በኢሕአፓ ዙሪያ ለታገሉ ኃያሎች በሙሉ የትንሣኤ ጥሪ ቀረበ

April 2014
የትንሳኤ ጥሪ

ጋዜጣዊ መግለጫ

ዉድ ወገኖቻችን !
ኢሕአፓ ከተመሰረተ ይሄዉና አርባ ሁለት አመቱን አስቆጠረ ።ለድርጂቱ መመስረት ዋና ዋና ናቸዉ የሚባሉት የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ጥያቄና የመሰረታዊ መብቶች ጥያቄ ግን አሁንም መልስ አላገኙም፣ እንዲያዉም ከመሰረታዊ የሕዝብ መብቶች ጥያቄ ባሻገር ባደጋ ላይ የወደቀዉን የሃገር ሉዓላዊነት ጥያቄ ለመመለስ ትግል ግድ እየሆነ መጥቶአል።

ዛሬ ኢሕአድግ/ወያኔ በሚከተለዉ የፖለቲካ መስመር ምክንያት እየተበረታቱ በቋንቋና በሃይማኖት ክልል ተሰባስቦ መደራጀት በመስፋፋት ላይ ነዉ።በዚህም ምክንያት ጥራት ያለዉና ጠንካራ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍሎች በማሰባሰብ ትግሉን የሚመራ ድርጅት ጎልቶ ሊወጣ አለመቻሉ አሳዛኝ ክስተት ሆኗል።

ያ ትዉልድ በኢትዮዽያዊነቱ በመኩራት ለመላዉ የኢትዮዽያ ህዝብ መብት መከበር ያደረገዉ ትግል እንደ ትልቅ ትዝታ በየቦታዉ የሚነሳ ቢሆንም ከመሰዋአትነት የተረፉት የዚያ ትዉልድ አካሎች በልዩ ልዩ ምክንያት አሁንም እየተከፋፈሉ በመምጣታቸዉ “ምነዉ የጀመሩትን ትልቅ አላማ ከግቡ ለማድረስ ተቻችለዉ ትግላቸዉን አይቀጥሉም? የከፈሉት መሰዋአትነት ሳያንስ ለምን ታሪካቸዉን አያስከብሩም? ምነዉ ተክቶን ታጋይ አልፎአል የኛም ትግል ይቀጥላል ፣ልጔዝ በድል ጎዳና በተሰዉት ጔዶች ፋና”እያሉ በመዘመር የገቡትን ቃል ኪዳን ለምን ከፍፃሜ አያደርሱም?” በማለት የሚጠይቀዉ የሕብረተሰብ ክፍል ቀላል አይደለም።

በተለይም ደግሞ አዲሱ ትዉልድ እንደ ዓረዓያ ሆኖ የሚታይ ኃይል ከፊቱ ማየት በመፈለጉ ከዚያ ቅን አገርና ወገን አፍቃሪ ትዉልድ ከፍተኛ ሥራ ሲጠብቅ ከግምት በታች ሆኖ መገኝቱ ለህሊና ሰላም የሚሰጥ ጉዳይ ሆኖ አልተገኝም። አዎ ምንም እንኳን የመከፋፈል ችግር ቢገጥመዉም በኢሕአፓ ሥም ተሰልፈዉ የሚታገሉ ሐይሎች እንዳሉ ሁላችንም የምናዉቀዉ ገሀድ ነዉ።በሌላ በኩል ደግሞ ከድርጂት ዉጭ ሆነዉ ለትገሉና ለድርጂቱ በነበራቸዉና አሁንም በላቸዉ ቀና አመለካከት ልባቸዉ የሚቃጠል በጣም በርካታ የዚያ ትዉልድ አካሎች መኖራቸዉ የሚካድ አይደለም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በደቡብ ክልል በጌድኦ ዞን በፖሊሶች ተባባሪነት በብሄርና እምነት ላይ ያነጣጥረ ጥቃት ተፈጸመ:: (ቢቢኤን ሰበር ዜና )

ታዲያ ይህን ሁኔታ የተገነዘብን የዚያ ትዉልድ አካሎች ያን ጀግና ኢትዮጲዊ ትዉልድ እንደገና አሰባስቦ መንቀሳቀስ ቢቻል ለኢትዮዺያና ለኢትዮዺያዉያን ትልቅ ጥቅም ያስገኛል የሚል ሙሉ እምነት ስለአለን ይህን ስብስብ ጀምረናል።

ይህ እንቅስቃሴ ለዚያ ባለራዕይ ትዉልድ የትንሳኤ ጥሪ ከመሆኑም ባሻግር አዲሱን ትዉልድ በተአምር ከመስዋእትነት ከተረፈዉ ከዚያ ትዉልድ ጋር እንደ ድርና ማግ አስተሳስሮ ለአገር ሉዓላዊነትና ለመላዉ ህዝብ መብት መከበር ሁሉንም የኢትዮዺያ ልጆች የሚያሳትፍ እንደ ጎሞራ እሳት የሚቀጣጠል ትግል ለመፍጠር አስተዋፅኦ ያደርጋል የሚል ፅኑ እምነት አለን።

ስለዚህ ያ ትዉልድ ላደረገዉ ትግል አክብሮት ያለዉ፣ ለከፈለዉም መሰዋትነት የሚቆረቆር፣በቅንነት የተከፈለዉ የመስዋእትነት ታሪክ ሲበላሽ አላይም የሚል፤ ለሃገሬ የወደፊት እጣ ፋንታ እጄን አጣጥፌ ፣አፌን ቆልፌ፣ለወሬ ተሰልፌ፣ በተግባር ሰንፌ መቀመጥ በቃኝ ያለ፣መላዉ የኢትዮጲያ ህዝብ በእኩልነት ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብተቶቹ ተከብረዉ እንዲኖር የምትፈልጉ፣ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ሉአላዊነትዋ ተከብሮ መቀጠልዋን የትወዱ፣ የዚያ ትዉልድ አካሎች በዚህ እንቅስቃሴ ንቁ ተካፋይ እንድትሆኑ በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

እንቅስቃሴዉ አንዱን ከዉስጥ አንዱን ከዉጭ የሚያስቀምጥ ሳይሆን ሁሉንም የዚያ ትዉልድ አካሎች በእኩልነት የሚያይና የሚጋብዝ በመሆኑ በተጠቀሰዉ የኢሜል (e-mail) እድራሻ በመጠቀም በቀጥታ በዚህ እንቅስቃሴ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።በቂ ዝገጅትም ካደረግን በኃላ የተሟላ ሥብሠባ በማድለግ በጋራ የምንሄድበትን አቅጣጫ የምንወስን መሆኑን ከወዲሁ እንገልጣለን።

ይህንን ስብስብ እንድንፈጥር ካነሳሱን ዓላማዎች በጥቂቱ :
1/አሁን በመታገል ላይ ባሉት የኢሕፓ አካሎችና ከዉጭም ባሉት ቆራጥ የኢሕአፓ ልጆች ማህከል መከፋፈሉ ቀርቶ ተሰባስበዉ ጠንካራ ኃይል ሆነዉ የሚወጡበትን ምንገድ ለማመቻቸት።

2/በጥናት ላይ የተመሰረተ እስከተቻለ ድረስ ሁሉን ጔዶች እና ሁሉንም እካባቢዋች ያካተተ ታሪካችን እንዲጻፍ ለማስተባበር የሚፅፉትንም ለመደገፍ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: በሳዑዲ አጎቴን ገድያለሁ ያለው ኢትዮጵያዊ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ

3/በኢሕአፓ የትግል ታሪክና መታሰቢያዎች ዙራያ የሚሰሩ ሥራዋችን በመተባበር ለመሰራት።

4/በትግሉ መሰዋዓትነት የከፈሉትን ጔዶች የህይወት ታሪክ በማፈላለግና በማሰባሰብ ሥርዓት ባለዉ መልክ እንዲዘጋጁ ለማድረግ ከሚያደርጉም ሀይሎች ጋር ለመተባበርና ለመርዳት።

5/ድርጂታችን ባካሄደዉ ትግል ላይ የተለያዩ ፅሑፎችን (መፃህፍትና አርቲክሎችን) በመፃፍ የዚያን ጀግና ትዉልድ ታሪክ የሚያጠፉትን ኃይሎች ለመቋቋም።

6/በሃገራችን ጉዳይ ላይ ሰፊና መሰረት ያለዉ ዉይይት በማካሄድ የሃገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ አወንታዊ ኃይል ሆኖ ለመዉጣት መዘጋጀት። የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው
በዚህ ስብስብ ውስት ለመሳተፍ ለመደገፍና ለመገናኛት በዚህ e mail ተጠቀሙ

Tinsae@yahoogroups.com
ማሳሰቢያ
በዚህ ዓይነት ተመሳሳይ አላማ የሚንቀሳቀሱ ቡዱኖች ካሉ አብረን ለመስራት ሙሉ ፈቃደኞች መሆናችንን አስቀድመን እንገልጻለን
ሰለ ትብብራቸሁ እናመሰግናለን

6 Comments

 1. There is no Way the freezing in time EPRP would re-incarnate again.EPRP is were a bunch of leftists who were trying to dismantle our fundamental values.EPRP is completely against our Christian values which is the anchor of our identity. EPRP is against our golden history.to him,history is just the a history of class struggle. Fulstop. There is no Ethiopian or European or American history..etc.to EPRP, there is no God who governs the universe….the fundamental doctrine of EPRP is derived from the the Mao’ red book which has been written for the chines farmer…EPRP is an ideal organisation who has never waked up and baled to see the reality at all…that is way he failed down easily and dissipated at the middle of no where while the unpopular TPLF is become successful in this regard. Surprisingly, still EPRP has never give a chance for himself to leArn from his failurity, in fact spends the vast majority of his time on character assassination if others.

  If EPRP doesn’t knows how we are living in a most dynamically changing world and should have a confidence to his name. Otherwise there is no way revolutionary party could get a chance at least at this time

 2. በመጀመሪያ ደረጃ ሕግ የሚባል ነገር ኣለ። ማንም ወፍዘራሽ ስደተግኛ እንደፈለገ የድርጅት ዓርማ መጠቀም አይችልም። በሕግ ያስጠይቃል ማለት ነው። ሰመዓታትን ደግሞ መዘከር የሚችለው የሰመዓታቱን ዓርማ ይዞ የቀጠለው ኢሕአፓና ኣባላቱጂ ተስፋ ቆርጦ ትጥቁን ፈትቶ፣ መሳሪያውን ኣስረኪቦ የተሰደደ ስደተኛ ሊሆነ አይችልም። ያፈረሰ ቄስ ኣይቀድስ ነውናም ወኔውን የሸና ተጋዳላይ ሰማዓታትን ይዘክር ዘንድ በጭራሽ የሞራል ስልጣንና መብት የለውም ማለት ነው። ከሞራል ማማ ከወረድህ በኃላ ሲያምርህ ይቅርጂ ከእንግዲህ በሰማዓታትም ሆነ ኢሕአፖ መማልና መገዘት ኣትችሉም።

  Gudu Kassa

 3. አይ አባ ኢሕ አፓ ዛሬም አለ እንዴ? ምነው ሌላ ስራ የላቸውም እንደ አቦ፤ የሞነቸፉ ጨጓራዎች በቃ የሌለ የተረሳ ትዝታ ይዛችሁ አታቀላሁ አለም ካላችሁ አገር ቤት ሂዱና ታዩ ፈርስ ጋላቢ በባዶ ሜዳ ምነው ሆናችሁ ችክ አትበሉ

 4. ehapa-emitgalibut yeneberew ye Amharaw hibreteseb ahun neqitwal-enante ema ye Amharan hibreteseb ke ke atsew jemiro be mengistu ena be weyane qertifachu yebelachu ye deqala sibsiboch nachu-yeterefachihutin demo Amaraw wed gibat meretachu yisedachiwal-agasses hula

 5. Saynt and for all EPRP haters,

  You guys are out of focus. I do not think you understand the enemy Ethiopia. It is better, if you fight woyane and its puppets . You can do that if your not part of woyane and paid spies. Live alone EPRP, the true Ethiopian organization that have sacrificed and still sacrificing to safeguard the interest of Ethiopia and its people. For bad dreamers of EPRP, do not expect that the organization would be eliminated with such delusion.

Comments are closed.

Previous Story

ዓባይ እንደ ዋዛ–ኢትዮጵያዊነትን አጥፍቶ ዓባይን ለመታደግ ይቻላልን? – አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር) – 2

Next Story

የኢህአዴግ መንግስት በሚቃወሙትና በሚተቹት ላይ እየወሰደ ያለውን አፈና እና እስር የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲታገለው ጥሪ እናቀርባለን!!!

Latest from ዜና

ልዕልት ሂሩት ደስታ ምን አይነት ሰው ነበሩ?

ከአንሙት ስዩም እስካሁን በኖርኩባቸው አመታት የተረዳሁትና የገባኝ አንድ ነገር አለ፡፡ በዝህብ ላይ መጥፎ ስራ የሰሩትን ወንጀለኞች ለፍርድና ለቅጣት የማቅረብና የማስፈረድ ልምድ ያለንን ያህል፤ መልካም ለሰሩት ግለሰቦች ግን ተመጣጣኝ የሆነ የስማቸው

Share