March 14, 2022
5 mins read

ብልጽግና 45 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን በማስመረጥ ጉባኤውን አጠናቀቀ

275731142 540942707387351 3024142383421978798 nአዲስ አበባ፡– የብልጽግና ፓርቲ 45 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን በማስመረጥ የመጀመሪያ ጉባኤውን አጠ ናቀቀ።

ለሶስት ቀናት የተካሄደው አንደኛው የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ ትናንትና ሲጠናቀቅ 225 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትንም አስመርጧል።

የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ትናንትና በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ግልጽና አሳታፊ በሆነ መንገድ የተካሄደው ጉባኤው 45 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትንና 225 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን አስመርጧል።

የማዕከላዊ ኮሚቴውም ሆነ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ የጾታን፣ የሃይማኖትን፣ የልምድና የዕድሜ ስብጥርን ያካተተ ነው። ዕውነተኛዋን ኢትዮጵያን ማየት የሚፈልግም የኮሚቴዎቹን አባላት መመልከት ይችላል ብለዋል።

ከአርብቶ አደሩም ከአርሶ አደሩም ማሕበረሰብ እንዲሁም ከከተሞች ጭምር የመጡ አባላት በኮሚቴዎቹ ተመርጠዋል።

ይህም ፓርቲው መሰረቱን በብዝሃነት ላይ ያደረገ መሆኑን በግልጽ ያሳያል ሲሉ ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኮሚቴም ሆነ የሥራ አስፈ ጻሚ ኮሚቴ አባላትም ፍጹም ከጽንፈኝነት የራቁና ጠንካራ የሚባሉትን የብልጽግና አባላትን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም በኢትዮጵያ አንድነት የማይደራደሩ፣ ብዝሃነት የሚቀበሉ፣ ሕብረ-ብሔራዊ አንድነት እንዲኖር የሚሰሩ፣ ፅንፈኝነትንና አክራሪነትን የሚታገሉ መሆን ከተቀመጡት መስፈርቶች መካከል ይጠቀሳሉ ብለዋል።

በተጨማሪም ሌብነትን የሚጠየፉ፣ ለኢትዮጵያ ሰላም መረጋገጥ በቁርጠኝነት የሚሰሩ እንዲሁም የኑሮ ውድነት ችግርን ለማቃለል በቁርጠኝነት የሚሰሩ መሆናቸው በመስፈርትነት መቀመጣቸውን ዶክተር ቢቂላ አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያዊነትና በኢትዮጵያ አንድነት የማይደራደር ሰው ብቻ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት እንደሚመረጥ ፓርቲው በግልጽ ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት ያደረገ የ225 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ መካሄዱን አስታውሰዋል።

የዕጩዎች ጥቆማ የተቀመጡ መስፈ ርቶችን መሰረት በማድረግ ከማለዳው ጀምሮ ፍፁም ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊና ግልጽ በሆነ መልኩ መካሄዱን ተናግረዋል።

በመጨረሻም ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባላቱ ውስጥ ጠንካራ የተባሉት 45 ሰዎች ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መመረጣቸውን ዶክተር ቢቂላ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት ፡-

1. ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

2. አቶ አደም ፋራህ

3. አቶ ደመቀ መኮንን

4. አቶ ደስታ ሌዳሞ

5. ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

6. አቶ አብርሃም ማርሻሎ

7. አቶ አሻድሊ ሀሰን

8. አቶ ጌታሁን አብዲሳ

9. አቶ ኡሙድ ኡጁሉ

10. አቶ ተንኳይ ጆክ

11. አቶ ኦርዲን በድሪ

12. አቶ አሪፍ መሃመድ

13. ዶ/ር አብርሃም በላይ

14. ዶ/ር ሊያ ታደሰ

15. ሀጂ አወል አርባ

16. ሀጅሊሴ አደም

17. አቶ ኤሌማ አቡበከር

18. ወ/ሮ ሀሊማ ሀሰን

19. አቶ ሙስጠፌ መሀመድ

20. አቶ አህመድ ሽዴ

21. ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ

22. አቶ ፀጋዬ ማሞ

23. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

24. አቶ ተስፋዬ በልጅጌ

25. አቶ ርስቱ ይርዳው

26. አቶ ተስፋዬ ይገዙ

27. አቶ ሞገስ ባልቻ

28. አቶ ጥላሁን ከበደ

29. አቶ መለሰ ዓለሙ

30. አቶ ሽመልስ አብዲሳ

31. አቶ ፍቃዱ ተሰማ

32. ዶ/ር አለሙ ስሜ

33. ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

34. አቶ አወሉ አብዲ

35. አቶ ሳዳት ነሻ

36. ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

37. ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ

38. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ

39. ዶ/ር ይልቃል ከፍያለ

40. ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ

41. አቶ ተመስገን ጥሩነህ

42. አቶ መላኩ አለበል

43. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ

44. ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ

45. አቶ ግርማ የሺጥላ ናቸው።

 

ጌትነት ተስፋማርያም

አዲስ ዘመን መጋቢት 5 /2014

Leave a Reply

Your email address will not be published.

hewan
Previous Story

እጅግ አሳዛኝ… ሄዋን ወልዴ ትባላለች የተወለደችዉ ጎንደር ከተማ ነዉ።

275730586 540391204318806 6367284282141283866 n
Next Story

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በርካታ ተማሪዎች በፀጥታ ኃይሎች ተደበደቡ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop