የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ የቦርድ አባላት ከስልጣናቸው ወረዱ፤ ቤተክርስቲያኑም በገለልተኛነቱ እንዲቀጥል ተወሰነ

May 12, 2014

ይታየው ከሚኒሶታ

ከአንድ ዓመት በላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ ሲያወዛግብ፣ ሲያነጋገር ቆይቷል። “ሃገር ቤት ያለው ሲኖዶስ እና ውጭ ሃገር ያለው ሲኖዶስ እስከሚስማሙ ድረስ ላለፉት 20 ዓመታት በገለልተኛነት እንደቆየነው መቆየት አለብን” በሚለው እና “ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ መቀላቀል ያለብን ጊዜ አሁን ነው” በሚለው ወገን በተነሳው እሰጥ አገባ ሲታመስ የቆየው የሚኒሶታው ደብረ ሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ዛሬ ምላሹን አግኝቷል፤ በድምጽ ብልጫም በገለልተኛነቱ እንዲቀጥል ተወስኗል።

ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንዲቀላቀል የሚፈልገው ወገን በአዲስ አበባው ሲኖዶስ ስር ያሉ አባቶችን ጋብዞ የነበረ ሲሆን በተለይ አቡነ ማርቆስ የተባሉ አባት ለ21 ዓመታት የቆየውን ቤተክርስቲያን “ህንጻ’ እያሉ ሲያንቋሽሹ እንዲሁም “መድሃኔዓለም ቤተክርስቲያንን አሳማ ያርቡበት” ሲል አሰድቧል በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ሲደርስበት ነበር። (የቪዲዮ ማስረጃውን ለማየት ይህን ይጫኑ)

ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ እንዲቀላቀል የሚፈልገው ወገን በዚህ ወቅት ከወያኔ ጋር በመቆም አልተሳካም እንጂ በዘ-ሐበሻ ላይም ክስ መስርቶ ነበር። ይኸው ወገን በሌሎች ኢትዮጵያውያን የሚጻፉትን አስተያየቶች እንዲታፈኑ በጠበቃቸው አማካኝነት ደብዳቤ ጽፈው የነበረ ቢሆንም ዘ-ሐበሻ ጆሮ ዳባ ልበስ ብላ ቆይታለች። ጠበቃቸው ለከሰሰችው ክስም ምላሽ አግኝታለች።

በነዚህ ሁኔታዎች የቀጠለው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ዛሬ በሕግ አደባባይ እጣፈንታውን የለየ ሲሆን “እግዚአብሔር አሸንፏል” ሲሉ ምእመናኑ ይገልጻሉ። እንደምእመናኑ ገለጻ “የወያኔ መንግስት ፖለቲካ በማይገባቸው እህትና ወንድሞቻችን ውስጥ በሃይማኖት ተቆርቋነት ስም ገብቶ፤ ካህናቱን በገንዘብ አታሎ ደብረሰላም ውስጥ ያለውን ከ1.7 ሚሊዮን ዶላር እጁ ለማስገባት ያደረገው ጥረት ከሽፏል፤ የወያኔ እቅድ 1.7 ሚሊዮን ዶላሩን በእጅ አዙር ወስዶ ወገንን ለመግደያ ጥይት ማዋል እንደነበር ደርሰንበታል” ብለዋል።

(በማህበራዊ ድረ ገጾች እየተበተኑ ካሉ ፍላየሮች መካከል አንዱ)
“እግዚአብሄር ታላቅ ነው” የሚሉት አንድ እናት “ለሰላም እና ለአንድነት ቆመናል። ካህናቱ ሁሉ ከጎናችን እንዲቆሙ ለምነናል፤ በተለይ አባ ሃይለሚካኤል እንደባትነታቸው ብዙ ጠይቀናቸዋል፤ ግን እርሳቸው ‘ቤተክርስቲያኑን ወደ ሃገር ቤቱ ሲኖዶስ መመለስ የቀደመ ህልሜ ነው’ ሲሉ ነግረውናል፤ ያን ግዜ አባ ሃይለሚካኤል ከማን ጋር እንደቆሙ አውቀናል ሲሉ ይናገራሉ።

“በዛሬው ምርጫ በተለይ ላለፉት 20 ዓመታት ታፍራና ተከብራ የኖረችውን ቤተክርስቲያናችንን ከአራቱ የቦርድ አባላት በቀር ሌላው ለሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ሊያስረክብ የነበረው ወገን ከስልጣኑ ተጠራርጎ በሕዝብ ድምጽ መባረሩ አስደስቶናል” ያሉን አስተያየት ሰጪዎች የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ወያኔ ያወጣውን ከፍተኛ ገንዘብ በማክሸፍ ለዚህ ድል መብቃቱ አኩርቶናል ብለዋል።

16 Comments

 1. What’s up Mr. Lealem and his followers, the game,or the (episode) Is over because you did not play by the rules. What i am advising you is apologize or express your regret for what you done to the innocent people. Please don’t be impossible or difficult to others the damage what you done to our church is beyond re-pairable. Good luck where ever you go. All i can say is i am happy not to see you running around in my church. God is great and God bless Gileltena or Gelagaye. bye now

  • በመጀመርያ ገለልተኝነት ምን ማለት ነው? በኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ገለልተኝነት የሚባል ታሪክ አላት ወይንስ ቀኖና ቤተክርስቲያን ይፈቅዳል? ቤተክርስቲያን በድምጽ ብልጫ ትተዳደራለች? ይህን አሳዛኝ እና የመለያየት ዜናን ስናነብ ልናያቸው የሚገቡ ጥያቄዎችን በጥቂቱ ለመዳሰስ ሞክሬያለው፤ በመጀመርያ ገለልተኛ ማለት ፕሮቴስታንት ማለት ሲሆን ከጴንጤ እምነት ውጪ በማንኛውም እምነት ወይንም የህምነት ተቃም ከበላይ አካል ተገንጥሎ እራሱን እንደፈቀደ የሚያስተዳድር ቤተክርስቲያን የለም ለምሳሌ ከሮማው ካቶሊክ የተገነጠለ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የለም፤ ከቸርች ኦፍ ኢንግላንድ የተገነጠለ ቸርች ኦፍ ኢንግላንድ ነኝ የሚል ቤተክርስቲያን የለም፤ከግብጽ አሌክሳንድራ ቅዱስ ሲኖዶስ የተለየ የግብጽ ቤተክርስቲያን የለም እንዲሁም ከግሪክ አቴንስ ቅዱስ ሲኖዶስ የተለየ የግሪክ ቤተክርስቲያን የለም ስለዚህ ለምን እኛ? በብዙ አጋጣሚሆች ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት የተከፈለባቸው አጋጣሚሆች ነበሩ እሩቅ ሳንሄድ የራሻ ኦርቶዶክስ ካልተሳሳትኩ ከ70 ዓመታት በላይ ተከፍለው ሳሉ ገለልተኛ የተባለ ሦስተኛ አካል አልፈጠሩም፤ ታድያ እኛ ለምን? የብልጋርያን ኦርቶዶክስ ብንመለከት እስካሁን አንደኛው እኔ ነኝ እጋዊ ሲል ሌላኛው እኔ የሚሉበት ሁኔ ታላይ እያሉ እንካን ገለልተኛ የሚል አካል እንዳልተፈጠረ ሁሉ ለምን እኛ? በኢትዮጽያን ኦርቶዶክስ እምነት ገለልተኛ የሚባል የለም

 2. ዉጤቱ ይሄን ይመስላል፣ ገለልተኛነትን የመረጠ (470) ወደ ኢትዮጵያ ሲኖድ መቀላቀልን የመረጠ (413) ልዩነት (57)
  እስኪ ስለዚህ ውጤት ሁላችሁም አስተያየት ስጡበት።

 3. 413 pure Christian who chosen haimanot over money.
  470 new faces God knows where they came from and never seen in Church before chosen money/junk politics over haimanot!!! Lesew bewash leras yewashal ends? Be truthful for yourself.

  • Who are you? Are you God? God is the only one who reads your heart like a book. God is the only one who knows who is a good Christians or not. You moron woyane, you know when you came this church. You came yesterday, but we are the founders. We are the pioneers for this church, The fact the matter is woyane doesn’t have shame. Woyane is characterized by pretending to be nice. Woyane killed innocent civilians and ask the people who killed the guy. woyane seeds hatred among people and pretend by asking why you guys separate each other. Woyane is specifically characterized by seeding hatred between brothers, hates unity, hates living together, killing innocent people, burning churches, hates Christians and Christianity …and the likes.
   Let me ask you this. Why you guys disturb and separat our church? If you are a pure Christian, why don’t cry for your brothers and sisters where their churches are burned by woyane in recent
   months. In Gojjam, 8 churches are burned since 8 months ago. The thing is you are yewoyane jelle, who is hiding to take people our church and our money. Everybody knows woyane. There is no way to explain about woyane.

 4. @ Behiwot what are you talking about? Ppl have a right to decide on the fate of the their church. Its not in Ethiopia where pro goverment parts are previladged. Let the people ruke please afterall its a religious institution.

 5. ““እንግዲያውስ የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ”። ሉቃስ 20:20-25
  ሰው የምድር ፍርዱን 470 ለ 413 ፈረደ፤ መድኃኔአለም ደግሞ በቅርቡ የሰማዩን ፍርድ 1 ለ 0 የፈርዳል።

 6. ይቀላቀል ባዮቹ በማጭበርበር ከሳውዝ ዳኮታ፣ ከዎርዚንግተን፣ ከሲንት ፖል ማርያም፣ ከራችስተር፣ ከኤርትራ ገብረኤል እና ጴንጤዎች ሳይቀሩ አሰልፈው ነበር። ግን አልተሳካም! የሰንበት ተማሪዎች ነን እያሉ የብልግና ስድብ ሲሳደቡ ተሰምተዋል ታይተዋል። ከዚህ በኋል ሁሉም ደስ ባለው መንገድ ይሂድ። ድሮም የሚጣላ ነገር አልነበረም። በግድ ከመንግሥት ጋር የቆሙትን ካልደገፋችሁ መባሉ ነው ጥፋቱ። ሁሉም ወደ ወደደው መሔድ ሲችል ይህ ሁሉ ሆነ። እኔ የሚቆጬኝ ያ ሁሉ የተሰበሰበ ሰው በአንድነት ሆኖ ታላቅ ካቴድራል ለመስራት፤ ገንዘብ ለማዋጣት ወይም የተለያዩት አባቶች እንዲታረቁ መፍትሔ ለመፈለግና ጥሪ ለማቅረብ ወይም ጫና ለመፍጥር ቢሆን ኖሮ እንዴት ያማረ ነበር! ለመለያየት መሆኑ እጅግ አሳዝኖኛል! ይህንን ነገር አምጥተው ህዝብን እንዲህ የሚያለያዩትን ልቦና ይስጥልን። መቼም ስለ ኃይማኖት ግድ ያላቸው ሳይህኑ በርግጥም ፖለቲካዊ ተልእኮ ያላቸው ሰዎች መሆናቸው ምንም አያጠራጥርም።

 7. ስላም ለሁላችሁም ይሁን።

  እግዚአብሔር ቀደም ብለን በወሰንነው ውሳኔ መሰረት በገለልተኝነት አቋማችን ጸንተን እንዲንቆም ስለረደን ምስጋና ይገባዋል። ጥቁሩን ልባቸውን ለመሸፈን ነጭ በነጭ ሆነው የመጡትን የወያኔ ሆዳም ተላላኪዎች የልባቸውን አይቶ ቅጣቱን ጌታ ሰጥቷል። ለዚህም ለአምላካችን ምስጋናና ክብር ይሁን። በማጭበርበር ፣ እሻጥር በመፍጠር ስብሰባው በግንቦት 11 አይካሔድም በማለት ስልክ መደወልና ሁሉም ዓይነት ድላላዎችን በመፈጸም ጸረ-ቤተክርስቲያን ደባ ብፈጽሙም ሳይካላቸው ቀርቷል። ከዚህ በኋላ ወያኔና ጭፍሮቹን ከሚኒሶታ ለማስወገድ በርትተን መስራት ይኖርብናል። የእምነት ተቋማት፣ የሀግርና የሕዝብ ጠላት የሆነው ወያኔ ስለሃይማኖት የሚያስብ መስሎ ቢያወራ ለማጥቃት መሆኑን በተክርስቲያናች ላይ የፈጸሙት ዘርፈ ብዙ ደባና ተንኮል ማስረጃ ነው። ከዚህ በኋላ ቤትተክርስቲያንቱን ከተኩላዎች ነቅተን መጠበቅ ይኖርብናል። እግዚአብሔር አምላካችንም ሁል ጊዜ ከእውነት ጎን ነው።
  እግዚአብሔር አምላካችን ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅ!

 8. This is $500 question for every body. What’s up with Mr. Gethawen(ex-merigeta) sun glasses in the meeting hall? Yeahnen tyaka beweletum seven memeles ychalal. Just for fun.

 9. በመጀመሪያ: ሰላምና: ፍቅርን: ይስጠን 413 በሙሉ: ልዩነቱ: የገባቸው: አይደሉም: በጥቂት: ሰዋች: የተታለሉ: ናቸው: 470 መተው: አያውቁም: ላላችሁት: የእናንተን: ሌብነት: ተንኮል: ላለማየት: ቤቱ: የቀረ: እንጂ: የቤተክርስቲያን: አባልና: መሰራች: ነው: እውነት: ምንግዜም: ቤሆን: ታማለች: ስለ: እናንተ: ተወርቶ: አያልቅም: ከዋናው: አባት: ጭራ: ድረስ: ያላቸው: ሐይማኖትን: በገንዘብ: የለወጣችሁ : ብር: ያሳበዳችሁ : መፅሐፍአና: ካሴት: አናይም: ስትባሉ: የዋሁን: ሰው: ለመሸጥ: ተነሳችሁ : እነ: ማሞ: ቂሎ: ሁሉ: የሚያሳዝነው: ግን: የሀባ : ሐይለሚካሔል : ነገር: ነው: ፍርዱን: ለእግዚአብሔር: ትተነዋል : እግዚአብሔር: የፍቅር: የሰላም: ሀምላክ : ነውና: ምንም: ቤሆን: ወገኖቻችን: ናችሁና: እንወዳችኾለን: ከሁሉም: በላይ: ግን: The Game is over Iam happy God is greet and god bless gelagaye amen!

 10. Congratulations to brothers and sisters at Minnesota! Congratulations! In London, the Law is catching up with Pro-Woyyane clergies and Woyyane supporters. It will be repeated here too.

  Ze-Habesha! Stay strong! Did they attempt to sue you? Well, they thought they were in Addis Ababa. Never mind!

  • አቶ ወንድሙ መኮንን ሐይማኖትን ከፖለቲካ ጋር አብረ አታቡካው ንጹ ኢትዮጵያዊ ነኝ ካልክ መለያየታችንን ሳይሆን አንድነትችንን መመኘት ይኖርብሀል አሆ የማንም ፓርቲ እና ቡድን የእኛን ሐይማኖት አይወክልም ምክንያቱም ሐይማኖታችን ድሮም ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ፤ ዛሬም ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ፤ ነገም ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ በርግጥ አይማኖታችን ድሮም ተፈትናለች፤ ዛሬም እየተፈተነች ነው፤ነገም ትፈተናለች ነገር ግን እኛ ሐይማኖታችን ስትፈተን እንደቀድሞ አባቶቻችን አብረናት መፈተን ከጎኗ መቆም አለብን እንጂ ችግርሽን እስክትፈቺ አትድረሽብኝ አልደርስብሽም ልንላት አይገባም፤ አንተ ዛሬ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ወያኔ ብለህ ጠራህው በርግጥ የምትለው እውነት ሆኖ ቢሆን አንድ ብድን ወይንም ፓርቲ መቶ ቅዱስ ላሊበላ የገነባቸውን ቤተመቅደሶች፤ግሸን ማርያምን፤ጽዮን ማርያምን፤የስላሴ ቤተክርስቲያናትን እነዛን ሁሉ ገዳማትን ባጠቃላይ 38ሺ ቤተክርስቲያናትን እና ከ2000 በላይ ገዳማትን ቢወስድብን በዚህ መልኩ ነበር የምትከላከለው ለንደን ተቀምጠ እንዲህ በማለት “congratulation to brothers and sisters at Minnesota! in London,the law is catching up with pro-Woyyane clergies and Woyyane supporters.it will be repeated here too” ትገርማለህ እኔ አንተን ብሆን የማውቀውን ፖለቲካ አጥብቄ ይዤ የማላውቀውን የህምነት ጉዳይ ለቀቅ አደርግ ነበር ምክንያቱም ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ ስለማይወጣ።

 11. I feel sad, how this can be exiting news? “Egziabhere Ashenfual” ?! are you serious? do you think Egziabhere will be happy with our division and separation?
  Almighty God will be happy when we unite and our life can teach others that being christian is good.

  I don’t have detail info about the politics going in that church. All my info is from your blog. I read all what you are posting here. I have a question for ZEHABESHA.com blogers, What is your motive???? your new sound like you are excited about this decision. what is the christian people motive in the unity of the church or money and politics? who is benefited from this except Devil and his angels? Why are we coming to church? whom we looking for? money or politics or GOD?

  I don’t think every EOTC christian is happy about current synodos in Addis, but separation is not the solution. The solution is pray, being together; this is the way of widening the gap. We should work to narrow it. I wonder what kind of cursed (yeteregeme) mind create this kind of division.

  “Let is be where we are until we know who create us!!!” St. Gebriel for Angles.

  I don’t know why everyone is so emotional and fast for decision instead of asking Almighty God with tear and prayer.

 12. አባት ሆይ የሚያረጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸወ አሁን ተውን ምትፈልጉትን አገናችው መባረክ ነውር የሆነበት ትውልድ ለመሆኑ ማን ነታችውን ታውቃላችው አሳማ ተባልን ብላችው አበዳችው አሳማነታችውን አስመሰከራችው አባቶቻችን አሳማ ያሉት ይህንን አይነት ትውልድን ነው ለማንናውም ሰላማችንን አታደፍርሱብን ከቻላችው ተነሱና የሀገራችንን ህዝብ አንታደግ ቸር ሰንብቱ::

 13. ወንድሞቼ እና እህቶቼ ከላይ ያለውን ዜና አንብቤ ተገርሜ ሳልጨርስ ከታች የተሰጡትን አስተያየቶች ስነብ ግራ ተጋባው ለምን ብትሉኝ ዘአበሻ የሚባለው ወብሳይት ኢትዬጵያ ኦርቶዶክስን ብሎ የተመሰረተ ስይሆን ጠቅላላውን ያገሪታን የፖለቲካና የማህበራዊ ኖሮን ለመዘገብ ተብሎ የተከፈተ ወብሳይት ነው ስለህኛ አይማኖት ከየትም ያገኘውን ወሬ ለማናፈስ ስልጣኑም እውቀቱም የለውም ለምሳሌ በዚህ ዘገባ ላይ በውጤቱ እጅግ ተደስተው እንደጻፉት በደንብ ያስታውቃል ውጤቱን እንዳየነው 413 እና 470 ሴሆን ዘአበሻ ዜናውን ሲዘግብ 470ዎቹ የሱ 413ዎቹ ደግሞ ጠላቶቹ አድርጎ ነው እጅግ በጣም የሚያሳዝን ጉዳይ ነው በምን መልኩ ነው ስለአንዲት ኢትዮጵያ ቆመናል የሚሉ ሰዎች 413 ምህመናን ቤተክርስቲያን ገለልተኛ መሆን የለባትም አዋርያት የመሰረታት አንዲት ቤተክርስቲያን ብለን እናምናለን እስካልን ድረስ መለያየት የለብንም በማለታቸው እንደ ጠላት ሲሰደበና ሲረገም የምናየው? እሺ በድምጽ ብልጫ ስለተሸነፎ እንበል በርግጥ ክርስትና በድምጽ ብልጫ ትተዳደራለች? ከረሳችውት አንድ ነገር ላስታውሳችው መዳኒታችን አምላካችንና ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሰቀል የተወሰነው በድምጽ ብልጫ ነው ጲላጦስ ነፍሰገዳዩን ቀማኛውን ልልቀቅላችው ወይንስ መምህራችውን ሲል ከጌታ እጅ የበሉት በጌታ እጅ የተፈወሱት እግሩስር ቁጭ ብለው የተማሩት እሱን ስቀለውና የገደለንን የቀማንን ወንበዴ ልቁው ብለው የፈረዱት በናንተ አባባል ማጆሪቲው ነው፤ ዛሬስ እናት ቤተክርስቲያን አስተምራ በእምነት በጸበል ፈውሳ ፊደል አስቆጥራ ማጆሪቲው እሳን ንቆ እራሲን በራሴ አስተዳድራለው ያንቺ ብራኬ እና እናትነት ባፍንጫዬ ይውጣ ብሎ ገለልተኝነትን መረጠ፤ዛሬስ በጌታ ዘመን እንደተፈጠረው አይነት አለመሆኑ ምን ያክል እርግጠኞች ነን?ማጆሪቲው ዛሬስ ልክ ነው?

Comments are closed.

Previous Story

(ሰበር ዜና) የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ በገለልተኛነቱ እንዲቀጥል የሚፈልገው ወገን አሸነፈ

habtamu
Next Story

Hiber Radio: አበበ ገላው ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ በጸረ ሕወሃት ትግል ላይ እንዲያተኩሩ ጠየቀ፤ ሌንጮ ባቲ ይናገራሉ

Latest from Blog

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡ ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

 በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ሳሙኤል አወቀ እንደ ቅድመ አያቶቹ ዝቅዝቅ መታየትን ያልተቀበለና በጥናት የታገለ ከመጀመሪያዎቹ ፋኖ ሰማእታት አንዱ ነው፡፡  ሰማእታትን መዘንጋት አድራን መብላት ነው፡፡ አደራን መብላትም እርምን መብላት ነው፡፡ እርምን መብላትም መረገም ነው፡፡እርማችንን

በትሮይ ፈረስነት የመከራና የውርደት አገዛዝን ማራዘም ይብቃን!!!   

June 16, 2024 ጠገናው ጎሹ በሥልጣነ መንበር ላይ የሚፈራረቁ ባለጌ፣ ሴረኛ፣ ሸፍጠኛና ጨካኝ ገዥ ቡድኖች መከረኛውን ህዝብ ከአስከፊ ድንቁርና እና ከሁለንተናዊ የመከራና የውርደት ዶፍ ጋር እንዲለማመድ  ከሚያደርጉባቸው እጅግ በጭካኔ  የተሞሉ ዘዴዎቻቸው መካከል ኮሚቲ፣

ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ

ሲሳይ ሳህሉ / ቀን: June 16, 2024 የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት
Go toTop