September 22, 2022
6 mins read

የዘመነ ካሴ መታሰር፤ የጭራቅ አሕመድ ዐዲስ ዘዴ – መስፍን አረጋ

zemeneጭራቅ አሕመድ አሊ፣ የኦነጉ ኦቦ

አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ፡፡

አንዴ ቢያታልለን የሱ ነው ኃፍረቱ

ሁለቴ ቢደግም የኛ ነው ጥፋቱ፡፡

 

ጭራቅ አሕመድ ይሄን ሁሉ የመከራ ዶፍ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚያወርደው በኦነግ ጥንካሬ ሳይሆን ራሱን የአማራን ሕዝብ በማዳከም ነው፡፡  የአማራን ሕዝብ ማዳከም የቻለው ደግሞ የአማራን ሕዝብ በባዶ ንግግር አፍዝዞ በማደንገዝ የአማራ ሕዝብ ዋና ጠላት እሱና እሱ ብቻ ሆኖ ሳለ፣ የአማራ ሕዝብ ዋና ወዳጅ እሱና እሱ ብቻ መስሎ በመቅረብ ነው፡፡ አሁን ላይ ግን ይህ ዘዴው ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከሽፎበታል፡፡  የአማራን ሕዝብ በባዶ ንግግር የማታለል ቁማሩ ተበልቶበታል፡፡  በዚህም ምክኒያት የአማራን ሕዝብ መብላቱን ለመቀጠል፣ ጭራቅ አሕመድ ሌላ ዓይነት ዐዲስ ቁማር መቆመር የግድ ሁኖበታል፡፡  የዘመነ ካሴ መታሰርም የዚሁ የዐዲሱ ቁማር አካል ነው፡፡

ዘመኔ ካሴን አታልሎና አባብሎ እጁ በማስገባት ያሰረው ጭራቅ አሕመድ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም (ምንም እንኳን ጭራቅ አሕመድን ማመኑ የራሱ የዘመነ ካሴ ጥፋት ቢሆንም)፡፡  ጭራቅ አሕመድ ዘመነን በማዋረድና ተከፋይ ብአዴኖቹን በዘመነ መዋረድ እንዲጨፍሩ በማዘዝ የአማራን ሕዝብ ለማዋረድና በጎጥ ለመከፋፈል ማድረግ የሚፈልገውንና የሚችለውን አድርጓል፡፡  ስለዚህም ከዚህ በኋላ የዘመነ ታስሮ መቆየት ለጭራቅ አሕመድ ምንም ፋይዳ የለውም፡፡

ስለዚህም ቀጣዩ የጭራቅ አሕመድ ርምጃ ዘመነን ከእስር ፈትቶ፣ የአማራ ሕዝብ ወዳጅ እሱና እሱ ብቻ መስሎ በመቅረብ፣ በአማራ ሕዝብ ያጣውን ተቀባይነት መልሶ ማግኘትና የአማራን ሕዝብ እንደ ቀድሞ እያታለለ መብላቱን መቀጠል ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር፣ ጭራቅ አሕመድ ዘመነን ያሰረው አማራን ለማዋረድ ሲሆን፣ የሚፈታው ደግሞ አማራን ለማረድ ነው፡፡

ስለዚህም ሰፊው የአማራ ሕዝብ ወይ፡፡  ዋና ትግልህ መሆን ያለበት ዘመንን ለማስፈታት ሳይሆን፣ ዘመንን ያሰረውን ጭራቅ አሕመድን ለማሰር ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድን ስታስር ዘመነ ካሴ ብቻ ሳይሆን ጭራቅ አሕመድ ያሰራቸው ሁሉም ጀግኖችህ ባንድ ጀምበር ይፈታሉ፡፡  ስለዚህም ቁልፉ ጥያቄ የአማራ ሕዝብ ጭራቅ አሕመድን የሚያስረው እንዴት ነው የሚለው ነው፡፡

ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ በልቶ የማይጠረቃ አረመኔ ኦነጋዊ አውሬ ቢሆንም፣ የአማራን ሥጋ የሚዘነጣጥልባቸው ጥርሶቹ ግን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ብአዴኖች ናቸው፡፡  በተለይም ደግሞ የጭራቅ አሕመድ ክራንቻወች (ማለትም ረዝመው ያገጠጡት ሁለቱ የፊት ጥርሶቹ፣ canines ) ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህ ናቸው፡፡  በመሆናቸውም፣ ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ መብላት አቅቶት፣ የሠው ሥጋ ጠኔ ናላውን አዙሮት፣ ራሱን ስቶ እጁን እንዲሰጥ ብአዴናዊ ጥርሶቹን ማርገፍ ብቻ በቂ ነው፡፡  በተለይም ደግሞ መንጋጋወቹን እነ ግርማ የሽጥላን እና ሰማ ጡሩነህን መንቀል፣ ክራንቻወቹን ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህን ደግሞ መመንገል የግድ ነው፡፡

የየቀበሌው የደመላሽ ፋኖ ዋና ሚና መሆን ያለበትም በየራሱ ቀበሌ ላይ የተተከሉትን የጭራቅ አሕመድን ብአዴናዊ ጥርሶች መንቀል፣ መመንገል፣ ማፍለስ ማወላለቅ ነው፡፡  የዘመነ ካሴ አረጋዊ እናት ሙሾ እያወረዱ፣ የደመቀ መኮንን አጎትና አክስት ውስኪ ሊቀዱ አይገባም፡፡  የአማራ ሕዝብ ደመቀ መኮንን፣ ተመስገን ጡሩነህን፣ ሰማ ጡሩነህን፣ ግርማ የሽጥላንና የመሳሰሉትን የጭራቅ አሕመድን ብአዴናዊ ጥርሶች በማወላለቅ ጭራቅ አሕመድን ጨርቅ ካደረገ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

2 Comments

  1. በዘመኔ ካሴ መታሰር እጁ ያለበት አቶ አገኘሁ ተሻገር ጉዳይ አስፈጻሚ አቶ ጥሩነህና አቶ ብርሃኑ ነጋም ጭምር ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

የአቢይ አህመድ ጨለማ ጉዞ!
Previous Story

ዕዉር ከመሪዉ ይጣላል  ፤ ለማኝ አኩፋዳዉን ይጣላል  

307489131 831079798346800 7541339490424483233 n
Next Story

ጀ/ል ስብሃት ኤፍሬም ፤ የአሁኑስ ፕሮፓጋንዳ  ” ለትግሉ ውጤታማነት ሲባል — ” ቢሆንስ? (ፊልጶስ)

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop