ማነህ ባለ ሳምንት? እኔ ነኝ የምትል የአብይ አህመድ የነገው የፖለቲካ ጭዳ

#image_title

አማራ ክልል ነው ያለህው? ደመቀ መኮንን፣ ይልቃል ከፋለ፣ ጄነራል አበባው ታደሰ፣ ሰማ ጠሩነህ ወይስ ለገሰ ቱሉ ትሆን?

ኦሮምያ ክልል ነህ ዘርን ከዘር ጋር ለማጨራረስ እንዲመች? አዳነች አበቤ (አዲስ አበቤዎችን ለመጨፍጨፍ እንዲመች)፣ ሽመልስ አብዲሳ? ጀዋር መሃመድ ወይስ ሌላው የአብይ አህመድ አራጋቢዎች (አማራ ላይ የዘር ማጥፋት እርምጃን ለማፋፋም)?

#image_title

አብይ አህመድና የኦሮሙማው ፖሊት ቢሮ!! የትኞቹ ከላይ የተጠቀሱት ጭዳዎች ናቸው በጥቁር ደብተራችሁ ላይ ተመዝግበው ያሉት?

በመሰረቱ የግድያው ጠንሳሽም ሆነ አስፈፃሚ በአብይ አህመድ የሚመራ የኦሮሙማው “አማራ ጠሉ” አክራሪና ነፍሰ ገዳይ ቡድን ነው። ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድሎ ጀዋር መሃመድንና በቀለ ገርባን ለማሰር የቻለ በመፈንቅለ መንግሥት ፍረጃ ባላንጣዬ ይሆናሉ ያላቸውን ጄኔራል አሳምነውንና የአማራን አመራርሮች ገድሎ ተላለኪ አሽከሮቹን ለመሾም የቻለ፣ ጄኔራል ሰአረ መኮንን ገድሎ የመከላከያን ስልጣን ለተላላኪው ብርሃኑ ጁላ ያስረከበ፣ ስልጣኑን ለማቆየት ሲል ለእናቱ ልጅና ለወለደውም ጭምር የማይሳሳ፣ ለአምስት አመታት፣ በሺህ የሚቆጠሩ አማሮች እንደ ዶሮ ሲታረዱ እንኳን ማዘን ቀርቶ አንዲት መግለጫ መስጠት የተሳነው (ከማፌዝ በስተቀር) ሰው በላውና አረመኔው አብይ አህመድ እንዴት የግርማ የሺጥላ ሞት አብጠለጠለው?

ገዳይ፣ ሟች የተገደለበትን ቦታ ከማንም በፊት ቀድሞ ያውቀዋል አድረጊው ስለሆነ። ገዳይ ከመግደሉ በፊት የግድያ ፕላን ያወጣል። ለምን እነደሚገድል ያውቃል። ግድያው ማንን እንደሚጠቅም ያውቃል። ግድያው እንደተፈፀመ ምን መረጃ መውጣት ምን መረጃ ደግሞ መሸፈን እንደሚያስፈልግ በግድያው ፕላን ይካተታል። መረጃን በመፈብረክና እንዳስተማማኝ አድርጎ በማቅረብ ብቃት እንዳለው ደግሞ አብይ አሕመድ እራሱው ፓርላማ ውስጥ ለተሰበሰበው የበግ መንጋ ቀደም ብሎ ለፍፏል። እንደዚህ ያለ የሴራ ግድያ፣ ለዚህ አእምሮው ለተነካ (psychopath) የስልጣን ጥመኛ ተራና ቀላል ተግባር ነው።

የሞተውም የአማራ የኦህዴድ ብልፅግና የጭነት አጋሰስ ነው፣ ታድያ ጩኸቱ ለምን ከጫኝዎቹ ወገን በረከተ? ለቀሩት አጋሰሶች ማስተዛዘኛ ነው?

ምነው፣ አንድ የአማራ ብልፅግና ሹም በሞተ ይህ ሁሉ የኦህዴድ ብልፅግና ጫጫታ? ምነው ያራሳችሁ የብልፅግና ሹም በሸኔ ሲረሸን “አፌን በዳቦ አላችሁ”? እንኳንስ አብይ አህመድ፣ እንኳንስ ብርሃኑ ጁላ፣ እንኳንስ ሽመልስ አብዲሳ፣ የፓርቲያችሁ ካድሬም እንኳን በሚድያ ብቅ ብሎ ልቅሶም ይሁን ፉከራ አላሰማም። የብልፅግና ፓርቲ ኦሮምያ ክልል ብቻ ነው እንዴ ያለው? የሌሎች ክልል የብልፅግና ተውካዮች ትንፍሽ ሳይሉ፣ በሞተው የአማራ ብልፅግና መሪ የኦህዴድ ብልፅግናን እንደዚህ እርር ድብን ያደረገው ለምንድነው? እንደ አያ ጅቦ አማራ ላይ ለመዝመት ነገር ፍለጋ? ተው አደብ ግዙ!! ጆሮ ለራሱ እሩቅ ነው። “የሚሉሽን ብትሰሚ ገበያ አትወጭም ነበር” የላሉ አበው። ሕዝብን የናቀ መዋረዱ አይቀርም። አልማር አላችሁ እንጂ ይህ ታሪክ እኮ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ኸረ ቆም ብላችሁ አደብ ግዙ። እንኳን አዋቂዎች ቀርተው ትላንት አፋቸውን የፈቱ ህፃናቶችም ጭምር በሕዝቡ ላይ በምታደርጉት ግፍ ግራ ገብቷቸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አሉላ፣ የዮሐንስ፣ የጎበና እና የምኒሊክ ትውልድ! (ግርማ ሞገስ)

ለመሆኑ ለምን ግርማ የሺጥላን መግደል አስፈለገ? የዶላር ጥማትን ለማርካት ወልቃይትንና ራያን ለወያኔ መስጠት። ይህን ለማሳካት ደግሞ ሰበብ ፈልጎ አማራውን ትጥቅ ማስፈታት። የሰፈር ፖለቲካ 100 (101 ሊሆን አይችልም)።

በመጀመሪያ ሚስጥሩ ለሁላችንም (ህፃናቶችንም ጨምሮ) ግልፅ ነው። የውጭ ምንዛሪ አልቋል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወደውጭ ከሚላከው የሚገባው እቃ በሶስት መቶ ፐርሰንት ይበልጣል። ከእነዚህ ከውጭ ከሚገቡ ወሳኝ ሸቀጦች መካከል ነዳጅና ምርታማ ኢንዲስትሪዎችን የሚያንቀሳቅሱ ቁሳቁሶች ይገኙበታል። ያለነዚህ ደግሞ ኢኮኖሚው ይሽመደመዳል። ሰራተኛወንም መክፈል ያዳግታል። የቀረውም የዶላር ክምጭት በሳምንቶች የሚለካ ነው።

የፋክተሪና የእርሻ ኢንደስትሪዎችን ከመገንባትና ከማስፋፍት ይልቅ፣ ቅድሚያ የሰጠው ለፓርክና ከተማን ማስዋብ ነው (በተለይም በአዲስ አበባና በአካባቢዋ)። ስንት ሥራ አጥ ተቀጠረበት? ተገልጋዩ ማነው? ዳቦ መግዛት የማይችለው የአ/አበባ ደሃ ሕዝብ? ወይንስ በእጅ የሚቆጠሩ የኦህዴድ ብልፅግና ካድሬኦችና ዲፕሎማቶች እንዲዝናኑበት? ለመሆኑስ ትርፍስ ይኖረው ይሆን ወይንስ በመንግሥት (በሕዝብ) ገንዘብ ድጎማ ነው አሁን የሚተዳደደረው? በአስር ሚልዮኖች የሚቆጠረው ወጣት ሥራ አጥ በሆነበት ጊዜ፣ ቅድሚያው ኢንደስትሪን አስፋፍቶና ሥራ ፈጥሮ ወጣቱን መደገፍና በዚያውም ልክ የመንግሥት ግብር ከፋይና የልማት ደጋፊ ማደርግ መቅደም ሊኖርበት አይገባም? ለአምሥት አመታት የአብይ ኦህዴድ ብልፅግና ያደረገው ግን የዚህ ሁሉ ተቃራኒ ነው።

በተጨማሪም፣ ዘወትር ኢትዮጵያን “ከምስራቅና ከመላው አፍሪካ እጅጉን በበለጠ አበለፅጋለሁ” (በፓርኮች ግንባታ ካልሆነ በተቀር) እያለ የሚቦትልከው አብይ አህመድ፣ ትላንትና አምስት መቶ ሺህ የሚደርሱ እህቶቻችንን (የዲግሪ ተመራቂዎችንም ጨምሮ) ከአረብ ሀገራት ዶላር ለመሰብሰብ ለግርድና እየመለመለ ነበር። እንግዲህ “ትንሿ አትነኬዋ፣ ሁሉንም አውቃሉሁኝ፣ ዳኛወም አሳሪወን እኔ ነኝ” የምትለው የአብይ አህመድ ዝግ ጭንቅላት፣ ከዚህ በፊት በዚህ ሥራ ላይ የተሰማሩት ደላሎች ያገኙዋት የበረችው ዶላርም ብትሆን ለምን ትቀርብኛለች በሚል ስንኩል የመንደር ዱርዬ እሳቤ ነው። በተረፈ በተለይም ከግርድናወም አልፎ ተርፎ፣ በኢትዮጵያውነታቸውም በተመሳሳይ የሥራ ስምሪት ከሌሎች ሐገር ሰራተኞች በዝቅተኛ ደምወዝ መቀጠራቸው ነው። ይህ የዜጎችን ስብዕና የሚያዋርድ ተግባር ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:   በሸፍጥ ፖለቲካ ያልተበከለው ነገራችን የቱ ነው? -- ጠገናው ጎሹ  

ታድያ፣ የዚህ የውጭ ምንዛሪ ክምችት፣ ሀገሪቷ ፍክተሪዎችን ከመገንባት ይልቅ ፓርኮችንና ከተሞችን በማስዋብ ላይ ስለተጠመደች የዶላር ካዝናዋ እጅጉን ተራቁቷል። በብዛት ዶላር የሚደጉሟት (አሁን እየከዳው ከመጣው ዳያስፖራው ውጭ) የአሜሪካና የአውሮፓ ሀገራት ነበሩ። ከእነሱ ይህችን ዶላር ለማግኘት ደግሞ አብይ አህመድ በመጀመሪያ ወልቃይትንና ራያን ለእንደራሴያቸው ለወያኔ ማሰረከብ አለበት። ትላንትና ከደሃ ገበሬዎች ሰብስቦ “በኤክስፖርት” ሥም የሸጠው ስንዴ ለሳምት የምትሆን ዶላር እንኳን ሊያገኝባት አልቻለም። እንዲያውም በብዙ አሰድባዋለች። እንደ ዛሬ አራት አመት ከአረብና ከአውሮፓ ሐገሮች ለምኜ አመጣለሁ የሚለው የዶላር ምንጮችም ደርቀውበታል።

ሰለዚህ ትላንትና ሽመልስ አብዲሳ፣ የአለቃው የአብይ አሀመድ የገደል ማሚቶ ሆኖ “የናንተን የነቀዘ ስንዴ ማን ይፈልጋል” እያለ ጉራውን በአደባባይ ቢቸበችብም፣ እፍረተቢስ የሆነው አብይ አህመድ ዛሬ ዶላሩን ለማግኘት ብሎ ለወያኔ በጥድፊያ ወልቃይትንና ራያን ማስረከብ አለበት። ይህን ለማድረግ ደግሞ የአማራ ክልል እንቅፋት ሊሆነው ነው። የአማራ ልዩ ሃይልና ፋኖ በመሀል ላይ ቆመውበታል። ቢሆንም፣ ለአምስት አመታት በዱለታና በግድያ ሴራ እዚህ ለደረሰው “ቁማርተኛውና ነፍሰ በላው” የኦህዴድ ብልፅግና አማራጩ ቀላል ነው። ፍልሰፍናው “ከኔ በላይ ነፋስ” ነው። ከወያኔ በትር ተከላክሎ ነፍስ የዘራለትን ባለውለታ የአማራ ልዩ ሃይልን ፋኖውንና ሚሊሽያውን በአስቸኳይ ለማፍረስና ለመበተን ቆርጦ ተነስቷል። የአማራን መሳሪያ አስፈትቶ ያለ ተከላካይ ማስቀረት። ካልተቻለ ደግሞ በአዲስ መልክ ባዋቀረው የኦሮሙማ መከላከያ ሰራዊት መጨረስ። ድሮስ ቢሆን አማራውን እንደጠላት የፈረጀው ብሔረሰብ አይደል?

ይህን አጣዳፊ ዶላርን ለማግኘት የሚደረግ የኦህዴድ ብልፅግና “የነፍስ ግቢ፣ የነፍስ ውጪ” እሩጫ፣ ለጊዜው በሱዳን የተነሳው ጦርነት ሊያግተው ቢችልም፣ በቅርቡ ደግሞ የምዕራባውያን ባንኮች ትዕዛዛቸው እስኪፈፀም ድረስ አንዲትም ሳንቲም እንደማይለቁ በማሳወቃቸው፣ ይህን ዘመቻ በምንም አይነት መልኩ ለመጀመር የቆረጠው የኦህዴድ ብልፅግና የአማራ ልዩ ሃይልን ፋኖንና ሚሊሽያን ለማጥትፋት እቅዱን በይፋ ጀምሮታል። ይህ የአማራን ሕዝብ የማጥፋት የጭፍጨፋ ዘመቻው ደግሞ በምዕራባውያን ሀገራት ነቀፌታ እንዳያስከትል ለማድረግ ሲል እራሱ የሾመውን አገልጋይ፣ ግርማ የሺጥላን ጭዳ በማድረግ “ፅንፈኛ ሃይሎች መንግሥትን በሃይል ለመገልበጥ” ገደሉት በማለት ቀድሞ ያቀነባበረውን ፕሮፓጋንዳ ለቋል። ጉዳይ ግልፅ ነው። ነፃነት ያለትግል አይገኝም። አማራው ዛሬ ለነፅነቱና ለህልውናው በሕይወቱ የሚታገልበት ወቅት ላይ ደርሷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የተዓማኒነት ጉድለት ያለበት መንግስት... ከግርማ ሰይፉ ማሩ

አስፈላጊውና ወቅታዊው መደረግ ያለበት የትግራይና የአማራ ሕዝብ ውይይትና ትብብር። የኦህዴድ ብልፅግናና እሱን የሚዘውረው የኦሮሙማ ፖሊት ቢሮ፣ ትግሬውንና አማራውን እያፋጁ በማጥፋትና ጨርሰው በማዳከም እራሳቸውን ማደራጀት ደጋግመው እንደተናገሩት ኢትዮጵያን “በራሳቸው መልክ ጠፍጥፎ መሥራት” ነው። ለዚህም ከፍተኛ ሥጋት የሆነባቸው የሰሜኑ ሕዝብ ነው። የሰሜኑን ሕዝብ እንዳሰቡት ካንብረከኩ (መቼም ለሞኝ ቀላል የመስላልና) የሌላውን ክልል ሕዝቦች አሁን እንደሚያደርጉት በየተራ እየዘመቱበት ተላላኪ ማድረግ ነው አላማቸው። ስለዚህ ለሺህ አመታት ተጋብቶ ተዋልዶ በጎረቤትነትና በአንድነት የኖረው የትግራይና የአማራ ሕዝብ በቁራሽ መሬት መጨራረስ የለበትም። ወያኔ ከመምጣቱ በፊት፣ ወልቃይትም ሆነ ራያ የአማራና የትግራይ ሕዝብ በሰላም አብረው ይኖሩ ነበር። ቤጊምድር፣ ትግሬ፣ ወሎ፣ ጎጃም፣ ወዘተ ተብሎ ይጠራ እንጂ “ትግርኛ ተናጋሪ። አማርና ተነጋሪ። ወዘተ” ተብሎ አይታወቅም ነበር። ዛሬ ቋንቋን ተገን አድርጎ የተወለደው የዘር ነቀርሳ እያፋጀን ይገኛል። ወልቃይት እንኳን ለዘመነት በጎረቤትነትና በአንድ ቤት ለኖሩት የትግራይና ያማራ ሕዝብ ቀርቶ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በባለቢትነት ሊኖሩበት የሚችል የኢትዮጵያ ግዛት ነው። ይህን ተገንዝባችሁ፣ ዛሬውኑ የትግራይና የአማራ ልሂቃኖች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ እናቶችና አዛውንቶች እንዲሁም ወጣቶች ጊዜ ስቃትወስዱ በቶሎ የውይይት መድረክ ፈጥራችሁ ይህንን “ዘረኛውና ጠባቡ የኦህዴድ ብልፅግና” ከፊታችሁ የተጋረጠውን አስከፊ እልቂት ልትታደጉ ይገባል

የኦህዴድ ብልፅግና የዛሬ ሁለት አመት ወንበሩን ለመደላደል አማራውን፣ አፋሩንና መከላከያን አዝምተቶ የትግራይን ህዝብ አውድሞ የስልጣንኑ ተቀናቃኝ የነበረውን ወያኔን አንበርክኳል (በመጠኑም ቢሆን)። ዛሬ ደግሞ ትላንና ወጋኝ ካለው ጠላቱና (ወያኔን) ከዚህ በፊት ብገፍ ያስጨፈጨፈውን መከላከያ ከፊት ለፊት አሰልፎ፣ ባለውለተኛዬ ብሎ ያወደሰውን የአማራ ሕዝብ ለመፍጀት ክተት ሰራዊት አውጇል። የትግራይ ሕዝብ! የአማራ ሕዝብ! የኢትዮጵያ ሕዝብ! የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት! ታድያ ምን ትላለህ ይህን የኦህዴድ ብልፅግና እብደት? ህዝባችን ለአምሥት አመታት ያጋጠመው፣ በግፍ የተመላ፣ ሕግና ሥርዓቱ የነቀዘ፣ የመፈናቀል፣ የግድያና በሰቆቃ የተሞላ የጨለማ ዘመን ነው።

የአማራ ሕዝብ የተደቀነበትን የኦህዴድ ብልፅግና አስነዋሪ ወረራ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ፣ በቁርጥ ቀን ልጆቹ ክንዱ የሰብረዋል።

ድል ነፃነትና ፍትህ ለተጓደለበት፣ የአምባገነንና የፋሽስት አገዛዝ ትንፋሽ ላሳጣው የኢትዮጵያ ጭቁን ሕዝብ።

ዘረኛነት ይውደም

 

ደርጀ አያኖ

ሚያዝያ 25 ቀን 2015

3 Comments

  1. Yes, Amhara opposition leaders especially Demeke Zewdu and Co. need to reach out to good intentioned Tigreans to work together.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share