September 21, 2022
1 min read

የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ለአቶ ሠማ ጥሩነህ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተሠማ

307018897 2740366432763845 6416153616472997589 n
307018897 2740366432763845 6416153616472997589 nየፍትሕ ቢሮው ለአቶ ሠማ ጥሩነህ ማስጠንቀቂያውን የሠጠው የኢትዮ 360 ሚዲያ ቅዳሜ መስከረም 8/2015 የአቶ ሠማን የትምህርት ማስረጃ ማጭበርበር አስመልክቶ በሠጠው ጥቆማ መነሻነት ተመስርቶ መሆኑ ተሰምቷል።
የፍትህ ቢሮው የሙስና ወንጀሉን ማጣራት ከመጀመሩ በፊት አቶ ሰማ ተምሮበታል ከተባለው የቻይና ዩንቨርስቲ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ኤንድ ኢኮኖሚክስ ተምሮ የተሠጠው የ(PHD) የምስክር ወረቀት ካለ በኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የአቻ ግምቱን በማሠራት እስከ መስከረም 12/01/2015 ዓ/ም ማስረጃውን ለሶስት ተቋማት እንዲያስገባ አዝዟል።
በዚህም አንደኛ ለክልሉ ፍትሕ ቢሮው፣ ሁለተኛ ለክልሉ ሲቪል ሠርቪስ ኮሚሽን፣ ሦስተኛ ለክልሉ የብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ማረጃውን የማያቀርብ ከሆነ ምርመራ ማጣራት እንደሚጀምር ማስታወቁ ተሠምቷል።
ይህንን የሠሙ የትምህርት ማስረጃ ያጭበረበሩ ሌሎች ባለ ስልጣናት ጭምር ጭንቅ ውስጥ መግባታቸው ታውቋል።

ለገ ግዮን

2 Comments

  1. እንዴት ያለ አደጋ ገጠመው ወይ ወዳጄ ነገሩ ዘለግ ብሎ ወደ ብርሃኑም፤አረጋዊም፤ዶ/ር አብይ እንኳን ለጊዜው ይዝለላቸው ተረብሸው ግብጽን ያስገባሉ፡፡ እንዴት ነው እሱስ ማስተር አይበቃውም ነበር እንዴት ያለ ጭካኔ ነው ዶክተር ይሻለኛል ብሎ ማስመረጥ፡፡ እንደው አይበለው እንጅ ዩኒቨርስቲው እንዲህ ያለ ሰው አላውቅም ቢል ቅጣቱ ምን ይሆን? አይ ቲክ ቶክ ይሰሩብሃል እንግዲህ፡፡

  2. በማስጠንቀቂያ ታለፈ ማለት ነው? ሌባ ሰረቀ ትብሎ ታዲያ ለምን ይታሰራል?ከዚህ በላይ ስርቆት አለ እንዴ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

307109249 636179791369674 2307424408475762334 n
Previous Story

በኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ይደረጋል ተብሎ ስለሚጠበቀው ድርድር የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር ምን አሉ

የአቢይ አህመድ ጨለማ ጉዞ!
Next Story

ዕዉር ከመሪዉ ይጣላል  ፤ ለማኝ አኩፋዳዉን ይጣላል  

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop