አንተ ቅዠታም ነገር ነህ::ይሄን ቫይረስህን ወደ ሌላ ሰው እንዳታስተላልፍ::

  7. i respect ur idea and thinking. you are advising historians to recored a correct history of the country. well, that is good. however, you, yourself do not have any citations to write this article over your ideas of meneliks idea about eritrea, about UK to save ethiopia from italian aggration, and your argument about the trutfulness of Tewodrose death. i my self do not trust you and you are not a man to advise others and write the history of ethiopia. at least you have to have one citation about your argument. to say about menelik and eritrea, why menelik goes to expand his territory to south, southeast and southwest, wheile giving his land on the north? because he know his capacity and his military strength, he sheft his attention to south that he can fight rather than fighting modern armed italia. this is what i think!

  8. ፀሀፊው ኢትዮጲያዊ ለመምሰል ቢጣጣርም አፃፃፉ የሻዕቢያ ልዑክ መሆኑን ያሳብቅበታል። እነዚህ ኤርትራኖች ከኛ ምን አላቸው? እኛ እስከነመፈጠራቸውም ረስተናቸው ሳለ እነሱ ግን እስካሁን ድረስ ስለኛ ይጨነቃሉ። ስንተዋቸው በተዉን ምናለበት? ችጋራሞች! ፀሀፊው አፄ ምኒሊክ ከአድዋ ድል በሁዋላ ወደኤርትራ ዘመቻቸውን ያለገፉት ሀገራቸው እንዳልሆነ ስለሚያውቁ ነው እያለ ይቀላምድልኛል። ነፀነታቸውን ከተቀዳጁና የተመድ አባል ከሆኑ ከሀያ አመታት በሁዋላ እንዲህ እያለ ቅጥፈት ምን ትርፍ ለማግኘት ይሆን? ይልቅስ እኛ ከጭንቅላታችን ስለፋቅናቸው እንዲህ ያለውን ተረትተረት እዚያው ልጆቻቸውን ያስተምሯቸው። ሌላው ደግሞ ኢትዮጲያ ለ5 ዐመታት በጣሊያን ቅኝ አገዛዝ ስር እንደወደቀች በድፍረት ሊነግረን ይቃጣል። ጉድ ነው! አይ የኤርትራውያን ምቀኝነት! አለምሁሉ ያወቀልንን በቅኝ ያለመገዛት ታሪክ ለመደለዝ ዐይን ያወጣ ቅጥፈት ውስጥ ትገቡ? በመሰረቱ የአለም አምስቱን ወረራ የአለም ታሪክ የመዘገበው በወረራነቱ (occupation) ነው እንጂ በወቅቱ ከነበረው ከፍተኛ የአርበኞች እንቅስቃሴና ጣሊያን ከማይቆጣጠራቸው ቦታዎች ብዛት የተነሳ እንደቅኝ አገዛዝ ሊቆጠር የሚችል አይደለም። እንግሊዞች ጣሊያንን ለማባረር ያደረጉልንን ከፍተኛ እገዛ አንተ እንዳልከው እየመረረን ሳይሆን በደስታ የምናስታውሰው ነው። የእነሱን እገዛ የካድንበት አንድም ጊዜ የለም፡ ይልቁንስ ለጀነራል ዊንጌትና ለጠ/ሚሩ ቸርችል ለስማቸው መታሰቢያ መንገድና ት/ቤት ሰይመንላቸዋል። የዊንጌትን እንግሊዛዊነት የምትነግረን ኢትዮጲያ የመሰለን መስሎህ ይሆን? ስለመሪዎቻችን ጭካኔም ቢሆን ምናልባት የምኒሊክን እንጃ እንጂ የሌሎቹን አሳምረን እናውቃለን ፅፈነዋልም። በየትም ሀገር ቢሆን የሚፈፀም ቅጣት ከዘመን ስልጣኔ ጋር አብሮ የሚሄድ መሆኑን ስለምናውቅ በታሪካችን አናፍርበትም። ከመቶ አመታት በፊት የነበሩ መሪዎችችንን ዛሬ በደረስንበት የንቃትና የአስተሳሰብ ደረጃ አንመዝናቸውም። ፀሀፊ ሆይ ይልቅስ አንተ ብትጽፍ የሚያምርብህ ሻዕቢያ በራሱ ዜጎች ላይ እየፈፀመ ስላለው ጭካኔ ነው። እኛን እርሳን።

  9. መንገሻ ሊበን የታሪክ ተወቃሽነትህን ካንተው ከራስህ ብትጀምረው ይሻላል። ምናልባት ተገቢውን ትምህርት በወቅቱ ሳትገበይ በመቅረትህ ሊሆን ይችላል የኢትዮጵያ ጉዳይ ሁሉ እንግዳ እየሆነ ወይም እየተንሸዋረረ ያስቸገረህ።

  10. It is sad that about a month ago i posted a comment opposing Dr Berhanu Nega and his G7 friends shamless campaign against Emperror Menilik and the battle of Adwa but the web master censored it now he allowed this kind of dirt tarnishing Ethiopia and her glorious history. Who is this web site working for?

  11. Mengesha,

    Have you been present when menelik cut women’s breasts? Are you talking about menelik of Adwa? or are you describing the cut and paste version of woyane’s menelik? Why the need to focus on the negative to a man who has done plenty of good for his country? Don’t you find it ironic the Christian king Yohannes got beheaded himself by his enemies? What does that indicate? Have you considered circumstances and norms of the time before passing judgement? Why spread hearsay about the last stand of Tewodros when you can get first hand testimonials from the British invaders themselves in a library or your computer?

    Notice how this guy picked apart Ethiopia and its heroes sowing confusion and doubt to gullible souls. The campaign to fabricate a brand new Ethiopian history is in full swing. “Ethiopian history is merely hundred years old”–“What is axum to the rest of Ethiopians?”–“The flag is nothing but a piece of rag”–“Amhara is the reason to all your ills”…etc. are all part of a campaign to belittle Ethiopia and its history. This guy(Mengesha) might sound polished and concerned about Ethiopian history, but in reality he is on a mission to vilify everything associated with Ethiopia. He hasn’t uttered a word about Meles Zenawi yet, but i have a feeling it is coming. If in the second part of his article he starts blaming historians for not recognizing Meles Zenawi’s leadership and legacy,then rest assured the man is a woyane agent masquerading as a concerned Ethiopian.

  12. such piece is not that much hard to identify from where it came. Please it is all nonsense as we are no more cheated by woyane -shabias . Why reverbating the fictitious and fabricated story concerning allegation against Menelik;s mutilation of the Oromo women breast.It is purely the view of Ultra extremist and pseudo fascist of the handful separatist Oromo elites who had for long been nurtured by Woyane ,Grazianis’brain child.Infact Menelik had shown mercy to number of Italian captives .But in contrary he was bitter on those who betrayed and spying for Italians have been subjected to loose one hand and one leg with an intention to teach Bandas of the past and the present. Thus those who are allied with woyane and help ,to the best of their abilities, in dismantling Ethiopian. should know what awaits them in future. Because now history is in the making that the woyanes days are numbered .So Bandas like Solomon.Neway,Lidetu,and others shall face trial and will be served “poetic justice.’

  13. some body brought the truth to the light …i think there are many hidden history in the past 60 or 100 year that our people never know the truth …ethiopia serving british and u.s.a for their geo poletical strategic interest…

  14. Now the truth is we are under weyane’s aparthide rule. That is our priority. No Tewodros..no Yohaness..no Minilik….no haileselase…no Mengestu…even no Meles now..WE ARE BEING RULED BY SAVANGER WEYANES. That is thr CRUDE FACT now. Don’t try to divert our focus by rasing the least important for this and coming generation. You better ask why weyane is displacing Amharas? Why the Somali Kilil president is lebling tegre as friendly and Oromos and Amaharas as enemies? why weyane is sabotaging the muslims demand? why weyane is arresting some officals on corruption charges? Try to correct the histry that you and I are making RIGHT NOW instead of trying to produce a complete and honest past history. If you feel that is important then do it by yourself in whatever way you want, but whatever happened in the past YOU CAN’T CHANGE IS rather tray to change the history IN THE MAKING RIGHT NOW before the next generation evaluate this genteration for this nonsense mess. So go to hell with your old tactic, it is actually expired. The people of Ethiopia have realized now it is what THEY do TODAY not what THEIR FATHERS did in the PAST that could change the destiny of THEIR CHILDERN. in the FUTURE. Try to learn from Soth Africans and Malesians how to go forward!! DEDEB!!!

  15. Ethiopis.
    ante dedeb Dedebit…! ” tmkhtegnochi ” yemilew sdbhn eziyaw yelemedkew E.T.V lay alaznbet. yh yesdb medrek aydelem..!! kezih beterefe mengesha baserachew tshuf zuriya …tarikna metsahaftn eyataqesu sefi wyytna krkr kemadreg ylq , mesedadebna mezelalefu mnm fayda slelielew…, ebakachihu besekene menfes ye agerachinn tarik bemigeba astemrun ! mesedadebna mezelalef lemanm aybejim…!!

  16. በመንገሻ ሊበን የተጻፈውን ጽሁፍ አንብቤዋለሁ። የጻፊውን ማንነት ምንነትና እንዴትነት ከማብጠርጠርና እሰጥ እገባ ውስጥ ከመዘፈቅ የጻሃፊውን ጽሁፍ በጥልቀት መርመሩ ላይ ማተኮር ተገቢ ይመስለኛል። በታሪክ ላይ ቀኖናዊነት አቋም ተሰባሪነትን እንጂ አለምላሚ አይደልም።አንድ አባባል አለ የኃላ አይን ሁሌም ትክክል ነው።ምክንያቱም ክንዋኔዎች ካለፉ በሃላ ፍንትው ብለው የሚታዩ በመሆናቸው ማናም ሊቀይራቸው የማይችል በመሆኑ በአንጻራዊነት ጊዜ ወደፊት እንጂ የሃላ መዘውር ስለሌለው። ታሪክም የትላንት ፍጻሜ እንጂ ዛሬ የሚቀመር ስሌት አይደለም። ዛሬ ታሪክ ለመሆን የግድ ወደ ትላንትነት መቀየር አለበት።
    እናም የእኛና የአካባቢያችን ታሪክ ምን ነበር የሚለውን ለማጤን ከተገቢም በላይ ተገቢ ነው። ምክንያቱም የአካባቢያችን ታሪክ በበላይነት ድርሻውን የሚወስደው ጦርነት ጦርነት ጦርነት ነበሩ አሁንም አሉ።ስጋቶችም አሉ።ታሪካችን የጦርነትና የእልቂት ከሆነ ለምንድነው ካለፉ ጦርነቶች መማር ያልቻልነው? እልቂት ምርጫችን ሆኖ? መቻቻል ተስኖን? ስልጣኔ እንደ ሰማይ ርቆን? በፍጹም። ከታሪክ መማር ያልቻልነው በእርግጠኝነት ታሪካችን ተዛንፏል።ወደ አንድ ጎን በእጅጉ አጋድሏል። ከተዛነፈው አልያም ከተንጋደደው ታሪክ ጀርባ ተጠቃሚ ቡድኖች ነበሩ።እነዚህ ቡድኖችም ለጥቅማቸው (በአብዛኛው ብሔራዊ ጥቅም ሳይሆን ለግል ስልጣናቸው) ሲሉ ታሪክን ደብቀው ሌላ ፈብርከዋል።ነጩን እንጂ አስተማሪ የሆነውን ድክመት ወይም ስሕተት ደብቀዋል።

Comments are closed.

Share