ማስተማር ወይስ ማደናገር? (ለተ/ሚካኤል አበበ የተሰጠ ምላሽ)

ታደለ መኩሪያ

ስለ ሙስሊም ኢትየጵያውያን መሪዎች  ለኢሳት ገንዘብ ማሰባስብ ዝግጅት ላይ  መገኘትና ስለታማኘ በየነ የዋህ አነጋገር ተክለማካኤል አበበ  ለአቀረበው ጹሑፍ ማስተባበያ የቀረበ ነው።

 

ወደ ዘርዝር ሐሣቡ ከመግባቴ በፊት ስለአንድ ገጠመኝ ጀባ ልበላችሁ፤ ጊዜው ቢረዘምም አይረሳም፤ በ1969 ዓ ም ነበር። ሻለቃ ዮሐንስ ምስክር ብቻውን በምኒልክ ቤተ መንግሥት የከተመውን የደርግ ፣ የካድሬ ጎራ የጦር ሜዳ ቀጠና አድርጓት መዋሉ ምንጊዜም ይወሳል። በዕለቱ እምድር ቁና ትሆናለች፤ ሻለቃ ፣ኮሌኔል፣ ጅንራል ፣ ሊቀመበሩ ሳይቀሩ ከታንክ ውስጥ እንደተጠለሉ ይነገራል። የካድሬው መንጋማ እንደ አሻሮ ተቆላ ተብሎለታል።

 

ታዳንስ አንድ ሻለቃ ዮሐንስ ምስክርን  ኮፍጣና ወታደር መሆኑን የሚያውቅ የዘብ ሃለፊ ሻለቃ ባሻ እሱ መሆን አለበት በማለት ሁኔታውን ያጣራል። እርሱ እንደሆነ ይደርሰበታል።  ‘ሻለቃ ዮሐንስ  ምስክር ነው! ተረጋጉ!’ እያለ ከአንዱ ማዕዘን ወደሌላው ይሯሯጣል። ምድረ  ሻለቃ፡ ኮሌኔል ጅንራል ፡  የደርግ አባል፣ የአብዮት አራማጅ ካድሬ  ሳይቀር፤ በየጠረጴዛው፣ ቁም ሳጥኑ ተሸሸጓል። ሊቀመበር መንግሥቱም  በታንኩ ውስጥ ኩሼ ብለዋል። የዘብ አላፊው ሻለቃ ባሻ፤ ሻለቃ ዮሐንስ ምስክር ብቻውን ይህን ሁሉ ቀውጤ እንደፈጠረ ሲያውቅ እራሱ ከሻለቃው በላይ ጀግና ለመሆነ ቃጣው። ወታደራዊ ሰላምታ እየሰጣቸው ሁሉንም  ከተሸሸጉበት እንዲወጡ አደረገ። ‘አንዱ ሻለቃ ዮሐንስ ምስክር ነው እንደብርጌድ የዘመተብን ደርሸበታለሁ በማለት ተኩራራ፣ ልቡንም አሣበጠ። ከዚያ በኋላማ ማን ይቻለው? የደርጉም ሊቀመበር የሻለቃነት ማዕረግ ሰጡት። ከእርሳቸው በመለስ ለማንም አልታዘዝም አለ። በደርግ ጽፈት ቤት ግቢ እንደልቡ ይፏልል ጀምረ። ጸረ አበዮተኛ እያለ መግደሉን አጧጣፈ።ለትንሹም ለተልቁም መሣሪያ መምዘዙን ጀመረ።  ቀደም ያሉት ካፈጸሙት ግድያ በልጦ ለመገኘት የብዙሃንን ነፍስ አጠፋ። ለእርሱ ግን መልካም ሥራ ይመስለው ነበር። ሌሎችም እንደሱ ሰው መሆናቸው ተረሳው።    ኮሌኔል አጥናፉ አባተን እርሱ እራሱ እደገደላቸው ይናገራል። የበላዮቹን በሥልጣናቸው እየገባ  በእርሱ ብሶ በሥልጣኔ ገባችሁብኝ  እያለ በራ ከረዩ ይል ጀመር። እንዲህ ነው ለሕግ ያለመገዛት እንደፈለጉ መፏለል።

ሁለተኛው በቅርብ የሆነ ነው።ነፍሳቸውን ይማረውና ዶክተር ዮናስ አድማሱ ወንደማቸው ዮሐንስ አድማሱ ስለታዋቂው ጻሐፊ ዮፍህታይ ንጉሴ ሥራዎች ጀምረውት የነበረውን ከፍፃሜው ደርሱ ለሕዝብ ይቀርባል።ሥነሥረዓቱን የመሩት ግለሰብ ያሳዩት የሥነምግባር ግድፈት ትዝብት ላይ እንደጣላቸው ተቺው ጠቀስ አድርገው አልፈውታል። መነሻቸው ለሥራው ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና ለማቅረብ  ነበር።ርዕሳቸውም ያተኮረው ‘ ሦስቱ ዮዎች’ ላይ ነበር። ዮናስ አድማሱ፣ ዮሐንስ አድማሱና ዮፍህታይ ንጉሤ። የነዚህን ታላቅ ዮዎች በመድረክ ላይ ያስተዋውቅ የነበሩት ግለስብ  ባለታሪኮቹ በሕይወት ሰለሌሉ እራሳቸው የታሪኩ ፈጣሪ ሆነው መቅረባቸው ነው ያናደዳቸው።ይህ ዓይነቱን መጥፎ ባህል መቼ ነው የምናስወግደው በማለት ነበር ስሜታቸውን የገለጹት።

 

 

ልጅ ተክለማርያም አበበ ጹሑፉን በቅርብ በሚያውቀው በሰባአዊ መብት ተከራካሪ ታማኝ በየነ ይጀምራል።ይሄውም የክርስቲያኑ ባዓል ሲከበር የዕስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን አለመከበሩን  ታማኝ በየነ በመናገሩ እንደየዋህነት ቆጥሮታል። አበው ሲተርቱ ‘ከጥምጥሙ ይቅደም መማሩ’ ይላሉ።

 

በ1966 ዓ ም ነበር። የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት የተከበሩ እንደልካቸው መኮንን ነበሩ። በአዲስ አበባ ከተማ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖታችን ተገቢውን እውቅና ይሰጠው ብለው ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣሉ። መሳ ለመሳ  የክርስትና ሃይማኖት በሰልፉ ላይ ነበር። በወቅቱ የ ቀ ኃ ሥ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዋናኛዎቹ ሰልፉን አስተባባሪዎች ነበሩ።ጥያቄው የፍትህ መሆኑን ይረዳሉ። የኢትዮጵውያን ተማሪዎች ከሚደነቁበትና አክብሮት ከሚቸርበት ተግባራቸው አንዱ ወግተኛ አለመሆናቸው ነው። አቶ ተክለሚካኤል  አበበ በእርሱ አስተሳሰብ የአቶ ታማኝን  የዋህነት ሲገልጽ ፣ብልህነቱ  ስለፍትህ የማያውቁ እሲኪያውቁ ቆሞ ያለመጠበቁ ይሆን?።

 

ሁለተኛው ደግሞ ለኢሳት ለሚደረገው የገንዘብ አሰባሰብ ዝግጅቶች ላይ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መድረኩን ተቆጣጠሩት ፖለቲካውንም ይቆጣጠሩታል የሚል ሥጋት ነው። ልጅ ተክሌ በመላ ምት ላይ ተሞርክዞ ስለ ዘጠና ሚለዮን ሕዝብ ትንተና አይስጥም፤ ነውር ነው። እንዴት ነውር እንደሆነ ወርድ ብዬ አሣያለሁ።

 

ልጅ ተክሌ  ጠላት ወዳጅ ከሚያከበረው ከአበበ ገላው በኢትዮጵያን ስሙ ሲጠራ የማይውለው ታማኝ በየነን አጅብህ  በትልልቅ የአሜሪካና የካናዳ ከተማዎች በመድረክ ላይ  ሰለታየህ እነርሱን ነህ  ማለት አይደለም። የልጅ ተክሌንም ሃይማኖት የጠየቀ አልነበረም።  ተክሌ  ከሃይማኖቱ በፊት ሰው መሆኑን የኢሳት ሰዎች እንደሚያውቁ እረዳለሁ። እስልምና ተከታይ ወንድሞቻችንም ከሃይማኖታቸው በፊት ሰው መሆናቸውን አይዘነጉም። የሰው ልጅና ፍተህ ሊነጣጠሉ ስለማይችሉ ለፍትህ የሚታገል ሁሉ ሰው ለመሆኑ የሚታገል ነውና ዘር፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ ፣ሞያ ወዘተ ሰው ከሆንን በኋላ የሚመጡ ናቸው። ለልጅ ተክሌ ይህ ይጠፋዋል አልልም፤ በኮታ እንደ ዘር ፓለቲካ  ሃይማኖትን ለመመድብ  መሞከር በአሁኑ ጊዜ የእስልምና ተከታዩን ወገናችንን የፍትህ ጥያቄ ዳር እስከ ዳር  ማጥለቅለቁን ያለማውቁን  ያለማቁ ይመስላል።

 

እንደሻለቃው ባሻና እንደመድረክ አስተዋዋቂው ከዚህም ከዚያም ተሯርጠው ስለነገሩ ጥቂት ካወቁ በኋላ በድንገት በአጋጠሚ ራስን አንድ ቦታ አስቀምጦ ከሌሎች ጋር መላተሙ አይጠቅምም። ይህ ድርጅት እቀፉ ያንን ሃይማኖት አትቀፉ ፣ እንዲህ አድርጉ ለማለት  አንተ ማነህ? የሚል ጥያቄ ያጭራልና ከወዲሁ ሰብሰብ ማለቱ አይከፋም። የቁጥጥር ኮሚቴ በኢሳት ውስጥ ይቋቋም ከሆነ መቀበልም ያለ መቀበልም የቦርዱ ነው።ያስተምራል ወይስ ያደናግራል ምርጫው የእነርሱ ነው።

 

ከዮፍህታይ ንጉሤ ስንኝ አንድ፣ ለመንገድ፤

ለጌሾው ወቀጣ አንደ ሰው አልመጣ፤

ለመጠጡ ጊዜ ከየጎሬው ወጣ።

ምስጋና ይግባቸው ለሦስቱ ‘ዮዎች’ ብዙ ከዚህ እንማራለን።

 

ታደለ መኩሪያ

tadele@shaw.ca

 

 

 

 

 

 

8 Comments

 1. Let us hope that Ligi Tekele learn his lesson from article such as this. Off the cuff remarks and shallow analysis written by individuals who are taking part in ESAT may undermine the crucial role that ESAT is playing! They should refrain themselves from such acts; of course, they are individuals who are entitled to air their views and it is imperative that they have to clearly state the view/s they are expressing is not that of ESAT’s but theirs!

 2. Mr Teklemichael seem to me one confused person who suffers due to political naiveity .I think he is the same Teklemichael who had deeply been engaged in persuading some people to rally behind Argash(the core woyane thug) to raise fund to ease her way to win parliament seat.Thus raised $5000 and sent back home when 100,000 ethiopian children make their life on street of Addis and elsewhere.The fund was raised with hope to liberate us from yalk of woyane slavery. The slavery which mainly enjinnered by the same woman and her thug comrades. It was a paradox to me to see such confused person as member in such,Esat- social media. highly partisan for the under dogged and muffled Ethiopian people. Esat,need to clean -up its back yard for quality product.

 3. Demo jemerachihu, ebakchihu neger atalametu ! Tesaschalehu belo yikerta keteyeke eseyew, kaleteyekem ok, wede wanaw telatachin woyane enatekur !

 4. የተክለሚካኤል ትችት ኢሳቶችንና ደጋፊዎቻቸውን ይህን ያህል የሚያንጨረጭራቸው ከሆነ ከኢህአዴግ ያልተሻሉ አምባገነኖች መሆናቸውን ነው የሚያሳየው። በመሰረቱ ኢሳት ገናለገና ኢህአዴግን የተቃወመ መስሎት ለኢትዮጲያ የምንጊዜም ጠላቶች ለምሳሌ ሻዕቢያ የሚያሳየው ጭፍን ድጋፍ የኢትዮጲያን ጥቅምና ጉዳት ያለገናዘበና በጣቢያው ላይ ጥቁር ነጥብ የጣለ ነው። የሙስሊሞችን ጥያቄ ከልክ ያለፈ ያውም የአክራሪዎቹን ጎራ ብቻ ከልክ በላይ ማፋፋመሙም ቢሆን ሀገሪቱን ለማጥፋት ከሚፈልጉ ሀይሎች ጋር መሰለፉን የሚያሳይ ነው። ኢሳት እነደፈለገ ቢያሽቀብጥም የሙስሊሞች ጥያቄ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ያለመ ነው። የሀይል ሚዛን ወደነሱ እስኪያጋድል ድረስ ግን ጥያቄያቸውን አለዝበው በማቅረብ ለማስመሰል መሞከራቸው አይቀርም።
  በተረፈ አበበ ገላው እና ታማኝን ደርሶ ጥልቅ ጀግና አደረካቸው። በየሄደበት ሰው ስላጨበጨበለት ብቻ ጀግና ሊሆን አይችልም። ታማኝ ማለት ለሀገሩ ምንም ቁምነገር አበርክቶ የማያውቅና ለማበርከትም ዐቅም የሌለው ተራ የመድረክ ፎጋሪ ነው። አበበ ገላው ዘላለምአለሙን በየስብሰባ አዳራሹ ላንቃው አስኪሰነጠቅ ድረስ ቢጮህም የሚለውጠው ነገር አይኖርም። ፈረነጆቹ እንደሆን በኛ ሀገር ስላለው አፈናና ጭቆና ከኛ የበለጠ መረጃ አላቸው። ሆኖም ወያኔ ሀገሪቱን በኢንቨስትመንት ስም ለነሱ አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ እስከሆነ ድረስ ለኛ ሰቆቃ ግድ የለቸውም።

  • ውድ አ.በ. አንድ ነገርን ታስተውል ዘንድ ማመላክት እወዳለሁ: ሁሉም እንዳቅሙ እንደችሎታው የበኩሉን ካበረክተ የድርሻውን ተወጥቶል ማለት ነው! ዻሩግን የስዎችን ተሳትፎ በማቀጨጭ የምናተርፈው ነገር ቢኖር ዳር ላይ ቆሞ መተችት ብቻ ነው! በተጨማሪም የህሊንና የአንባቢህን ጥያቄ “አንተ/አንቺ ምን አበርክተህ/ሽ?” መመለስ የሚያስችል የሞራል ብቃትን ስለሚጠይቅ እራስን መመርምርን ይጠይቃል ጣትን ክመጠቆም በፊት::

   ሌላው ቁምነገር ደግሞ – ስው በጠፋበት : ትግሉ እስክናካቴው ሊዳፈን በተቃረበበት : የበደል ጽዋ ሞልቶ በሚፈስብት በአሁኑ ወቅት የግንባር ስጋ ሆነው የበኩላቸውን ጥረት የሚያደርጉትን ሲሆን ማበረታታት እናም ሲሳሳቱም ቹ ማለት እንጂ ስብእናቸውን ለማኮስስ ባንሞከር ደግ ይመስለኛል::

 5. Ene bebeola leg takelan Habe badenb egarlhge degmo mebto eko new yefelgawn yemetafe gen tehto betam beza mebezato degom ke jerbaw ande negar yale yemeselale selazy lEG TAKELAY pls metafehn atkoart yalezya weyanen meselan kote endanele kokome adergleg keep it up bro God bluss u

 6. A.BE.:WHAT DO YOU EXPECT THESE TWO HEAROS ARE WHERE EVER THEY GO ETHIOPIAN PEOLE NOT ONLY WELCOMEING THEM THEY REACH TO SHAKE THEIR HANDS,TRY TO TAKE PICTURES TOGETHER WITH THEM THIS IS THE SIGN OF BRAVENESS AND BEING PURE ETHIOPIANISM,PLEASE TRY IT, GO ANYWHERE AND RUN YOUR MOUTH,AND WAIT IF SOME ONE OR GRUPS CLAMPING FOR YOUR ASS.IT WON’T HAPPENS THEN WHY YOU TRY TO DEGRADE THESE FREEDOM FIGHTERS.WHAT THEY ARE DOING IS THEY RAISE THEIR VOICES FOR ME FOR YOU AND FOR ALL OTHER ETHIOPIANS.

Comments are closed.

Previous Story

የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠላቶች – በገ/ክርስቶስ ዓባይ

Next Story

ለአቡነ ማቲያስ መመሪያ ሊሰጡ ሄዱ የተባሉት ኣባይ ፀሃየ ከደጅ እንዲመለሱ ተደረገ (ጥብቅ መረጃ)

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop