አማራ ከእንግዲህ እንደ ድሮው እየተወቀሰ የእነሱ የስሌጣን መወጣጫ ሆኖ አንገቱን ደፍቶ መኖር አይፈልግም። ነቅቷል። የአማራ ህዝብ ክብሩንና ጥቅሙን የከለከለበትን የኢትዮጵያዊነት ግርዶሽ አአስወግዷል። ይሄንን ስል ኢትዮጵያዊነትን ጨርሶ ጥሏል እያልኩ አይደለም።
አማራ ኢትዮጵያን መውደዱ፣ እንደ አማራ የመጣበትን ፈተና እንዳያሳየው አድርጎ የከለለውን የኢትዮጵያዊነት ግርዶሽ አስወግዷል ማለቴ ነው። አማራው በአማራነቱ እንዳይደራጅ የሸፈነውን ኢትዮጵያዊነት ግርዶሽ ቀዳዶታል። ማስተዋል ጀምሯል። አማራ በጥንቃቄ የትግል ግልፀኝነት ላይ እየደረሰ ነው።
የአማራ ብሄርተኝነት ማደግ ተገንጣይ ብሄርተኞችን አስደንግጧል። የአማራ ብሄርተኝነት በዚህ ፍጥነት ያድጋል ብለው አላሰቡም ነበር። በዚያ ላይ ከጦርነቱ መሳሪያ አትርፏል ብለው ስላሰቡ፣ ቢጨንቃቸው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለት ጀምረዋል። ይሄን የሚሉትም የአማራ መጠናከር አማራን እየረገሙ ወደ ስልጣን መውጣትን ስለሚያስቀርባቸው ነው።