የማረሚያ ቤቱ ድራማ በርዕዮት እምቢተኝነት ከሸፈ

April 23, 2013

(ፍኖተ ነፃነት) ባሳለፍነው እሁድና ሰኞ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ለመጠየቅ በዛ ያሉ የሞያ አጋሮቿና አድናቂዎቿ በስፍራው ተገኝተው ነበር፡፡የጠያቂዎቹ በዛ ብሎ የመገኘት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ርዕዮት በቅርቡ የዩኔስኮን የ2013 አለም አቀፍ ሽልማት በማግኘቷ እንኳን ደስ አለሽ በማለት የደስታዋ ተካፋይ መሆናቸውን ለመግለጽ ነበር፡፡ የባልንጀሮቿን የደስታ ምኞት እየተቀበለች ለሁሉም ሽልማቱ የእርሷ ብቻ እንዳልሆነም ትገልጽ ነበር፡፡

ርዕዮት ጠያቂዎቿን በመቀበል እያነጋገረች በነበረችበት ሰዓት(ሰኞ ዕለት) የቪዲዩ ካሜራ በመደገን ለመቅረጽ ይሞክር የነበረ አንድ ሰው በጋዜጠኞች እይታ ስር ይወድቃል፡፡ርዕዮት ላይ ያነጣጠረው ካሜራ የፈለገውን እንዳያገኝም በስፍራው የነበሩ ሰዎች ጋዜጠኛዋን በመክበብ ምስሏን እንዳይቀርጽ አድርገዋል፡፡በጠያቂዎቿ እንደተከበበች ርዕዮትን መቅረጽ ያልሆነለት ስውሩ ጋዜጠኛ በመጨረሻ ርዕዮትን ነጥሎ ለማናገር ይሞክራል፡፡በዚህ ወቅት ግን የጠያቂዎች ሰዓት በማለቁ የርዕዮት ጠያቂዎች ማረሚያ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡

የፍኖተ ነጻነት ምንጮች እንዳረጋገጡት ጋዜጠኛው ርዕዮትን በማግኘት ‹‹አንቺ ጋዜጠኛ አይደለሽ፣በራስሽ የምትተማመኚ ከሆነስ ለምን ለመቀረጽ እምቢ ትያለሽ›› ይላታል፡፡ርዕዮትም ‹‹ከአንተ ጋር ከመነጋገሬ በፊት የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች ማነጋገር እፈልጋለሁ›› በማለቷ ሃላፊዎቹ ይመጣሉ፡፡ርዕዮት ቀጠለች‹‹ይህ ጋዜጠኛ የሚፈልገውን ቃለ ምልልስ የመስጠት ችግር የለብኝም፣ ነገር ግን የተናገርኩትን ቆራርጦና ጨማምሮ ሊያቀርበው የሚችል በመሆኑ የነጻ ሚዲያ አባላት በቃለ ምልልሱ ወቅት እንዲገኙ ይደረግ ፣ ከዚህ ውጪ ግን ለጥያቄው ምንም አይነት ትብብር እንደማላደርግ ይታወቅልኝ››በማለት አቋሟን ግልጽ አድርጋለች፡፡

እንደሚታወቀው መንግስት በሽብርተኝነት ከስሶ በእስራት እንድትቀጣ እያደረጋት የምትገኘው ጋዜጠኛ የጤንነቷ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን ተከትሎ በአገር ውስጥና በውጪ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ ይገኛል፡፡የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄን ጨምሮ የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑት ሚስ አና ጎሜዝ፤የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ጋዜጠኛዋ ተገቢውን የህክምና ክትትል እንድታገኝ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡

ከዚህ ቀደም ፖለቲከኛና ዳኛ የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በታሰሩበት ወህኒ ቤት ለህመም ተጋልጠዋል የሚሉ መረጃዎች በመውጣታቸው ጫና የተፈጠረበት መንግስት ብርቱካን በጤንነት ላይ ይገኛሉ ለማለት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አማካኝነት አንድ ዘገባ መስራቱ አይዘነጋም፡፡ርዕዮት ማረሚያ ቤቱ ያስገባው ስውሩ ጋዜጠኛ ከእውቅናዋ ውጪ ሊሰራው የነበረውን ድራማ ቀድማ በመንቃቷ ሊሳካ አልቻለም፡፡

ባሳለፍነው እሁድና ሰኞ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘውን ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን ለመጠየቅ በዛ ያሉ የሞያ አጋሮቿና አድናቂዎቿ በስፍራው ተገኝተው ነበር፡፡የጠያቂዎቹ በዛ ብሎ የመገኘት ዋነኛ ምክንያት ደግሞ ርዕዮት በቅርቡ የዩኔስኮን የ2013 አለም አቀፍ ሽልማት በማግኘቷ እንኳን ደስ አለሽ በማለት የደስታዋ ተካፋይ መሆናቸውን ለመግለጽ ነበር፡፡ የባልንጀሮቿን የደስታ ምኞት እየተቀበለች ለሁሉም ሽልማቱ የእርሷ ብቻ እንዳልሆነም ትገልጽ ነበር፡፡

ርዕዮት ጠያቂዎቿን በመቀበል እያነጋገረች በነበረችበት ሰዓት(ሰኞ ዕለት) የቪዲዩ ካሜራ በመደገን ለመቅረጽ ይሞክር የነበረ አንድ ሰው በጋዜጠኞች እይታ ስር ይወድቃል፡፡ርዕዮት ላይ ያነጣጠረው ካሜራ የፈለገውን እንዳያገኝም በስፍራው የነበሩ ሰዎች ጋዜጠኛዋን በመክበብ ምስሏን እንዳይቀርጽ አድርገዋል፡፡በጠያቂዎቿ እንደተከበበች ርዕዮትን መቅረጽ ያልሆነለት ስውሩ ጋዜጠኛ በመጨረሻ ርዕዮትን ነጥሎ ለማናገር ይሞክራል፡፡በዚህ ወቅት ግን የጠያቂዎች ሰዓት በማለቁ የርዕዮት ጠያቂዎች ማረሚያ ቤቱን ለቅቀው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡

የፍኖተ ነጻነት ምንጮች እንዳረጋገጡት ጋዜጠኛው ርዕዮትን በማግኘት ‹‹አንቺ ጋዜጠኛ አይደለሽ፣በራስሽ የምትተማመኚ ከሆነስ ለምን ለመቀረጽ እምቢ ትያለሽ›› ይላታል፡፡ርዕዮትም ‹‹ከአንተ ጋር ከመነጋገሬ በፊት የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች ማነጋገር እፈልጋለሁ›› በማለቷ ሃላፊዎቹ ይመጣሉ፡፡ርዕዮት ቀጠለች‹‹ይህ ጋዜጠኛ የሚፈልገውን ቃለ ምልልስ የመስጠት ችግር የለብኝም፣ ነገር ግን የተናገርኩትን ቆራርጦና ጨማምሮ ሊያቀርበው የሚችል በመሆኑ የነጻ ሚዲያ አባላት በቃለ ምልልሱ ወቅት እንዲገኙ ይደረግ ፣ ከዚህ ውጪ ግን ለጥያቄው ምንም አይነት ትብብር እንደማላደርግ ይታወቅልኝ››በማለት አቋሟን ግልጽ አድርጋለች፡፡

እንደሚታወቀው መንግስት በሽብርተኝነት ከስሶ በእስራት እንድትቀጣ እያደረጋት የምትገኘው ጋዜጠኛ የጤንነቷ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መገለጹን ተከትሎ በአገር ውስጥና በውጪ መንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና እየተደረገ ይገኛል፡፡የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄን ጨምሮ የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑት ሚስ አና ጎሜዝ፤የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትና ሌሎች አለም አቀፍ ተቋማት ጋዜጠኛዋ ተገቢውን የህክምና ክትትል እንድታገኝ መጠየቃቸው አይዘነጋም፡፡

ከዚህ ቀደም ፖለቲከኛና ዳኛ የነበሩት ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በታሰሩበት ወህኒ ቤት ለህመም ተጋልጠዋል የሚሉ መረጃዎች በመውጣታቸው ጫና የተፈጠረበት መንግስት ብርቱካን በጤንነት ላይ ይገኛሉ ለማለት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አማካኝነት አንድ ዘገባ መስራቱ አይዘነጋም፡፡ርዕዮት ማረሚያ ቤቱ ያስገባው ስውሩ ጋዜጠኛ ከእውቅናዋ ውጪ ሊሰራው የነበረውን ድራማ ቀድማ በመንቃቷ ሊሳካ አልቻለም፡፡

2 Comments

  1. ርዕዮት የኔ ጀግና! ተራሮችን አንቀጠቀጥን ያሉትን ያነቀጠቀጥሽ ምርጥ ሴት! እንኳን ደስአለሽ። ፈጣሪ በቅርቡ ለመፈታት ያብቃሽ፣ እስከዚያው ግን በመንፈስ አብንሽ ነን አድናቂዎች ።

Comments are closed.

OCCUPY THE UNITED NATIONS Flayer Amharic
Previous Story

ድምፅ ለሌለው ወገናችን በጋራ ድምፅ እንሁን !!!

Goj2
Next Story

ጎጃም አዘነ – ክየጐንቻው!

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop